ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው። … [Read more...] about ይቅርታ! ከዜሮ በታች ከሆኑ ሰዎች ጋር አብረን አንደመርም !!
Archives for July 2018
ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!
አፍቃሪ ህወሓት የሚዲያ ተቋማት የማኅበራዊ ድረገጽ ተዋናዮቹን ጨምሮ “ቀለበት ውስጥ ገብተናል” በማለት የተጀመረውን ለውጥና ከኤርትራ ጋር የተያዘውን አስደማሚ የሰላም ሂደት ሲቃወሙ ሰንበተዋል። አሁንም ምክንያት በመለጣጠፍ እየተቃወሙ ነው። ድርጅታቸው ህወሓት የአልጀርሱን ስምምነት ያለ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ አራት ኪሎ ላይ ከወሰነ በኋላ ትግራይ ገብቶ ውሳኔውን የማያውቀው እስኪመስል ድረስ እየሸራረፈ ሲቃወም ሰንብቷል። በመጨረሻ ባወጣው መግለጫ የሰላም ድርድሩ ግልጽነት የጎደለውን መሆኑንን ለምክንያትነት ካወሳ በኋላ በዋናነት በድንበር ላይ ያለው የመከላከያ ኃይል እንደማይነሳ አቋሙን አስታውቋል። መከላከያ ሠራዊት የአገር ሃብትና ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግሥት ነው። ታማኝነቱ ደግሞ ለሕዝብና ለሕገመንግሥቱ ሲሆን ዋና አዛዡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው። በዚህ እውነትና … [Read more...] about ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!
አቶ ኦባንግ ለምን በይፋ አምባሳደራችን አይሆንም?
አሁን ኢትዮጵያ ልትጓዝበት እየተጠረገ ያለው መንገድ ከቀደሙት ሁሉ የተለየ ይመስላል። አዲሱ መንገድ ጥላቻን በመስበር የኢትዮጵያን ህዝብ ያለ ልዩነት በፍቅር ተጋምዶ እንዲጓዝበት ታስቦ የሚዘጋጅ ነው። ይህ የሆነበት ዋና ምክንያት የሩቁን ትተን ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የተኬደበት የጥላቻ፣ የዘረኝነት፣ የቂም፣ የመለያየት፣ የጎጠኝነት ድምሩ አጠቃላይ አገራዊ አደጋ በማስከተሉ ነው። ይህ እውነት ሊካድ በማይችል መልኩ የታየ በመሆኑ አዲሱን ጥርጊያ ማበጀት ብቸኛው አማራጭ ሆኗል። እያደር እየከረረና እየፋመ የመጣው የዘረኛነት በሽታ፣ ስርዓቱ የቆመበትን የጎጥ አስተሳሰብ ለማስጠበቅ የሚከተለው መንገድ የፈጠረው ጥላቻ፣ በስርዓቱ ውስጥ በስልትና በዕቅድ የተፈጠረው ሃብት የማጋበስ በሽታ፣ የፍትህ ዝቅጠት፣ የርትዕ መጓደል፣ የሰው ልጆች መሰረታዊ መብቶች መሞት፣ ድህነት፣ ችጋር፣ ጠኔ፣ ረሃብ፣ … [Read more...] about አቶ ኦባንግ ለምን በይፋ አምባሳደራችን አይሆንም?
አብዲ ኢሌይ “ከተጠያቂነት አያመልጥም” – ፊሊክስ ሆርን
ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት (ሂውማን ራይትስ ዎች) በቅርቡ በሶማሊ ክልል ስለሚፈጸመው እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አዲስ ዘገባ ማውጣቱ ይታወቃል። የክልሉ ርዕስ መስተዳድር የሆነውን አብዲ ኢሌይን በቀጥታ ተጠያቂ የሚያደርገው ይህ ዘገባ ከወጣ በኋላ አብዲ የተለያዩ “ዕርምጃዎችን” ሲወስድ ተስተውሏል።እነዚህም “ዕርምጃዎች” እስረኞችን ሁሉ መፍታት፣ በክልሉ የሚፈጸመውን ስቅየት ማቆም፣ … ያካተቱ ናቸው ቢባልላቸውም ለምሳሌ በኦጋዴን እስርቤት የነበሩትን የመፍታት ሳይሆን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር ተግባር ነው የተፈጸመው በማለት “ዕርምጃዎቹን” ውድቅ የሚያደርጉ ጥቂቶች አይደሉም። ከዚህ ሌላ አብዲ ኢሌይ በክልል ምክርቤቱ ስብሰባ ላይ እስካሁን በክልሉ ለተፈጸሙት ወንጀሎች ህወሓትን በቀጥታ ተጠያቂ ሲያደርግ መስማታቸውን የክልሉ አክቲቪስቶች አረጋግጠዋል። … [Read more...] about አብዲ ኢሌይ “ከተጠያቂነት አያመልጥም” – ፊሊክስ ሆርን
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ100 ቀናት
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 100 ቀናት የሥልጣን ጊዜ አስመልክቶ ጽህፈት ቤታቸው በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑትን ጉዳዮች በሚከተለው መልኩ ማብራሪያ ሰጥቶበታል። ውስጣዊ መረጋጋትን ከመፍጠር አኳያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት በሁሉም ረገድ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮች ባረበቡበት ወቅት ነው። መንግስት ውስጣዊ መረጋጋት ማስፈን ተስኖት ሁለት ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የተገደደበት፣ እዚህም እዚያም ግጭቶችና ትርምሶች የሚፈሉበት፣ በማንኛውም ቅፅበት አዲስ አበባ በኹከት ልትናጥ እንደምትችል የምታስፈራበት፣ ተረጋግቶ መስራትና መኖር አዳጋች የሆነበት፣ ኢኮኖሚው ተንገጫግጮ የነበረውን ፍጥነት ለማስቀጠል የተቸገረበት፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ጫፍ የደረሰበት፣ ኢህአዴግ በየጊዜው መግለጫ ቢያወጣም ተሰሚነቱ/ተዓማኒነቱ እጅግ የቀነሰበት፣ … … [Read more...] about ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ100 ቀናት
“ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ድንበር የለም” – ህወሓት የትግራይን ሕዝብ የሚያስትበት ቅስት ሲሰበር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና አብረዋቸው የተጓዙ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑካን በኤርትራ የ27 ዓመታት ታሪክ የመጀመሪያ የተባለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ይህ ዓለም ከዳር እስከዳር ያዳረሰ ታላቅ ግንኙነት በሰዓታት ልዩነት ውስጥ የህወሓትን ውስን አመራሮች ዕቅድና የትግራይን ህዝብ የሚያስቱበትን ቀስት ሰብሯል። መሪዎቹ የሃገራቱን ሕዝብ የጋራ ፍላጎት፣ እኩልነትና ሉዓላዊነትን ከግምት ውስጥ ያስገባ ውይይት እያደረጉ መሆኑንን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው የገለጹት ንግግሩ በተጀመረ በቅጽበት ውስጥ ነው። አቶ የማነ እንዳሉት ሁለቱ መሪዎች ፈጣንና አዎንታዊ ውጤት የሚያስመዘግብ ስምምነት ይፋ እንደሚያደርጉ ነበር ፍንጭ የሰጡት። ይህንኑ ተከትሎ የጸብ፣ የጥላቻ ግንብ መናዱንና የ“ፍቅር ድልድይ” መዘርጋቱን ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር … [Read more...] about “ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ድንበር የለም” – ህወሓት የትግራይን ሕዝብ የሚያስትበት ቅስት ሲሰበር
የአብዲ ኢሌይ መጨረሻ ሲጀምር
የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ድርጅት (ሒውማን ራይትስ ዎች) በዛሬው ዕለት (ጁላይ 4) “እንደ ሞቱ ሰዎች ነን፤ የሶማሊ ክልል በሚገኘው የዖጋዴን እስር ቤት የሚካሄደው ስቅየትና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች” “We are Like the Dead’: Torture and other Human Rights Abuses in Jail Ogaden, Somali Regional State, Ethiopia” በሚል ርዕስ የ88 ገጽ ዘገባ አውጥቷል። ዘገባው ፍጹም ጭከናና መረን የለቀቀ የማሰቃየት፣ አስገድዶ የመድፈር፣ ቶርቸር የማድረግ፣ እና የማዋረድ ተግባራትን በታሳሪዎች እንዴት እንደሚፈጸም የሚያትት ሲሆን ይህም ለታሳሪዎች የቤተሰብ ጥየቃን፣ ከጠበቃ ጋር የመገናኘትን እንዲሁም ምግብ እስከ መከልከል የደረሰ እንደሆነ ያስረዳል። እስር ቤቱ የሚመራው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ሞሐመድ ኦማር ወይም በቅጽል ስሙ … [Read more...] about የአብዲ ኢሌይ መጨረሻ ሲጀምር
የኢትዮ – ሱዳን አዋሳኝ ድንበር ጉዳይ እና የህወሓት መጨረሻ
ለረዥም ዓመታት በሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል የዘለቀው ግንኙነት ወጥ የሆነ መልክ ያለው አልነበረም። የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን ከመጽናቱ ቀደም ብሎ በነበሩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ነገሥታትና የጦር አበጋዞች በኢትዮ - ሱዳን ጠረፍ አካባቢ ከግብጽ ተስፋፊ ኃይልና ከሱዳን የንቅናቄ (መሃዲስት) ኃይል ጋር ተደጋጋሚ ጦርነት ተፈጥሮ ያውቃል። በአፄ ኢያሱ ብርሃነ ሰገደ የንግስና ዘመን የኢትዮጵያ ድንበር “ገዳሪፍ”ን አልፎ ከሚገኘው “ስናር” እስከተባለው (ሱዳን ውስጥ ያለ የቦታ ስም ነው) ቦታ ድረስ ነበር (ተከለ ፃዲቅ መኩሪያ፣ “ከአፄ ልብነ - ድንግል እስከ አፄ ቴዎድሮስ” የሚለውን መጽሃፍ ያስታውሷል) የሚለዉን የታሪክ ጭብጥ እናቆየውና በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ዋዜማ የካሳ ኃይሉ (ኋላ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ) የአባቱ ልጅ የሆነው ደጃች ክንፉ በ1829 “ወድ ከልተቡ” በተባለ ሥፍራ በሱዳን … [Read more...] about የኢትዮ – ሱዳን አዋሳኝ ድንበር ጉዳይ እና የህወሓት መጨረሻ