በፖለቲካ ሳይንስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “አብዮት” የሚለው ቃል “አዲስ ሥርዓትን በመሻት የነባሩን መንግስታዊ ወይም ማህበራዊ ሥርአት በግዳጅ ማስወገድ” በሚል የትርጉም ማዕቀፍ ላይ ሊያርፍ ይችላል፡፡ ‹የሰው ልጅ አብልጦ የሚሻው የተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት በየአገራቱ አስካልተመሰረተ ድረስ አብዮት በየትኛውም የዓለም ክፍል አይቀሬ ክስተት› እንደሆነ የፖለቲካ ሳይንስ መምህራኑ አብዝተው ያስተምራሉ፡፡ ሰሚ የለም እንጂ፡፡ ኢህአዴግ የሚባል ገዥ መደብ ፣ ሩብ ክፍለ ዘመን ያህል አገሪቱን እንደ “መንግስት” በመራበት ተራዛሚ የአገዛዝ ዘመኑ ከፍ ሲል ከአምሮ በላይ የሆኑ፣ ስልጣን ላይ በወጣ ስብስብ ይፈፀማሉ ተብለው የማይታሰቡ ውስብስብ የፖለቲካ ሴራዎችን በመስራት ያደረሰው ሰብአዊ ውድመት፤ ዝቅ ሲል ደግሞ ከሰውነት በታች በወረደ የዝቅተኝነት ስሜት በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው የማህበረ ኢኮኖሚ … [Read more...] about የአብዮቱ አይቀሬነትና ጥቁምታዎቹ!
Politics
ኦባማ የአፍሪካን ገዢዎች እያዋዛ ደቆሳቸው!
ኦባማ በአፍሪካ ኅብረት ያደረገው ንግግር ብዙ ጥያቄዎችን መልሷል፤ የኦባማ ጉብኝት ያስከተለው ጫጫታ ሁሉ መልስ አገኘ፤ የሰው ልጆች በመሀከላቸው ምንም ዓይነት የአድልዎ ልዩነት ሳይደረግባቸው በሰውነታቸው ብቻ በተፈጥሮ ያገኙትን ክብራቸውንና ሞገሣቸውን አስከብረው መኖር እንዳለባቸው በአጽንኦት ተናገረ፤ ዛሬ የአሜሪካኑ ፕሬዚደንት ያደረገው ንግግር ከፕሬዚደንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ እስከ ፖሊሶች፣ መርማሪዎችና አዛዦቻቸው፣ እስከጦር ኃይሉና አዛዦቻቸው፣ አስከዓቃብያነ ሕግና ዳኞች፣ እስከወህኒ ቤት ጠባቂዎችና አዛዦች በየሥልጣን ተዋረዱ ላይ ሆነው የኢትዮጵያውያንን የሰውነትና የዜግነት እኩልነት አፈራርሰው በጎሣ መሠረት ላይ ሊበታትኑት የሚሞክሩትን በኃይለኛ ቃላት ከመሬት በታች ከቶአቸዋል፤ ማሰብና ማስተዋል የጎደለው፣ ከአፍንጫ የራቀ አመለካከት የሌለበት፣ አገርን የሚያጠፋ፣ ከሰውነት ጎዳና … [Read more...] about ኦባማ የአፍሪካን ገዢዎች እያዋዛ ደቆሳቸው!
ለህወሃት/ኢህአዴግና መሰል የአፍሪካ አምባገነኖች የባራክ ኦባማ መልዕክት
በቅድሚያ ለህወሃት/ኢህአዴግ “የአንድን አገር (ኅልውና በማስጠበቅ) አንድ አድርጎ ማቆየት የሚችለው መሪው (ወይም በኢህአዴግኛ ፓርቲው ወይም ግምባሩ) እርሱ ብቻ እንደሆነ የሚናገር ከሆነ ያ መሪ (ፓርቲ ወይም ግምባር) አገሩን ከመገንባት ከሽፏል ማለት ነው … ማንም ሰው (ፓርቲ/ግምባር) ዕድሜልኩን መሪ/ፕሬዚዳንት መሆን የለበትም፤ አዲስ ሃሳብና ትኩስ ኃይል ወደ ሥልጣን ሲመጣ ያቺ አገር ከቀድሞው እየተሻለች ትሄዳለች፡፡” ቀጠሉ - “ሰዎች ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ለምን መቆየት እንደሚፈልጉ እኔ አይገባኝም፤ በተለይ ብዙ ገንዘብ እያላቸው …” ልማታዊ አምባገነኖቹን የሚመለከት ነበር፡፡ ለሕገመንግሥት ቀያሪዎችና ሕግ አሻሻዮች “አንድ መሪ በሥልጣን ለመቆየት በጨዋታው መሃል ሕግ ለመቀየር ሲሞክር (በዚያች አገር) ያለመረጋጋትና የነውጥ አደጋ ያስከትላል፡፡” ራሳቸውን ከአፍሪካ “ዘላለማዊና … [Read more...] about ለህወሃት/ኢህአዴግና መሰል የአፍሪካ አምባገነኖች የባራክ ኦባማ መልዕክት
“ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ እንደመርሳት እቆጥረዋለሁ”
"ኦባማ ኢህአዴግን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠ ነው ማለታቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ውሃ የሚቸልስ ነው" የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ሀምሌ 20/2007 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ ቤተ መንግስት ውስጥ ለአሜሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የሚያደረገው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ ለነገረ ኢትየጵያ ገልጸዋል፡፡ የራት ግብዣው ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጥሪ የተደረገላቸው ኢ/ር ይልቃል "አሸባሪ አድርጎ የሚቆጥረን ኢህአዴግ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ሲመጡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ለማስመሰልና ዕውቅና ለማግኘት ያደረገው በመሆኑ አልገኝም" ብለዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል አክለውም "የኢትዮጵያ ህዝብ ጭቆና እና ስቃይ ውስጥ ባለበት በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ … [Read more...] about “ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ እንደመርሳት እቆጥረዋለሁ”
የሱዛን ሳቅ
ፕሬዚዳንት ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ከመጀመራቸው በፊት የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ሱዛን ራይስ ወደ ኬኒያ እና ኢትዮጵያ ስለሚደረገው ጉብኝት መግለጫና ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሸ ሰጥተው ነበር፡፡ የጉብኝት ዝርዝር መርሃ ግብር በማስረዳት ንግግር የጀመሩት ራይስ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢህአዴ ሹማምንትና ከአፍሪካ ኅብረት ኃላፊዎች እንዲሁም ከአህጉሪቱ መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ አስረድተዋል፡፡ ከጠያቂ ጋዜጠኞች መካከል ተራው የደረሰው አይዛክ አምባሳደር ራይስን ስለ ጉዞው የጸጽታና ደኅንነት ጉዳይ ከጠየቀ በኋላ ከዚህ በፊት ሌላኛዋ ጋዜጠኛ (ክሪስቲ) ያነሳችውን ሃሳብ በማጠናከር “ፕሬዚዳንት (ኦባማ) የኢትዮጵያና የኬኒያ መሪዎች በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ አድርገው ይቆጥሯቸዋል?” በማለት ጠየቀ፡፡ ሱዛን ራይስ ማስረዳት ጀመሩ የጸጥታውና የደኅንነቱ … [Read more...] about የሱዛን ሳቅ
ኦባማ ባዲሳባ፣ የሚጠበቁ ምጸቶች
(ሀ) ፕሬዚደንት ኦባማ ነገ እሑድ አዲስ አበባ ይገባሉ (ከመግባታቸው በፊት የተጻፈ ነው)። አንዱን ቀን - እንደደንቡ ሰኞ - በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ራት እንደሚኖር ይጠበቃል። የታሪክ ምጸቱን ከዚያ ጀምረን እናደንቃለን። ራቱ ምኒልክ በሠሩት፣ ዛሬም በስማቸው በሚጠራው ቤተ መንግሥት ይሆናልና፤ መቼም ለራት ሼራተን፣ አለዚያም መቀሌ - አዳማ - ባህርዳር - አዋሳ - አሳይታ--- አይወስዷቸውም ብዬ ነው። ራቱንም ቦታውንም መቃወሜ አይደለም። አገር የመሥራት ሙከራ ቀልድ አይደለም፣ የሙከራው ሒደትና ውጤት ምንም ይሁን የሞካሪዎቹ ስም ድንገት ተንኖ አይጠፋምና እንዲህ ያለውን ታሪካዊ ምጸት ይጋብዘናል ለማለት ነው። (ኦባማ ከጋዜጣዊ መግለጫ በስተቀር የፖሊሲና የፖለቲካ ጉዳዮችን በስፋት የሚናገርበት መድረክ ስለመኖሩ አላወቅንም። ከኖረ ግን፣ አድዋን ማንሳቱ ሳይታለም የተፈታ ነው፣ ምኒልክንም … [Read more...] about ኦባማ ባዲሳባ፣ የሚጠበቁ ምጸቶች
ብርሃኑ ነጋ “… ዱር ወጡ …”
* የሠራዊቱ ሞራል ከፍ ብሏል ከአርበኞች ግንባር ጋር የተዋሃደው የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የፓርቲው የአመራር አባላት የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ታጣቂዎቻቸው ወደሚንቀሣቀሱባት ኤርትራ ጠቅልለው መሄዳቸውን የአመራር አባላቱ አስታወቁ፡፡ ብርሃኑ አስመራ መግባታቸው ከተሰማ በኋላ የሠራዊቱ ሞራል ከፍ ማለቱና ከአገር ውስጥ ግምባሩን ለመቀላቀል የሚፈልገው ሕዝብ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል፡፡ ቁጥራቸው ይፋ ያልተደረገ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአመራር አባላትን ይዘው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ኤርትራ ያመሩት ሌሎች አማራጮችን ጨምሮ በብረት ትግልና በሕዝባዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያን ገዥ ፓርቲ ለማስወገድ መሆኑን የአመራር አባላቱ ይናገራሉ፡፡ “ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ጓዶቻቸው ትግል ወደሚካሄድባቸው አባባቢዎች ያመራሉ” ሲሉ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል ዶ/ር ታደሰ ብሩ … [Read more...] about ብርሃኑ ነጋ “… ዱር ወጡ …”
ክብሩ የተነካው የክብር ዶክትሬት
እንደብዙዎቹ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ዩኒቨርሲቲው በየጊዜው የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን በንግግር እንዲከፍቱ ለመረጣቸው ታላላቅ ሰዎች የክብር ዶክትሬት ይሰጣል፡፡ እ.ኤ.አ. 2009 ላይ ግን የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን በንግግር ለከፈቱት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የክብር ዶክትሬት ላለመስጠት መወሰኑን አስታወቀ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፕሬዚዳንቱ ልምድና የሥራ ውጤት ለክብር ዶክትሬት ጣሪያ አልደረሰም የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ ጉዳዩ በተወሰነ መልኩ ውዝግብ አስነስቶ የነበረ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የመክፈቻ ንግግር አድራጊዎችንና የክብር ዶክትሬት የሚሰጣቸውን ግለሰቦች የሚመርጥበት የራሱ ነፃ የሆነ ሒደት እንዳለው፤ የክብር ዶክትሬቱ የሚሰጠውም ለትልቅ ስኬት መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡ በወቅቱ ዲግሪው የክብር ከመሆኑ አንፃር ዩኒቨርሲቲው አሠራሩን መሠረት በማድረግ በውሳኔው … [Read more...] about ክብሩ የተነካው የክብር ዶክትሬት
ሃዲያ ሞሃመድ! ያልተዘመረላት ጀግና
ያልተዘመረላት፣ ያልተነገረላት ጀግና ኢትዮጵያዊት ሴት ናት። እንደሌሎች "እኔ ምን አገባኝ? አርፌ ልቀመጥ" ብላ፣ ባርነትንና ዉርደትን አሜን ብላ ተቀብላ፣ ሕሊናዋን ሸጣ፣ የገዢው ፓርቲ አዉደልዳይ ሆዳም ካድሬና አገልጋይ ሆና፣ በዘረኝንትና በጠባብነት በሽታ ተለክፋ መኖር ትችል ነበር። ግን አላደረገችውም። ከደቡብ ክልል ከወላይታ ሶዶ ናት። የወያኔ ቡችላው ሃይለማሪያም ደሳለኝ መጣሁበት ካለው። እንደ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሌሎች አሽከር አልሆነችም። እንደ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አልተንቦቀቦቀችም። እንደ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሕሊናዋን አልሸጠችም። የወላይታ ጀግና የሆነውን የንጉስ ጦናን ወኔ ተላብሳ፣ ለእዉነት፣ ለፍትህ፣ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለኢትዮጵያ አንድነት ቆመች። የወላይታ ሕዝብ በባህሉ፣ በቋንቋም በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ፣ መብቱ ሲደፈር የማይወድ፣ ታታሪ ሕዝብ ነው። ይች ሴት … [Read more...] about ሃዲያ ሞሃመድ! ያልተዘመረላት ጀግና
ያልተፈቱት “አሸባሪዎች”
1 - ተመስገን ደሳለኝ 2- እስክንድር ነጋ 3- ናትናኤል መኮንን 4- አንዳለም አራጌ 5- ውብሽት ታዬ 6- አበበ ቀስቶ 7- ሃብታሙ አያሌው 8- ድልንኤል ሺበሺ 9- አብርሃ ደስታ 10- የሽዋስ አሰፋ 11- ዘላለም ወርቅአገኘሁ 12- አቤል ዋበላ 13- ናትናኤል ፈለቀ 14- በፍቃዱ ሃይሉ 15- አጥናፍ ብርሃኔ 16- ፍቅረማርያም አስማማው 17- እየሩሳሌም ተስፋው 18- ብርሃኑ ተክለያሬድ 19- ኦልባና ለሌሳ 20- ቴድሮስ አስፋው 21- ማትያስ መኩርያ 22- ብሌን መስፍን 23- ተዋቸው ደምሴ 24- ንግስት ወንዳፈራሁ 25- ሜሮን አለማየሁ 26- ደሴ ካህሳይ 27- ናትናኤል ያለምዘውድ 28- ሰንታየሁ ቸኮል 29- ማስተዋል ፈለቀ 30- ንግስት ወንድይፍራው 31- ሂሩት ክፍሌ 32- እማዋይሽ አለሙ 33- ሰለሞን ከበደ 34- የሱፍ … [Read more...] about ያልተፈቱት “አሸባሪዎች”










