• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የድርድር ቅድመ ጸብ “በተቃዋሚዎች” መካከል እና የጠብ-መንጃ “ሰላም” እስከመቼ?

February 6, 2017 10:38 pm by Editor 2 Comments

ቅድሚያ “የታሰሩ ይፈቱና አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳ” የሚለው ኢህአዴግን ሳይሆን “ተቃዋሚዎችን” አላስማምም፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች “ቅድሚያ ይፈቱ” የማያስማማቸው ተቃዋሚዎችን አንድ የማድረግ ሃሳብም አለ። ይህንን ሃሳብ የሚያራምደው ደግሞ ኢዴፓ ነው። የህብረቱን ጥያቄ በፕሮግራም ደረጃ አርቅቆ በይፋ ጥሪ ያቀረበውን ኢዴፓ ተቃዋሚዎች የሚያቀርቡትን ቅድመ ሁኔታ አይደግፍም። ይህንኑ ተከትሎ ኢዴፓ በኢህአዴግ ይደገፋሉ ተብለው ከሚታሙትና የቤተሰብ ጥርቅም የሆኑትን ካልሆነ በዚህ አቋሙ ያሰበውን ሊያሳካ እንደማይችል አስተያየት እየተሰጠ ነው።

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ አካሄድ እንደተቀየረና ከቀድሞው ይልቅ እየከረረ መሄዱን ሁሉም ወገኖች ይስማሙበታል። በደጋፊና ተከታይ ብዛት ተጽዕኖ ፈጣሪ ወይም ተሰሚነት አላቸው የሚባሉት የብሄር ፓርቲዎች ይህንን የከረረውን ፖለቲካ የማርገብ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ራሱ ኢህአዴግ ያመነበት፣ የውጭ ድጋፍ ሰጪ አጋር አገሮችም ሃሳብና ማሳሰቢያ የሰጡበት፣ ፓርቲዎቹም “እውነት ኢህአዴግ ከልቡ ከሆነ” እያሉ ማረጋገጫ የሚጠይቁበት ጉዳይ ነው።

ድርድር የሚባለው ጉዳይ የመጣውም ከዚሁ መንፈስ እንደሆነ እሙን ነው። ጉዳዩን ተአማኒ የሚያደርገው ደግሞ “ሕገመንግስት እስከመቀየር ወይም እስከማሻሻል የሚደርስ ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ ነኝ” ሲል ኢህአዴግ የድርድር ቡፌ ማዘጋጀቱ ይሆናል። በተጓዳኝ የእርቅ ጉዳይ መነሳቱም ጉዳዩ የታሰበበትና የታቀደበት ስለመሆኑ አመላካች ነው። ጥርጣሬ ቢኖርም ድርድርም ሆነ እርቅ የሚለው ሃሳብ ብዙዎችን አስማምቷል። ተስማምተዋል የሚባሉት ወገኖችና ፓርቲዎች “እስኪ እናየዋለን” ሲሉ ኢህአዴግ የመጨረሻ ፈተና ለራሱ እንደሰጠ እየተናገሩ ነው።

ከውጭ ብቻ ሳይሆን ኢህአዴግ አስቸኳይ ጊዜ ያወጀበት የውስጥ ችግሩ ውስጥ ውስጡን ሲብላላና እየተቀጣጠለ ሄዶ የቀበሌ መዋቅሩን ሳይቀር አስልሎ ስለበላው እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እየመሰከሩ ነው። የቀበሌና የወረዳ መዋቅሮች ስለመንኮታኮታቸው ዋናው ማስረጃ ደግሞ በመላው አገሪቱ እስኪባል ድረስ የተዛመተው ተቃውሞ ዋና ማስረጃ ሲሆን፣ ተቃውሞውን ተከትሎ በሺህ የሚቆጠሩ ከፍተኛና ዝቅተኛ አመራሮች እንዲወገዱ፣ ከሃላፊነት እንዲነሱ ወይም ዝቅ እንዲሉ፣ አለያም ተራ ዜጋ ሆነው ሲፈለጉ “አለሁ” እንዲሉ ፋይል ተክፍቶባቸው እንዲቀመጡ መደረጋቸው ነው።

ራሱ ኢህአዴግ ከመነሻው “ትክክል ነው” ያለው ሕዝባዊ ቁጣና አመጽ፣ ለጊዜው በአስቸኳይ አዋጅ ጋብ እንዲል ሲደረግ፣ ከዛው ጎን ለጎን የጠፋው የሰው ህይውት፣ በስር ላይ የደረሱ በደሎች የብዛታቸውን ያህል ቂም አምርተዋል። ይህ የተጠራቀመ ቂም በየትኛው ጊዜና ሰዓት የበቀል ክንዱን ከፍ እንደሚያደርግ ባይታበለም፣ ሁሉንም ጉዳይ “በይቅርታ እናትመው” መባሉ አሁንም የጉዳዩን አሳሳቢነትና ነገሮች በዚህ ሊቀጥሉ እንደማይችሉ አመላካች ነው። ለዚህም ይመስላል አሜሪካ “ነግረናል ወሳኔውና ምክሩን ስራ ላይ ማዋል የኢህአዴግ ፈንታ ነው” በማለት ማስጠንቀቋን ያስታወቀችው።

ከዚህ አንጻር ቀደም ባሉ ጊዜያት እንደሚካሄደው አይነት ተራና ለውጪው ፖለቲካ ግብአት እንዲመች የሚደረጉ ውይይቶችና ድርድሮች ጊዜ ያለፈባቸው ይመስላሉ። ከዚህ ቀደም ኢህአዴግ ስለ ድርድርና ሽምግልና ሲጠየቅ “ለድርድር የሚያበቃ ምንም ጉዳይ የለም” ሲል እንዳልነበር የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጫና / እዚህ ላይ ተቃዋሚ ሲባል በቤተሰብ የተሰባሰቡትንና እንድ ቅንጅት፣ ኦብኮና ሌሎች ከምዝገባ ፈቃድ የዘለለ ልዕልና የሌላቸውን አያካትትም/ ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም ህዝብ አስገዳጅ ሁኔታን ፈጥሯል። ስለዚህም ድርድሩ በሙሉ መስጠትና መቀበል መርህ እንዳይሆን የሚያግደው ጉዳይ እንደማይኖር ከግምት በላይ ይታመናል። እንደራደር ያለው ኢህአዴግም አሁን አፈ ቀላጤ ድርጅቶች ምንም ሊረዱት እንደማይችሉ ያመነ ይመስላል።

የድርድሩ ጉዳይ እንዲህ በስሎና ነፍሮ የመታ ሆኖ ሳለ አንቱ የተባሉ የፖለቲካ መሪዎችን አስሮ፣ ደጋፊውችን አጉሮና አባላትን እያሳደዱ የሚደረግ የሰላም ድርድር ለተቃዋሚዎች ክህደት፣ ለራሱ ለኢህአዴግ ደግሞ ድንቁርና ከመሆን አይዘልምና ጥያቄው “ቅድመ ሁኔታም” ድረስ ሊያደርስ ባልቻለ ነበር። ሲሆን ሲሆን “ብረት አንስተናል” የሚሉትን ቢያካትት ፋይዳው የጎላ፣ ውጤቱም ተስፋው የበዛ በሆነ ነበር። ይህ ለጊዜውም እንኳን ባይቻልም በአገር ቤት ጽንፈኞችን ሲታገሉና ሲያሽመደምዱ የነበሩትን ጨምሮ የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎችን እየወነጀሉ “እንታረቅ” ማለት ሲጀመር ድርድሩን የከሸፈ እንዳያደርገው ስጋት አለን የሚሉትን ወገኖች በቀናነት መቀበልና ማድመጥ ይጠበቃል፤ ግድም ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ነው ባለፈው ቀዳሜ አቶ ልደቱ አያሌውንና የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹን የቪኦኤዋ አዳነች ፍስሃዬ ባነጋገረችበት ወቅት አስገራሚ የተባለው አለመግባባት የተደመጠው።

በጥያቄና መልሱ ከተነሱት ነጥቦች መካከል “ቅድም ድርድር” የሚለው ዋናና ቁልፍ ጉዳይ አንዱ ነበር። አቶ ልደቱ “በቅድመ ሁኔታ አናምንም” ሲሉ አቶ ሙላቱ “ያልተነካ ግልግል አያውቅም” ሲሉ በንፅፅር መልስ ሰጡ። እሳቸው ይህን ሲሉ የታሰሩባቸውን የድርጅታቸው አመራሮች፣ ደጋፊዎችና አባላት ከግምት ውስጥ አስገብተው ነበር።

አንድ በስውዲን የግጭት አፈታትና አወጋገድ ሳይንስ ትምህርት እየተከታተለ ያለ ተማሪ ተማሪ እንዳለው “ኦፌኮ በቀለ ገርባን፣ መረራ ጉዲናን፣ የማይዘመርለትን ኦልባና ለሊሳን.. ሌሎች አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች አሳስሮ ከኢህአዴግ ጋር ምን ብሎ ይደራደራል? ተደራድሮስ ለሕዝቡ ምን ይዞ ይመጣል? ከዛስ የድርጅቱ ህልውና ምን ይሆናል?” ሲል ይጠይቃል።

አያድርገውና ኢዴፓ ልክ እንደ ኦፌኮ መሪዎቹ፣ አባላቱና፣ ደጋፊዎቹ ቢታሰሩ “በቅድመ ድርድር አላምንም፤ አባሎቼን፣ አመራሮቼን፣ ደጋፊዎቼን ለምን ታሰሩ ብዬ አልጠየቅም ይል ነበር?” ሲል አስተያየት ሰጪው ይጠይቃል። አያይዞም አቶ ልደቱ በግልጽ ኢህአዴግ ሆነው ቢገላገሉ እንደሚሻል ይጠቁማል።

አቶ ልደቱን የሚደገፍ ሌላ አስተያየት ሰጪ “አቶ ልደቱ እንዳሉት ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ ድርድር ከሚጨናገፍ ጉዳዩን ቀዳሚ አጀንዳ ማድረግና መመልከቱ የተሻለ ነው” ይላል። አያይዞም አቶ ልደቱ እንዲህ ያለውን ጉዳይ በዝምታ ቢያልፉና ለወደፊት ፓርቲያቸው አቋም እንደሚይዝበት ቢያስታውቁ የተሻለ እንደሚሆን ጠቁሟል።

አዳነች “የታሰሩት አመራሮች ካልተፈቱና፣ አስቸኳይ አዋጁ ካልተነሳ ድርድሩን አትቀበሉም ማለት ነው?” ስትል ደግማና ደጋግማ እየጠየቀች፣ በአቶ ልደቱ በኩል ማስተባበያ እያሰጠች ባስኬደችው ቃለ ምልልስ አቶ ሙላቱ “የሚደራደሩለትን አስሮ ማን ይደራደራል” ሲሉ መልሰውላታል። አቶ ልደቱንም “ያልተነካ ግልግል አያውቅም” ሲሉ ኢዴፓ እሳቸው እንደሚመሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ፓርቲ መከራና ስቃይ እንዳልደረሰበት ለማሳየት ሞክረዋል።

ቀደም ሲል “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ አንፈልግም” ብለው የነበሩት አቶ ልደቱ ፣ በዚህኛው ቃለ ምልልስ አዋጁ እንዲነሳ ፣ የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎች እንዲፈቱ ምኞቱ እንዳላቸው ተናግረዋል። ኢዴፓ አመራሮቹ ባይሆኑም የታሰሩ አባላት እንዳሉትም አመልክተዋል። ሁሉም ሆኖ ግን ኢዴፓ በመርህ ደረጃ ለድርድር ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ የድርድር አካሄድን ያደናቅፋል የሚል የቆየ እምነት እንዳለው ነው አቶ ልደቱ ያመለከቱት።

“በሰው አገር የከበረና በጨለማ የጨፈረ አንድ ነው’ የሚለውን የትግራይ ተረት ያስታወሰው የግጭት አወጋገድ ትምህርት ተማሪ” አቶ ልደቱ አሁን እየተከተሉ ያሉት አካሄድ ስልታዊ ነው። ተቃዋሚዎችን ሳይሆን ገዢውን መንግስት በስልት ማስደሰትና እሱን ሆኖ መናገር፤ ይህ ማለት በሌሎች ቁስል እንጨት ስደድበት እንደማለት ይቆጠራል። እርገጠኛ ነኝ ስለዚህ ጉዳይ ዋናው የኢህአዴግ ሰው ቢጠየቁ ከአቶ ልደቱ የተለየ መልስ የላቸውም” ሲል አቶ ልደቱ ቢያንስ ተቆርቋሪነታቸውን ሊያሳዩ በተገባ ነበር ሲል ትዘብቱን ያስቀምጣል። አያይዞም “ኢዴፓ በዚህ አቋሙ ከማን ጋር ተዋህዶ ለመስራት ነው የውህደት ጥሪ ያቀረበው? ኢህአዴግ የፈጠራቸውን አሰባስቦ የተሻሻለው ሌላ ኦህዴደ ወይም ብአዴን ወይም ደህዴን ከመሆን አይዘልም። እንዲህ ያለው አካሄድ ላለፉት 25 ዓመታት ተሰርቶባቸው ውጤታቸው በገሃድ ታይቷል” ሲል አስተያየቱን ያጠቃልላል።

አቶ ልደቱና የእሳቸው ፓርቲ አካሄድ የተመረጠ እንደሆነ የሚናገረው አስተያየት ሰጪ በበኩሉ “ኢህአዴግ ለለውጥ በሩን የሚዘጋው ጽንፈኛ አካሄድ ስለሚያስፈራው ነው። ስለዚህም እንደ አቶ ልደቱ አይነት አካሄድ ካልሆነ በስተቀር እስኪሞት ይንገዳገዳል እንጂ ውንበሩን ለማንም አይሰጥም። አንድ እውነት አለ። ብአዴንና ኦህዴድ እንደ ድርጅት አሉ አይባልም። ለዚህም ነው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያስፈለገው። ስለዚህ አሁን ስጋት ውስጥ ያለን መንግስት ምቾት የሚነሳ የትግል ስልት የትም አያደርስምና በፖለቲካዊ መለሳልስ ነገሮችን በዝግ በር መያዙ ያዋጣል” ባይ ነው።ይህ አስተያየት ሰጪ ሚዲያዎችና አስተያየት ሰጪዎች ድርድሩን አስመልከቶ ጥንቃቄ ቢወስዱ፣ የማበረታት ስራ ላይ ቢያተኩሩና፣ አገሪቱ የገባችበት አደገኛ ሁኔታ እንዲገፈፍ ቢሰሩ የተሻለ እንደሆነ ይመክራል። ገና በጅምር ላይ ባለ ጉዳይ ብዙ ማለቱ ማንኛውንም ወገን እንደማይጠቅምም ያሰምርበታል።

ድርድሩ አጀንዳ መቅረጽን ጨምሮ በአራት ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ የተደረሰበት መሆኑ አይዘነጋም። በድርድሩ ድምጽ ብልጫ አንዱ የመወሰኛ አማራጭ መሆኑና ኢህአዴግ ፈለፈላቸው የሚባሉት ሁሉ የሚካተቱበት መሆኑ ብዥታን የፈጠረ መሆኑም አይዘነጋም። ከድርድሩ በፊት ተደራዳሪዎች እርስ በእርሳቸው አለመግባባታቸው ገኖ መውጣቱ አሳዛኝ እየተባለ ነው። አይኑን በጨው ያጠበው የኢትዮጵያ ፖለቲካ የተቅውሞ ኮሪድር ይህን ይመስላል። ቀኑ ሲደርስ ኢህአዴግ ምን ይል ይሆን? (ምንጭ: ዛጎል ዜና)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Lusif says

    February 9, 2017 10:50 pm at 10:50 pm

    Do not underestimate the ruling party. When, one does, he is just standing on his grave, without the slightest knowledge when he will go in.
    The ruling party is strong and has every resources at its disposal and services. The oppositions need to match that strength to the minimum. Currently, that equation is not there. The balance is tilted towards the ruling party. Any effort by the oppositions seem fruitless, unless the ruling party is generous and willing enough to avoid farther crises and violence b/n itself and the people.
    One thing the ruling party should know is that resource will be consumed, will be exhausted,strength will gradually vanish, then what?????? The sooner the better to find in enduring solutions. It is the best way for every citizens.

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    February 11, 2017 09:56 pm at 9:56 pm

    Guys!!! EPRDF is stronger than ever!!! Economically, Politically,and Socially he showed enormous movements!!! In fact, the people of Ethiopia is expecting more from the ruling party. Heavy industries, and cottage industries are to be given priorities. The cottages are helping the individuals to make the financial support as well, to encourage the local business men to participate. Otherwise, the contraband activities must be monitored by Federal Police.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule