ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት (ሂውማን ራይትስ ዎች) በቅርቡ በሶማሊ ክልል ስለሚፈጸመው እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አዲስ ዘገባ ማውጣቱ ይታወቃል። የክልሉ ርዕስ መስተዳድር የሆነውን አብዲ ኢሌይን በቀጥታ ተጠያቂ የሚያደርገው ይህ ዘገባ ከወጣ በኋላ አብዲ የተለያዩ “ዕርምጃዎችን” ሲወስድ ተስተውሏል።እነዚህም “ዕርምጃዎች” እስረኞችን ሁሉ መፍታት፣ በክልሉ የሚፈጸመውን ስቅየት ማቆም፣ … ያካተቱ ናቸው ቢባልላቸውም ለምሳሌ በኦጋዴን እስርቤት የነበሩትን የመፍታት ሳይሆን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር ተግባር ነው የተፈጸመው በማለት “ዕርምጃዎቹን” ውድቅ የሚያደርጉ ጥቂቶች አይደሉም። ከዚህ ሌላ አብዲ ኢሌይ በክልል ምክርቤቱ ስብሰባ ላይ እስካሁን በክልሉ ለተፈጸሙት ወንጀሎች ህወሓትን በቀጥታ ተጠያቂ ሲያደርግ መስማታቸውን የክልሉ አክቲቪስቶች አረጋግጠዋል። … [Read more...] about አብዲ ኢሌይ “ከተጠያቂነት አያመልጥም” – ፊሊክስ ሆርን