• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ኢጂኣኦ” – የቻይናና አህያ ፍቅር – ቻይና በዓመት 4 ሚሊዮን የአህያ ሌጦ ትፈልጋለች

April 6, 2017 10:52 pm by Editor 2 Comments

  • “አህያ ሲጠፋ እህል ማን ሊሸከም ነው? ሴት?!”
  • የአህያ ሥጋና ቆዳ ንግድ እንደ ህገወጡ የአውራሪስ ቀንድ ንግድ እንዳይሆን ተሰግቷል

“አህያ ልባችን ነው። አህያ ህልውናችን ነው። አህያ ቤተሰባችን ነው። አህያ ውለታውና ተግባሩ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ገዢዎቻችንም ቢሆኑ የአህያን ጥቅም በአግባቡ ያውቁታል። በበረሃ ሁሉን ችሎ እዚህ ያደረሳቸው አህያ ነው። እናም ጉዳዩ ከወሬ በላይ ነውና በሰከነ መልኩ ለማሰብ ፍላጎቱ ካለ ጊዜው ገናነው” ሲሉ የቱሉ ቦሎው ነዋሪ ይናገራሉ።

የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ያናገራቸው የቱሉ ቦሎ ነዋሪ እህል ነጋዴ ናቸው። እንደ ምሳሌ የሚያነሱት ጉዳይ የሚደመደመው በጥያቄ ነው። እንዲህ ይላሉ “አህያ ሲመናመን ከገጠር ማን ተሸክሞ ወደ ገበያ ያመጣ? ያው የፈረደባት ሴት በወገቧ ልትሸከም?”

ለወትሮው “ሴት፣ የሴቶች መብት፣ የሴቶች የህግ ባለሙያዎች ማህበር …” በሚል ተቋቁመው በጾታ ስም ንግድ ከሚያካሂዱት ተቋማት ይህ ጉዳይ አለመነሳቱ ከፍተኛ ትዝብትን የጣለ ጉዳይ ሆኗል። በባልና ሚስት ጉዳይ ተንደርድረው በመግባት ፍቺን የሚያውጁት የሴት ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ማህበራት የአህያ እርድ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ግንባታውን ሳይሆን የችግሩን አሳሳቢነት እንኳን ለመጠቆም አለመሞከራቸው አሳፋሪ እንደሆነ ለዘጋቢያችን የጠቆሙት አሉ።

አህያ ለመግዛት ያቀዱና የቤት ውስጥ ጣጣቸውን ለማቃለል ያሰቡ እንዴት ነው ከቻይና ጋር ተወዳድረው የሚገዙት? የገጠሪቱ ኢትዮጵያ፣ በተለይም ኢህአዴግ የሚምልበትና 80 በመቶ ይሆናል የሚባለው አርሶ አደር በአህያ ከመጫን ወደ ጫንቃው እንዲዛወር፣ ሴቷም በጀርባዋ ወደመሸከም “እንድታድግ” መፍረድ አግባብ ነው? ይህ ጥያቄ ምላሽ ያስፈልገዋል። ለዛሬው “ሰባት ሚሊዮን አህያ አለን” የሚለው አስተሳሰብ መልስ እንደማይሆን ከወዲሁ እየጠቆምን፣ ጉዳዩን ችግሩ ካጋጠማቸው አገሮች ተመክሮ አንጻር እንየው። ቻይና በዓመት አራት ሚሊዮን የአህያ ሌጦ ትፈልጋለችና ኮታውን መሙላት የኢህአዴግ ተግባር ሊሆን ነው ማለት ነው።

የአፍሪካን አምባገነኖች በሚፈልጉት ጥቅም፣ ወንበራቸው እንዳይንገዳገድ እየረዳችና እየደለልች ሃብት የምትዘርፈው ቻይና የአህያ ፍላጎቷን ለማሟላት የተጠናከረ እንቅስቃሴ ላይ ነች። በዚሁ የዝርፊያ ተግባራቸው የተለያዩ አገራትን ረግጠዋል። እንዳሰቡትም አድርገዋል። በስተመጨረሻ ችግሩ ሊጋፉት የሚችሉት ባለመሆኑ ከተለያዩ የምዕራብና ሰሜን አፍሪካ አገራት ተባረሩ። የአህያ እርድ ንግድ የጣፈጣቸው ቻይናውያን በምትኩ ዓይናቸውን ወደ ምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ተክለዋል።

በራሷ ምድር የአህያ ፍላጎት መጨመርና የአቅርቦቱ መቀነስ ያሳሰባት ቻይና ጉዳዩ የአፍሪካ አህዮች ላይ ትኩረት እንድታደርግ አስገድዷታል። እኤአ በ1990ዎቹ 11 ሚሊዮን የነበረው የቻይና አህዮች ቁጥር በ2013 ወደ 6 ሚሊዮን ማጋደሉን የአገሪቱ የእንስሳት ዓመታዊ መጽሐፍ ያስረዳል። በዚህም የተነሳ በቀላሉ የሚደለሉትን የአፍሪካ አገሮች ተጠግቶ ማለቡ አማራጭ የሌለው በመሆኑ ቻይና ከዘመተችባቸው አገሮች መካከል በህገወጥ አህያ ንግድ የተጠለፈችው ደቡብ አፍሪካ ትጠቀሳለች።

በደቡብ አፍሪካ በአህያዎች ላይ የተካሄደው ህገወጥ እርምጃ ዜጎችን እያሳሰበ መጥቷል። አንዳንዶች “ንግዱ በህጋዊ መልክ ይካሄድ” ሲሉ ሌሎች ግን “በህጋዊ መንገድ ቢካሄድም ህገወጡን ንግድ ማስቆም አይቻልም” ሲሉ ይከራከራሉ።

ከሸኮናው እስከ ቆዳው በቻይናውያን ዘንድ የሚፈለገው አህያ በደቡብ አፍሪካ ዋጋው ከ30 ዶላር ወደ 160 ዶላር አሻቅቧል። ይህ ትርፋማ ንግድ የሳባቸው ህገወጥ ነጋዴዎች በቻይናውያን አስተባባሪነት በየቦታው የሚያገኙትን አህያዎች እየሸጡ ነዋሪውን ችግር ውስጥ መክተታቸውን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ። “በዚህ አካባቢ አህዮች በነጻነት ይመላለሱ ነበር። አሁን ግን ምንም አህያ የማይታይበት ሁኔታ ነው ያለው” የሚለው ደቡብ አፍሪካዊው የሞጎሳኒ መንደር ነዋሪ ነው። “እዚህ አካባቢ ያለነው ሰዎች የአህያ ሥጋ አንበላም፤ እንደሚታወቀው በአካባቢው ሥራ የለም፤ አህያ ያለው ግን ሠርቶ መብላት ይችል ነበር” በማለት ሌላኛው የመንደሩ ነዋሪ ለጃፓን ታይምስ ይናገራል።

ከአህያ ሌጦ የሚሠራው “ኢጂኣኦ” ፎቶው ከዊኪፒዲያ የተወሰደ ነው

የአህያ ዘራፊዎቹ ዋንኛ ትኩረታቸው ቆዳው ላይ ነው። ቻይና የአህያ ቆዳ በመቀቀል “ኢጂኣኦ” የተባለ ሙልጭልጭ መሳይ “ጄላቲን” ትሠራለች። ይህንንም በተለያዩ መድሃኒቶች ውስጥ በመጨመር ለደም ዝውውር፣ ሰውነትን ከበሽታ ለመከላከል፣ የራስ ማዞር፣ የዕንቅልፍ ዕጦትን፣ ሳል፣ የወር አበባ አለመስተካከልን ለመከላከልና ለማከም ይጠቀሙበታል። ሸኮናውም እንዲሁ ይኸው ሙልጭልጭ ጄላቲን የሚሠራበት ሲሆን ሥጋው ከከብት ሥጋ ይልቅ ጠቀሜታ አለው በሚል ቻይናውያኑ የአህያ ሥጋ በርገርና ወጥ በመሥራት ይመገቡታል። “ኢጂኣኦ” በመድኃኒት ውስጥ ካለው ጥቅም በተጨማሪ በሙቅ መጠጦች ውስጥ ሲጨመር ቶሎ ስለሚቀልጥ አብሮ ይጠጣል፤ ከኦቾሎኒ ምግቦች ጋር ተቀላቅሎም እንደ ሻይ (ቡና) ቁርስ ይቀርባል።

ቻይና ዴይሊ እንደሚለው ከሆነ፤ ቻይና በያመቱ 5ሺህ ቶን “ኢጂኣኦ” የምታመርት ሲሆን ለዚህም 4 ሚሊዮን የአህያ ሌጦ ያስፈልጋታል። ይህ የቻይና ፍላጎት በአህያ ስርቆትና ወንጀል መበራከት ህይወታቸውን ያቃወሰው ደቡብ አፍሪካውያኑ “አንድ የሆነ ነገር ካልተደረገ ልክ የአውራሪስ ቀንድ በህገወጥ መንገድ መሸጡ ያስከተለብን ዓይነት ቀውስ አሁን ደግሞ በአህያ ሌጦ ፍላጎት ተመሳሳይ ችግር መፈጠሩ አይቀሬ ነው” ይላሉ። ይህ ሁኔታ ለቻይናውያኑን በህጋዊ መንገድ የአህያ ቄራ እንዲከፍቱ መንገዱን የጠረገላቸው ይመስላል።

ጃፓን ታይምስ እንደዘገበው፤ ከጥቂት ወራት በፊት በጆሐንስበርግ ፖሊስ ከ5ሺህ በላይ የአህያ ሌጦ በቁጥጥር ሥር አውሏል። በአንድ ወቅት የአንዲት መሸታ ቤት ባለቤት ከሆነ ቻይናዊ ጊቢ ውስጥ በርካታ የአህያ ቆዳ መገኘቱን የፖሊስ ዘገባን የጠቀሰው ዜና ያስረዳል።

ሕገወጡን ንግድ ለመቆጣጠር በሚል ደቡብ አፍሪካ ወደ ህጋዊ የአህያ ንግድ ሥርዓት ለመግባት እየተንደረደረች ትገኛለች። አጎራባች የሆነችው ቦትስዋና በህጋዊ መልኩ የአህያ ውጪ ንግድ (ኤክስፖርት) ወደ ቻይና ጀምራለች። ናሚቢያ ደግሞ የቻይናን የአህያ ገበያ ፍላጎት ለማሟላት ቄራ ግንባታ ላይ ነች። በስልት የተቀነባበረው ህገወጥ ንግዱ የፈጠረው ቀውስ ህጋዊ ዕውቅናን አስገኝቷል። “ከቀውስ ውስጥ ሥርዓት” ይሏል ይህ ነው።

በተቃራኒው በአህያ ንግድ ላይ በህጋዊ መልኩ ተሰማርተው የነበሩ የምዕራብና ሰሜን አፍሪካ አገራት በንግዱ ላይ ዕቀባ አድርገዋል። ቡርኪናፋሶ ማንኛውም ወደ ኢስያ የሚደረግ የአህያ ሥጋና ሌጦ ላይ ዕገዳ አድርጋለች። ባለፉት ሦስት ወራት ቡርኪናፋሶ 18ሺህ አህዮችን ለዓለምአቀፍ ንግድ ስታቀርብ ይህ አኻዝ ካለፈው ዓመት በአንድ ሺህ የጨመረ መሆኑ ታውቋል።

የኒጀር መንግሥት በበኩሉ በአገሪቱ ክልል ውስጥ የሚካሄድ ማንኛውንም የአህያ እርድ አቅቧል። እኤአ በ2015 27ሺህ ብቻ የነበረው የአህያ ኤክስፖርት በያዝነው ዓመት በ200 እጅ ያህል በማደግ 80ሺህ አህዮች በቁማቸው ለኤክስፖርት መላካቸውን ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል። በኒጀር የአንድ አህያ ዋጋ ከ34 ዶላር ወደ 147ዶላር ማደጉ የነዋሪውን ህይወት አቃውሷል። አህያን ለመጓጓዣ የሚጠቀሙት ገበሬዎችና ነጋዴዎች የዋጋ ንረቱ በቂ አህያ እንዳይኖራቸው ከማድረግ በተጨማሪ በሚያቀርቡት ምርት ላይ ተጽዕኖ አሳደሯል።

በኬኒያ የአህያ ቄራ የከፈቱት ሉ ጂንግ

በምዕራብና ሰሜን አፍሪካ የተደረገው ዕቀባ ያሳሰባት ቻይና ፊቷን ወደ ምስራቅና ደቡባዊ የአፍሪካ አገራት አዙራለች። በናሚቢያና በቦትስዋና በህጋዊ መልኩ ፍላጎቷን እያረካች ካለችበት ሁኔታ በተጨማሪ በምስራቅ አፍሪካም እንዲሁ የአህያ ማረጃ ቄራዎችን እያቋቋመች ትገኛለች።

በኬኒያ ሁለት የአህያ ቄራዎች በቀን እስከ 400 አህዮችን ያርዳሉ። ቆዳና ሥጋቸውን ለገበያ ያቀርባሉ። ባለቤቶቹ እንደሚሉት የአህያ ማርቢያና ማደለቢያም አዘጋጅተዋል። ሆኖም እያረቡ ማረዱ በቂ ስላልሆነ ከጎረቤት አገራት እስከ ታንዛኒያ የዘለቀ የአህያ አቅራቢዎችን መስመር ዘርግተዋል። ቻይናዊው ባለቤት እንደሚሉት በቀን ከ400 እስከ 600 አህዮች አንዱ በ77 ዶላር ሒሳብ ይቀርቡላቸዋል።

ለጥቂት መቶ ሰዎች የሥራ ዕድል ከፍተዋል የሚባሉት ቄራዎች የሚያርዷቸው አህዮች ጉዳይ አንዳንድ የኬኒያ መንግሥት ባለሥልጣናትን እጅጉን አሳስቧል። በታረዱት ልክ የሚተካ አህያ ከሌለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀውስ እንደሚከሰት ስማቸው ያልገለጹ ምንጭ ለዴይሊ ኔሽን ተናግረዋል። ሆኖም ከተለያዩ ምንጮች የሚሰማው መረጃ እንደሚያመለክተው በኬኒያ ቅርብ ጊዜያት ውስጥ ተጨማሪ ቄራዎች እንደሚከፈቱ ነው።

ለአገር ውስጥ ፍጆታ ገና ባይቀርብም ኬኒያ እኤአ በ1999 የአህያ ሥጋ መብላት እንደሚቻል በሕግ ፈቅዳለች።

በኬኒያ የGoldox አህያ ቄራ ባለቤት ከሚያደልቧቸው አህያዎች ጋር

በነገራችን ላይ በአዲስ አበባ በመቶ የሚቆጠሩ አህዮች ባለቤት የሆኑ ሃብታሞች አሉ። እነዚህ ባለሃብቶች የአህያ ሾፌር ቀጥረው ነው የሚያሰሩት። በግላቸውም አህያ ገዘተው ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩ የቀን ሰራተኞችም አሉ። አንድ ላይ ሲደመር ችግሩ የሚፈጥረው ማህበራዊ ቀውስ የሰፋ ነው። ጎተራ ያለ አህያ አይሞላም። ማሳ ላይ ያለ ክምር ያለ አህያ አይነሳም። የገጠሩ ህዝብ አስፈጭቶ፣ ሸምቶና ሸጦ ወደ ደሳሳ ጎጆው የሚመለሰው በአህያ ነው። ሲራራ ነጋዴውም እንዲሁ። አህያ ትራንስፖርት ነው። የውሃ ጋሪ የሚስበው አህያ ነው። …

የአህያ ቄራ መከፈቱ ጉዳይ በበርካታው ሲወራ የሰነበተ ጉዳይ ቢሆንም የአህያ ማረጃ እስከመክፈት ሲደረስ በተለይ የሃይማኖት ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው የመደገፍ ያህል እንደሆነባቸው አንዳንዶች አስተያየት ሲሰጡ ተሰምተዋል።

ከላይ የቱሉቦሎው ነዋሪ እንዳሉት አህያ ለኢትዮጵያውያን ላባቸው፣ ህይወታቸው ነው። ምናልባት ህወሃት “የአህያውን ዘመን አልፌዋለሁና አይመለከተኝም” ካላለ!! “ደሳለኝ” ብለው የሚያቆላምጡት አህያ እንዳልነበራቸው አህያ እንዲጠፋ መቃብሩን ኦሮሚያ ላይ ተከሉ!! ልክ እንደ ሰይጣን ህወሃትም ወዳጅ የለውም!


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    April 10, 2017 10:28 pm at 10:28 pm

    ቻይናዎች የማይበሉት ነገር በዓለም ላይ የለም፡፡ በመሰረቱ ወያኔ ያለምንም ቅድመ ጥናት የአህያ ስጋና ቆዳ ለገቢያ መፍቀዱ የቱን ያህል ጭፍኖች እንደሆኑ ያመለክታል። ይሁን እንጂ ቻይና የወያኔ አለቃና የበደል ተባባሪ በመሆኑዋ ወያኔ ልብ አግኝቶ እምቢኝ ማለትም አይችልም። የሃገራችን ሃበሳ ለህዝቦቹዋ ብቻ ሳይሆን በምድሪቱ ለሚገኙ እንስሣትና አዕዋፍትም ጭምር ጸር ነው። በወያኔ የማይሸጥ ነገር የለም። በመሆኑም የአህያን ሥጋ ለጥብስ መፍቀድ ማተብ የለሽ ዘረኛ መሆናቸውን በይበልጥ አጎልቶ ያሳያል። ለሃገር ለወገን ለህዝብ የማያስብ መንግሥት የዛሬን እንጂ የነገን መገመትና መለካት አይፈልግም። ጥቂቶች ጮቤ እየረገጡ አዕላፍ በሚያለቅሱባት ኢትዮጵያ ጠበንጃ ያነገቱ የአንድ ብሄር ስብስቦች የሚፈነጥዙባት እንደሆነች አይናችን ያያል። ዛሬ የአህያ ሥጋ ነገ ደግሞ የውሻ ሥጋን ወያኔ ለሺያጭ እንደሚያቀርብ ጥርጥር የለውም። ወያኔ አረመኔ ነው። እጅና እግራቸው በታሰሩ ሰዎች ላይ የሚጸዳዳ፤ ሰዶማዊ ግብረስጋ የሚፈጽም፤ በህግ ተፈልገው የታሰሩ ሰዎችን በእስረኞች የሚያስደበድብ፤ ቤተሰብን በጥቅል የሚቀጣ፤ ያለፍርድ ሰውን በጠራራ ጸሃይ የሚገል ከሽያጭ የተረፈችውን ሃገር በዘርና በቋንቋ ከፍሎ ለራሱ የፓለቲካ ግብ የሚያተራምስ የጨካኞች ጥርቅም ወያኔ ነው። ወያኔ የአህያን ሥጋ ለገቢያ ቢያቀርብ የሚያስገርም ነገር አይደለም። ሥራቸው ሁሉ ጽልመታዊና ምህታታዊ ነውና! አሁን በተያዘው መንገድ የምሥራቅ አፍሪቃ አህዮች በጅብ ሳይሆን በቻይና ተበልተው ማለቃቸው ነው። መኖር ስንት ያሰማል፡ ያሳያል። አታድርስ ነው።

    Reply
  2. Samuel says

    April 10, 2017 10:37 pm at 10:37 pm

    What else must be expected of a Tigre regime that is peopled by men without a shame culture? To Tigres who eat locusts like their Yemeni cousins, our national sensibilities do not matter. For Tigres who sold our navy, and our country at large, selling donkeys is no big deal.

    Before the unscrupulous Chinese make a deal with the equally Godless Tigres to trade in human flesh, Ethiopians flesh that is, we must give these sub-human fascist a marching order.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule