ተባዕት ዶሮ ከ280 - 360 ብር እየተሸጠ ነው! በግ ከ2,200 - 3,800 ብር የሽያጭ ዋጋ ደርሷል! ድልብ በሬ ከ25,000- 37,000 እየተሸጠ ነው! በረዥም ጊዜ ሂደት እየተዋረሰ የመጣው ኃይማኖታዊ በዓል አከባበራችን ከምግብ እና መጠጥ ጋር በጽኑ የተቆራኘ ነው፡፡ የአጽዋማትን ፍች በተመለከተ ከተቀመጡ ኃይማኖታዊ መርሆች ይልቅ ተለምዷዊ ድርጊቶች ገዥ ሐሳብ ሆነው ቀርበዋል፡፡ በዓላትን የታከከ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ደግሞ የአገሪቱ ኢኮኖሚ መገለጫ ሆኗል፡፡ መንግስታዊ ኃላፊነቱን በዘነጋ አገዛዝ ውስጥ ላለችው ኢትዮጵያ የመሠረታዊ ሸቀጦችና የቁም እንስሳት ዋጋ ንረት መታየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ የህዝቡ የድህነት ቁስል ላይ ለመቆም የማይሳቀቁ ስግብግብ ነጋዴዎች የዋጋ ንረቱን በማጐን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ቀጥሎ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ለመንግሥት ሠራተኞች … [Read more...] about በበዓል ዋጋ ንረት የምትታመሰው አዲስ አበባ!
Middle Column
ማዕከላዊ፤ የዜጐች ዋይታ ማማ! የስቃይ ማዕከል!
በማዕከላዊ ስቃይ ተፀንሶ ይወለዳል፤ ጡት ጠብቶ ዳዴ ብሎ ጐልምሶ ያረጅበታል!! እንደገና አዲስ የማሰቃያ ስልት ይወለዳል!! በማዕከላዊ በንጹሐን ዜጐች ደም የጨቀዩ ገራፊዎች ይርመሰመሱበታል!! ከዝግጅት ክፍሉ፡- ማዕከላዊ አገዛዙን በወታደራዊ የበላይነትና በደህንነቱ አቅም በቁጥጥር ስሩ ያዋለው ህወሓት፤ ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ እያደረሰ ያለውን ቃላት የማይገልፁት የዜጐች ስቃይ በተመለከተ ጎልጉል ድረገጽ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን ዜጐችና ቤተሰቦቻቸውን በማነጋገር ይህን ዘገባ በሁለት ክፍል አጠናቅሯል። ዘገባው የጋዜጠኛነት ሙያ የሚጠይቀውን (“የሕዝብ አይንና ጆሮ በመሆን የተደበቀውን ፈልፍሎ ማውጣት!” የሚለውን) ቀዳሚ መርህ በማድረግ በዳሰሳ ጥናት ተደግፎ የተዘጋጀ መሆኑን እንገልፃለን። የኢትዮጵያዊያን የስቃይ ጎሬ በሆነው ማዕከላዊ እስርቤት በ“ምርመራ” ወቅት በዜጎች ላይ … [Read more...] about ማዕከላዊ፤ የዜጐች ዋይታ ማማ! የስቃይ ማዕከል!
“ኢጂኣኦ” – የቻይናና አህያ ፍቅር – ቻይና በዓመት 4 ሚሊዮን የአህያ ሌጦ ትፈልጋለች
“አህያ ሲጠፋ እህል ማን ሊሸከም ነው? ሴት?!” የአህያ ሥጋና ቆዳ ንግድ እንደ ህገወጡ የአውራሪስ ቀንድ ንግድ እንዳይሆን ተሰግቷል “አህያ ልባችን ነው። አህያ ህልውናችን ነው። አህያ ቤተሰባችን ነው። አህያ ውለታውና ተግባሩ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ገዢዎቻችንም ቢሆኑ የአህያን ጥቅም በአግባቡ ያውቁታል። በበረሃ ሁሉን ችሎ እዚህ ያደረሳቸው አህያ ነው። እናም ጉዳዩ ከወሬ በላይ ነውና በሰከነ መልኩ ለማሰብ ፍላጎቱ ካለ ጊዜው ገናነው” ሲሉ የቱሉ ቦሎው ነዋሪ ይናገራሉ። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ያናገራቸው የቱሉ ቦሎ ነዋሪ እህል ነጋዴ ናቸው። እንደ ምሳሌ የሚያነሱት ጉዳይ የሚደመደመው በጥያቄ ነው። እንዲህ ይላሉ “አህያ ሲመናመን ከገጠር ማን ተሸክሞ ወደ ገበያ ያመጣ? ያው የፈረደባት ሴት በወገቧ ልትሸከም?” ለወትሮው “ሴት፣ የሴቶች መብት፣ የሴቶች የህግ … [Read more...] about “ኢጂኣኦ” – የቻይናና አህያ ፍቅር – ቻይና በዓመት 4 ሚሊዮን የአህያ ሌጦ ትፈልጋለች
ተራዛሚው የኦሮሚያ ድርቅ እና ያዘለው አደጋ!
በኦሮሚያ በሦስት ዞኖች ብቻ 241 ት/ቤቶች ተዘግተዋል፤ 114,751 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል! በቦረናና በጉጂ ዞኖች 127,010 ከብቶች በዘንድሮው ድርቅ ሞተዋል! ድርቅ ከፍ ሲልም ችጋርና ረሃብ ለኢትዮጵያ ተጠባቂ የስጋት ምንጭ ሆነው እንደቀጠሉ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ በተለይም ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ካሳለፍነው አስከፊ የርስ በርስ እና ከጐረቤት አገራት ጋር ከተደረጉ ጦርነቶች ጐን ለጐን ድርቅ፣ ችጋር፣ ረሃብ ሌላኛው የኢትዮጵያ አስከፊ የታሪክ ምዕራፍ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በቀደሙት ጊዜያት በየአስር ዓመታት ልዩነት ኢትዮጵያን በሰፊው ይጐበኛት የነበረው ድርቅ፤ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት አገሪቱን ደጋግሞ ሲያጠቃና የከፋ ማኅበራዊ ቀውስ ሲያስከትል ታይቷል፡፡ በተራዛሚው ጦርነት ፍፃሜ ማግስት በአገሪቱ የተከሰተው የ1988 ዓም ድርቅ የአማራ፣ የሶማሌ፣ የአፋር እና … [Read more...] about ተራዛሚው የኦሮሚያ ድርቅ እና ያዘለው አደጋ!
የብአዴን መክዳትና የ“በቀል” ፍርሃት የወለደው “የኢኮኖሚ አብዮት” በኦሮሚያ፤
“ህወሃት የፈጸመው ግፍ በየትኛውም ዘመን የሚረሳ አይሆንም” በህወሃት ገደብ የለሽ የሥልጣን ፍቅርና የቁስ ሰቀቀን ውልቅልቋ እየወጣ ያለችው ኢትዮጵያ ከፍታው ርቋት የቁልቁለቱን ጉዞ ተያይዛዋለች። ለወጣበት ዘውግ ልዕልና የሚተጋው ህወሃት ህግና ሞራል በማይዳኘው ድርጅታዊ ቀኖናው እየተመራ ኢትዮጵያን ማድማቱን ቀጥሎበታል። እስር፣ ቶርቸር፣ ስቃይ፣ ስደት፣ ሞትና የግዞት ኑሮ ከህወሃት ዘውግ ጥላ ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እድል ፈንታ ሆኗል። ከነዚህ በመከራ ከሚዳክረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል አንዱ የኦሮሞ ሕዝብ ነው። እውነታው ግን ሰፊና ለም የሆነ መሬት ላይ የሰፈረው የኦሮሞ ሕዝብ በቁመቱ ልክ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱ ሊከበርለት እንዳልቻለ ወራሪው ህወሃት ራሱ ለፖለቲካ ፍጆታም ቢሆን ያመነውና ማንም ሊከደው የማይችል የአደባባይ ሃቅ ነው። በአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ላይ … [Read more...] about የብአዴን መክዳትና የ“በቀል” ፍርሃት የወለደው “የኢኮኖሚ አብዮት” በኦሮሚያ፤
“ፋሲል ከነማ” – የትውልድ ዓመጽ አርማ!
“ቸቸላ” - በጎንደር የአማራ የልብ እሳት ማብረጃ ማማ!! ፋሲል ከነማ - ቶራ ቦራ! ማስታወሻ፤ ቶራ ቦራ አፍጋኒስታን ውስጥ ያለና ቢንላደን የሚደበቅባቸው ተራራዎችና የዋሻ ምሽጎች ናቸው። ፋሲል ከነማም የቶራ ቦራ ምሳሌ ነው። ቶራ ቦራ ብዙ ጊዜ ይደበደባል ግን ጉዳት አይደርስም። ቢደርስም ይህ ነው የሚባል አይደለም። ፋሲል ከነማም ምሽግ ነው! ቶራ ቦራ! በተቃራኒው ዱሮ ትልቅ የፖለቲካ ዋሻ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ ቶራ ቦራነቱ ቀርቶ ሜዳ ሆኗል። ማንም እንደፈለገ የሚፈነጭበት ግልብ ሜዳ! ሁሉም ባይሆኑም አስገራሚና ሊፋቅ የማይችል የምስረታ ታሪክ ያላቸው ክለቦች አሉን። አሁን አዲስ አበባ ስታዲየም የሚንከላወሱት ብቻ ሳይሆኑ በመላው አገሪቱ፣ በየሰፈሩ፣ በየከተማው ... ተቋቁመው የከሰሙት ክለቦች የምስረታ ታሪክ የሚያጠናው ቢገኝ ከቅሪላው ጀርባ ያለውን ጉዳይ … [Read more...] about “ፋሲል ከነማ” – የትውልድ ዓመጽ አርማ!
በህወሃት የታፈነው ድርቅ ወደ ረሃብ እያደገ ነው፤ ት/ቤቶች ተዘግተዋል!
የኢትዮጵያ ሶማሌ ዘጠኙም ዞኖች ሙሉ በሙሉ የድርቁ ሰለባ ሆነዋል! በክልሉ 437 የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከድርቁ ጋር በተያያዘ ተዘግተዋል፤ 183,090 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል! የእርስበርስ ዕልቂት ያሰጋል! የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሁለት ወራት ውስጥ ባወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች ምስራቅ አፍሪካ የከፋ ድርቅ መከሰቱንና ዓለም የዕርዳታ እጆቹን ለአገራቱ እንዲዘረጋ በተከታታይ ሪፖርቶቹ ተማጽኗል፡፡ እንደ በዘገባው ከሆነ ድርቁ የከፋባቸው ተጠቃሽ አገራት ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ የተጠቀሱት መንግሥታት ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የዕርዳታ እጃቸውን በመዘርጋት፤ በተባበሩት መንግሥታት በኩል የአውሮጳ ህብረትና ሌሎች ለጋሾች በከፋ ድርቅ ላይ ለሚገኙት አገራት ዕርዳታ እየሰጡ ናቸው፡፡ በተባበሩት መንግስታት … [Read more...] about በህወሃት የታፈነው ድርቅ ወደ ረሃብ እያደገ ነው፤ ት/ቤቶች ተዘግተዋል!
አድዋን ወደ ፖለቲካ ድል መቀየር ለምን ተሳነን? እርግማን ሦስት “ምኒልክ የእኛ ነው”
ከዝግጅት ክፍሉ:- “አድዋን የሚያህል ወታደራዊ ድል ስለምን ወደ ፖለቲካዊ ድል መቀየር ተሳነን?” በሚል ርዕስ ተከታታ ጽሁፎች ስናትም ሰንብተናል፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ሙሉ ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡ እርግማን ሁለት “ሚኒልክ ኤርትራን ሸጠ፤ ትግራይን በደለ” የሚለው ሁለተኛው ክፍል ደግሞ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ በሦስተኛው ክፍል የመጨረሻውንና ማጠቃለያውን ይዘን ቀርበናል፡፡ አፄ ምኒልክ ባልዋለበት ማዋል የዘመናችን “ፖለቲከኞች” ከታሪክ የሚያገኙት ግብር - አልባ ትርፍ ሆኗል፡፡ የአፄውን አገር የማቅናትና የግዛት አንድነትን የማስከበር ዘመቻ በ“ቅኝ ግዛት” የሚተረጉሙት እንዳሉ ሁሉ የማዕከላዊ መንግስት መቀመጫ ከትግራይ ወደ ሸዋ በመዞሩ ምኒልክን “ባንዳ” እና “አገር ሻጭ” እያሉ የአባቶቻቸውን ዝንፈት በአደባባይ ምኒልክ ላይ የሚለጥፉ ብልጣብልጥ “ፖለቲከኞች” … [Read more...] about አድዋን ወደ ፖለቲካ ድል መቀየር ለምን ተሳነን? እርግማን ሦስት “ምኒልክ የእኛ ነው”
የሕይወት ዋጋ – “አጥንታቸውን እሾህ ያርገው”
በ2009 ዓ.ም. ቆሼ የሚባል ሰፈር ወይም መንደር ተፈጠረ፤ ቆሼ ማለት ቆሻሻን ማቆላመጫ ነው፤ ቆሻሽዬ ማለት ነው፤ ቆሼ የቆሻሻ ተራራ ነው፤ በዚያ የቆሻሻ ተራራ ዙሪያ መሄጃ የሌላቸው ሰፈሩበት፤ ጥንት ሴትዮዋ እንዳለችው፡- እሾህ ብቻ ሆነ እግሬን ብዳብሰው እንዴት መራመጃ መሄጃ ያጣል ሰው! ሴትዮዋ ይህንን ያንጎራጎረችው ከብዙ ትውልዶች በፊት ነው፤ ጉልበተኞች የኢትዮጵያን ሰዓት ሰንገው ስለያዙት አይነቀነቅም! ባለህበት ሂድ! ነው፤ ዛሬም መሄጃ የለም፤ ቆሻሻንም የሙጢኝ ቢሉ ማምለጥ አይቻልም፡፡ እነዚህ አንድ መቶ አሥራ ሦስት ሟቾች በርግጥ ሰዎች ናቸው? በርግጥ ኢትዮጵያን ናቸው? የምናገረው ጠፍቶኛልና ጥያቄዎች ብቻ ልጠይቅ፡-- ቤታቸውን ጉልበተኞች አፍርሰውባቸው፣ መሬታቸውን ሰማይ-ጠቀስ ወይም መንገድ ለመሥራት መሬታቸውን ወስደውባቸው የሚደርሱበት አጥተው፣ ባዶ ቦታ ፈልገው … [Read more...] about የሕይወት ዋጋ – “አጥንታቸውን እሾህ ያርገው”
የቆሻሻ ፖለቲካ ተምሳሌት – ቆሼ!! “ድህነት ዋናው ጠላታችን ነው”
የግፍ ክምር ናዳው ምን ያህል የሚከፋ ይሆን? አዲስ አበባ ቃላት የማይገልጹዋት፤ ስሟ ግብሯን የማይወክል የግፍ ከተማ ናት፡፡ በአንድ በኩል ሥጋ በል ለሆኑ የቤት እንሰሳዎቻቸው የዕለት ተዕለት ምግብ ከሱፐርማርኬት የታሸገ ሥጋ ገዝተው የሚመግቡ ባለጠጎች፤ በሚስታቸውና በልጆቻቸው እንዲሁም በደርዘን ውሽሞቻቸው ሥም የተንጣለሉ ቪላ ቤቶችንና ግዙፍ ህንፃዎችን የገነቡ የገዥው ኃይል ማኅበራዊ መሰረት የሆኑ የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪ የከተማ ዘራፊዎች (Marauders’ city) “ወጋ ትበለይኪ” እያሉ የሚምነሸነሹባት፤ ደሃ-ገፊ መሐል አሟቂ፤ የቁስ ሰቀቀን የተጫናቸው የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ዘዋሪ ልሒቃን ከተማ ናት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዕለት ምግባቸውን ከቆሻሻ ገንዳ የሚለቅሙ አንጀታቸው በረሃብ የታጠፈ ጐስቋላ ምንዱባን በጐዳና የሚኖሩባት፤ የወር ደመወዛቸውን ለአልቦ-አንጀት (ርህራሄ የለሽ!) … [Read more...] about የቆሻሻ ፖለቲካ ተምሳሌት – ቆሼ!! “ድህነት ዋናው ጠላታችን ነው”










