- አህያን ጅብ ብቻ ሲበላው ነው የምናውቀው!
“ደሳለኝ” ተብሎ ስለሚጠራው አህያ፤ በወያኔ ሚዲያ የተተረከልን ታሪክ መሳጭ ነው። እነሱ ጫካ ውስጥ በነበሩበት ወቅት፣ አስገደ ገብረስላሴ በ45 ብር ገዝቶ ለወያኔ ማጓጓዣ ይሆን ዘንድ አበረከተ። ይህ “ደሳለኝ” የሚባለው አህያ ከባድ ጭነት እየተሸከመ ያገለግላቸው ነበር። በአንድ ወቅት በጦርነት ተሸነፉና ይዘውት የነበረውን ስፍራ ለቅቀው ተበታተኑ። ከቀናት በኋላ አንዳንዶቹ ወደቀድሞ ምሽጋቸው ተመልሰው ለመምጣት እንኳን ሲቸገሩ ደሳለኝ ግን መንገዱን ሳይስት እዚያው ስፍራ ይጠብቃቸው ነበር። በመጨረሻም የአህዮች አለቃ ተባለና “ብፃይ” (ጓድ) የሚል የማዕርግ ሹመትን አገኘ።
አሁን ደሳለኝ በህይወት የለም። ወያኔዎች ግን በበኩር ልጁ እየተጽናኑ እንደሆነ ይናገራሉ። አባቱ አብሮን ብዙ ተጉዟል ሲሉ፣ “ለልጁ” የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ሹመት ሰጥተውታል።
ሃይለማርያም “ደሳለኝ” ይባላሉ። ሹመት እንጂ ስልጣን የላቸውም። “የአክሱም ሃውልት ለወላይታው ምኑ ነው?” ሲባሉ “ምንም!” ብለው የተቀመጡ ሰው ከእንስሳው በተሻለ እንዴት ሊያስቡ ይችላሉ? ስልጣኑ ቢኖራቸው ኖሮ በኢትዮጵያ የአህያን እርድ ባልፈቀዱ ነበር። እምነታቸውም ይህንን ለማድረግ የሚከለክል ይመስለኛል።
የሚገርመው ግን ወያኔዎቹ ባለውለታቸው የሆነ ሁሉ ላይ ቢላ መሳላቸው ነው። ባለውለታቸውን ያርዳሉ። ሊበሉትም ይችላሉ! ህወሃቶች ይሉኝታና ውለታ የሚባሉትን ነገሮች ጨርሰው አያውቋቸውም። … ጀግና በመባል የተዘመረለት ብጻይ ደሳለኝ፤ መሳርያ ተሸክሟል፣ በጦር አውድማ ውሏል፣ መንገድ መርቷል … ዛሬ ግን እንዲታረድ ፈርደውበታል። … ስንቱን አረዱ፣ ስንቱን አፈኑ፣ ስንቱ ባለውለታቸውን አሰቃዩ! …
አስደንጋጩ የአህያ ቄራ ዜና በምድራችን በታወጀ ማዕግስት፤ አንዱ ባለ ጊዜ አደባባይ ወጥቶ እንዲህ አለ።
“በሬ ከበላህ አህያ በምንም ነውር አይሆንም። ሳይንሳዊ ምክንያት የላችሁም። አገሪቱ ደግሞ በሃይማኖት ሕግ አትተዳደርም። ቆሻሻ የሚበላ ሕዝብ ይዘን አህያ ለምን – ስትሉ አታፍሩም? እሱን በልተን ከረሃብ በወጣን በማን እድል! …”
የአህያ ቄራው የመከስት ጉዳይ አስደምሞን ሳያበቃ፣ ጭራሽ የአህያ ስጋ ብሉ እያሉን ነው ሰዎቹ። ከየትኛው ህብረተሰብ እንደወጡ፣ የትኛው ማህበረሰብ እንዳሳደጋቸው ከቶውን ሊገባን ባይችልም፤ ድፍረትና ንቀታቸው ግን አዲስ ነገር አይደለም።
ዛሬ፤ ግዜ ጥሎት የእነሱን ቆሻሻ እየበላ የሚኖረው ሕዝብ ላይ ጣቱን እያወጣ ሲናገር፤ ነገን ጨርሶ የረሳው ነው የሚመስለው። የቆመ የመሰለው እንደሚወድቅ፣ … እነሱ ጥለውት የወደቀ ወገን ሁሉ ነገ እንደሚነሳ ዘንግቷል።
ይህ ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው ህዝብ ግን፤ ቅዱሳን መጽሃፍት (ሰኮናው ያልተሰነጠቀ እንስሳ በክርስትናም ሆነ በሙስሊም እምነት አይበላም) የሚከለክለሉትን የአህያ ስጋ ከሚበላ፤ ቆሻሻውን ቢለቅም ይመርጣል። እቤቱ ተወልዶ ያደገን እንስሳ አርዶ ከመብላት ይልቅ ሞቱን የሚመርጥ ሕዝብ እንደሆነ ወያኔዎች መቼም ሊገባቸው አይችልም። አንድ ሰው ይህ እንዲገባው ኢትዮጵያዊ ስነ-ምግባር፣ ከፍ ሲል ደግሞ ስበዕና ሊኖረው ይገባል። እነሱ ደግሞ ለሁለቱም ያልታደሉ፤ በአስተሳሰባቸውም ለእርድ ከሚያቀርቡት አህያ ያልተሻሉ ናቸው። ስለዚህ አይገባቸውም። ሕዝቡን አናውቀውም ብሎን የለ ስብሃት ነጋ። “እብድና ሰካራም የልቡን ነው የሚናገረው።” የሚለው አባባል አንዳንዴ ልክ ነው።
የአህያ ቄራ በደብረዘይት መከፈቱን ጉዳይ ስናወጋ የሰሙ አንዲት አዛውንት፤ በቁጣ ተናገሩን። “እረ እሱ ይቅር ይበላችሁ። ምን የሚሉት ቀልድ ነው የምታወሩት? አሁን በዚህ የአብይ/ሁዳዴ ጾም እንዲህ እየተባለ ይቀለዳል?” አሉ። ነገሩ ቀልድ መምሰሉ አይደንቅም። ለእኝህ ወይዘሮ ቀልድ የመሰለው ይህ መራራ ሃቅ እኛንም ያሳመነው የደብረዘይቱ የአህያ ቄራ ተከፍቶ አራጆቹ ቢላ መሳል ሲጀምሩ ነው። መቼም የሁዳዴ ጾም ላይ ናቸውና ከዚህ በላይ ተናግሮ ስሜታቸውን የበለጠ መጉዳት አስፈላጊ ባይሆንም፤ እውነቱን ማወቅ ስለነበረባቸው ዜናውን አስደመጥናቸው። ለደቂቃ ዝም ካሉ በኋላ ይህችን ቃል ተናገሩ። “እግዚዖ የፈጣሪ ቁጣ!”
ይህችንም የተናገሩት ባህር ማዶ ስላሉ ነው። ሃገር ቤት ቢሆኑ ኖሮ በዚህ ንግግራቸው በአሸባሪነት ወይም ደግሞ በጸረ-ልማት ሊከሰሱ ይችሉ ይሆናል።
ባለ “ራዕዮቹ” እኝህን እናት “ወግ አጥባቂ” ይሏቸዋል። ግና እምነታቸውን፣ ወጉን፣ ባህሉን እና ከሁሉም በላይ ፈጣሪያቸውን የሚያከብሩ መሆናቸውን የሚገነዘቡላቸው ከከርሳቸው በላይ ሊያስቡ የሚችሉ ሰዎች ብቻ ናቸው። እንደ አጋሰስ ሳይሆን እንደ ሰው ቢያስቡማ ኖሮ ይህንን ዜና ቢያንስ ከሁዳዴ ጾም ፍቺ በኋላ ይለቅቁት ነበር።
እንዲህ አይነት ነውር እና ርኩሰት መታየት ከጀመረ ቆየ። አንዳንዶቹን ነውሮች ሕዝብ እንደዋዛ እየለመዳቸው የመጣ ይመስላል። ግብረሰዶምን በጳጳሱ ቡራኬ ሲያስገቡ አይተናል፣ ጄሶ እና ሰጋቱራ በጤፍ እንጀራ ውስጥ እየደባላቁ የሚሸጡትም እነሱ ናቸው፤ ካንሰርና ሄፒታይተስ የሚያመጣ አደገኛ ንጥረ ነገር በበርበሬ ውስጥ እየጨመሩ ሕዝብን መፍጀታቸውን ሰሞኑን ያጋለጠው የጀርመን መንግስት ነው። …
“አገሪቱ ደግሞ በሃይማኖት ሕግ አትተዳደርም” ብሎናል። ይህ ሰው እዚህ ላይ እርግጥ ተናግሯል። ስለ ሃይማኖት የምናወራው ፈጣሪያቸውን የሚያከብሩ፤ ሃይማኖት ካላቸው ሰዎች ጋር እንጂ ከአረመኔዎች ጋር አይደለም። እምነት ቢኖራቸውማ፤ በስነምግባር እሴቶቻችን ሃገሪቱን ያስተዳድሩ ነበር። የሃይማኖት ሕግ ማለት ሌላ ነገር አይደለም። ፈሪሃ-እግዚአብሄር ያለው ሰው ሁሉ የሚያደርገው ነገር ነው። ሃገሪቱ በስነ-ምግባር በታነጹት እሴቶቿ ሳይሆን ይልቁንም አንባገነኖቹ በፈቀዳቸው ግዜ በሚያወጡት አዋጅ ነው እየተዳደረች ያለችው። … ይህም ያልፋል፤ እስኪያልፍ ግን ያለፋል። ስመ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ደራሲ የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ ከቋጠራቸው ማራኪ ስንኞች አንዷን እዚህ ላይ ልዋስ፤
ማሽላና ስንዴ በአንድ አብረን ስንቆላ፣
እያረረ ሳቀ የባህር ማሽላ።
ከሰል የሚሆኑ ብዙ እንጨቶች ሳሉ፣
ዝግባ ለምን ይሆን ይቆረጥ የሚሉ።
ባሳለፍነው አመት አጋማሽ ላይ የቡርኪና ፋሶ መንግስት የአህያ ስጋ ኤክስፖርትን የሚከለክል ህግ ባጸደቀ ግዜ፤ ቻይና እጅግ ተቆጣች። ያለ ምንም ልዩ ማደለብያ፣ የተፈጥሮ ሳር ብቻ እየበላ የሚያድገው የአፍሪካ አህያ ስጋ ፍላጎት በታላቋ ቻይና እየጨመረ በመጣ ግዜ ነው ቡርኪና ፋሶ አህያ እንዳይታረድ የከለከለችው። ያም ሆኖ ቻይኖች እጅ ወደ መጠምዘዙ አልገቡም። የቡርኪና ፋሶ መንግስት ለሕዝቡ ሞራል ሲል የብዙ ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዳጣ ያውቃሉ። በብዙ ነገር መደለል ይሞክሩ ነበር። ግን ሌላ የተሻለ አማራጭ አለ። ከገዛ ዜጋው የሞራል እሴት ይልቅ፣ ለከርሳቸው እና ለኪሳቸው ብቻ የሚያስቡ ጉዶች በአፍሪካ ቀንድ ላይ አሉላቸው። እናም ቻይኖቹ የማረጃ ካራቸውን ይዘው ወደኛ ብቅ አሉ። ወያኔም በአንድ ሳይሆን በሁለት እጆቹ ጨብጦ ተቀበላቸው። በአህያ የተጀመረው የእርድ ዘመቻ ወደ ውሻና ድመትም በቅርቡ እንደሚዛመት መገመት አያዳትም።
በኢ-ሰብአዊነት ላይ የተሰማሩ የውጭ “ኢንቨስተሮች” ከሌላ ሃገር በተለያየ ምክንያት ሲባረሩ ኢትዮጵያ የመጨረሻ አማራጫቸው ሆናለች። እንደ ባጣ ቆይህ ወደ ሀገራችን ሲሮጡ ይህ የአህያ እርድ የመጀመርያው አይደለም። የሆላንድ የምርመራ ጋዜጠኞች በሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቭዥን ባለፈው አመት ያቀረቡትን ዘጋቢ ፊልም ብቻ መጥቀሱ ጉዳዩን በደንብ ያስረዳዋል።
ሼር የተባለው የአበባ አምራች ኩባንያ ከኬንያ እንደተባረረ፤ ጓዝና መርዙን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ብቅ አለ። ዶላሩን ብቻ ያዩ የኛዎቹ ጉዶች አይናቸውን ሳያሹ ነበር የተቀበሉት። ይኸው ኩባንያ የአበባ እርሻ በኬንያ ጀምሮ ከባቢውን በመበከሉ እና የሃገሪቱን ውሃ ሃብት በማምከኑ መባረሩን ያውቃሉ። ለወያኔ ከዚህ ሁሉ ዶላር ይበልጣል።
የሆላንድ ጋዜጠኞች ያቀረቡት የምርመራ ዘገባ እጅግ ዘግናኝ ነበር። አንዲት ጽጌሬዳ ለማምረት በአማካኝ 7 ሊትር ውሃ ይፈጃል። የአካባቢው ሕዝብ ግን አንዲት ሊትር ውሃ በቀን ለማግኘት በሚቸገርበት አካባቢ ነው። የአበባ አምራቹ በቀን ከ 3 እስከ 4 ሚሊዮን እግር ጽጌሬዳ ያመርታል። መሬቱ ዳግም ሌላ ነገር አያበቅልም። ከዝዋይ ሃይቅ ውስጥ የሚገባው መርዝ ደግሞ አሳ ተመጋቢ ዜጎች ልጅ እንዳይወልዱ መካን ያደርጋቸዋል። የህክምና ባለሙያዎች እንዳጋለጡት ከሆነ ደግሞ መርዙ በዜጎች ላይ ከዚህ በፊት ተከስተው የማይታወቁ በሽታዎችን (ምናልባት ካንሰር) እንዳስከተለ አልሸሸጉም።…
ለሆዱ እንጂ ለዜጋው ግድ የሌለው ቡድን በህዝቡ አናት ላይ መቀመጡን ነጮቹም ያውቃሉ።
ሕዝብ የአህያ ስጋ እንዲበላ ያሳሰበው ካድሬ የኦሪት ህግ ከሙሴ ጋር እንደተቀበረ ይነግረናል። የፈጣሪ ህግ ዘላለማዊ ነው። እነሱ እንደሚሉት የሚሻር፣ የሚቀየር ወይንም የሚቀበር አይደለም። ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን ህግን ሊሽር ሳይሆን ሊፈጽም እንደመጣ አስተምሯል። የሙሴ ህግ አልተሻረም። ህወሃት ሽሮት ከሆነ ግን አናውቅም። ሙሴ ከፈጣሪ ያገኘውን ቃል ነው ህግ ያደረገው።
አህያ ለአገልግሎት እንጂ ለምግብነት አልተፈጠረም። ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው ህዝብ ደግሞ አህያ አያርድም። አህያም አይበላም። አህያን ጅብ ብቻ ሲበላው ነው የምናውቀው።
ከህብረተሰቡ ሞራል ይልቅ ዶላሩ ቢበልጥባቸው እንኳን የአህያ ቄራ ከመገንባት፣ አህያውን በቁሙ ወደ ቻይና መላኩ የተሻለ አማራጭ ነበር። የአህያ ጭንቅላት እንኳን ባነሰ የሚያስቡ ሰዎች ስልጣን ላይ እስከተቀመጡ ድረስ ከዚህ የባሰ ነገርም ሊመጣ እንደሚችል መገመት አይከብድም። እነዚህ ሰዎች ለዘለዓለሙ የምኒሊክ ቤተ መንግስት ውስጥ እንደማይኖሩ እርግጥ ነው። የማይለወጥ ነገር የለም። ትእቢት የውድቀት ምልክት ናት። እነሱም አንድ ቀን ይወድቃሉ። ግን ይህንን ሁሉ ግፍ፣ ይህንን ሁሉ ንቀት፤ ይህንን ሁሉ ወንጀል ተሸክመው የትኛው ምድር ይቀበላቸው ይሆን? (ፎቶ: የአህያ ቄራ በኬኒያ)
ክንፉ አሰፋ
yalew akele says
እግዚኦ የፈጣሪ ቁጣ!!!
Ras Dejen says
That is what people can expect from an ‘enemy in power’. Enemy does anything which can hurt its opponents anyway. Because its is in power it can do anything tagging it with solemn names and/or sexing it with fictitious claims/stories.
Ethiopians, please go on cleaning Ethiopia from the ‘voracious grasshoppers ‘ (TPLF and its cronies).
በለው! says
…. የሆርን አፌርስ አምደኛ ታድሶ/ተሃድሶ አልተማረም የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጎጠኝነትን ዘረኝነት አስተምረው እኛ ወጣቱ ላይ ሲሰርፅ ነው የምንነቃው” ኃይለመለስ
** “የዴሞክራሲ አብዮት በኢኮኖሚ አብዮት አይጨናገፍም!”ሰላምና ሉዓላዊነትን ከማስከበር ባለፈ የፖሊስን ተግባር እየተወጣ፣ የመንግስትን ክፍተት እየሸፈነ እና የሕዝብን ጥያቄ ወደ ጎን እየገፋ መቀጠል አይችልም። ስለዚህ፣ ከተወሰነ ግዜ በኋላ የመከላከያ ሠራዊት ለኢህአዴግ መንግስት የሥልጣን ማራዘሚያ ሆኖ መቀጠል ይሳነዋል። ይህ መቼ እንደሚሆን በእርግጠኝነት መገመት ቢከብድም ግዜው የኢህአዴግ መንግስት መጨረሻ ስለመሆኑ ግን ጥርጥር የለውም። ከዚህ አንፃር፣ ሥር-ነቀል ታሃድሶ ከማድረግ ይልቅ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በማራዘም ችግሩን ለማድበስበስ መሞከር ራስን ለውድቀት ማመቻቸት ነው።” ” የሜንጫ አብዮትን እንደጀመርነው እናስጨርሰዋለን!”ማለቱ ነው ።
**”የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው “ኢኮኖሚ አብዮት” በተሳሳተ እሳቤ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ግቡን አይመታም።ይህ የኢኮኖሚያ አብዮት በስህተት ላይ ስህተት በመደጋገም፣ አንዱን ስህተት በሌላ ስህተት ለማረም መሞከር ነው። ”
** ዛሬ በቻይና አንድ ኪሎ ግራም “Ejiao” እስከ £300 ፓውንድ በሚደርስ ዋጋ ይሸጣል። በዚህ ምክንያት በቻይና የአህያ ቁጥር እ.አ.አ. በ1991 ከነበረበት በእጥፍ መቀነሱን ዘገባዎች ያስረዳሉ። በዚህ ምክንያት በዓለም አቀፉ ገበያ ውስጥም ከፍተኛ የሆነ የፍላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠን ተፈጥሯል። ለዓለም ገበያ በአንድ አመት ውስጥ 1.8 ሚሊዮን የአህያ ቆዳ ለሽያጭ የሚቀርብ ሲሆን ዓመታዊ የገበያ ፍላጎቱ ግን 4 እስከ 10 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል።
*-ለምሳሌ በቡርኪና ፋሶ የአንድ አህያ የመሸጫ ዋጋ እ.አ.አ. 2014 ከነበረበት 60 ዶላር ወደ 108 ዶላር ጨምሯል።እኛ በሀገራችን የጅብ ቆዳን ለባህላዊ መድሃኒትነት እየተጠቀምን ቻይናዎች የአህያ ቆዳ ለተመሣሣይ ዓላማ እንዳያውሉ መከልከል በፍፁም አግባብ ሊሆን አይችልም!። ..”የቻይና እና ቬትናም የአህያ እርካታ በኦሮሞ ሕዝብ ጉሮሮ ላይ በተሰነቀረ ጠባብነት ይሳካልን? ከኦሮሞው ላይ ፻፰ ዶላር ትገዙታላችሁ? ገበሬው ምርቱን ውሃውን ቁሳቁሶችን በምን ያጓጓዝ?ከተማ እንዳይስፋፋ የማስተር ፕላኑን ቱማታ ከበቀለ ገለባ ፅሑፍ ብዙ ይረዷል። የኢኮኖሚ አብዮት ተፃራሪ የኢኮኖሚ ምሁር ለባዕድ ኢኮኖሚ ዕድገት ምን አስቃዠውና ሕዝብና ሃይማኖተኞችን ለመሳብ ደፈረ ?
.. ይህ ተግባር “ከእምነቴና ሃይማኖቴ ጋር አብሮ አይሄድም። ስለዚህ አህዮቼን ለድርጅቱ አልሸጥም” ካለም መብቱ ነው። በአህዮቹ ላይ የመወሰን ስልጣንና መብት ያለው አርሶ አደሩ እንጂ የተወሰኑ የከተማ አፈ-ጮሌዎችና የሃይማኖት ሰባኪዎች አይደሉም!። በተሃድሶ ሰበብ የውሸት አስረውት ታሳሪውን እንዴት ይሰልል እንደነበር “በጦላይ የተሃድሶ ማዕከል በአንድ የማደሪያ ክፍል ውስጥ በአማካይ 100 ሰልጣኞች (እስረኞች) አብረው ያድራሉ። እኔ በነበርኩበት ክፍል ውስጥም 98 ሰልጣኞች (እስረኞች) ነበርን። ገመቹ የአምስት ልጆች አባትና በጣም ታታሪ ሰው ነው። ዘወትር በሥራ እንደተጠመደ ነው። ከስልጠና መልስ የተለያየ ቀለም ያላቸውን የሲባጎ ገመዶችን በመጎንጎን የኢትዮጲያና የኦሮሚያ ባንድራ ምስል ያላቸው የጥርስ መፋቂያዎችን እየሰራ አንዱን በ10 ብር ይሸጣል። ገመቹም ወደ አርሲ ሮቤ ሲመለስ በየትኛው የሥራ መስክ ተደራጅቶ መስራት እንደሚፈልግ በመጠይቁ ላይ ሞልቷል። ያን ዕለት ማታ “ገሜ… አሁንማ መንግስት በማህበር አደራጅቶ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግልህ ነው። በየትኛው የሥራ-መስክ ለመሰማራት አቀድክ?” ስል ጠየቅኩት። የገመቹ ምላሽ ግን በጣም አስገራሚ ነበር።
… “ማ… እኔ?! እኔ አምስት ልጆች አሉኝ። ከማንም ሰነፍ ጋር ተደራጅቼ አገልጋይ ከምሆን ከልጆቼ ጋር ተደራጅቼ ብሰራ ይሻለኛል። የመንግስት ድጋፍ ከምር ከሆነ ለእኔና ልጆቼ ብድር ቢሰጠን መልካም ነበር” አለኝ።” ቆፍጣናው ገመቹን በግ፡ፍየል፡ዶሮ፡ላም በሬ አርብተው የአማራ ሃይማኖትና ባሕል አዲስ አበቤን ከምታበለፅግ አህያ አርባና ሃይማኖተ ቢስ ሆነህ በዶላር በዩሮ ፅደቅ እያለ የሚያሸብር ቱሪናፋ መድሐኒት ማቀነባበሪያ እዚሁ ይከፈት አላለም፡ጅብ የሚበላው አህያ ከሌለ የገመቹ ልጆች እንደሚበሉ አይገባውም ጀዝባ…! የጆሮ ጠቢነቱን ቆሌ የገፈፈውን ኢትዮጵያዊ የአሩሲ ሮቢ ገበሬ ጤናና በረከት ከሞላው ቤተሰቡ ጋር ይሁን ድንቄም ምሁር !?
****************!
አነጋጋሪ አህያ …
“ሰፌድ የለም እንጂ ሰፌድማ ቢኖር በክልሉ ሁሉ በሰፌድ ወርቅ ይነጠር ነበር ።” ኃይለመለስ
“በኦሮሚያ በሦስት ዞኖች ብቻ 241 ት/ቤቶች ተዘግተዋል፤ 114,751 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል! በቦረናና በጉጂ ዞኖች 127,010 ከብቶች በዘንድሮው ድርቅ ሞተዋል! ”
*”የኦሮሞን የበሬ ስጋ እየበላህ ለኦሮሞ አህያን ስጋ ለቻይና እና ለቬትናም ለመከልከል አትችልም!” “የኦሮሚያ ክልል ኢኮኖሚ አብዮት አይሳካም !” የአንቦ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ስዩም ተሾመ
*የየካ፡ እንጦጦ፡ ለገጣፎ፡ሽሮ ሜዳ ጅቦች እንዲህ ሌት ተቀን የሚያሽካኩት የአህያ ሥጋና ቆዳን መድሃኒት ፈልስፈው በደስታ ነው ? “የቻይና እና የቬትናም የኢኮኖሚ የአብዮት በእኛ አህዮች አይሳካም! መንግሥት እራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ መንግስታዊ መብት፡ተዘዋውሮ የመኖር እንጂ የዘር ማጥፋትን ያቁም!፡ በልቶ፡ጠጥቶ የሚኖር ፍጡራን ህልውናችን ያክብርልን!ተቃዋሚዎች የድርድር ግዜና ተወካዮቻችን በ፱፪ ኛው አባል ሆነው መንግስት በግላችን ይደራደረን!”አህያና ጅብ ለምዕተ ዓመት የዘለቀው አብሮነት በህወሓት /ኢህአዴግ ቻይና አፍቅሮተ ንዋይ ጣልቃ ገብነት እኛና እናንተን ከኢትዮጲያ ሕዝብና መንግስት ጋር ያስተሳሰረን የእያንዳንዳችንና የሁላችንም ነፃነት መከበር ነው።”ኢትዮጵያ አህዮች አብዮታዊ ግንባር!(ኢአአግ)
,,, “ሀገር” የሚለው ቃል “በውስጡ ህዝቦች የሚኖሩበት፣ የተወሰነ ጂኦግራፊያዊ ክልል ያለውና በአንድ መንግስት አስተዳደር ስር የሚገኝ ግዛት” የሚል ፍቺ ይሰጠዋል። “ሕዝብ” የሚለውን ቃል ደግሞ “በተወሰነ መልከኣምድራዊ ክልል ውስጥ የሚገኙና በአንድ መንግስት ስር የሚተዳደሩ ጠቅላላ ሰዎች፤ የአንድ ብሔር ወይም ብሄረሰብ፥ ጎሳ፥…ወተዘ አባል የሆኑ ሰዎችን” መሆናቸውን ይጠቅሳል። ስለዚህ፣ “ሀገር” እና “ሕዝብ” የሚሉት ቃላት ፍቺ በአንድ ዓይነት ፅንሰ-ሃሳብ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን መገንዘብ ይቻላል።”
***ሉዐላዊ ሀገርንና ሕዝብ ሌሎች በገንዘብ የሚሸጡ እና የሚለውጡትን ዕቃ (ሸቀጦች)ናቸው ይላልን? ህወሓት በእነዚህ አውቆ አበድ ምሁራን ከልሎ እያጯጯኹ ሀገርንና ሕዝብ ለማባላት ለማለያየት ተጠቅመውባቸዋል ሲነኩም ለአድነኝ ውለታቸውን በሕግ እያጣቀሱ ያላዝናሉ። ሴት እህቶቻችንን በአውሮፕላን በሕጋዊ መንገድ የሸጡ ፡ጎረቤት ኤርትራና ሱዳን ዜጎቻችንን ሲዘርፉ፡የሰው ልጅ የሆድ ዕቃ ተበልቶ ሲሸጥ ፡ለጋ ሕፃናት ለኢንቨስትመንት መደራደሪያ የስሜት ማርኪያ እንደ ከብት ሲነዱ አዳሜ ሀገሩን ሸጦ ክልል የገዛ ዕለት መንግሥት ሕዝብ ባሕል ሃይመኖትም አከተመ። በሕገመንግሥታዊ ጥቅማጥቅም የተጠረነፈ ኢትዮጵያ እንድትፈርስ በቀን ይባንናል፡ዓይኑን ጨፍኖ አፉን ሸፍኖ ይፀልያል ። “የእኔ መብትና ነፃነት ካልተከበረ ከኢትዮጲያ ሕዝብና መንግስት ጋር ውል የለኝም!።”ወይ ሀገር በማሸበር ወይም በመበታተን ካቆመበት ይቀጥላል ለተሃድሶ የገቡት ጭራሽ መረን ለቀው ሀገር ሕዝብና ታሪክን በማጠልሸት ሠልጥነዋል በዘ ፍቃዱ ኀይሉን የአድዋን ድል መዘቅዘቅ ልብ ይሏል ። የመናገር ነፃነት አፍ መክፈት ነውን ? ምንም እንኳን ሃይማኖት አልባ ምሁራን ፡ መንግሥትና ሥርዓት ቢኖረንም እየተስተዋለ! በሕግ አምላክ በለው !