• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች

October 10, 2023 09:07 am by Editor Leave a Comment

“አቋጥሬ አይጫረሰ ነው” አሉ አንድ አዛውንት መላው እንደጠፋቸው በመግለጽ። “አቋጥሬ ምንድን ነው?” ሲባሉ፣ በአጭሩ ደምን መበቀለ ወይም ነብስን በነብስ ማካካስ የሚባለው የቆየ ልማድ ነው።

“ጎበዝ ተጫረሰ” ያሉት የጎጃም ብቸና ከተማ አቅራቢያ ነዋሪ አዛውንት “እንደው መላም የለው” በማለት ብዙም ማብራራት አይፈልጉም። ዜናውን ያጋራን የአዲስ አበባ ተባባሪያችን ቤተሰቦቻቸው ጋር መጥተው ያገኛቸው አዛውንት ክፉኛ ሃዘን ገብቷቸዋል።

አማራ ክልል እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፋኖ ሃይሎች ወደ ከተማ ሲገቡ እስር ቤት ተከፍቶላቸው የወጡ ታራማሚዎች ቀደም ሲል የከሰሷቸውን ሰዎች መበቀላቸውን አዛውንቱን ጠቅሶ የዘገበው ተባባሪያችን፣ አንዱ ሌላውን እያደፈጠ ምላሽ በመስጠት በቀሉ ሳይታሰብ ተስፋፍቷል። የማቆሚያው መላም ቀላል አይመስልም።

እሁድ ተለቅልቆ ሰኞ ተበራዬ፥

ተሰው ሚስት አይሄድም ወረታውን ያዬ!

ኧረ አንቺው ነይልኝ እኔስ አልመጣም፥

እንደ ወረታው በጉዴ አልወጣም፡፡

ወረታው ተበጀ ምን ወንድም አለው፣

እንደ አህያ እሬሳ ወድቆ የቀረው!

ይልሃል የአገር ሰው ለጥቁር ደም ሲያመቻችህ።

ምስጋና – ጥቁር ደም ይህን የአንዳርጌ መስፈን ልብ ወለድ ድርሰት

በዚሁ መነሻ በተለያዩ የጎጃም መንደሮችና ከተሞች ተመሳሳይ ችግር ስለመኖሩ ለማጣራት በተደረገ ሙከራ ነገሩ ቀጣዩ የማህበራዊ ቀውስ ሊሆን እንደሚችል ፍርሃቻ ያላቸውን ተባባሪያችን አመልክቷል። ያነጋገራቸው የብቸና አቅራቢያ ነዋሪ በቀን የሚገዳደሉትን ሰዎች አማካይ ቁጥር ጠቅሰው ”አይ አገር ደም እየቋጠረ ነው። ነገሩ ሁሉ ግምኛ ነው” ሲሉ ባንድ ወገን ከጎንደር የሚወለዱት አዛውንት ሁኔታውን ገልጸውታል። ክፉኛ ማዘናቸውን በሚያሳይ መልኩ ቁና ተንፍሰው ”ተወኝ እስኪ” በማለት ዝምታን መርጠዋል።

ከአማራ ክልል የድርቅ፣ የረሃብና የማህበራዊ ቀውስ ዜናዎች እየበረከቱ ነው። ፋታ የማይሰጡ የድርቅ አሳሳቢ ችግሮች ከአስድንጋጭ የሞት መረጃ ጋር እየተሰሙበት ያለው አማራ ክልል ከጦርነት ያለገገመ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ የከፋ ቀውስ እንዳይከሰት ስጋቱ ከፍተኛ ነውልል በዚህ ሁሉ ስጋት ላይ “ለአማራ ህዝብ እንታገላለን” ከሚሉት ጎን ለጎን ታጠቀው የሚዘርፉ፣ ህዝብ ላይ መዋጮ እየጣሉ የሚያሰቃዩ እንዳሉም ህዝብ እየገለጸ ነው።

ቲክቨሃ የአሜሪካንን ድምጽ ጠቅሶ “በአማራ ክልል ባህር ዳር እና ጎንደር ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ነዋሪው የዋጋ ንረቱን መቋቋም አልቻለም” በሚል ርዕስ ከስር ያለውን ዜና አስፍሯል።

የባህር ዳር ነዋሪው አቶ አለሙ ይርዳው ባለፈው ሳምንት ጤፍ ለመግዛት ወደ ገቢያ በወጡበት ወቅት ከወር በፊት በ10 ሺህ ብር የገዙት ጤፍ በሺዎች ብር ጨምሮ እንዳገኙት ገልጸዋል።

እኚሁ ነዋሪ ከ6 እና 7 ወር በፊት አንድ ኩንታል ጤፍ 6,700 ብር ገደማ መግዛታቸውን አስታውሰው አሁን 13,000 ብር መባሉን ገልጸዋል።

”በጣም ደንግጫለሁ፤ ከእጥፍ በላይ ነው የጨመረው ዝቅተኛው ጤፍ 11 ሺህ 500 እና 12 ሺህ 500 ነው የሚባለው እኔ የገዛሁት 13 ሺህ ብር ነው” ብለዋል።

ለምን በዚህ ልክ እንደጨመረ ነጋዴዎችን ጠይቀው የተሰጣቸው ምላሽ ”ከትራንስፖርት አንፃር አቅርቦት የለም፣ በየቀኑ መንገድ ይዘጋል” የሚል እንደሆነ ገልጸዋል።

ከጤፍ በተጨማሪ ሽንኩርት አንድ ኪሎ 110 ብር እንደገዙ አመልክተዋል። ቲማቲምን ጨምሮ ሌሎችም የዕለት ዕለት ግዢዎች ላይ ዋጋ ጨምሯል ብለዋል።

”13 ሺህ ብር ጤፍ ተገዝቶ እንዴት መኖር እንደሚቻል አይገባኝም ፤ በተለይ መካከለኛ እና ዝቅተኛ እንደኔ አይነት ገቢ ያላቸው የወር ደሞዝተኞች መኖር የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው” ሲሉ አክለዋል።

ይህንን እየፈጠረ ያለው አንደኛው ወቅታዊው የመንገድ መዘጋት ነው፤ በተጨማሪ ስግብግብ ነጋዴዎች ወቅቱን ተጠቅመው ሰው እንደተቸገረ አውቀው በከፍተኛ ዋጋ እየሸጡ በመሆኑ ነው ብለዋል።

አማራ ክልል በተለይ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ጤፍ አምራች ቢሆንም የአካባቢው ነዋሪ በዚህ ዋጋ ለመሸመት መገደዱ አስደንጋጭ ነው ያሉ ሲሆን ለዚህ ምክንያት እየሆነ ያለው ግጭት በፍጥነት ካልቆመ ህዝቡ በኑሮ ይጎዳል ብለዋል።

አንድ ስማቸው እንዲገልፅ ያልፈለጉ ከምዕራብ ጎጃም አዴት እና ጎንጂ ቆለላ ጤፍ አምራች አካባቢዎች ጤፍ እያመጡ የሚሸጡ ነጋዴ ፤ በወቅታዊ ግጭት ምክንያት አርሶ አደሩ ምርቱን ወደገበያ እንደማያወጣ ገልጸዋል።

”አርሶ አደሩ በሰላም ውለን መግባት ስላልቻልን ምርቱን እያወጣ አይደለም። ነጋዴው ደግሞ ያገኘውን ይዞ ይመጣል” ብለዋል። እኚሁ ነጋዴ ጤፍ 12 ሺህ ብር እየሸጡ እንደሆነ ተናግረዋል።

የጎንደር ነዋሪ የሆኑት ይፍቱ ስራማረው፤ የዋጋ ንረቱ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው ብለዋል። ”እውነት ለመናገር እንኳን በሁለት ዓመት ውስጥ በዚህ ወር ውስጥ እንኳን ከፍተኛ ጭማሪ ነው ያለው። 30 እና 20 ብር ስንገዛው የነበረው እቃ አሁን 100 ቤት ውስጥ ነው።

ሽንኩርት ከግርግሩ በፊት ከ50 – 55 ብር ነበር አሁን ሱቅ ውስጥ እስከ 120 ብር ዋና ገበያ እስከ 80-100 ብር ይሸጣል። 

ሞኮሮኒ ፓስታ ከአንድ ወር በፊት ነው የጨመሩት የ20 ብር ጭማሪ አለው ፤ ጤፍ 115 ብር – 120 ብር ይባላል በኪሎ ፤ አቅርቦትም ስለሌለ ይሆናል ” ሲሉ ተናግረዋል።

አዘዞ ከተማ የሚኖሩት የችርቻሮ  ነጋዴዋ ወ/ሮ አለሚቱ ደሴ ፤ ጤፍን ጨምሮ ሌሎች እህሎች ተወዷል ብለዋል።

”የገበያው ሁኔታ በጣም ከባድ ነው ለሻጭም ለገዢም … ቀይ ጤፍ 90 ብር ነው፣ ነጭ ጤፍ  100 ብር አሁን ላይ ነው በጣም የጨመረው 60 እና 70 ብር ነበር፤ ግጭት ከጀመረ አንስቶ እስከ 100 ብር ገብቷል።  ሽንኩርትም እስከ 100 ብር እየተሸጠ ነው። ” ብለዋል።

እህል እየተቀበሉ ያሉት የገጠሩ ማህበረሰብ ይዞ ሲመጣ እንድሆነ የገለፁት ወ/ሮ አለሚቱ ”ባለው ችግር የገጠሩ ነዋሪዎች እንደልባቸው መንቀሳቀስ አልቻሉም” ሲሉ ገልጸዋል። (ethio12)

በዳያስፖራ ያለው ደግሞ በጥቂት ጥቅመኞች እየተነዳ አገር ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከመረዳትና መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ተነስ፣ ታጠቅ፣ በለው፣ ዝመት፣ ተሰዋ ወዘተ ይላል። ከአገር ውስጥ የሚውጡ መረጃዎች የሚጠቁሙት ግን ጦርነት በቃን፣ ሰላም እንፈልጋለን፣ ማደግና ልጆቻችንን ማሳደግ እንፈልጋለን የሚል ነው። እንዲያውም አንዳንዶች ዳያስፖራ ያለው ለውጊያ ገንዘብ ከሚያዋጣ ተበድሮም ቢሆን ለሰላም ቢሠራ የተሻለ ነው፤ የራሱን ልጆች በሰላም አገር ትምህርት ቤት እየላከ፣ እያስተማረ፣ ከሩቅ ሆኖ ገፋ በለው ከሚል እዚሁ ገብቶ ከኛው ጋር ሥቃዩንም፣ መከራውንም፣ ጦርነቱንም፣ ቢያየው ጥሩ ነበር ይላሉ።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: amhara region, ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule