• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአብዲ ኢሌይ መጨረሻ ሲጀምር

July 4, 2018 11:44 pm by Editor 1 Comment

የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ድርጅት (ሒውማን ራይትስ ዎች) በዛሬው ዕለት (ጁላይ 4) “እንደ ሞቱ ሰዎች ነን፤ የሶማሊ ክልል በሚገኘው የዖጋዴን እስር ቤት የሚካሄደው ስቅየትና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች” “We are Like the Dead’: Torture and other Human Rights Abuses in Jail Ogaden, Somali Regional State, Ethiopia” በሚል ርዕስ የ88 ገጽ ዘገባ አውጥቷል።

ዘገባው ፍጹም ጭከናና መረን የለቀቀ የማሰቃየት፣ አስገድዶ የመድፈር፣ ቶርቸር የማድረግ፣ እና የማዋረድ ተግባራትን በታሳሪዎች እንዴት እንደሚፈጸም የሚያትት ሲሆን ይህም ለታሳሪዎች የቤተሰብ ጥየቃን፣ ከጠበቃ ጋር የመገናኘትን እንዲሁም ምግብ እስከ መከልከል የደረሰ እንደሆነ ያስረዳል። እስር ቤቱ የሚመራው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ሞሐመድ ኦማር ወይም በቅጽል ስሙ አብዲ ኢሌይ በሚታዘዘው ልዩ ፖሊስ ሲሆን አብዛኛዎቹ እስረኞች የተከሰሱት ከኦጋዴን ነጻ አውጪ ግምባር (ኦብነግ) ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ነው። ሌሎችም የተቃዋሚ ቡድን አባላት በዚህ አስርቤት የሚገኙ ሲሆን አብዛኛዎቹ መቼም ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ያልቀረበ እንደሆነ በሪፖርቱ ተመልክቷል።

የሪፖርቱ ዋና አቀናባሪና በሒውማን ራይትስ ዎች ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ፊሊክስ ሆርን “አዲሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ/ር የደኅንነት ሰዎች ኢትዮጵያውያንን ማሰቃየታቸውን ቢያምኑም በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ እየፈጸሙ ለፍርድ ሳይቀርቡ እና ተጠያቂ ሳይሆኑ የመቅረትን ባህል (እስከ ጥግ) ሊዋጉት ይገባል” ብለዋል። ሲቀጥሉም “በዖጋዴን አስር ቤት ውስጥ የሚፈጸመው አሰቃቂ ተግባር በተመለከተ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ሌሎች የሶማሊ ክልል ባለሥልጣናትና ልዩ ፖሊስ ላይ ፈጣንና ግልጽ ምርመራ ሊደረግ ይገባል” ብለዋል።

ዘገባው የተጠናቀረው ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎችን በማነጋገር ሲሆን ይህም የደኅንነት ሰዎችን፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትን እና 70 በእስር ቤቱ ታስረው የነበሩ እንዲሁም እኤአ ከ2011 እስከ 2018 በዖጋዴን እስር ቤት የተፈጸመውን በሰነድ የተደገፈ ማስረጃ መሠረት በማድረግ ነው።

ከታሣሪዎች አንደበት (ስማቸው ለደኅንነታቸው ተቀይሯል)፤

አብዱሳሌም፣ ዕድሜ 28፤

“ለሦስት ዓመታት በእስር በቆየሁባቸው ጊዜያት በፍጹም ጭለማ ውስጥ ለብቻዬ ታስሬ ነበር፤ ማታ ሲሆን ሊያሰቃዩኝ  ያወጡኝ ነበር፤ (የእስር ቤት ኃላፊዎች) ብዙ ነገሮችን ፈጽመውብኛል፤ የብልቴን የዘር ከረጢት በኤሌክትሪክ አቃጥለውኛል፤ በሽቦ ካሰሩኝ በኋላ በላስቲክ ውስጥ በርበሬ (ሚጥሚጣ) በራሴ ላይ አድርገው (አፍነውኛል)፣ በጣም እንዳልጮህ አፌን አስረውታል፤ ቀን ቀን በጣም ትንሽ ምግብ ይሰጡኛል፤ አንድ ዳቦና አንዳንዴ ጥቂት ወጥ ያለበት፤ በዚሁ ኦጋዴን እስር ቤት የነበረችውን ሚስቴን አስገድደው ደፍረዋታል፤ የኔ ያልሆነ ልጅም እዚያው ወልዳለች”።

ሌሎቹን እስረኞች ለማስፈራራት ታሳሪዎች በእስረኛው ሁሉ ፊት ዕርቃናቸውን ተደርገው ተገርፈዋል፣ ተደብድበዋል፣ ሌሎች አሣፋሪ ተግባራትን እንዲፈጽሙ ተደርገዋል።

ሆዳን፣ ዕድሜ 30፤

“በየምሽቱ ሰዎችን ሲገርፉ፣ ሲደበድቡ እሰማለሁ፤ ብዙ የሰቆቃ ጩኸትም እሰማለሁ፤ ጠዋት ላይ ሰዎች በክፍሌ ደጃፍ ቁርስ እየበሉ በቀስታ ባለፈው ማታ የተፈጸመውን አንስተው ያወራሉ፤ ‹ትላንት ማታኮ እከሌና እከሌ በድብደባ ተገድለዋል፤ እገሊትና እነገሊት ደግሞ ተደፍረዋል፣ ተደብድበዋል› ይላሉ፤ በየጠዋቱ የሞቱትን ወይም ወደ ክፍላቸው ያልተመለሱትን እንቆጥራለን፤ ነገ የኔ ተራ ይሆን በሚል በየቀኑ በማያቋርጥ ፍርሃት ውስጥ እንኖራለን”።

ፋጡማ፣ ዕድሜ 30፤

“እጃችንን የፊጥኝ በገመድ ያስሩና ከአናቴ በላይ ከፍታ ባለው የውሃ ገንዳ ውስጥ ይደፍቁናል፤ በአንድ ጊዜ በገንዳው ውስጥ 10 ሰዎች ያደርጋሉ፤ … የተለመደውን ጥያቄ ‹ከኦብነግ ውስጥ ማንን ታውቂያለሽ? እንዴት ነው የምትረጂያቸው?› በማለት ይጠይቁናል፤ አንዳንዶቹን ከውሃው ሲያወጧቸው ምንም አይንቀሳቀሱም፤ ሞተው ይሆን እኔ አላውቅም”።

ዓሊ፣ ዕድሜ 32፤

“ሲመሽ ግምገማ ይጀመራል፤ ይህንን ታሳሪዎች ናቸው እርስበርሳቸው የሚያደርጉት፤ ሲነጋ ለጠባቂዎቹ ሪፖርት ይቀርብላቸዋል፤ ብዙ የካደ በጣም ይሰቃያል፤ ጥሩ የተናዘዘ ቅጣቱ ይቀንስለታል፤ ጥፋተኛ መሆኑን በደንብ ያመነ በግምገማው ወቅት ብዙዎች ያጨበጭቡለታል፤ ነገርግን አላምንም ያለ እዚያው ካባሱ (የእስረኞች አለቃ) ይደበድበዋል”።

ሞሐመድ፣ ዕድሜ 28፤

“በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዕርቃናቸውን ሆነው አይቻለሁ፤ ማታ ነበር ደግሞ ይዘንብ ነበር፤ ውጭውም ጭቃ ነበር፤ ከክፍላችን እንድንወጣ አድርገውን ነበር፤ ልብሳችንን እንድናወልቅ ነገሩን፤ ከዚያም ጭቃው ላይ እንድንከባለል አደረጉን፤ ከዚያ አንዳንዶቻችን ወደየክፍላችን ዕርቃናችንን ተወሰድን፤ ሌሎቹ ደግሞ አንዱ የሌላውን ብልት በመያዝ በመስመር እንዲሄዱ ተነገራቸው፤ ወደ ክፍል ከተወሰድን በኋላ እንድንወጣ አይፈቀድልንም፤ ይህንን ክስተት ጠባቂዎቹ እየሳቁ ፎቶ ያነሳሉ”።

አብዲራህማን፣ ዕድሜ 31፤

“ሁልጊዜ አንዳችን ሌላችንን እንድናዋርድ ይነገራናል፤ ከሁሉ የከፋው የተከሰተው ግን አንድ ቀን በርከት ያልን እስረኞችን አመጡንና አንዳችን ሌላችንን እስንሞት እንድንደበድን ነገሩን፤ ለዚህም የብረት መደብደቢያ ሰጡን፤ እምቢ ካልኩ ራሴን መግደል እንዳለብኝ ተነገረኝ፤ እምቢ የሚሉትን ራሳቸው ይደበድቡናል – የከፋው ግን የሚደርስብን የስነልቦና ቅጣት ነው”።

ዓይና፣ ዕድሜ 30፤

“እኔ እዚያ በነበርኩበት ጊዜ የተወለዱት ህጻናት በሙሉ ከሌሎች ሴት እስረኞች ከተደረገላቸው በስተቀር አንዳቸውም ምንም የባለሙያ ዕገዛ አልተደረገላቸውም፤ እኔ ራሴ መውለጃዬ ሲቃረብ (የሕክምና ዕርዳታ) እንዲደረግልኝ ጠይቄ ነበር፤ ልዩ ፖሊሱ የመለሰልኝ ‹ልጁን ሽንት ቤት ጨምሪው፤ ምንም አይጠቅሙን፤ ምክንያቱም ካደጉ በኋላ የኦብነግ ደጋፊ ነው የሚሆኑት› በማለት ነበር፤ ለመውለድ ወደ ሆስፒታል እንድወሰድ ስጠይቅ ሳቁብኝ፤ ተጨማሪ ውሃ እንዲሰጠኝ ስጠይቅ ከለከሉኝ፤ ስለዚህ እዚያው እስር ቤት ውስጥ ወለድኩ፤ ሴቶቹ ስለታም ብረት ስለነበራቸው ዕትብቱን ቆረጡልኝ ከዚያም አሠሩልኝ”።

ዓሚና፣ ዕድሜ 34፤

“የሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን ለመመርመር ሲመጣ ከበድ ያለ ጉዳይ ያላቸውን አወጧቸው፤ አዳዲሶቹን ተዋቸው፤ ከተደበቁት ሰዎች አንዷ ነበርኩ፤ ወደ ጋርባሳ ወታደራዊ የጦር ሠፈር (ሚሊታሪ ካምፕ) ነበር የተወሰድነው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ እዚያ ለሰባት ቀን ተቀምጬ ነበር፤ አረጋውያን ሴቶችን፣ ፊታቸው ላይ የተመቱትን፣ ወይም ቁስል ያለባቸውን ወይም ህጻናት ልጆች ያላቸውን በሙሉ አውጥተዋቸው ነበር”።

አብዲ በቅርቡ ከኢጋድ ኃላፊነቱ በቀጭን ደብዳቤ በፍጥነት ከተባረረው ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር አለምሰገድ አብርሃ፤ ፎቶ ምንጭ ኢንተርኔት

“አንድ ጊዜ በሰዉ ሁሉ ፊት መሬት ላይ ዕርቃኔን እንድተኛ አደረጉኝ፤ ከዚያም ጭቃ ላይ እንድንከባለል በማድረግ በዱላ ደበድቡኝ ነበር” ይላል ለአምስት ዓመት ያለ አንዳች ክስ የታሰረው የ40 ዓመቱ ሆዳን። “አንድ ቀን አንድ አዛውንት ሰው ከሴት ልጁ ጋር ዕርቃኑን እንዲቆም አደረጉት … በሌሎች እስረኞች ፊት እንዲህ ስትደረግ ኃፍረት ይሰማሃል”።

ታሣሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ከፍተኛ የልዩ ፖሊስ አባላት በእስረኛው ላይ ቶርቸር (ስቅየት)፣ አስገድዶ መድፈር፣ ምግብ መከልከል እንዲፈጸም የሚያደርጉ ብቻ ሳይሆን ራሳቸውም በማሰቃየቱና አስገድዶ በመድፈሩ ላይ ይሳተፋሉ። በእስር ቤቱ ውስጥ የእስረኛው ቁጥር ከመጠን በላይ መሆን፣ ከዚያ ጋር ተያይዞ የሚፈጸመው ስቅየት፣ ምግብና ውሃ ክልከላ፣ ከንጽህና ጉድለት ጋር የተያያዙ በሽታዎች እንዲከሰቱ በማድረግ ለበርካታዎች ሞት ምክንያት ሆኗል።

እርጉዝ እስረኞች ልጆቻቸውን በዖጋዴን እስር ቤት ወልደዋል፤ አንዳንዶቹም አስገድዶ ከመድፈሩ ጋር በተያያዘ የተፀነሱ ናቸው። ሴት እስረኞች ልጆቹን በሚወልዱበት ጊዜ ተገቢ የጤና እንክብቃቤ ቀርቶ ውሃ እንኳን እንዳላገኙ ልጆቹንም በእስር ክፍላቸው እንደወለዱ ይናገራሉ።

ልዩ ፖሊስና የክልሉ ኃላፊዎች ተጠያቂነት

የዛሬ 10 ኣመት አካባቢ የኦብነግን ጥቃት መልሶ ለማጥቃት በሚል የህወሃት ሠራዊት በዖጋዴን እጅግ አሰቃቂ የመብት ጥሰቶችን ፈጽሟል። ልዩ ፖሊስ የሚባለው የተቋቋመው ከዚህ በኋላ ነበር። ይህ በህወሓት አደራጅነት የተቋቋመው የጭከና ቡድን በአብዲ ኢሌይ መሪነት በተደጋጋሚ በሶማሊ ክልል ግፍ ሲፈጽም ቆይቷል። ከዚህም አልፎ በኦሮሚያ ክልል ሰርጎ በመግባት በመቶዎች የሚቆጠሩ ገድሏል፤ አንድ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ደግሞ ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል።

ሒውማን ራይትስ ዎች እንደሚለው የሶማሊ ክልል ልዩ ፖሊስ መታደስ አለበት ከፍተኛ አመራሮቹም ለፍርድ መቅረብ አለባቸው። የኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን እኤአ በ2011 በበርካታ ጊዜያት የኦጋዴንን እስር ቤት ጎብኝቶ ነበር። ይህንን ተከትሎ ተቀናበረ የሚባለው ሪፖርት ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም፤ ለደረሰው የሰብኣዊ መብቶች ጥሰት የተወሰደ ካለ ምን ዓይነት እርምጃ እንደተወሰደ ምንም የተነገረ ነገር የለም።

ፎቶ፤ አብዲ ኢሌይ ከህወሓት “ጄኔራሎች” ጋር፤ ከኢንተርኔት የተገኘ

ነገር ግን በርካታ የቀድሞ እስረኞች እንደሚሉት ኮሚሽኑ ወደ እስር ቤቱ ሲመጣ በግልጽ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚታወቁ በርካታ ህጻናትና እርጉዝ ሴቶች በምሥጢር ክፍል እንዲደበቁ ተደርገዋል፤ ወይም ከእስር ቤቱ ወጥተው ወደ ሌላ ስፍራ ተወስደዋል። ሌሎች ደግሞ ለኮሚሽኑ ምን ማለት እንዳለባቸው በኃላፊዎች ተነግሯቸዋል፤ ይህንን ችላ ብለው በግልጽ የተናገሩ አሰቃቂ የአጸፋ ቅጣት ተቀብለዋል።

ስለዚህ በኦጋዴን አስር ቤት የሚፈጸመውን በተመለከተ የሰብዓዊ መብቶችን ጥሰት የሚመረምሩ ኤክስፐርቶች ያሉበት የፌዴራል ኮሚሽን ጠ/ሚ/ሩ ማቋቋም አለባቸው፤ ይህ ምርመራ ሥልጣንን እና የሥራ ደረጃን ሳይሌ መካሄድ አለበት ይላል የዘገባው መረጃ። “በኦጋዴን እስር ቤት የሚፈጸመውን ግፍ በቸልታ ልናየው የሚገባ አይደለም” ይላሉ ፊሊክስ ሆርን፤ “ዶ/ር ዐቢይ ስቅየትን በአደባባይ መኮነናቸውን መቀጠል አለባቸው፤ ከዚህም በተጨማሪ በኦጋዴን እስር ቤት የሚፈጸመውን በተመለከተ እርምጃ በመውሰድ ስቅየትን በማስቆም ተጠያቂነትን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በግልጽ ማሳየት ይገባቸዋል” ብለዋል።

ይህ የግፍ ቁልል የተከማቸበት ዘገባ፤ በኦጋዴን እስር ቤት ግፍና ስቅየት በመፈጸምና በማስፈጸም ተዋናኝ የሆኑትን የፌዴራሉ መንግሥት የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌንና ሌሎች ከፍተኛ የሶማሊ ክልል ባለሥልጣናትን ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ የሚያደርግ ነው።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።

ከዚህ በፊት ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ ያቀናበረውን እና “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ የታተመውን እዚህ ላይ ማንበብ ይቻላል።

ኢትዮጵያ: በሶማሌ ክልል እስር ቤት ዉስጥ የሚፈጸመው ማሰቃየት ከፍተኛ የመንግስት ባላስልጣናት በማይቋረጥ የመብት ጥሰት ዉስጥ እጃቸው አለበት።

“ልክ እንደ ሞቱት ነን” ሰቆቃ እና ሌሎች ግፎች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኦጋዴን እስር ቤት ዉስጥ።

(የመግቢያ ፎቶ፤ Satellite image of Jail Ogaden, Jijiga, Ethiopia, recorded on May 27, 2016. © CNES 2018 – Airbus DS 2018; Source Google Earth. All other pictures credit, HRW)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics, Social Tagged With: Full Width Top, HRW, human right abuse, Middle Column, ogaden, torture, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Yalabedew Somalie says

    July 8, 2018 03:58 am at 3:58 am

    Ebdu Elie,

    Your days are numbered along ewith that of TPLF – your step parent!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule