
- “ቸቸላ” – በጎንደር የአማራ የልብ እሳት ማብረጃ ማማ!!
- ፋሲል ከነማ – ቶራ ቦራ!
ማስታወሻ፤ ቶራ ቦራ አፍጋኒስታን ውስጥ ያለና ቢንላደን የሚደበቅባቸው ተራራዎችና የዋሻ ምሽጎች ናቸው። ፋሲል ከነማም የቶራ ቦራ ምሳሌ ነው። ቶራ ቦራ ብዙ ጊዜ ይደበደባል ግን ጉዳት አይደርስም። ቢደርስም ይህ ነው የሚባል አይደለም። ፋሲል ከነማም ምሽግ ነው! ቶራ ቦራ! በተቃራኒው ዱሮ ትልቅ የፖለቲካ ዋሻ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ ቶራ ቦራነቱ ቀርቶ ሜዳ ሆኗል። ማንም እንደፈለገ የሚፈነጭበት ግልብ ሜዳ!
ሁሉም ባይሆኑም አስገራሚና ሊፋቅ የማይችል የምስረታ ታሪክ ያላቸው ክለቦች አሉን። አሁን አዲስ አበባ ስታዲየም የሚንከላወሱት ብቻ ሳይሆኑ በመላው አገሪቱ፣ በየሰፈሩ፣ በየከተማው … ተቋቁመው የከሰሙት ክለቦች የምስረታ ታሪክ የሚያጠናው ቢገኝ ከቅሪላው ጀርባ ያለውን ጉዳይ መረዳት ይቻል ነበር። የአገሪቱ የስፖርት ሙዚየም ስለመኖሩ ብዙ ማረጋገጫ ባይኖርም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ካሉት ተግባራት መካከል አንዱና ትልቁ ጉዳይ መረጃን በውል አደራጅቶ ማስቀመጥም ጭምር ይመስለናል።
ሁሉንም ባንዘረዝርም መሐል አራዳ ህዝብ የወለደው ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ክቡር ዘበኛውና ምደር ጦሩ የወለዳቸው መቻልና መኩሪያ፣ ኦሜድላና አየር ኃይልን የሚወክለው ንብ፣ የድሬዎች ባቡርና ጥጥ፣ የአስመራዎቹ እምባይሶራ፣ ቴሌ፣ ቀይባህር ወዘተ የመሳሰሉት ይነሳሉ። ኢትዮጵያ ቡናም የዚሁ የህዝባዊ ክለብነት መለያ የሚሰጠው ነው። ደጋፊዎቹና አመራሮቹ ከቅንጅት ፖለቲካ ጋር በተያያዘ አሳዛኝና አሳፋሪ የሚባል ችግር ገጥሟቸዋል። በተለይም ቅዱስ ጊዮርጊስን በውል በማይታወቅ ድርድር የግል ያደረጉት አሽከሮች ተቀናቃኛቸው የሆነውን የቡናን አመራሮች ለማሸማቀቅ ደህንነት ቢሮ ሲሮጡ የነበረው በዚሁ ቅንጅት ባመጣው ጣጣ እንደ ነበር የሚረሳ አይደለም።
ቅዱስ ጊዮርጊስ የደጋፊዎችን ማህበር አፍርሶ በማይታወቅ ድርድር ተሽጦ ህዝባዊነቱን ለግለሰቦችና በሽፍንፍን ቸብቸበውት ሸራተን ለተሞሸሩት አስርክቦ፣ በህግ በማይታወቅ አግባብ የግለሰብ ኪስ ናፋቂ ሆኖ ቀርቷል። ከከሰሙት የሚሻለው ስሙን ተሸክሞ በመንከላወሱ እንጂ፣ በገቢር የልብ ወዳጆቹን ከስሮ የቀትር ከበሮ በሚደልቁ አስመሳዮች፣ የኮንዶሚኒየም ቤት የተግዛላቸው አስጨፋሪዎች፣ ታክሲ የተገዛላቸው አወዳሾች፣ እንዲሁም የቀንና የሳምንት የአረቄ ሂሳብ በሚቆረጥላቸው ከንቱዎች ተከብቦ የሚገኝ ክለብ ነው።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ጉዳይ ከተነሳ ብዙ የሚነካኩ ጉዳዮች አሉና እዚህ ላይ እናልፈዋለን። አንባቢዎቻችን ግን ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተለይ መረጃዎችን ለጎልጉል ብትልኩ በደስታ የምናስተናገድ መሆኑንን በዚህ አጋጣሚ ለመጠቆም እንወዳለን።
መሐል አራዳ ጉዳይ አሁን ጊዮርጊስን የወሰዱት “ባለሃብት” ለዘመናት ባጠሩት የፒያሳው ኳስ ሜዳ ላይ ቀይ መለያ ለብሶ የሚጫወተው ምትሃተኛ ቡድን ነው። በባዶ እግሩ ፑንት እየመታ የሚያገባው ዲናሬ ከመሐል አራዳ የሚረሳ ተጨዋች አይሆንም። መሐል አራዳ በኢህአፓ የፖለቲካ ምች የተመታ፣ በፖለቲካ የተቀኘ ቡድን ነበር። መሐል አራዳን እናቶች ከመሃረባቸው ሳንቲም እያዋጡ የሚረዱት፣ ሲጫወት ደግሞ ሜዳ ደርሰው የሚደገፉት እልልታና ዝማሬ የሚያቀርቡለት ቡድን ነበር።
ሰራተኛ ሰፈር ሁሉም ቤት ውስጥ መሐል አራዳ አለ። በቀይ ሽብር ሜዳ ላይ የተገደለ ተጫዋችን መለያ ህዝብ ቆራርጦ በመካፈል እቤታቸው መግቢያ ላይ አኑረውታል። ይህንን አስለቃሽ ታሪክ የሰራተኛ ሰፈር እናቶች የሚጠይቃቸው ቢያገኙ ይተርኩታል። ህዝባዊ ክለብነቱን እንደያዘ ቀጥሎ … ኖሮ ኖሮ… አሁን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆኖ እየኖረ ይሁን የሚታወቅ ነገር የለም። ይህንን ጉዳይ ጠንቀቀው የሚያውቁት በአንድ ወቅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ባለቤት ነን ብለው እንደተነሱ አፋቸውን እንዲዘጉ የተደረጉት የፒያሳ ሰዎች ብቻ ናቸው።
አሁን የከነማ ክለቦች እያበቡ ሲሄዱ ደግሞ ባጭር ጊዜ ገኖ የወጣው የፋሲል ከነማ ቡድን ነው። ለዛሬ የፋሲል ከነማን እግር ኳስ ቡድን /ማህበር አለመሆኑ ይገርማል/ አካሄድና የስምዖን ልጅ የሚነዳው ዳሽን ቢራ ዙሪያ ያጠነጠነ፣ እንዲሁም ፖለቲካ የቀደመው ታሪኩ በስፋት ይወሳሉ።
“ፋሲል ከነማ” – የትውልድ አመጽ አርማ!
“ትግል ፍሬ”
1960 ዓ.ም ጎንደር ከተማ ላይ የያኔ ወጣቶች በአገሪቱ የነበሩ ትልልቆቹን የእግር ኳስ ቡድኖች (አሥመራ ቡድን፣ ሸዋ ቡድን፣ አየር ኃይል ቡድን፣ …) እያሰቡ፤ አንድ ትንሽ የእግርኳስ ቡድን በራሳቸው ጥረት መሰረቱ። በጨርቅ ኳስ የተጀመረው የእግር ኳስ ቡድኑ ስብስብ ብዙ የተለየ እንቅስቃሴ ሳያድርግ ስድስት ዓመታት ተቆጠሩ። ስብስቡ የሰፈር ጨዋታዎችን ከማካሄድ ሳይሻገር ኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ አስተናገደች። ሕዝባዊ አብዮት።
የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት የአገሪቱን ፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ መዋቅሮች ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ መዋቅሩንም ቀየረው። የለውጡ አካል የነበረችው ጎንደር፤ በሥር ነቀል ሂደቱ ውስጥ ስታልፍ በከተማው ውስጥ ከስድስት ዓመታት በፊት የተመሰረተው የእግርኳስ ቡድን እንደዘመኑ መንፈስ አዲስ የቡድን ስያሜ ያዘ። “ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን” ተሰኘ። አሁን ጊዜው 1967 ዓ.ም ሆኗል።
የትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች በአብዛኛው የቀበሌ 16 በተለምዶ “ቸቸላ” ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ልጆች ናቸው። በጊዜ ሂደት ግን ከየአቅጣጫው ቡድኑን የተቀላቀሉት የከተማዋ ወጣቶች አልጠፉም። መካሻ፣ አባቡ፣ ሰጠኝ፣ አራጋው፣ … የትግል ፍሬ እግር ኳስ ቡድን ሞተር ነበሩ። በእግር ኳስ ያበደ ልባቸው በፖለቲካ ለመቅለጥ ጊዜ አልፈጀበትም። አብዛኛዎቹ የቡድኑ አባላት በኢህአፓ የፖለቲካ መስመር ተጠለፉ። እንደዘመኑ መንፈስ፤ ህብዑ ገቡ። ይህም ሆኖ ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ከአቻዎቹ ጋር የእግር ኳስ ግጥሚያ ከማካሄድ አልቆመም። የግጥሚያ ሜዳው በየጊዜው ይቀያየር ነበር። ጎንደር ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በተለምዶ “ኳስ ሜዳ” ተብሎ በሚጠራው ሜዳ፣ ፋሲለደስ መዋኛ ግቢ ፊት ለፊት (ዛሬ ላይ ፋሲለደስ ስታዲየም ተብሎ የተሰየመዉ)፣ ፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ … የእግር ኳስ ውድድሮች በተዘጋጁ ቁጥር ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ተሳታፊ ነበር።
በዚህ የታሪክ ሂደት ውስጥ፤ አንድ ኤርትራዊ ወጣት ጐንደር ከተማ 02 ቀበሌ ከቤተሰቦቹ ጋር ይኖር ነበር። መብራህቱ ገ/ህይወት — ገጸ-ብዙዉ በረከት ስምዖን! የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱንም በፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነበር የተማረው። በጊዜው ጐንደር ከተማ ላይ መብራህቱ ገ/ህይወት (በረከት ስምዖን) መናኛ ወጣት ነበር። የትግል ፍሬ ተጫዋቾችም ሆኑ ደጋፊዎችና የከተማው ወጣቶች የደርግን የአፈና ተግባር አምርረው ያወግዙ ነበር። ኢህአፓ ለከተማው ወጣቶች የአምላክ ያህል ተቀባይነት ነበራት። ያ – መናኛ ወጣት በዚህ መስመር ተስቦ ለመግባት በቃ። በረከት ስምዖን!! የማታ ማታ የኢህአፓም ሆነ የትግል ፍሬ እግር ኳስ ቡድን ተከታይ ትውልድ ጸር ይሆናል ብሎ የገመተ አንድም ወገን አልነበረም። የሆነው ግን ይህ ነበር። የኢህአፓን የትግል መስመር በመካድ ንጉሥ አንጋሹን ኢህዴን/ብአዴንን በመመስረት ለምኒልክ ቤተመንግሥት አፈ ልጓምነት የበቃው በረከት፤ ዛሬ ላይ በዳሽን ቢራ ስፖንሰር አድራጊነት ሥም መዳፉ ስር ያስገባው ፋሲል ከነማ፤ ያኔ የትግል ፍሬ በመባል ይጠራ ነበር። ለስምዖን ልጅ “ያኔ በእርስዎ የወጣትነት ዘመን ጎንደር ከተማ ላይ ዝነኛ ከነበሩት የእግር ኳስ ክለቦች ሦስቱን ይንገሩን” የሚል ጥያቄ ቢቀርብለት “ትግል ፍሬን” ሳይጠቅስ እንደማያልፍ በርግጠኝነት ለመናገር ይቻላል። ለቡድኑ እጁ እስኪላጥ ድረስ አጨብጭቧል። የኢህአፓን የትግል መስመር ቢክድም ትግል ፍሬን አይረሳም። ለበለጠ ማብራሪያ ከመብራህቱ ገ/ህይወት (በረከት ስምዖን) የዘመን ተጋሪዎች ዉስጥ ጎንደር ከተማ፤ ጋሽ አስረስን ይጠይቁ። የሜክሲኮው ዳኛ!!
ወደ ትረካችን ስንመለስ … የደርግ ምህረት የለሽ ቅጣት በኢህአፓ ወጣቶች ላይ እየበረታ መጣ። የመላኩ ተፈራ ፈርዖናዊ እብሪት በጎንደር አደባባዮች ላይ ናኘ። ከተማዋ በደም አበላ ታጠበች። ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ቅርቃር ውስጥ ገባ። የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች መመናመን ጀመሩ። ያም ሆኖ የቀይ ሽብር ዘመን አልፎ እንኳ ቡድኑ አልከሰመም። መደብዘዙ ግን አልቀረም።
ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን “አለም የለምም” ሳይባል ዓመታት ነጐዱ። ደርግ በድራማዊ አጀብ እንደተከሰተው፤ በትራጄዲ ሁነት ተሰናበተ። ትግል ፍሬ እንደ አጀማመሩ ባይሆንም ቡድኑ በሥም ደረጃ ይንቀሳቀስ ነበር። የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሌላ “ደርጎች” የምኒልክ ቤተመንግሥትን ሲቆጣጠሩ፤ ትግል ፍሬ በሥም ከሰመ። ለሁለት ዓመት ብቻ። 1985 ዓም የትግል ፍሬ ተከታይ ትውልድ በአዲስ መንፈስ “ፋሲል” በሚል ሥያሜ የእግር ኳስ ቡድን ተቋቋመ። (“ፋሲል ከነማ” የሚለው ስያሜ የሽግግር መንግሥቱ ጊዜ ካበቃ በኋላ በተፈጠረው የከተሞች አደረጃጀት የመጣ ስያሜ መሆኑን ልብ ይሏል)
1985 እና ከዛ በኋላ የነበሩ ዓመታት እንደ ቀዳሚዎች ዓመታት ከፖለቲካ – ኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች አኳያ ለጐንደር ፈታኝ ጊዜያት ነበሩ። ማህበራዊ ቀውሶች በተጨማሪነት ቢስተዋሉም በእግር ኳስ ረገድ ግን ጥሩ መነቃቃት ነበር። ዛሬ ላይ “ታየ በላይ ሆቴል” የተገነባበት ቦታ “ሜክሲኮ ሜዳ” ይባል ነበር። በዚህ መለስተኛ ሜዳ በመሬት አርድ የእግር ኳስ ደጋፊዎች የታጀበ የእግር ኳስ ውድድር መርሃ ግብሮች ነበሩ። አራዳ፣ ውሃ ልማት፣ ፖሊ፣ ኳሊበር፣ ኒያላ፣ ኢዲዲሲ … የተሰኙ የእግር ኳስ ቡድኖች ቀንደኛ ተፋላሚዎች ነበሩ። ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ የተሻለ የመጫወት ጥበብ ያላቸው ተጫዋቾች ለፋሲል እግር ኳስ ቡድን መጋቢ በመሆን አገልግለዋል። የያኔው ፋሲል ከ“ሜክሲኮ” ጨዋታ ከፍ ባለ መልኩ ከወረዳ የእግር ኳስ ቡድኖች ጋር ይጫወት ነበር። “ፋሲል ከነማ የትውልዶች ቅብብል ውጤት ነው” የሚባለውም ለዚህ ነው።
በዚህ የታሪክ ሂደት ከሽግግር መንግስቱ በኋላ በተፈጠረው የከተሞች አደረጃጀት ፋሲል የእግር ኳስ ቡድን፤ “ፋሲል ከነማ” በሚል ስያሜ በከተማ አስተዳደሩ ደረጃ ታቀፈ (“ከነማ” ማለት “ከተማ ነዋሪዎች ማህበር” መሆኑን ያስታውሷል)
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አደረጃጀትና የአሰራር ዝግመታዊ ለውጥን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ለዓመታት በከተማ ደረጃና በብሔራዊ ሊግ ደረጃ ሲጫወት ቆይቶ፤ በ2008 የውድድር ዘመን ብሄራዊ ሊጉን በበላይነት በማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፕሪሚሪሊግ ተሳታፊ ለመሆን በቃ። የትውልድ ቅብብሎሽ በታየበት በዚህ የታሪክ ሂደት መሰረት ክለቡ 49 ዓመታት ያስቆጠረ አንጋፋ ክለብ ነው።
ቡድኑ “ትግል ፍሬ” ይባል በነበረበት ወቅት፤ “በሕዝብ የተመረጠ ዴሞክራሲያዊ መንግስት አሁኑኑ!” የሚለው የኢህአፓ የትግል መፈክር የተቀነቀነበት፤ ከዓመታት በኋላ ደግሞ በክለብ ደረጃ “ፋሲል ከነማ” የሚል ስያሜ ይዞ “ዘረኛው ህወሓት ይውደም!”፣ “ሌባ ነው ሌባ ሕወሓት ሌባ!” የሚሉ ፅኑ አቋሞች በደጋፊዎቹ በኩል በህብረ ዝማሬ ታጅቦ የሚቀርብበት ህያው የፖለቲካ መድረክ፤ የትውልድ አመፅ አርማ ሆኗል። ከ“ትግል ፍሬ” እስከ “ፋሲል ከነማ”፤ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎችን በትውልዶች ቅብብል በስፖርት ሜዳ ላይ ያንፀባረቀ የአፄዎቹ ክለብ – ፋሲል ከነማ!!
ፋሲል ከነማ ከስኬት እስከ ተግዳሮት!
“ፋሲል ከነማ በትውልዶች ቅብብል የቆመ የከተማችን እግር ኳስ ክለብ ነው” የሚለው አቋም የክለቡ ደጋፊዎች የጋራ ምልከታ ነው። በተለይም ክለቡ በብሔራዊ ሊግ ቆይታው በነበረበት የገንዘብ እጥረት የተነሳ ፈታኝ ጊዜያትን አሳልፏል። በ2008ዓም የብሔራዊ ሊጉ የውድድር ዘመን ፋሲል ምድቡን በበላይነት እየመራ እንኳ ከተማ አስተዳደሩ ለክለቡ የበጀተው በጀት በዓመቱ አጋማሽ አልቆ ነበር። በክለቡ ስም የንግድ ትርዒት (ባዛር) እና የሙዚቃ ዝግጅት (ኮንሰርት) በማዘጋጀት ገቢ በማሰባሰብ፤ በጐንደር ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ፤ በከተማዉ ወጣቶችና አጋር የስፖርቱ ቤተሰቦች ጥረት እንዲሁም “እንዳያማህ ጥራው፣ እንዳይበላ ግፋው” በሆነ መልኩ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በሰጠው ገንዘብ ዓመቱን እንደምንም ቆይቶ ብሔራዊ ሊጉን በድል በማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለመቀላቀል በቃ።
ለብዙዎቹ የአገሪቱ እግር ኳስ ተከታታዮች ክስተት በሆነ መልኩ የፋሲል ከነማ ስኬታማ የሚባል ጉዞ ያለ ደጋፊው ማዕበል የሚታሰብ አልነበረም። የክለቡ ደጋፊዎች ፋሲል ከነማን እንደ አንድ የጎንደር የታሪክ አካል አድርገው ይመለከቱታል። ከዚህ ምልከታቸው በመነሳት ለክለቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ ማቀጣጠያ ዘዴያቸውም ታሪክ ነው። “የጎንደር ክብሯ ታሪኳ ነው!” የሚሉት የክለቡ ደጋፊዎች፤ የፋሲል ከነማ ክለብ ዋና መለያ “አፄዎቹ” ሆኗል። አዲስ አበባ ስታዲየም እንደዋዛ ስላቅ “ክቡር ትሪቡን፣ ካታንጋ፣ ሚስማር ተራ፣ ከማን አንሼ”፣…የሚባሉ የስታዲየሙ መቀመጫዎች በአረጀው የጐንደሩ ፋሲለደስ ስታዲየም እንዲያ ያሉ ስያሜዎች አይታሰቡም። ይልቁንስ ክቡር ትሪቡኑ በክለቡ መጠሪያ (መለያ) “አፄዎቹ” ሲባል፤ ቀሪ የስታዲየሙ የተመልካቾች መቀመጫዎች “ቋረኞቹ”፣ “ዞብል”፣ “እቴጌ ምንትዋብ”፣ … የሚሉ ስያሜዎችን በመስጠት ከጎንደር ታሪካዊና ትውፊታዊ ሁነቶች ጋር የማዛመድ ሥራ ተሰርቷል።
በፖለቲካ አፈና፣ በማህበራዊ ሕይወት ብክነትና በኢኮኖሚ መገፋት ተበታትነው የነበሩት የጎንደር ከተማና አካባቢዋ ወጣቶች ፋሲል ከነማ ምክንያት ሆኗቸው በአንድነት ጥላ ስር ተገናኝተዋል። ታሪክ ሲገጣጠም የህወሓት ተስፋፊነት ውጤት የወለደው የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ የተቀጣጠለበት ዘመንና የፋሲል ከነማ የስኬት ጉዞ አንድ ላይ ተገጣጠመ። የወልቃይት ጉዳይ የታፈነው አመፅ ማስፈንጠሪያ ሆኖ በማገልገሉ አደባባዮች በተቃውሞ ድምፅ ተሞሉ። ብላቴናዎቹ እየጣሉ ወደቁ። በሌላኛው ጫፍ አፈሙዝ ተጠምዶባቸው ድጋፋቸውን የማያጎድሉት የፋሲል ከነማ ብርቱ ደጋፊዎች፤ ዛሬም እንደ ቀደመው “ትግል ፍሬ” ቡድን አገዛዙን በተደጋጋሚ ባማረ ህብረ- ዝማሬ ሲቃወሙት ታይቷል።
በፋሲለደስ ስታዲየም፤ ኮለኔል ደመቀ ዘውዱና ጓዶቹ ሥማቸው እየተነሳ ተዘምሮላቸዋል። አርበኛ ጐቤ መልኬ ታስቦበታል። የትውልዱ አመጽ እንደዘመኑ መንፈስ፤ ባማረ ህብረ-ዝማሬ ተንፀባርቋል። ፋሲል ከነማ የጎንደር ክለብ ብቻ ሆኖ አልታየም። ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በመገፋትና በበደል ሂደት ቅርጽ ለመያዝ እየተዉተረተረ ያለዉ የአማራ ብሄርተኝነት ማቀጣጠያ መድረክ እስከመሆን ደርሷል። ከማርቆስ ጎንደር፣ ከባህርዳር ጎንደር፣ ከደብረታቦር ጎንደር…የሚተሙ ወጣቶች የእግር ኳስ ፍቅር አክንፏቸው ሳይሆን የጋራ በደል ስሜት ሳላዛመዳቸው ነው። የጋራ በደል ስሜት ቋንቋ ከሚያዛምደው በላይ የጋራ ተግባቦት ይፈጥራል። የጨቋኙ ክንድ የሚፈተነውም በዚህ የተግባቦት መንገድ በሚፈጠረው ጥምር ኃይል ይሆናል።
የሆነው ሆኖ ዛሬ ላይ ፋሲል ከነማ በአገሪቱ ቀዳሚ የደጋፊ ሃብታም ከሚባሉ ክለቦች አንዱ ሆኗል። የድጋፍ መሰረቱ የሰፋውን ያህል ግን የገቢ አቅሙን ማሳደግ አልቻለም። ትላንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ ዘመናዊ አደረጃጀትና ዘላቂ የገቢ/ስፖንሰር ምንጭ ዕጥረት የክለቡ ፈተና ሆነው ይቀጥላሉ። የፈተናዎቹ ሥረ-ምክንያትም ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸዉ ናቸዉ።
የዘመናዊ አደረጃጀት ፈተናዎች በከፊል፡-
- የፋሲል ከነማንና የደጋፊዎቹን ስኬታማ ጉዞ የሚጠመዝዘው መዋቅራዊ ጉልበትና ፖለቲካዊ ተልዕኮ ያለው የክለቡ ቦርድ አመራር አወቃቀር (የፖለቲካ ቡድን ስብስብ መሆኑ) ፣
- የክለቡ ሥራ አስፈፃሚ አባላት የጥቅም ትስስር፣ ከሙያ ባለቤትነት ውጪ ቴክኒካዊ ውሳኔዎች ላይ ጣልቃ መግባትና በፖለቲካ ሥራ መጠመድ፣
- የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች ከህዝባዊ የክለብ ውገና ይልቅ ብአዴናዊ ዝንባሌ ማሳየት፣ የማሊያ ሽያጭ የነጋዴዎች መጠቀሚያና ከግል ጥቅም ጋር መያያዙ፣ የደጋፊዎች አደረጃጀት መዋቅራዊ አለመሆን፣ የደጋፊ መታወቂያ በቅጡ አለመዘጋጀት …
- የተጫዋቾች የመኖሪያ ካምፕ ጥገናና እድሳት መጓተት፣ ለተጫዋቾች የካምፕ መግቢያ /ምሽት ላይ/ ሰዓት ገደብ ቢኖርም የክትትልና ቁጥጥር መላላት፣
- የአሰልጣኙና ምክትል አሰልጣኙ ተናቦ ያለመስራት ችግር፤ የቴክኒካል ስታፍ አለመዋቀር፣ በሙያው የሰለጠነ የበረኞች አሰልጣኝ አለመቅጠር፣ ብቁ የህክምና ክፍል /ወጌሻን ጨመሮ/ አለማደራጀት፣ ከፍተኛ ገንዘብ የወጣባቸውን ተጫዋቾች ያለ አገልግሎት ማስቀመጥ፣ ለተስፋ ቡድኑ (“ፋሲል ከነማ B”) ትኩረት አለመስጠት፣ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለማቋቋም ፍላጎት አለመኖሩ/መዘንጋቱ፣ ወዘተ ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው።
የዘመናዊ አደረጃጀት እጦት ፋሲል ከነማን ብዙ ዋጋ የሚያስከፍለው ይመስላል። ክለቡ በተጨባጭ ካለበት ፖለቲካዊ ግፊት አኳያ ዘመናዊ አደረጃጀት የሌለው መሆኑ፤ አንድም ዘላቂ ውጤታማነቱን ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተዋል ሌላም “የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት” በሚል ሰበብ ክለቡን ጠልፎ ለመጣል ምቹ መደላድል ይፈጥራል። እንዲህ ያሉ ተጠባቂ ስጋቶችን ለመከላከል፤ የክለቡ ደጋፊ ማህበር አመራሮችና ሥራ አስፈፃሚው ቅንነት የታከለበት የሥራ ትጋት ብቸኛ መፍትሔ ቢመስልም አመራሮቹ ካላቸው ፖለቲካዊ ዝንባሌ አኳያ የሚታሰብ አይደለም። የክለቡን ቴክኒካል ስታፍ ሙያተኞች እጦትና የብቁ ህክምና ክፍል አለማደራጀት ላይ ያሉ ችግሮችን ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የሚመለከታቸው ሙያተኞች ጋር በመቀራረብ ችግሮችን ማቃለል ይቻል ይሆናል። ሌሎች ችግሮችንም እንደየደረጃቸው ለመፍታት የፋሲል ከነማን እውነተኛ ቤተሰቦች ጥረት ይጠይቃል።
የዘላቂ ገቢ/ስፖንሰር እጦት ፈተናዎች በከፊል፡-
የኢትዮጵያ እግር ኳስ በዓለምአቀፍም ሆነ በአህጉራዊ መድረኮች ረብ ያለው ውጤት ባያስመዘግብም፤ የክለቦች ዓመታዊ ወጪ አንድ የክልል ክፍለ ከተማ ዓመታዊ በጀትን መፎካከር ጀምሯል። የተጫዋቾች ወርሃዊ ደመወዝ በአማካይ 60,000.00 (ስድሳ ሺህ) ብር በደረሰበት ሁኔታ ክለቦች ዘላቂ የገቢ/ስፖንሰር ምንጭ እስካልፈለጉ ድረስ በገበያው ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ መቆየት ይቸግራቸዋል። በተለይም ህዝባዊ ክለቦች።
ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳትፎ እንግዳ የሆነው ፋሲል ከነማ፤ ያለ ስፖንሰር እንደ ዉጤታማ ተከላካዩ ያሬድ ባየህ ላሉ ተጫዋቾች በወር 83,333.00 (ሰማንያ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት) ብር እየከፈለ በውድድሩ መቆየት ፈተና እንደሚሆንበት መረዳት አይከብድም። በአናቱም ያለአግልግሎት ለተቀመጡ ተጫዋቾችና ሙሉ ቡድኑ ረብጣ የወር ደመወዝ እየከፈሉ ማስቀመጥ ለአንድ ህዝባዊ ክለብ ከፈተና በላይ ነው።
አንባቢ ግንዛቤ እንዲኖረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን ተሳታፊ ክለቦች ወርሃዊ የደመወዝ ወጪ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ከዚህ በታች ያለውን ሠንጠረዥ ይመልከቱ ፡-
ተ.ቁ | የክለብ መጠሪያ | የደመወዝ ወርሃዊ ወጪ | መግለጫ |
1 | አዲስ አበባ ከነማ እግርኳስ ክለብ | 1,426,832.05 | በብር |
2 | ወልዲያ ከነማ እ/ክለብ | 1,229,657.00 | በብር |
3 | አርባ ምንጭ ከነማ እ/ክለብ | 1,259,492.00 | በብር |
4 | መከላከያ እ/ክለብ | 1,400,396.00 | በብር |
5 | አዳማ ከከነማ እ/ክለብ | 1,223,327.94 | በብር |
6 | ቅዱስ ጊዮርጊስ እ/ክለብ | 1,170,166.63 | በብር |
7 | ድሬደዋ ከነማ እ/ክለብ | 1,169,148.99 | በብር |
8 | ኤሌትሪክ እ/ክለብ | 998,833.00 | በብር |
9 | ደደቢት እ/ክለብ | 996,060.92 | በብር |
10 | ኢትዮጵያ ቡና እ/ክለብ | 986,993.00 | በበር |
11 | ሲዳማ ቡና እ/ክለብ | 983,292.00 | በብር |
12 | አዋሳ ከነማ እ/ክለብ | 960,135.00 | በብር |
13 | የባንኮች እ/ክለብ | 957,897.38 | በብር |
14 | ፋሲል ከነማ እ/ክለብ | 810,911.00 | በብር |
15 | ጅማ አባቡና እ/ክለብ | 771,521.00 | በብር |
16 | ወላይታ ዲቻ እ/ክለብ | 404,456.66 | በብር |
የመረጃ ምንጭ፡- ሐበሻ ስፖርት የጥር /2009 ዓ.ም ዕትም፤
ከዚህ በላይ በተመለከተው መረጃ መሰረት ፋሲል ከነማ ከወርሃዊ የደመወዝ ወጪ በተጨማሪ የአውሮፕላን ጉዞ፣ ከሜዳ ዉጭ በሚኖር ጨዋታ የሆቴል ወጪ፣ የምግብ፣ የህክምና፣ የስፖርት ቁሳቁስ፣…ወዘተ አይቀሬና ከባድ ወጪዎች፤ ክለቡ ዘመናዊ አደረጃጀት ካለመከተሉ ጋር ተያይዞ ከሚታይበት የሃብት ብክነትና ምዝበራ ጋር ሲደመር የፋሲል ከነማ ግስጋሴ በካዝናው መራቆት ዳገት ላይ መቆሙ አይቀሬ ያደርገዋል።
በተለይም እስካሁን ባለው የማሊያ፣ ስካርፍ፣ መለያ ባንዲራ ሽያጭ ላይ ክለቡ ምንም ተጠቃሚ አለመሆኑ፤ ከስቴዲየሙ ትኬት ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ክለቡ ለማጠናከር መዋል ሲገባው ለከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ምክር ቤት ገቢ እንዲሆን መደረጉ፤ ፋሲል ከነማን የሚያህል የደጋፊ ሀብታም የተመዘገቡና የአባላት መዋጮ የከፈሉት አባላት ብዛት 153 ብቻ ሆነው መገኘታቸውና መስል ተያያዥ የገቢ ችግሮች ፋሲል ከነማ ካዝና የዝናውን ያህል መሆኑ ቀርቶ ክለቡን ለማሰንበትም አጠራጣሪ አድርጎታል።
በዚህ መሀል የበረከት ስምዖኑ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ የፋሲልን ዘላቂ የገቢ/ስፖንሰር እጦትን ተጠቅሞ በስፖንሰርነት ሥም መዳፉ ስር አስገብቶታል። ያውም እጅግ አሳዛኝና ርካሽ በሆነ ተራዛሚ የስፖንሰርነት ውል። የክለቡ የቦርድ አመራሮች፣ ሥራ አስፈፃሚዎችና የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች ፖለቲካዊ ቅኝት ብአዴናዊ በመሆኑ ስፖንሰርነቱ ያለ ደጋፊ ይሁንታ በቅሬታ ውስጥ መፈፀሙ የሚጠበቅ ነበር።
ይሁንና የስፖንሰርነቱ ውል ይዘት ለብአዴን ፖለቲካል-ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያለዉ መሆኑ ሁሉንም የክለቡን ደጋዎች ያስቆጣ ሆኗል። ብአዴን እንደ “ፖለቲካ ድርጅት”፣ “እመራዋለሁ” በሚለው ክልል ውስጥ የቅቡልነት ችግር ያለበት ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። የህዝቡ ጥላቻና ንቀት ዉጤት የድርጅቱ ንብረት የሆነውን ዳሽን ቢራ ምርት ብዙሃኑ የጎንደር ከተማና አካባቢው ቢራ ተጠቃሚ መጠቀም በማቆሙ (boycott) ያጋጠመውን የገበያ ኪሳራ ለመሸፈን በስፖንሰርነቱ ላይ መውጫ ቀዳዳ ሲፈልግ ታይቷል። ብዙዎቹን ፋሲል ከነማ ደጋፊዎችን ያስቆጣዉም ይሄዉ ተግባሩ ነዉ።
በውሉ መሰረት፤ የስፖንሰርነቱ ቆይታ ዘመን አምስት ዓመታትን ይሸፍናል። የገንዘብ መጠኑ 75 ሚሊዮን ብር የሚል ቢሆንም፤ 42.5 ሚሊየን ብር በካሽ በአምስት ዓመታት ውስጥ ተቆራርጦ ይከፍላል። ቀሪው 32.5 ሚሊዮን ብር ደግሞ ከህዝባዊ አመፁ በኋላ የዳሽን ቢራ ምርት የከፋ የገበያ ድርቀት ባጋጠመው “ሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ ከሚሸጠው ቢራ በሳጥን (ካሣ) ሁለት ብር ተሰብስቦ ለክለቡ ገቢ ይደረጋል” ይላል፤ የስፖንሰርነቱ ውል ይዘት።
ነገሩ “ላም አለኝ በሠማይ…” ዓይነት ነገር ነዉ። የቢራ ምርቱ ተፈላጊነት ቁልቁል በወረደበት ሠዓት፤ “ሰሜን ጎንደር ላይ ከምሸጠዉ ቢራ ከሳጥን (ካሣ) ሁለት ሁለት ብር ሰብስቤ 32.5 ሚሊዮን ብር እከፍላለሁ” የሚለው የውል ይዘት “ዓይናችሁን ተጨፈኑ ላሞኛችሁ” እንደማለት ያለ የጅል ድፍረት ነው። የከተማውና የአካባቢው ህዝብ አሁን በያዘው አቋም ከዳሽን ቢራ ምርት ጋር የሚታረቅ አይመስልም። በተለይም ወጣቱ። ከዚህ ውል በኋላም በማህበራዊ ድረ-ገፆች የሚታየው ቁጣ በቀላሉ የሚታይ አይደልም። ከቶም ቢራውን እንደ አዲስ (boycott) የማድረግ ዘመቻ ተጀምሯል።
የዳሽን ቢራ ፋብሪካ የቦርድ አመራሮችና የክለቡ አመራሮች ተያያዥና ተዋረዳዊ የፖለቲካ ቅኝት ያላቸው በመሆኑ በውሉ መሰረት ገንዘቡ ተቆራርጦ እንኳን በትክክል የሚከፈል ስለመሆኑ ማመን ይከብዳል። የስምዖንን ልጅ በረከትን በምን ተዓምር እንዲህ ባለ ማህበራዊ ችሮታ ማመን ይቻላል?! ያልፈጠረበትን ነገር!! ይልቁንስ የክለቡ ደጋፊዎች የአባልነት ወርሃዊ መዋጮቸዉን በማጠናከር፣ የስቴዲየም ዙሪያ ማስታወቂያዎችን በስፖንሰር መልኩ በመፈለግ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ገንዘብ፣ የሙያተኞችና የቁሳቁስ (በተለይም የህክምና) ድጋፍ በማጠናከር፣ የማሊያ፣ ስካርፍ፣ ስቲከርና ባንዲራ ሽያጭ ለክለቡ ገቢ እንዲሆን ግፊት መፍጥር፣ በዉጭ አገር ሚኖሩ የክለቡን ድጋፊዎች የገንዘብ ድጋፍ በመጠየቅና በክለቡ ሥም የንግድ ትርዒቶችን የሙዚቃ ድግሶችን በማዘጋጀት ገቢዉን ማጠናከር ያልተሄደበት መንገድ በመሆኑ በደጋፊዎች ዘንድ ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል የሚል አስተያየት የክለቡ ጉዳይ ያገባናል ከሚሉ ይሰማል።
የወንድ በር!
ፋሲል ከነማ ካስቆጠረው ዕድሜና ከመጣበት የታሪክ ሂደት አኳያ በአደረጃጀት ተገቢ በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል ማለት ስህተት ይሆናል። በየዘመኑ ግን ህያው የፖለቲካ መድረክ በመሆን የትውልድ አመጽ አርማ ሆኖ አገልግሏል። እያገለገለም ነዉ!!
“ስፖርታዊ ጨዋነት” የሚባል ነገር ፖለቲካዊ ጨዋነት ባላቸው አገራት እንጂ እንደ ኢትዮጵያ ባለች ገደብ የለሽ የዘር ልክፍት ፖለቲካዊ ብልግና በሚታይባት አገር ውሃ የሚቋጥር ጉዳይ አይደለም። ባይሆን የፋሲል ከነማ ተጋጣሚ ክለብ ደጋፊዎችን፤ ተጫዋቾችንና አጠቃላይ የቡድን አባላት ላይ የጸብ ትንኮሳና ጥቃት አለመፍጠር ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። የእስካሁኑ ተሞክሮም ከሞላ ጎደል ይሄን ያመለክታል። በዛኛው ጽንፍ ላለው ዘረኛ ብረት አንጋች ኃይል ግን እጅ መስጠት የሚታሰብ አይደለም። በእምቢተኝነት መጽናት የትውልዱ መንፈስ መገለጫ ነው። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታም ከስቴዲየሙ ውስጥ በአገዛዙ ላይ የሚሰሙ የተቃውሞ ድምፆችን ማቆም የሚቻል አይደለም። ጥልቅ በደልና መገፋት እስካለ ድረስ ተቃውሞ የትም ቦታ መታየቱ አይቀርም። ፋሲል ከነማ በአንድ ላይ ለመገናኝት ምክንያት ለሆናችው ወጣቶች፤ መድረኩ በዋዛ የማይታለፍ ድንቅ አጋጣሚ ነዉ። እናም ከ“ትግል ፍሬ” እሰከ “ፋሲል ከነማ” ድረስ በትዉልዶች ቅብብል ህያዉ የፖለቲካ መድረክ የሆነው እግርኳስ የትውልዱ አመጽ አርማ ሆኖ ይቀጥላል።
ዘመን ሲፈቅድ የህወሓቱ የንግድ ኢምፓየር “ኤፈርት”ም ሆነ የብአዴኑ “ጥረት”፤ የኦህዴዱ “ዲንሾ”ም ሆነ የደኢህዴኑ “ወንዶ” የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት ይሆናሉ። ያኔ መቀሌ ከነማም ሆነ ፋሲል ከነማ ያለ አድሎ ህዝባዊ ክለብ ይሆናሉ!! እስከዚያዉ ግን ፋሲል ከነማ የትዉልዱ አመጽ አርማ ሆኖ ይቀጥላል…
ከዝግጅት ክፍሉ፤ ከላይ እንደተባለው ከክለቦች ጀርባ ያለው ታሪክ ቢዘገብ ወይም ለታሪክ ቢቀመጥ የሚል እምነትና ኃላፊነት የሚሰማችሁ ጽሁፍ አዘጋጅታችሁ ብትልኩልንን እንወዳለን። (ፎቶዎቹን የወሰድነው ከBest Moments of Fasil Kenema Fans/ፋሲል ከነማ ፌስቡክ ገጽ ነው)
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Sad to drag ehapa into your half baked narrative – I gues you grew in a family of derg or meison cadres or yourself was one. Mebrahatu or Simeon doesn’t represent ehapa but then you will dig any dirt and shit to get ehapa in the wrong. Melaku teferra did the red terror and yet you blame ehapa – need I say more? Get a lifefor yourselve golgule – faceless cowards -for history of ehapa or others is gone past that no cadre remnant can change but distort!!!
Dear Ehapa,
Thanks for taking your time to comment.
Nothing better or unique is expected. So feel free to express your thoughts. If you think the narratives of “that generation” are distorted here, come up with a rejoinder. We will entertain it.
We replied because you mentioned Golgul by name.
Regards,
Editor
Le us try again – hope you get it this time and to make ity simple itemised
1) This narrative is about gonder kenema, right? or is a editorial policy that unverified comments are ‘entertained’ even though they have nothing to do with the story line.
2) I don’e eve understand what this has to do with berket simone. Agin the author/s takes liberty to make sweeping generalisations based on a single ‘fact’.
3) You can’t blaem ehapa and say nothing whom ehapa had a dight with – one-sided means that.
4) Can you elaborate what nothing better or unique is expected means? If it is a dig at ehapa, who ceased to exit as was, then get this. Ehapa was unique – in many ways. Better? Yes, it was by any yardistic you want to compare it with other present or past parties.
Let us hear from you – facts not just crude and alubalta remarks.
Are you offended that your golgule was mentioned and you replied? Who do you think golgule is – a news recylcler and one-sided site of has and had been left overs
ehapa
ባገርኛው ይሻለናል ምክንያቱም እዚህ ላይ በፈረንጅኛ የተየቡትን አቃንቶ ማንበቡ መከራ ሆነብን።
በቁጥር 1-3 የጠቀሱትን በተመለከተ ጽሁፉን በቅጡ ያላነበቡ መሆኑን ያመለከተን ስለሆነ ሳይበሳጩ በጥንቃቄና በርጋታ እንዲያነቡት እንመክራለን።
ቁጥር 4ን በተመለከተ እዚያው ጠይቀው እዚያው ስለመለሱት የኛ ምላሽ አስፈላጊ አይመስለንም።
“ጎልጉል”ን በስም የመጥቀሱ ጉዳይ ችግር ኖሮበት ወይም እርስዎ እንዳሉት ሳይሆን ማንኛውም ሰው ወይም “ህጋዊ ሰውነት” ያለው ስሙ ከተጠቀሰ ምላሽ መስጠት ይገባዋል የሚል ዕምነት ስላለን ነው።
በሌሎቹ “አስተያየቶች” ላይ ስላተቱት ስድብ የራስን ማንነት ማሳያ አድርገን ከመቁጠር በስተቀር ምንም መልስ ስለማያስፈልገው ትተነዋል።
በመጨረሻ፥ እኛ ምናልባት እርስዎ እንዳሉት “የደርግና የመኢሶን … ቤተሰብ፥ ካድሬ፥ …” ልንሆን እንችላለን (ግን አይደለንም) ብንሆን እንኳን ማስታወስ ያለብዎት ጉዳይ እኛ ቢያንስ ኢትዮጵያ እንደ ዶሮ ተገነጣጥላ ከዚያ ህዝቧ “ከተስማማ” ወደፊት “ትሰፋ” የሚል ርዕዮት አላራመድንም። ወይም አሁን ህወሃት የሚኮራበትን “የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መገንጠል” በሚለው ከውጪ የተቀዳ ርዕዮት ሰለባዎች አይደለንም።
ቀሪ “ስድቦች” ካለዎት ይቀጥሉ እኛ አብቅተናል።
የጎልጉል አርታኢ
Is that what we call selctive editing? Only want to hear what one wants even afte providing a feedback and comments forum. Self appointed news recylce and one-sided opinion sites are no differnt from either side of the ethio political divide pro or against woyane, Golgule – your precious cover name – just proved, yet again, it is no different form Aiga forum etc.
How many such self glorified site we saw in the past two decades and half plus – some like ethiopian reviev – another self appointed has-been – are shadows of themselves in a limbo – above the dead below the living. Take a deep breath and accept the fact that you are a drop in an ocean – be it in the diaspora or at home with 100 million people. So get your ego checked and leave comments be – tweeter or other such amy provide a lesson to your 3rd world mentality – Golgule!
And another illiterate comparison – tora bora is likened to fasil kenema. Of all the places and battles you can choos within ethiopia you go to a terrorist hide out to make a ‘point’ – stupidity as palin as day. The author/s are avictim of their ‘deep’ historical or cuurent warld affais ‘knowld’ge’? The person/s who were hiding in the said maountain range – it is their followers that beheaded ethiopians in libya. And yet you have to use tora bora to liken fasil kenema – idiots.