- ግድያ፣ አፈና፣ ቶርቸር፣ ረሃብ፣ የጅምላ ጭፋጨፋ – ስኬት
በቅርቡ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ እርሱ “አሽከር” ለሚባለው የኢህአዴግ ሸንጎ ንግግር ሲያደርግ ኢህአዴግ የወሰዳቸውና እየወሰደ ያለው እጅግ አረመኔነት የተሞላበት አሠራር የሚደነቀ መሆኑን አስታውቋል። “መቶ በመቶ መርጦኛል፤ እመራዋለሁ” በሚለው ህዝብ ላይ ለታወጀው ክተት አስፈጻሚ መሆኑ፣ ንጹሃንን መጨፍጨፋቸው፣ መታሰራቸው፣ መታፈናቸው፣ ለስቃይ መዳረጋቸው “ስኬት” መሆኑንን ማመልከቱ “የዘመኑ አስገራሚ ትንግርት” እየተባለ ነው።
በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖችን በግፍ አስሮ የሚያሰቃይ አገዛዝ ራሱን በጥንካሬ ሲፈርጅ መስማት አሳዛኝና አሳፋሪ እንደሆነ የሚጠቁሙ እንዳሉት “ግድያ፣ አፈና፣ ማሰቃየት፣ ረሃብ፣ የጅምላ ጭፋጨፋ … ስኬት ተብሎ ሲቀርብ የሚያዳምጥና የሚያጨበጭብ ሸንጎ ህይወት የሌለው በድን ነው” ቢያንስ ለማስመሰል እንኳን የሚከራከር “ሰው” አለመታየቱ የሥርዓቱ የመገልማት ውጤት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን የላኩልን ገልጸዋል።
እናት ልጇ አስከሬን ላይ ተቀመጣ በምትገረፍበት፣ ህዝብ በጅምላ በሚጨፈጨፈበት አገር መሪ መሆን አንገት የሚያስደፋ መሆን ሲገባው፣ ደረት ገልብጦ “ዓለም ጠንካራ ናችሁ አለን ማለት የስብዕና መገልማት ነው” ሲሉ ተቃውሞ ያሰሙ ጥቂት አይደሉም።
“ድህነትና ረሃብ የሚፈጀውን ህዝብ እየመሩ ማሽካካት ከነተበ አዕምሮ ባለቤቶች የሚሰማ የትዕቢት ጣር ነው” ሲሉ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ እንደሚሉት “ሃይለማርያም የኮሪዶር ወሬና ያደባባይ ዜና መለየት እስኪሳነው ድረስ ታውሯል” ሲሉ ይነቅፉታል። ኢህአዴጎችን ልክ እንደ መንደር ቡድን ኳስ ተጫዋቾች የመሰሏቸው አስተያየት ሰጪ፣ “ህጻናት የበረኪና ዋንጫ ከወሰዱ በኋላ ‘ወንዳታ’ እየተባባሉ እንደሚሞከሻሹት ሁሉ፣ ኢህአዴጎችም ‘ጠንካራ ተባልን ብራቮ፣ ወንዳታ፣ ጫር …’ እየተባባሉ የሚማማሉ በደምና በዝርፊያ የሰከሩ፣ እስከ አፍንጫው የታጠቁ የተሰበሰቡበት የባንዳዎችና የተላላኪዎች ማኅበር ነው” ብለዋል፡፡
እኒሁ ክፍሎች ሰሞኑንን ራሳቸው የሰየሟቸውን የሃይማኖት “አባቶች” ስብስበው ያስተላለፉት የሰላም ጥሪ አሁንም ካላቸው የታወረ አስተሳሰብ የሚመነጭ ማታለል እንደሆነ ተጠቁሟል። የሃይማኖት አስተዳዳሪዎችን ሰብስቦ የመክፈቻና የመዝጊያ ቡራኬ የሰጡት የኢህአዴግ ካድሬዎች የእምነት ተቋማት ምን ያህል ነጻነት የሌላቸው አጎብዳጅና ታዛዥ መሆናቸውን ያረጋገጠ ነው።
ያስቀየሙትን፣ የገደሉትን፣ በቂም የሚቀጠቅጡትን፣ የሚያስሩትን፣ የሚያሳድዱትን ህዝብ ይቅርታ በመጠየቅ ወደ እውነተኛ እርቅ መምጣት የተቀደሰ ሃሳብ ቢሆንም እነሱ ግን አርከሰውታል። ህዝብ በማንኛውም ጉዳይ እንዳያምናቸው ከማድረግ የዘለለ ውጤትም አያመጡም ሲሉ አስተያየት ሰጪዎችህ ተናገረዋል። ሃይለማርያምን አውቀዋለሁ የሚሉ አስተያየት ሰጪ እርሱን አባል አድርጋ የምትጓዝ የሃዋርያት ቤተክርስቲያን ዝምታን መምረጧ አሳዛኝ እንደሆነ አመልክተዋል።
ሃይለማርያም አሁን ድረስ በቤተክርስቲያኒቱ አባልነት ታቅፎ የተያዘ መሆኑንን የጠቆሙት አስተያየት ሰጪ፣ “ቤተክርስቲያን በገሃድ ህዝብ ላይ የጦርነት አዋጅ ያወጀን ሰው ተሸክማ ስትሄድ ዝምታ አግባብ አይደለምና ምዕመናን ይህንን ጥያቄ በማንሳት አስቸኳይ መልስ እንዲሰጣቸው ሊጠይቁ ይገባል። ይህ ካልሆነ የሃዋሪያት ቤተክርስቲያን በሃይለማርያም ታዛዥነት ለፈሰሰው የንጹሃን ደም እውቅና የመስጠት ያህል ይቆጠርባታል” ብለዋል። አያይዘውም የቤተክርስቲያኗ ዓለምአቀፍ አገልግሎት (ሚኒስትሪ) ይህንን እንዲያውቀው የሚመለከታቸው ሁሉ ደብዳቤ በመጻፍ እንዲያጋልጡ ጠይቀዋል። በተለይም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ለዚህ ጉዳይ ይፋዊ ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ ገፍተው እንዲሄዱ አሳስበዋል። ቤተሰቦቻቸውም ቢሆኑ ከዚህ አይነቱ ጉዳይ ራሳቸውን ነጻ ማድረጋቸውን በይፋ ሊመሰከሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የዝግጀት ክፍላችን ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ አስተያየት ለሚልኩ ሁሉ በሩ ክፍት ሲሆን ለተጠቀሰው የሃዋሪያት ቤተክርስቲያን ኦፊሳላዊ ጥያቄ እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ለማሳወቅ ይወዳል። (ፎቶ: Getty Images እና ዋኢማ)
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
ተሰማ እሸቴ says
በሚመራው ሳይሆን በሚገዛው ህዝብ ላይ ተብሎ ርዕሱ ይስተካከል። መምራትና ወያኔ ስለማይተወቁ ነው።
Editor says
ተሰማ እሸቴ
ከአክብሮት ምስጋና ጋር አስተካክለናል፡፡
ህወሃት “አስተዳደር” ወይም “መንግሥት” አይደለም – ሆኖም አያውቅም – መሆንም አይችልም! ለዚህ ነው በጽሁፎቻችን ሁልጊዜ “አገዛዝ” እያልን የምንጽፈው ነው፡፡ እርስዎም ትክክል ብለዋል፡፡
በዚህ ወቅት ለፈጸምነው ስህተት እያዘንን እርስዎም በፍጥነት የማረሚያ አስተያየት ስለላኩልን እናመሰግናለን፡፡
የጎልጉል አርታኢ
Yearada Lij says
I will also add for the editor to use the right organization that governs the country that is TPLF and No EPRDF. EPRDF is a cover up. Please use TPLF not EPRDF it is time to call a sped is a sped.
Editor says
Yearada Lij,
Thanks for your comment as well. Often times we use that as TPLF/EPRDF – ህወሃት/ኢህአዴግ
Again we appreciate you.
Editor
dergu temelese says
የጎጃም ሀዘን እና አጼ ዮሀንስ የመተማ ዘመቻ
አጼ ዮሀንስ ደርቦሾችን ልክ ለማስገባት ወደ መተማ ከመዝመታቸው በፊት ጎጃምን ወረው ጦራቸው የህዘቡን ቤቶች አቃጥሏል፣ ሴቶችን ደፍሯል፣ከብቶችን አርዷል፣ ነድቷል፣ የጎጃም ገበሬ በወዙ እና በላቡ ያፈራውን ሀብትና ንብረት በማጣቱ አምርሮ አዝኗል፡፡
በዚህም ምክንያት የጎጃም ህዝብ ሀዘኑን እንደሚከተለው በስንኝ ቋጥሯል፡፡
በሰላም ከመጡ ዮሀንስ ከመተማ፣
ጎጃም ማተብ የለው እግዜርም የለማ፡፡
ደርቡሾች የጎጃም ህዝብ ሀዘንም ረድቷቸው የአጼ ዮሀንስን ገድለውና አንገት ቆረጠው መውሰዳቸው በታሪክ ተጽፏል፡፡
ታሪክ ራስን ይደግማል
የወቅቱ የአጼ ዮሀንስ ልጆች ( ህወሀቶች) ኢትዮጵያውያንን እየገደሉና እየዘረፉ ነው፡፡
1/ ብአዴን የሚባል ለሆዳቸው ያደሩና ወገናቸውን የካዱ ባንዳዎችን አደራጅተው በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ እና በረቀቀ መንገድ ጎንደርን እና ጎጃምን እየዘረፉ ነው፡፡ የነገ አገር ገንቢ ወጣቶችንም እየጨፈጨፉ ነው፡፡ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የአማራ ህዝብ በተለያዩ ስልቶች እንደአጠፉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳይቀር ተነስቶ ራሳቸውም ተጨቃጭቀወበታል፡፡ ከስልቶቹም መካከል የኤድስ ህሙማንን ከሠራዊቱ ሰብስቦ በብር ሸለቆ በማስፈር፣ ትገሬ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችን በአማራ ክልል ገጠሮች በማሰማራት ሴቶች ለህክምና ሲሄዱ መሀን የሚያደርጉ መድሀኒቶችን በመውጋት፣ በበደኖ፣ በወተር፣ በሊማሊሞ፣ በሀረር፣ በባህርዳር በጥይት እና ከእነ ህይወታቸው በመቅበር ገድለዋል፡፡
2/ የወቅቱ የዮሀንስ ልጆች የጋምቤላን መሬት በኢንቬስትመንት ሰበብ ለመውረር ከ420 በላይ አኝዋኮችን በጠራራ ጸሀይ ገድለዋል ነባር ነዋሪዎችንም አፈናቅለዋል፡፡
3/ ከ 700 ሺ በላይ ሶማሌዎችን የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅትን ትደግፋላችሁ በማለት በተለያዩ ጊዚያት በጅምላ እንደገደሉ ከ800 ሺ ህዝብ በላይ መኖሪያ ቀየውን ጥሎ እንደተፈናቀለ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሆኖ ሥርዓቱን ያገለገለው እና የኢሳ ጎሳ ተወላጅ የሆነ ሻለቃ አሊ የተባለ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በ21/ 04/ 2009 ማጋለጡ እና በ20/05 /2009 ደግሞ የክልሉ ሆድ አደር ባለስልጣን ለማስተባበል መሞከሩ ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ ወያኔ እየተከተለ ያለው የመግደል እና የመዝረፍ ፖሊሲ ሀይ ባይ ያጣ እና ዳፈው ለልጅ ልጅ የሚተርፍ እየሆነ ነው፡፡
Mulugeta Andargie says
The Golguls!! You are dreaming, as I think, and as if you are concerned, for the unity of the country, you are trying distributing fake news for the readers.Please, try to filiter your propaganda!!! People are giving his own opinion without limit!!!
dergu temelese says
ዓለማቀፋዊነት በብሔረተኝነት ሲደፈቅ
ሊታመን በማይችል ፍጥነት ዓለማቀፋዊነት በብሔረተኝነት እየተደፈቀ ነው፡፡ የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕን ወደ ስልጣን ማማ ያወጣቸው ምንድን ነው ብለን ራሳችንን ብንጠይቅ ሶስት ምክንያቶች እናገኛለን፡፡
1ኛ/ የፖለቲከኞች ለከት ያጣ ውሸት እና ሙስና ህዝቡን ማስመረሩ እስኪ ወደ ነጋዴ እንዙር ማሰኘቱ፣
2ኛ/ በርካታ የአሜሪካ ህዝብ በእስላሞፎቢያ ( የእስላም ፍርሀት በሽታ) መጎዳቱና በቂ ህክምና ያለማግኘቱ እንዲሁም ስደተኞች ላይ ጥላቻ መፍጠሩ፤
3ኛ/ የስውር (ምስጢር) ማህበራት ሌላ የአለም ጦርነት ለማስነሳት ያላቸውን ዕቅድ ለማስፈጸም አመቺ ሁኔታ ማግኘታቸው ናቸው፡፡
የፖለቲከኞች ለከት ያጣ ውሸት እና ሙስና
ፖለቲከኞች ዲሞክራሲ፣ ሰላም፣የህግ የበላይነት ወ.ዘ.ተ…የመሳሰሉትን ወርቃማ እና አንጸባራቂ ቃላት 70 ዓመታት ሙሉ ለህዝቡ እንደ ቀለብ ሲሰፍሩለት የቀዩ ቢሆንም የጠብታ ያህል ግን ህዝብን ሊያርስ የሚችል እውነት ያለመሆኑ አንዱ የትራምፕ መመረጥ ምክንያት ነው፡፡ ገሀዱ ሀቅ የሚያሳየው ዲሞክራሲ ሳይሆን ኮንስፓይረሲ (የፖለቲካ አሻጥር)፣ ሰላም ሳይሆን ጦርነት ( የጦር መሻሪያ ለመሸጥ)፣ የህግ የበላይነት ሳይሆን ህግን መጣስ በበርካታ ፖለቲከኞች በአደባባይ እየተስፋፉ መጥተው ህዝቡን አሳዝነዋል፡፡ ሂላሪ ክሊንተን በሳል የፖለቲካ ሰው ቢሆንም በኢ-ሜላቸው በርካታ አስነዋሪ የሙስና ተግባራት ሲፈጽሙ እንደቆዩ የተጋለጡ ማፈሪያ ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ በባለቤታቸው በኩል በሚሊዮኖች የሚቀጠር ገንዘብ በሙስና አግኝተዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ በሳል የቢዝነስ ሰው ቢሆኑም የፖለቲካ ሀ ሁ የማያውቁ ናቸው፡፡ የሚናገሩት ሁሉ እብድ ናቸው እስከሚያሰኛቸው ለመሪነት ብቁ ያለመሆናቸውን እያወቀ ህዝብ መረጣቸው፡፡ ምክንያቱም ህዝቡ አጭበርባሪ ፖለቲከኞችን ከምንመርጥ ነጋደው ይግባና ከቻለ ይምራ ያለበለዚያ ይለይለት በሚል ውሳኔ ነው፡፡
የአሜሪካ ህዝብ በእስላሞፎቢያ ( የእስላም ፍርሀት በሽታ) መጎዳቱ
በርካታ አሜሪካውያን ከኒዮርክ መንትያ ህንጻዎች (9/11) ጥቃት እና ከአረቡ አብዮት በኋላ የእስልምና አክራሪዎች ሰለባ እንሆናለን የሚል ስጋት አለባቸው፡፡ ስጋታቸውን ያባባሰው ደግሞ በአቅራቢያቸውም በአክራሪዎች የደረሱ ፍንዳታዎች ናቸው፡፡ ማህበራዊ ድረ-ገጾችም ለአክራሪነት መስፋፋት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ስለሆነም አሜሪካ በስደተኞች የተመሠረተች አገር ብትሆንም ነባሮቹ አሜሪካውያን በአዲሶቹ ስደተኞች ላይ ፍርሀት አደረባቸው፡፡ ይህን አጋጣሚ ዶናልድ ትራምፕ ለምርጫቸው በሚገባ ተጠቅመውበታል፡፡ ራሳቸው ከጀርመን በመጡ ስደተኛ አያቶች የተገኙ ሆነው ሳለ የሜክሲኮ እና የአረቡ ዓለም ስደተኞችን ባለመቀበል የአሜሪካውያን ሰላም እንደሚከበር ቀስቅሰው ተመረጡ፡፡
የስውር (ምስጢር) ማህበራት ሌላ የአለም ጦርነት ለማስነሳት ያላቸውን ዕቅድ
መነሻቸውን እና ማዘዣ ጣቢያቸውን ከጀርመን ባቫርያ ግዘት ያደረጉ እና በአሜሪካ፣ በእንግሊዝ፣ ሩስያ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ቻይና፣ካናዳ የተሰራጩት የምስጢር ማህበራት ከእያንዳንዱ ፖለቲከኛ ወይም የአገር መሪ ፣ የቢዝነስ ሰው፣ ጄኔራል፣ ሳይንቲስት፣ የዜና አውታር፣ የሀይማኖት መሪ እና የሽብር ቡድን ጀርባ ሆነው የዓለምን ሀብት ለመቆጣጠር እንደሚሠሩ በርካታ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ እነዚህ ኢሉሙናቲ፣ ስከል ኤንድ ቦንስ፣ ኬኬኬ ወ.ዘ.ተ… በመሳሰሉ መጠሪያዎች የሚታወቁ የምስጢር ማህበራት የመጀመሪያውን እና የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ቀስቅሰዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ቢያልቅም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት አትርፈዋል፡፡ ህይወት ለአንዱ ሰርግ እና ምላሽ ሲሆን ለሌላው ሀዘን ነው፡፡
በዓለማችን ውስጥ የሚገኙ ታዋቂ የዜና አውታሮች ብነዚህ ማህበራት ይመራሉ፡፡ በቅርብ ጊዜ ኦክስፋም ባደረገው ጥናት የዓለማችን 8 ሰዎች ሀብት ከ3.6 ቢሊዮን ህዝብ ሀብት ጋር እኩል መሆኑን አሳውቋል፡፡ እነዚህ ፍጡራን አሁንም 100 ፐርሰንት የዓለምን ሀብት መቆጣጠር ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህም እንደ መሣሪያ የሚጠቀሙት ጦርነትን ነው፡፡ የ3ኛው የዓለም ጦርነትም አይቀሬ ነው፡፡ የዶናለድ ትራምፕ መመረጥ፣ የብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት መውጣት፣ በፈረንሳይ እና ጀርመን መጪ ምርጫዎች የብሔረተኞች ማሸነፍ ለሶስተኛው የኣለም ጦርነት መነሻ ምልክት ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው፡፡
ዓለማቀፋዊ የፖለቲካ ሥርዓት መኖር አመልካች የነበሩት የተባበሩት መንግሥት ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረት እና የተለያዩ ቃል ኪዳን ድርጅቶች መዳከም ለአዳዲስና ጦረኛ ብሄረተኛ ቡድኖች መፈልፈል ምክንት ይሆናል፡፡ የእስልምና አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል ሰበብም በመካከለኛው ምሥራቅ እና በአፍሪካ ግልጽ የጦርነት ዕቅድ ከወዲሁ እየወጣ ነው፡፡ ትራምፕ ኢራንን ማስጠንቀቁ እስራዔል እና መካከለኛው ምሥራቅ ወደ ግጭት የሚገቡበት የመጀመሪያ በር መሆኑ ነው፡፡
የእስለምና አክራሪነት የሚባለው ነገር ለምዕራባውያን ፖለቲከኞች እንደ መቀስቀሻ ከመሆኑ ባላፈ የእስልምና ወይም ክርስትና ሀይማኖት አክራሪነት የሚባል ነገር ጨርሶ የለም፡፡ አልቃይዳም ሆነ ሌሎች ቡድኖች ሀይማኖትን ተገን አድርገው የምራባውያንን ወረራ የሚታገሉ እንጂ የሀይማኖት ድርጅቶች አይደሉም፡፡ የ ISIS መሪ አቡበከር አልባግዳዲ አይሁድ መሆኑን የሚመሰክሩ ዓረቦች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ይህች ህግ እና ሥርዓት እየጠፉባት የመጣች ዓለም ወደ ሙሉ እና 3ኛው የዓለም ጦርነት አምርታ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦችን እልቂት ለማስተናገድ የምስጢር ማህበራት እየደገሱላት ነው፡፡