• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የሳሙኤል ግድያ ለታጋዮችም ለገዳዮችም ትልቅ ትምህርት ነው!”

July 5, 2015 11:54 pm by Editor Leave a Comment

ስለ ሳሙኤል ግድያ ብዙ ነገር ተብሏል፡፡ ብዙዎች ቁጭታቸውን ገልፀዋል፡፡ ለእኔ ከሳሙኤል አወቀ ግድያ ምን እንማራለን? የሚለው ነው ትልቁ ቁም ነገር፡፡ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ንግግር ተናግረው የተገደሉ ሰዎች ጋር የሚመደብ ሰው ነው፡፡ የሳሙኤል ትውልድ አካል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፡፡ እንደገሚገሉት እያወቀ፣ ነገር ግን ያ ሞቱ ከንቱ እንዳይሆን አስፈላጊውን መረጃ አስቀምጦልናል፡፡ አቡነ ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስተምረው ህዝቡ ለጣሊያን እንዳይገዛ ሰብከው ተገድለዋል፡፡ ለዚህም ሀውልት ቆሞላቸዋል፡፡ ይህ መታሰቢያ ለኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ልዕልና እና የአልበገሬነት ምልክት ሆኖ ለዘላለም ይኖራል፡፡

የአቡነ ጴጥሮስን ታሪክ ተማሪዎችም ይማሩበታል፡፡ የሳሙኤልን ንግግርም ወደፊት እድሜ ከሰጠን እኛ እናየዋለን፡፡ እኛ ባንደርስበት እንኳ መጪው ትውልድ ሳሙኤል ለሀገሩ ሲል ዋጋ እንደከፈለ መታወሱ የማይቀር ነው፡፡ ምክንያቱም ይህን አይነት ታሪክ የሰሩ ሰዎች በህዝቡ ውስጥ ትንሽና የተመረጡ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ በመሆኑም ሳሙኤል ከመካከላችን የተገኘ ልዩና ዕንቁ የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡ ሳሙኤል እኔ በምመራው ፓርቲ፣ በእኔ ትውልድ ውስጥ እንዲህ አይነት ታሪክ መስራቱ ትልቅ የመንፈስ ጥንካሬ ሰጥቶኛል፡፡ ህይወት ምን እንደሆነም አስተምሮኛል፡፡

በህይወት መቆየትን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረውት ከትግል እንድንወጣ የሚመክሩን በርካቶች ናቸው፡፡ እነሱ የሚሉን ህዝብ ሲጨቆን ዝም በሉ ነው፡፡ ሳሙኤል ደግሞ እንዲህ አይነቱን ነገር መስራት እንደሌለብን በደሙና በአንድ በማትተካ ህይወቱ አሳይቶናል፡፡ እንደዚህ የሚሉንን ሰዎች ለመናቅ ሳሙኤልን ማሰብ ብቻ በቂ ነው፡፡ ገንዘብ ሲቸግረኝ ሳሙኤል ህይወቱን ማጣቱን ማስታወስ ይገባኛል፡፡ ለህይወት ትኩረት ስሰጥ፣ መኖር ስመኝ፣ መንፈሴ ሲላላ በእኔ ትውልድ ዘላለማዊ ሆኖ ያለፈውን ሳሙኤልን ማስታወስ አለብኝ፡፡ የሳሙኤል ግድያ ለታጋዮችም ለገዳዮችም ትልቅ ትምህርት ይሰጣል፡፡ በእኔ እምነት ሳሙኤልን የገደሉት በግል ስለሚጠሉት አይመስለኝም፡፡ ሳሙኤል የብሩህ አእምሮ ባለቤት ነው፡፡

የመረጃና የአቋም ሰው ነው፡፡ በጣም ጠንካራ ልጅ ነው፡፡ ይህን አስተሳሰቡንና እምነቱን ነው የጠሉት፡፡ ይህ ሲጠፋ ለሌሎቹም መቀጣጫ መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ ግን በሳሙኤል ደም እኛ ተሰባስበናል፡፡ መፍራትና ወደኋላ ማለት እንደሌለብንም አስተምሮናል፡፡ ከዚህ ባለፈ በዚህ ትግል ውስጥ ለነገ የሚባል ነገር እንደማይሰራ የሳሙኤል ግድያ አሳይቶናል፡፡.የሰው ልጅ በባህሪው ሞኝ ነው፡፡ ዛሬን ብቻ አይደለም ዘላለምንም የምንኖር ነው የሚመስለን፡፡ ለሳሙኤል ግድያ ግን ህይወት ምን ማለት እንደሆነች አሳይቶናል፡፡ ዛሬውኑ ልትጠፋ የምትችል ከንቱ እንደሆነች አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም የሳሙኤል ሞት ትርጉም ያለውን ነገር ዛሬ አድርጌ እንዳልፍ እንጅ ለነገ እንዳልል ትልቅ ትምህርት ሆኖኛል፡፡ ዕቅድ አንድ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ሞት አብሮን ያለ መሆኑን ተረድተን ለሀገራችን የሚጠቅመውንና ዛሬ ማድረግ ያለብንን ነገር ዛሬውኑ መስራት እንዳለብን ነው፡፡ እንደ ሳሙኤል በዚህ አለም የማያልፍ ነገርን ሰርተን ማለፍ አለብን፡፡ በነፃነት ትግል ውስጥ ሳሙኤል ስም ሲነሳ ይኖራል፡፡ እንደ ሳሙኤል በህይወት ትርጉም ያለው ነገር መስራት ለህይወትም ትልቅ ትርጉም ይሰጣል፡፡ በኢትዮጵያ ከሉሲ ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠር ሰው ሞቷል፡፡ ዋናው ነገር ግን 80ና 90 ቆይቶ መሞት አይደለም፡፡ እንደ ሳሙኤል በአጭር እድሜው ያመነበትን ሰርቶ መሞት ትልቅ ትርጉም አለው፡፡

እኛም 90ና 80 አመትን መጠበቅ ሳይሆን በ27 አመትም መቀጨት እንዳለ አውቀን አሁን መስራት ያለብንን በፍጥነት ማከናወን አለብን፡፡ በዚህ ግለኝነት፣ አግበስባሽነት በነገሰበት ሀገር ላይ ህይወትን ያህል ነገር ከፍሎ በደሙ ለእኛው ትውልድ አስተምሮ ሄዷል፡፡ ለሀገር፣ ለህዝብና ለእውነት መቆም የተከበረ ስራ መሆኑን ያውም ህይወቱን እንደሚያጣ አውቆት ለዓላማው በፍላጎቱ ሲሞት ከዚህ በላይ አስተማሪ አያስፈልግም፡፡ በወቅቱ ‹‹ይህ ትውልድ አይረባም፣ ሀገሩን አይወድም፣ ከዝሙትና ከመጠጥ ያለፈ ነገር አያውቅም፣ አይችልም›› የሚባለውን ሳሙኤል የሚባል ብርቱ ልጅ ከመካከላችን ወጥቶ እውነት እንዳልሆነ በተግባር አሳይቶናል፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ የጠፋው ከሳሙኤል አይደለም፤ ለራሳችን የቃል ኪዳን ሰው መሆን ነው፡፡ የሳሙኤልን ቃል የራስ አድርጎ መውሰድ፡፡ ክብር፣ ሞገስ፣ እውነትና ቃል ኪዳን ለራስ ነው፡፡ እሱ አከበርንለትም አላከበርንለትም የሚያምንበትንና የድርሻውን ሰርቶ ሄዷል፡፡ ለራሳችን ለእውነት፣ ለህዝብ፣ ለሀገር መቆም የሚያስከብር መሆኑን አስተምሮን አልፎአል፡፡

ይህንን ሳሙኤል እያወቀው ሞቶ የሰጠንን ክብር፣ ቃልና መስዋዕትነት ሳናጓድል አደራ የማንበላ ሰዎች እንዳንሆን፡፡ እኔ የምታገለው ለማንም አይደለም፡፡ ይች እግዚያብሄር የሰጠኝ እድሜ ትርጉም ያላት ሆና እንድታልቅ ስለምፈልግ ነው፡፡ ሳሙኤል በልጅነት እድሜው ቤተሰቦቹን አሳዝኖ ለእኛ ዋጋ ከፍሎልናል፡፡ ይህን ቃል ኪዳን ድርጅታችን እንደ ሰማያዊ፣ እያንዳንዳችን እንደ ግለሰብም፣ እንደማህበረስብና እንደትውልድም እንዳንበላ ብርታቱን ይስጠን እላለሁ፡፡

(ነገረ ኢትዮጵያ)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am
  • የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው December 7, 2020 12:38 am
  • የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ December 6, 2020 11:41 pm
  • “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ December 2, 2020 12:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule