• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አብዲ ኢሌይ “ከተጠያቂነት አያመልጥም” – ፊሊክስ ሆርን

July 14, 2018 11:55 pm by Editor 6 Comments

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት (ሂውማን ራይትስ ዎች) በቅርቡ በሶማሊ ክልል ስለሚፈጸመው እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አዲስ ዘገባ ማውጣቱ ይታወቃል። የክልሉ ርዕስ መስተዳድር የሆነውን አብዲ ኢሌይን በቀጥታ ተጠያቂ የሚያደርገው ይህ ዘገባ ከወጣ በኋላ አብዲ የተለያዩ “ዕርምጃዎችን” ሲወስድ ተስተውሏል።እነዚህም “ዕርምጃዎች” እስረኞችን ሁሉ መፍታት፣ በክልሉ የሚፈጸመውን ስቅየት ማቆም፣ … ያካተቱ ናቸው ቢባልላቸውም ለምሳሌ በኦጋዴን እስርቤት የነበሩትን የመፍታት ሳይሆን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር ተግባር ነው የተፈጸመው በማለት “ዕርምጃዎቹን” ውድቅ የሚያደርጉ ጥቂቶች አይደሉም።

ፊሊክስ ሆርን

ከዚህ ሌላ አብዲ ኢሌይ በክልል ምክርቤቱ ስብሰባ ላይ እስካሁን በክልሉ ለተፈጸሙት ወንጀሎች ህወሓትን በቀጥታ ተጠያቂ ሲያደርግ መስማታቸውን የክልሉ አክቲቪስቶች አረጋግጠዋል። አብዲ ይህንን በተናገረ ምሽት የተወሰኑ የሚዲያ ሰዎችን ጠርቶ የህወሓት አመራሮች በተለይም የደኅንነት ኃላፊ የነበረው ጌታቸው አሰፋ በርካታ ወንጀሎችን አስገድዶ ያስፈጽመው እንደነበር፣ በክልሉ ሥራ ጣልቃ በመግባት ከፍተኛ ችግር ይፈጥርበት እንደነበር ተናግሯል። ከዚህ ጋር አያይዞም እስካሁን ስህተቶች መፈጸማቸውን በማመን እነዚህ ስህተቶችን በይቅርታ በማለፍ፣ በመደመር ወደፊት አዲሱን የዐቢይ አሕመድን አስተዳደር እየደገፉ መሔድ ተገቢ እንደሆነ ተናግሯል። ሆኖም ግን አብዲ በክልሉ በከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጣን ላይ ያሉትን የህወሓት ጄኔራሎች ላይ ግን ምንም የተናገረው አልነበረም።

አብዲ ኢሌይ ይህንን የተናገረው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቱ ዘገባ ከወጣ ጥቂት ቀናት በመሆኑ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የዘገባው ዋና አቀናባሪ የሆኑትንና በድርጅቱ የኢትዮጵያና የኤርትራ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑትን ፊሊክስ ሆርን አነጋግሯል። ይህ በስልክ በተደረገ አጭር ቃለ ምልልስ ዋና ተመራማሪው አብዲ ኤሌይ ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ በአጽዕኖት ተናግረዋል። ፊልክስ ሆርን በተለይ ለጎልጉል የሰጡትን አጭር ቃለምልልስ ከዚህ በታች አቅርበነዋል።

ጎልጉል፤ የድርጅታችሁ መግለጫ ከወጣ በኋላ አብዲ ኢሌይ የተናገረውን የሰሞኑን ንግግር ሰምተውታል?
ፊሊክስ፤ አዎ ሰምቼዋለሁ፤ ባለፉት ሁለት ቀናት ከኢትዮጵያ ሶማሊዎች በኢሜል እና በስልክ መልዕክቶች “ስደበደብ” ነው የቆየሁት፤ ሁሉም በመልዕክቶቻቸው በጣም ተናድደዋል፤ በጣም ተቆጥተዋል፤ አብዲ ነጻ እንዳልሆነ ነው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፤ ስለዚህ አብዲ ኢሌይ የፈለገውን ቢልም ከኃላፊነት አያመልጥም።

ጎልጉል፤ አብዲ ኢሌይ በቪዲዮውም ሆነ በምክርቤት ንግግሩ ይህንን ወንጀል ያሠሩን የህወሓት ሰዎች ናቸው በማለት እነ ጌታቸው አሰፋን ተጠያቂ ለማድረግ ሞክሯል፤ ይህንን እንዴት ተመለከቱት?

አብዲ በቅርቡ ከኢጋድ ኃላፊነቱ በቀጭን ደብዳቤ በፍጥነት ከተባረረው ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር አለምሰገድ አብርሃ፤ ፎቶ ምንጭ ኢንተርኔት

ፊሊክስ፤ አብዲ ኢሌይ ማለት ተስፋ የቆረጠ ሰው ነው፤ ስለዚሀ አሁን የፈለገውን ለማለት ይችላል፤ ግን ተጠያቂ ከመሆን አያመልጥም። ፍትህን መጋፈጥ አለበት፤ በእጆቹ ላይ ደም አለበት፤ በጦር ወንጀለኛነትና በሰብዓዊ ፍጡር ላይ በሚፈጸም ወንጀሎች መከሰስ የሚገባው ሰው ነው፤ ጠ/ሚ/ሩ በኃላፊነት ሊጠይቁት ይገባል፤ ምክንያቱም እርሳቸው የጀመሩት አስተዳደር ግልጽነትኛ ተጠያቂነት ይኖረዋል ብለዋል። ይህንን በተግባር ሲፈጽሙ መታየት አለባቸው።

ጎልጉል፤ ዘመኑ የይቅርታ ነው ለሠራነው ጥፋት ይቅርታ ተደርጎልን ወደፊት እንሂድ፤ ያለፈውን እንተወዉ ብሏል፤ ስለዚህስ ምን ይላሉ?
ፊሊክስ፤ በጣፋጭ የብስኩት ማሰሮ ውስጥ እጁን አስገብቶ ተያዘ እንደሚባለው የእንግሊዝኛ አገላለጽ ነው የአብዲ ኢሌይ የአሁኑ ሁኔታ፤ (ሲሰርቅ ስለተያዘ ነው እንደማለት ነው) እጅ ከፍንጅ ተይዟል ስለዚህ ነው ይህንን ያለው። የኢትዮጵያ ሶማሊዎች ፍትህ ማግኘት ይገባቸዋል።

ጎልጉል፤ የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ይሆን ይህንን እንዲል ያደረገው?
ፊሊክስ፤ (በእንግሊዝኛ የሚነገረውን አባባል በመጥቀስ በግርድፍ ትርጉሙ) የመጨረሻው ገለባ ወይም የሣር ሰበዝ ነው የግመሏን ጀርባ የሚሰብረው እንደሚባለው ብዙጊዜ የድርጅታችን ዘገባ ከወጣ በኋላ ተጠያቂ የምናደርጋቸው ሰዎች ጉዳይ ያከትማል፤ የሒውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ብዙውን ጊዜ የብዙዎችን ነገሮች ፍጻሜ መምጫ ሲሆን ተመልክተናል እና ይህ ሪፖርት የእርሱን ፍጻሜ የሚያመጣው ሊሆን ይችላል ብለን እንገምታለን።

ጎልጉል፤ ከአብዲ ኢሌይ በቀጥታ ምላሽ ሰምታችኋል? ወይም ለእርስዎ በቀጥታ መልስ ሰጥቷል?
ፊሊክስ፤ የተለያዩ ምላሾች ከማንበብ በስተቀር ለእኔ በቀጥታ ምንም የተላከ መልዕክት ወይም ምላሽ የለም።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Interviews, News Tagged With: abdi illey, abiy ahmed, Full Width Top, jail ogaden, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Whatsinaname says

    July 16, 2018 03:12 pm at 3:12 pm

    Who are the people in the main picture either side of Ibdu sew?

    Reply
  2. Whatsinaname says

    July 17, 2018 04:15 pm at 4:15 pm

    Editor Hoyisha,

    My comment asking who are the people wit Ibdu Illie is removed – why? You didn’t like it or it was not relevant or just a nuisance? I still insist on you or the author – you ask him – to identify the people for the readers sake and of the good journalistic practice. No pit hiding your head in sand and pretend comments you don’t like weren’t made. It is for your own good. As you can see anybody can have a web portal and copy/paste images and re-cylcle news and find ‘authors’ to contribute. What differentiate the good, the bad and ugly – well documented articles. Now that the wind of change is blowing many a journalist, a portal, news outlets are soon to become surplus to requirements – dwindling readers and viewers. Keep that in mind.

    Yours sincerely

    Reply
    • Editor says

      July 18, 2018 05:37 am at 5:37 am

      Whatsinaname

      ብዙ መንጫጫት አያስፈልግም፤ እንኳን ያንተን አይደለም የወያኔ ጀሌዎችንም አስተያየት አናነሳም፤ ምን እና ማንን ፈርተን ነው የምናነሳው? ኢትዮጵያውያንን አብረው ተባብረው እንዳሠሩ ያደረጋቸው እስካሁንም የጎዳቸው ነገር ግምትና ሤራ ነው፡፡ “ከበስተጀርባው ምን አለ? ይህ ለምንድነው የሆነው? …” የተሰኙ አላስፈላጊ ጥርጣሬዎችና የሤራ ንድፈሃሳቦች፡፡

      ሰሞኑን የአንተን ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም አስተያየት አላወጣንም ነበር፡፡ አሁን ሁለቱም አስተያየቶችህ ወጥተዋል፡፡ ለጥያቄህ መልስ ለመስጠት ከወታደሮቹ አንዱ ኳርተር ወይም አብርሃ ወ/ማርያም ነው ይባላል፤ እርግጠኛ አይደለንም፡፡ ሌሎቹን አናውቃቸውም፤ ለማወቅ ያደረግነው ሙከራችንም አልሠራም፡፡ ግምት አለ፡፡ ግን በግምት ለመጻፍ አንፈልግም፡፡ ፎቶውን ግን ተጠቅመንበታል፡፡ ምክንያቱም የአብዲ ኢሌይንና የወያኔ ወታደሮችን የጠበቀ ግንኙነት ከበቂ በላይ በግልጽ ያሳያልና፡፡

      ይሄ አንተ ሁልጊዜ እንደምታስበውና የሙያው ባለቤት ነኝ እንደምትለው አይደለም፤ ወይም ይህ እንደ ምዕራብ ሚዲያ እያንዳንዱ ነገር በግልጽ የሚነገርበት ጉዳይ አይደለም፡፡ ፎቶውም መገኘቱ በራሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ሹሞች እንኳን ፎቶ መነሳት አይደለም ስማቸውንም እንድታውቅ አይፈልጉም፡፡ እንደማንኛውም ወታደር ደረታቸው ላይ ስማቸው ሊጻፍ ይገባ ነበር፡፡ ግን የለም፡፡ ወያኔዎች እስከዚህ ድረስ ጉዳይ የላቸውም፡፡ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ እንዳልሆንህ ባለፉት ጊዜያት እንደነገርከን ሁሉ ይህንንም ጉዳይ የምታጣው አይመስለንም፡፡ (ለምሳሌ ጌታቸው አሰፋ የኢትዮጵያ ደኅንነት ዋና ኃላፊ ሆኖ ለ17ዓመታት ሠርቷል፤ ፎቶውን አይተህ ታውቃለህ? አሁን ኢንተርኔት ላይ የሚገኙት ሁለት ወይም ሦስት ፎቶዎች ግምታዊ ናቸው)፡፡

      ከዚህ ሌላ ይህንን ብለሃል “As you can see anybody can have a web portal and copy/paste images and re-cylcle (the spelling is WRONG) news and find ‘authors’ to contribute. What differentiate the good, the bad and ugly – well documented articles”. ከጻፍነው ዜና ውስጥ የትኛው ነው “re-cylcle news”? ፊሊክስ ሆርንን ያነጋገርነው እኛ ነን፡፡ አጭር ቃምልልስ ያደረጉት ከእኛ ጋር ነው፡፡ ይህንን በግልጽ አስቀምጠናል፡፡ የቱ ጋር ነው ይህ መረጃ “re-cylcle news” የሆነው? ከየትኛው ሚዲያ ላይ ነው እውቅና ሳንሰጥ ወስደን ያተምነው? ከማን ነው የሰረቅነው (ያው በትህትና ሰርቃችኋል ነው ያልከን)?

      ጎልጉል እንደሌሎቹ የማስታወቂያ ጥማትና የ“click” ናፍቆት የለበትም፡፡ ሥራውን የምንሠራው በነጻ ነው፡፡ ለዚህ ነው እዚህ ላይ መጥተህ ስታነብ ምንም ዓይነት ማስታወቂያ ሳይረብሽህ ወይም ኮምፒውተርህን “adware” እና “malware” ሳያጠቃው በሰላም ገብተህ ምትወጣው፡፡

      “Now that the wind of change is blowing many a journalist, a portal, news outlets are soon to become surplus to requirements – dwindling readers and viewers.” ለሚለው አስተያየትህ ብዙም አንጨነቅም፡፡ ከላይ እንዳልነው የማስታወቂና “click” ጉዳይ አያሳስበንም፡፡ አምስት አንባቢ ካለን ሥራችንን እንቀጥላለን፡፡ የዶ/ር ዐቢይ የለውጥ ተግባር የታሰበው ደረጃ ደርሶ እኛን ሥራፈት ቢያደርገን ከዚህ የሚዲያ አገልግሎት በመጀመሪያ የምንለቀው እኛ እንሆናለን፡፡ ምክንያቱም ዕድሜልካችንን የወያኔን ህጸጽ እየፈለጉ መጻፍ በራሱ በባህርይ ላይ የሚስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ አለ፤ ከዚያ እንገላገላለን፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ከእንዳንተ ዓይነቱ እንደ የተጨማደደ የካሴት ክር (broken record) ደግሞ ደጋግሞ እንደሚዘፍነው ዓይነት የአውቃለሁ ባይ ግልብና ገለባ አስተያየትም እንገላገላለን፤ እንደዚህ ዓይነት ምላሽ በመስጠት አሉታዊ ኃይል ከመልቀቅም እንገላገላለን፡፡ ትፋታናለህ፤ እንፋታሃለን፡፡ ያኔ እኛ ብቻ ሳንሆን አንተም “ታርፋለህ”፡፡ ስለዚህ አንተም ማረፊህን አስቀድመህ አስብበት፡፡

      የጎልጉል አርታኢ

      Reply
  3. Whatsinaname says

    July 18, 2018 04:18 pm at 4:18 pm

    Wow That’s a mouth full of a reply. So you are on the war path editor hoyisha? Unless you got up on the wrong side a simple thanks but no thanks was enough. As for me thanks that shows the arrogance and rudeness of these self appointed web outlets. What came to my mind and, others probably, is ‘Balegein Kasadege Yegedele Yitsedqal’. Thanks to the web you can spit and vomit at the slightest ‘irritation’ – thank God you are not in position of power. How are the woyanes differ from you you then? You don’t have power and guns but much alike in words and actions.

    If this irritates you more then have your head and views examined!!!!

    Reply
    • Editor says

      July 18, 2018 09:14 pm at 9:14 pm

      Whatsinaname

      ከዚህ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ ሃሳብ ተለዋውጠን ያለንን ችግር ኣስረድተንህ ስናበቃ ተመልሰህ ያንኑ የነቀፋና ህጸጽ የሞላበትን ኣስተያየት ጻፍክ። ከዚያም ጨምሮ ስድብ ቀላቀልክበት። በዜናው ላይ የተሠራውን መልካም ነገርና ሌሎች ፎቶዎችን እንዴት ከነምንጫቸው እንደጠቀስን ምንም ጥቆማ ሳታደርግ ወደለመድከው ነቀፋ ሄድህ። ይህ በራሱ ያንተን ውስጣዊ ችግር የሚያሳይ ነው። በዕድሜህ ኣንድ አንቀጽ ወይም ፓራግራፍ ጽፈህ ብታውቅ ኖሮ እኛን እንደዚህ ለመዝለፍ አትቃጣም ነበር። ችግሩ መሥራት ሳይሆን መንቀፍ ዋና ሥራህ ስለሆነ ነው።

      ከዚህ በኋላ መልስ ላንሰጥህ ወስነናል። ይህ የመጨረሻችን ነው። አንተ ግን የለመድከውን ነቀፋ መቀጠል ትችላለህ። ጸያፍ ስድብ እስከሌለው ድረስ እንደምናትምልህ ቃል እንገባለን።

      ደህና ሰንብት።

      የጎልጉል አርታኢ

      Reply
  4. whatsinaname says

    July 19, 2018 12:20 am at 12:20 am

    Ok I will rest my case then – let us agree to disagree. I just want to say you are in the public eye the second you started publishing. I will ignore your uninformed and based conclusion that I have never written anything.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule