ቅድሚያ "የታሰሩ ይፈቱና አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳ" የሚለው ኢህአዴግን ሳይሆን “ተቃዋሚዎችን” አላስማምም፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች "ቅድሚያ ይፈቱ" የማያስማማቸው ተቃዋሚዎችን አንድ የማድረግ ሃሳብም አለ። ይህንን ሃሳብ የሚያራምደው ደግሞ ኢዴፓ ነው። የህብረቱን ጥያቄ በፕሮግራም ደረጃ አርቅቆ በይፋ ጥሪ ያቀረበውን ኢዴፓ ተቃዋሚዎች የሚያቀርቡትን ቅድመ ሁኔታ አይደግፍም። ይህንኑ ተከትሎ ኢዴፓ በኢህአዴግ ይደገፋሉ ተብለው ከሚታሙትና የቤተሰብ ጥርቅም የሆኑትን ካልሆነ በዚህ አቋሙ ያሰበውን ሊያሳካ እንደማይችል አስተያየት እየተሰጠ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ አካሄድ እንደተቀየረና ከቀድሞው ይልቅ እየከረረ መሄዱን ሁሉም ወገኖች ይስማሙበታል። በደጋፊና ተከታይ ብዛት ተጽዕኖ ፈጣሪ ወይም ተሰሚነት አላቸው የሚባሉት የብሄር ፓርቲዎች ይህንን የከረረውን … [Read more...] about የድርድር ቅድመ ጸብ “በተቃዋሚዎች” መካከል እና የጠብ-መንጃ “ሰላም” እስከመቼ?
Middle Column
መስጊዳቸው ለተቃጠለባቸው የአይሁድ ቤተመቅደስ ቁልፍ ተሰጣቸው
በቴክሳስ ጠቅላይ ግዛት በቪክቶሪያ ከተማ መሰጊዳቸው ለተቃጠለባቸው ሙስሊሞች በከተማዋ የሚገኘው የአይሁድ ምኩራብ በሩን ከፈተላቸው፡፡ እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በቪክቶሪ ቴክሳስ የሚገኘው እስላማዊ ማዕከል (መስጊድ) ቃጠሎ ደርሶበት ነበር፡፡ ይህንን የተመለከቱ በከተማው የሚገኘው የአይሁድ ማኅበረሰብ አባላት የአምልኮ ቦታቸውን ለሙስሊም ወገኖቻቸው መሰብሰቢ እንዲጠቀሙበት የምኩራባቸውን ቁልፍ ሰጥተዋቸዋል፡፡ “አሁን ያገኘነውን ዓይነት ዕርዳታና ድጋፍ አናገኝም ብዬ በፍጹም አልተጠራጠርኩም” ያሉት የእስላማዊ ማዕከሉ ፕሬዚዳት ዶ/ር ሻሒድ ሐሽሚ ናቸው፡፡ እንደ እርሳቸው የቀዶ ጥገና ባለሙያና የአይሁድ ቤተመቅደስ አባል የሆኑት ዶ/ር ጌሪ ብራንፍማን ወደ ዶ/ር ሻሒድ ቤት በመሄድ ቁልፉን አስረክበዋቸዋል፡፡ መስጊዱን እንደገና ለመሥራት ከዘጠና … [Read more...] about መስጊዳቸው ለተቃጠለባቸው የአይሁድ ቤተመቅደስ ቁልፍ ተሰጣቸው
ጻዕረ ሞትና መስፍን ወልደ ማርያም
አንደኛ፣ ገና በልጅነቴ አሥር ዓመት ግድም ሲሆነኝ አንድ በድቀድቂት ከእንጦጦ ወደታች የሚወርድ ኢጣልያዊና እኔ ተጋጠምን፤ እሱ በዚያ በጥቁር ድንጋይ ኮረት በረበረበበት መንገድ ላይ ሲጓዝ ወደ እንጦጦ የሚወጣ ወታደሮችን የጫነ ከባድ መኪና ቆሞ ነበር፤ በዚያ መኪና ላይ አንድ ዝንጀሮ ነበር፤ የኔ አትኩሮት በዚህ ዝንጀሮ ላይ ነበር! እንደሚመስለኝ ዝንጀሮውን እያየሁ ስሮጥ ከድቅድቂቱ ጋር ተገናኘን፤ እኔ ከስር በተረበረበው የጥቁር ድንጋይ ኮረት ላይ፣ ድቅድቂቱ ደግሞ የእኔን ራስ ጨፍልቆ! ምኒልክ ሀኪም ቤት ከስንት ቀኖች በኋላ የካቶሊክ መነኮሳት አስታማሚዎች ከነመለዮአቸው አልጋዬ አጠገብ ቆመው በትልቅ የበሽተኞች ድንኳን ውስጥ በአንዱ መደዳ ውስጥ ተኝቼ ነቃሁ፤ መድኃኔ ዓለም ማንን ልኮ የእኔን ጭንቅላት ከድንጋዩና ከድቅድቂቱ መክቶ እንዳዳነኝ አላውቅም፡፡ ሁለተኛ ከሶደሬ መውጫ ላይ በመቶ … [Read more...] about ጻዕረ ሞትና መስፍን ወልደ ማርያም
ፖለቲከኞችን አስሮ ድርድር፤ ካድሬ አሰልፎ እርቅ – “አዙረኝ አታዙረኝ” እንዳይሆን
ከውጭ ያለው ችግር ከተፋዘዘ ብሄራዊ ስሜት ጋር!! ኢህአዴግ በከፋ ቀውስ ውስጥ ይገኛል። ቀውሱ ከውስጥ ብቻ ሳይሆን ከውጭም ነው። ሰሞኑን ይፋ የሆኑ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ውጥረቱ በውስጥ ካለው ብሄራዊ አንድነትና ኅብረት መደብዘዝ፣ ህዝብ እያደር ስርዓቱን መጠየፉ፣ የራሱ የፓርቲው መበስበስና በሙስና መርከስ፣ የውስጥ የእርስ በእርስ መከዳዳታን በአይነ ቁራኛ መጠባበቅና ከአቻ ፓርቲዎች መንሸራተት ጋር ተዳምሮ አስጊ ሆኗል። ከውጭ - የሚደገስልን ቀውስ በጨረፍታ ለማንሳት ያህል ግብጽ ዑጋንዳን ይዛ በደቡብ ሱዳን ውስጥ እያቦኩ ያሉት ጉዳይና ደቡብ ሱዳን በማስታውቂያ ሚኒስትሯ አማካሪ በኩል አቋሟን ይፋ ማድረጓ ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያበረክተው የቀውስ ፍም ተደርጎ እየተወሰደ ነው። ከኢህአዴግ የቅርብ ሰዎች እንደሚሰማው ዑጋንዳ በደቡብ ሱዳን ድንበሯ አካባቢ ኃይል … [Read more...] about ፖለቲከኞችን አስሮ ድርድር፤ ካድሬ አሰልፎ እርቅ – “አዙረኝ አታዙረኝ” እንዳይሆን
ቀዝቃዛዉ ጥምቀትና የበረከት ስምዖን “ግብረኃይል” በጎንደር
ጥምቀትን ያለ ጎንደር ማሰብ የሚቻል አይደለም። ጥምቀት ከኃይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር ባህላዊ ገጽታ የሚንጸባረቅበት ጉምቱ የአደባባይ በዓል ነበር። የጎንደር ጥምቀት እንኳን ለቱሪስቶች ለቀየዉ ነዋሪዎችም ታይቶ የሚጠገብ አልነበረም። በየዓመቱ በአማካይ 1500 የሚደርሱ ቱሪስቶች ከተለያዮ የአለማችን ክፍሎች ተሰባስበዉ ጎንደር ላይ ይከትሙ ነበር። ታይቶ የማይጠገበዉን የጥምቀት ትዕይንት ከከተራ እስከ ሚካኤል ንግስ ድረስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚጎበኙት የዉጭ አገር ቱሪስቶች ብቻ ሳይሆን የአገር ዉስጥ ጎብኝዎችም በስፋት ይታደሙ ነበር። “ነበር እንዲህ ቅርብ ኑሯል ለካ” እንድትል ንግስት ጣይቱ ብጡል፤ የ2009 የጥምቀት በዓል አከባበር በጎንደር፡-ያን አስደማሚ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ትዕይንት “ነበር” አድርጎት አልፏል። የወልቃት የአማራ ማንነት ጥያቄን አስታኮ የተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ አመጽ … [Read more...] about ቀዝቃዛዉ ጥምቀትና የበረከት ስምዖን “ግብረኃይል” በጎንደር
በሚገዛው ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀ አገዛዝ – ተግባሩን “ስኬት” ሲል ገመገመ
ግድያ፣ አፈና፣ ቶርቸር፣ ረሃብ፣ የጅምላ ጭፋጨፋ - ስኬት በቅርቡ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ እርሱ “አሽከር” ለሚባለው የኢህአዴግ ሸንጎ ንግግር ሲያደርግ ኢህአዴግ የወሰዳቸውና እየወሰደ ያለው እጅግ አረመኔነት የተሞላበት አሠራር የሚደነቀ መሆኑን አስታውቋል። “መቶ በመቶ መርጦኛል፤ እመራዋለሁ” በሚለው ህዝብ ላይ ለታወጀው ክተት አስፈጻሚ መሆኑ፣ ንጹሃንን መጨፍጨፋቸው፣ መታሰራቸው፣ መታፈናቸው፣ ለስቃይ መዳረጋቸው “ስኬት” መሆኑንን ማመልከቱ “የዘመኑ አስገራሚ ትንግርት” እየተባለ ነው። በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖችን በግፍ አስሮ የሚያሰቃይ አገዛዝ ራሱን በጥንካሬ ሲፈርጅ መስማት አሳዛኝና አሳፋሪ እንደሆነ የሚጠቁሙ እንዳሉት “ግድያ፣ አፈና፣ ማሰቃየት፣ ረሃብ፣ የጅምላ ጭፋጨፋ ... ስኬት ተብሎ ሲቀርብ የሚያዳምጥና የሚያጨበጭብ ሸንጎ ህይወት የሌለው በድን ነው” ቢያንስ … [Read more...] about በሚገዛው ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀ አገዛዝ – ተግባሩን “ስኬት” ሲል ገመገመ
የማናውቀው ታሪካችን
ታሪካችንን ባለማወቃችን ሁሌም ወደኋላ በመገስገስ ላይ እንገኛለን፤ ሰሞኑን አንዳንድ ዜና መዋዕሎችን ማንበብ ጀምሬ እስካሁን አራት ያህል አንብቤአለሁ፤ ከዚህ በፊት እየተንገዳገድሁ በግዕዝ አንብቤአቸዋለሁ፤ ዛሬ የሲራክ አሳታሚ ድርጅት በአማርኛ እያሳተማቸው በመሆኑ ምስጋና ይድረሰውና ሳልንገዳገድ በአማርኛ እያነበብሁ ነው፤ በዚህ ንባቤ ውስጥ አንዳንድ ያገኘኋቸው ሀሳቦች ስለራሳችን ያለን እውቀት ምን ያህል ጎደሎ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው፤ ለዛሬው ሁለት ሀሳቦችን ከላሊበላ ዜና መዋዕል፤ አንድ ደግሞ ከሱስንዮስ መርጫለሁ፤ እኔን እንዳስደነቁኝ ሌሎችንም ያስደንቃሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ አንደኛ፤ ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በ1160 ዓ.ም. የነገሠው ገብረ መስቀል የሚባለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት "በነገሠ በአሥር ዓመቱ መራ ከተባለው አጠገብ የነበረውን ቤተ መንግሥት ወደሌላ ለማዛወር አስቦ … [Read more...] about የማናውቀው ታሪካችን
የህወሃት ራስህን አድን “ጥልቅ ተሃድሶ” ሦስት ኦህዴድን ፈጠረ
ህወሃት በተለያዩ ጊዚያት አደጋ ሲገጥመው የሚዘይደው የማምለጫ ስልት በአካባቢው ባሉ “አጋሮቹ” ዘንድ “ዘመቻ ራስህን አድን” የሚል ስያሜ አለው። ይኸው ዘመቻ በኦሮሚያ ኦህዴድን እንዳራባው ነው የሚነገረው። የጎልጉል የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት ኦህዴድ ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ ችግር ተዳፈነ እንጂ አልበረደም። ይልቁኑም በድንገት አስተዳደራዊ መዋቅር ሊናጋ ይችላል የሚል ስጋት አለ። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) አንጋቾቹን አሰማርቶ በሺህ የሚቆጠሩ ኦሮሞ ወገኖችን መፍጀቱ፣ በየማጎሪያው ሰብስቦ ማሰቃየቱና በዚሁ ሳብያ የተፈጠረው ማኅበራዊ ቀውስ ከፍተኛ እንደሆነ የሚናገሩት የመረጃው ሰዎች፣ በዚሁ ሳቢያ ኦህዴድ ወደ ሦስት አካልነት መራባቱን፣ ይህ ድርጅታዊ መባዛት የ“ጥልቁ ተሃድሶ” ውጤት እንደሆነ ነው የሚናገሩት። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባሰባሰበው መረጃ መሰረት … [Read more...] about የህወሃት ራስህን አድን “ጥልቅ ተሃድሶ” ሦስት ኦህዴድን ፈጠረ
ኢህአዴግ በአሜሪካ የጉዞ ማዕቀብ ክፉኛ ተሽመድምዷል
አሜሪካ ባልተለመደ ሁኔታ ኢህአዴግን ከመውቀስ አልፋ እያስጠነቀቀች ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ የጉዞ ማዕቀቡ እንዲነሳለት እየወተወተ ስለመሆኑ በተለያዩ መገናኛዎች ተደምጧል። የጎልጉል መረጃ አቀባይ የዲፕሎማሲ ምንጮች እንዳሉት አሜሪካ ለኢህአዴግ ጥያቄ መልሷ “ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም” የሚል ሆኗል። እነዚሁ ክፍሎች እንደሚሉት ቅድመ ሁኔታ ተቀምጧል። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የዴሞክራሲ፣ የሠብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ የሚመራ ልዑክ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ የአራት ቀን የስራ ቆይታ ባደረገበት ወቅት “በግልጽ ተወያይተናል” የሚል መግለጫ ቢሰጥም፣ እንደሚባለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። ለቪኦኤ አማርኛው ክፍል ብቻ መግለጫ የሰጡት ቶም ማሊኖዊስኪ “ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ሃላፊነት” እንደሆነ መናገራቸው የተደረሰና … [Read more...] about ኢህአዴግ በአሜሪካ የጉዞ ማዕቀብ ክፉኛ ተሽመድምዷል
በጋምቤላ የከሸፈው “ኢንቨስትመንት”
በጋምቤላ የአኙዋክ ተወላጆች ተጨፍጭፈውና ከመሬታቸው ተፈናቅለው “ለሰፋፊ እርሻ” በሚል ሲቸበቸብ ከነበረው መሬት “ወደ ሥራ የገባው” 15በመቶው ብቻ መሆኑን ህወሃት/ኢህአዴግ አስታወቀ፡፡ ለ“እርሻ ልማት” በሚል 5ቢሊዮን ብር ብድር ተሰጥቷል፡፡ የመሬት ካርታ “ከቢሮ ውጪ በመኖሪያ ቤቶችና በጫት ቤት ውስጥ” ሲሰራ ቆይቷል፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኃላፊ የነበረው ኢሳያስ ባህረ ከሥልጣኑ የተነሳው “ብድር በመስጠቱ ሂደት ለተወሰኑ የባለሃብቶች ቡድን በማድላቱ ነው” ተባለ፡፡ በጋምቤላ በደል ደረሰብን በማለት አቤቱታ ያሰሙ የትግራይ “ባለሃብቶች” ለሃይለማርያም የቀረበው ሪፖርት “የተዛባ ነው” አሉ፡፡ በጋምቤላ ይህ ነው የማይባል ግፍና የዘር ማጽዳት ተካሂዶ ከምስኪን ረዳተቢሶች የተነጠቀው መሬት ከጥቅም ውጪ ሆኗል፡፡ ገና ከጅምሩ አሠራሩ ሁሉ ትክክል እንዳልሆነ በተለያዩ ሪፖርቶች … [Read more...] about በጋምቤላ የከሸፈው “ኢንቨስትመንት”










