የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክተው ትላንት መግለጫ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ በ2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል። በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ ለፈተና ከተቀመጡ በድምሩ 845,677 ተማሪዎች 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡት 27, 267 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። በዚህም 160 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን በሬሜዲያል ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚቀበሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል። የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ትምህርት ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል። 376 ተፈታኞች በቡድን፤ 483 ተፈታኞች ደግሞ በግል ጥፋት ፈጽመዋልጥፋቶቹም፤ለሌላ … [Read more...] about ከ3,106 ትምህርት ቤቶች 1,328ቱ (44%) አንድም ተማሪ አላሳለፉም
Archives for October 2023
“አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች
“አቋጥሬ አይጫረሰ ነው” አሉ አንድ አዛውንት መላው እንደጠፋቸው በመግለጽ። “አቋጥሬ ምንድን ነው?” ሲባሉ፣ በአጭሩ ደምን መበቀለ ወይም ነብስን በነብስ ማካካስ የሚባለው የቆየ ልማድ ነው። “ጎበዝ ተጫረሰ” ያሉት የጎጃም ብቸና ከተማ አቅራቢያ ነዋሪ አዛውንት “እንደው መላም የለው” በማለት ብዙም ማብራራት አይፈልጉም። ዜናውን ያጋራን የአዲስ አበባ ተባባሪያችን ቤተሰቦቻቸው ጋር መጥተው ያገኛቸው አዛውንት ክፉኛ ሃዘን ገብቷቸዋል። አማራ ክልል እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፋኖ ሃይሎች ወደ ከተማ ሲገቡ እስር ቤት ተከፍቶላቸው የወጡ ታራማሚዎች ቀደም ሲል የከሰሷቸውን ሰዎች መበቀላቸውን አዛውንቱን ጠቅሶ የዘገበው ተባባሪያችን፣ አንዱ ሌላውን እያደፈጠ ምላሽ በመስጠት በቀሉ ሳይታሰብ ተስፋፍቷል። የማቆሚያው መላም ቀላል አይመስልም። እሁድ ተለቅልቆ ሰኞ ተበራዬ፥ተሰው ሚስት አይሄድም … [Read more...] about “አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች
እሸቴ አሸባሪ፤ ቲዲኤፍ/ትሕነግ “ሰማዕት” – የዘመናችን ጉድ!
በክህደት የሚታወቀው ትሕነግ “ዝረፉ፣ ጨፍጭፉ፣ አውድሙ” ብሎ ልኮ ላስጨረሳቸው ሁሉ በጅምላ “የሰማዕትነት ማዕረግ” አከናንቦ ሐዘን አውጇል። ይህ የትሕነግ የሰማዕትነት ማዕረግ የመንዙን መብረቅ እሸቴን፣ ኮሎኔል ማራኪዋ ምክትል ዐሥር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄን፣ የክምር ድንጋዩ ትንታግ ጌጤ መኳንንት አባ ረፍርፍ፣ በስልኩ ብቻ 15 የጁንታ ታጣቂዎችን ማርኮ፤ 40ዎቹን እንዲደመሰሱ ያደረገው የጋይንቱ ጀግና ሰፊው በቀለ ናደው፣ የምድር ድሮኖች (አፋር) - የዕቶን ውስጥ ነበልባሎችን፣ አገር ብለው ከየአቅጣጫው የተመሙ የኢትዮጵያን ልጆች “አሸባሪ” አድርጎ መፈረጅ መሆኑን ስንቶች ተረዳን? ሸዋ ደብረብርሃን አፍንጫ ሥር፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ አፋርን አካልሎ ደጋግሞ የወረረ፣ የዘረፈ፣ መነኩሴ የደፈረ፣ ንጹሐንን የጨፈጨፈና ንብረት ያወደመ፣ እንስሳት ሳይቀር የረሸነ፣ … [Read more...] about እሸቴ አሸባሪ፤ ቲዲኤፍ/ትሕነግ “ሰማዕት” – የዘመናችን ጉድ!



