ከአዘጋጆቹ፡- ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የፌስቡክ ወዳጃችን “የአማራ ክልል ዳኞችን ድምፅ አስተጋቡልን” በማለት በውስጥ መስመራችን የላኩልንን ከዚህ በታች አቅርበነዋል፡፡ ጋዜጠኝነት “ወንጀል” በሆነባት ኢህአዴግ በሚገዛት አገራችን በስም የተጠቀሱትን ሹመኛ ለመጠየቅና ሁኔታውን ለማረጋገጥ አንችልም፡፡ ሆኖም ግን መረጃው ስህተት ነው የሚል የኢህአዴግ አካል ምላሽ ከሰጠን ለሕዝብ እናቀርባለን፡፡
“የአማራ ክልል ዳኞችን ድምፅ አስተጋቡልን”!!!!!
ደመወዝና ጥቅማጥቅም ስላነሰን ከእነ ልጆቻችን ተራብን፣ ተጠማን፣ ብለን ሀሳብ እንዳንሰጥ “ችግር አለባቸው” እየተባልን ከነአካቴው ከስራ ልንወገድ ሆነ፡፡ ጎን ለጎን ሌላ ስራ ፈጥረን እንዳንሰራ ዳኛ በንግድ ስራ መሰማራት አይችልም ተባልን፡፡ ኧረ የት እንድረስ!!!
ደመወዝና ጥቅማጥቅም ይስተካከልላቸው ተብሎ ከክልሉ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባላት ውስጥ ኮሚቴ ተዋቅሮ ነበር፡፡ ኮሚቴውም በሀገሪቱ ባሉ ክልሎችና ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤትን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በመዞር የደመወዝና ጥቅማጥቅማችን በአሁኑ ጊዜ ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማነጻጸር በሚገባ አጥንተው ለዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አቅርበውት ነበር፡
ነገር ግን የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ የኔነህ ስመኝ የርሳቸው የተንደላቀቀ ህይወት ባለበት እንዲቀጥልና ለክልሉ በጀት ተቆርቋሪ ናቸው ተብለው ከአስፈፃሚው አካል ርካሽ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ሲሉ የተሻሻለው ደመወዝና ጥቅማጥቅም ውሳኔ አግኝቶ ለ2008 ዓ.ም በጀት ሳይያዝለት እንዲያልፍ አውቀው እያጓተቱት ይገኛሉ!!!
ስለሆነም እናንተ (ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ) የ2008 ዓ.ም በጀት የሚያዘው እስከ ሰኔ 30/2007 ዓ.ም መሆኑን ተረድታችሁ በቀረችው 15 ቀን ባልሞላችው ጊዜ ፕሬዚዳንቱ በጀት ሳያስይዙ ጊዜው እንዳያልፍ እናንተ ይህን መልዕክት ፖስት በማድረግ ተባበሩን!!!
በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን!
Demelash gobezu says
You jurists, you complaining about your private income while hundreds of thousand amharas are masacered, killed by your masters cadres of voyane. Did’ntt you feel shame,did’nt you know to whom you are serving shame on you.you really are among the enemies of amharas!!!
Demelash gobezu says
You told those stomach head jurists right. They have already sold themselves for woyane