• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ብርሃኑ ነጋ “… ዱር ወጡ …”

July 21, 2015 08:27 am by Editor 3 Comments

* የሠራዊቱ ሞራል ከፍ ብሏል

ከአርበኞች ግንባር ጋር የተዋሃደው የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የፓርቲው የአመራር አባላት የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ታጣቂዎቻቸው ወደሚንቀሣቀሱባት ኤርትራ ጠቅልለው መሄዳቸውን የአመራር አባላቱ አስታወቁ፡፡ ብርሃኑ አስመራ መግባታቸው ከተሰማ በኋላ የሠራዊቱ ሞራል ከፍ ማለቱና ከአገር ውስጥ ግምባሩን ለመቀላቀል የሚፈልገው ሕዝብ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል፡፡

ቁጥራቸው ይፋ ያልተደረገ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአመራር አባላትን ይዘው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ኤርትራ ያመሩት ሌሎች አማራጮችን ጨምሮ በብረት ትግልና በሕዝባዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያን ገዥ ፓርቲ ለማስወገድ መሆኑን የአመራር አባላቱ ይናገራሉ፡፡

g--7“ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ጓዶቻቸው ትግል ወደሚካሄድባቸው አባባቢዎች ያመራሉ” ሲሉ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል ዶ/ር ታደሰ ብሩ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡ “ታጋዮቻችን ወዳሉባቸው ቦታዎች ያመራሉ፤ ታጋዮቻችን ኤርትራ ውስጥም እንዲሁም የኢትዮጵያ ውስጥም የገቡ አሉ፤ … ለመታገል ነው የገቡት፤ ለመሞት ነው የገቡት” ብለዋል፡፡ የቪኦኤው ሄኖክ ሰማግዜር ቁጥራቸው ምን ያህል የሆነ የግንቦት 7 አመራር አባላት ወደ አስመራ እንደሄዱ ላቀረበው ጥያቄ ታደሰ ብሩ ሲመልሱ ከደኅንነት አኳያ እንዲሁም አመራር አባላቱ በተለያየ ጊዜያት የሄዱ በመሆናቸው ቁጥራቸውን ለጊዜው ለመግለጽ እንደሚቸገሩ አስረድተዋል፡፡ ሆኖም የንቅናቄው ማዕከላዊ አመራር እዚያ እንዲሆን በመወሰኑ አመራሩ በሙሉ እዚያ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አመራሩም ሆነ ብርሃኑ ነጋ ለምን ያህል ጊዜ እዚያ እንደሚቆዩ ወይም ጠቅልለው ስለመግባታቸው ሲጠየቁ ታደሰ ብሩ የሰጡት ምላሽ “ትግሉ በድል እስኪያልቅ፣ እስኪጠናቀቅ ድረስ እዚያ ይቆያሉ” በማለት አስረድተዋል፡፡ ዶ/ር ብርሃኑም ከበክኔል ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምህርነት ሥራቸውን ለቅቀው ሙሉ ጊዜያቸውን ለትግሉ ለማዋል ጠቅልለው የገቡ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲው እንዴት እንደለቀቁ ወይም በምን ስምምነት እንደለቀቁ የመሳሰለውን አስተዳደራዊ ሁኔታ ለመመለስ እንደማይችሉ ዶ/ር ታደሰ ብሩ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ግምባሩ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለማካሄድ አቅሙን ገንብቶ የተዘጋጀ መሆኑን ከግምባሩ ወታደራዊ አማካሪዎች የታመነበት መሆኑን በመናገር ወደፊትም አቅሙን እየገነባ እንደሚሄድ የኢትዮጵያ ሕዝብም ድጋፉን እየሰጠ እያገዘው እንደሚሄድ ጥሪ አዘል መልክዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በማስከተልም ትግሉ የአርበኞች ግንቦት 7 ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ የነጻነት ትግል እንደመሆኑ ሕዝቡ ትግሉን የራሱ አድርጎ እንደሚወስደው የሚታመን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዋንኛው ለማሳካት የሚፈልጉት ዓላማ ምን እንደሆነ ለተጠየቁት፤ የአርበኞች ግንቦት 7 ገና ከጅምሩ ሲመሰረት ጀምሮ ሊያሳካ የሚፈልገው መንግሥት ለመያዝ ሳይሆን መንግሥት የሚያዝበትን ሥርዓት ለማምጣት ነው፤ እስካሁን ሥልጣን በኃይል ወይም ጉልበት የሚያዝ በመሆኑ አሁን ግን ነጻነት፣ ሰላም፣ እኩልነትና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት የሚያስችል ሥርዓት ማምጣት ዋንኛ የግንቦት 7 አርበኞች ግምባር ዓላማ እንደሆነ አመራር አባሉ ታደሰ ብሩ አስታውቀዋል፡፡ ጉልበት መጠቀም የግምባሩ ዋንኛ ዓላማ እንዳልሆነ ይህም ግድ ሆኖ የተገባበት መሆኑን በመጥቀስ ዋንኛው ዓላማ የዴሞክራሲ ሥርዓትን መመሥረት እንደሆነ በማስረዳት ቃለምልልሳቸውን አጠናቅቀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል እዚህ ላይ ያዳምጡ፡፡

በሌላ በኩል ኢሣት ሰኞ ባሰራጨው የዜና ዘገባ መሠረት የብርሃኑ ነጋ ገና አስመራ መግባት በሠራዊቱ ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃትን መፍጠሩን፤ ግንባሩንም ለመቀላቀል የሚጠይቀው ሕዝብ ከምንጊዜውም ይልቅ እየጨመረ መምጣቱን ዘግቧል፡፡ የዜናው ሙሉ ንባብ ከዚህ በታች ይገኛል፡፡

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስመራ መግባት በሰራዊቱ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል

የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል መሬት ላይ ወርዶ መምራት ይገባል” በሚል እምነት በከፍተኛ ውጣ ውረድ ከአሜሪካ ኤርትራ መግባታቸው እንደተሰማ በአርበኞች ግንቦት7 ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ፣ አስመራ በሚገኘው የድርጅቱ ጽህፈት ቤት አቀባበል ያደረጉላቸው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ተናግረዋል።g---7

በዋና ጽህፈት ቤቱ የሚሰሩ የፖለቲካ እና የውጭ ግንኙነት ክፍል አባላት ለፕሮፌሰሩ በጋራ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የገለጸው ሻለቃ አክሊሉ፣ ከአባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በሰራዊቱ ውስጥ የታየው መነቃቃት ለነጻነት የሚደረገው ትግል እንዲፋጠን፣ በተለይም ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የሚደረገውን ተቀራርቦ የመስራት ድርድር እንዲፋጠን እንደሚያደርገው ሳለቃ አክሊሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ አስመራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል። የፕ/ር ብርሃኑ አስመራ መድረስ ዜና ይፋ ከሆነ ጀምሮ፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ኢሳት ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ።

አርበኞች ግንቦት7ትን ለመቀላቀል የሚጠይቀው ህዝብ እየጨመረ መምጣቱንም ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፕ/ር ብርሃኑ ግንቦት7ትን በሊቀመንበርነት ሲመሩ ቆይተው ፣ አርበኞች ግንቦት7 ውህደት ከፈጸሙ በሁዋላ የውህዱ ድርጅት ሊቀመንበር ሆነዋል። በውህደቱ ላይ ለመገኘት የነበራቸው ውጥን ከጉዞ ሰነድ ጋር በተያያዘ ባለመሳካቱ፣ ለመሪነት የተመረጡት በሌሉበት ነው። ይሁን እንጅ በውህደቱ ወቅት ለጉባኤተኛው በስልክ ባስተላለፉት መልክት፣ አንዳንድ ችግሮች ተፈተው በቅርቡ በረሃ ወርደው እንደሚቀላቀሉዋቸው ቃል ገብተው ነበር።

በምርጫ 97 በተደረገው ምርጫ አሸንፈው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ብርሃኑ፣ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ከሁለት አመት ላለነሰ ጊዜ በእስር ቤት አሳልፈዋል። ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው በክኔል ዩኒቨርስቲ በመምህርነት ሲያገለግሉ ቆይተው ከወራት በፊት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማእረግ አግኝተዋል።

ከዚህም ሌላ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሐምሌ 12፤ 2007ዓም “ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው” በሚል ርዕስ ባሰራጨው መግለጫ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትግሉ ሜዳ መውረዳቸውን አስታውቆ ነበር፡፡ የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይነበባል፡፡

ሐምሌ 12 2007 ዓ.ም./July 19, 2015

ህወሓት በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያ ላይ ያሰፈነው ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ እንዲያበቃ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑበት g     7የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲመሠረት እና የሀገራችን አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ለማኖር አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ተገዶ የገባበት የመረረ የአመጽ ትግል መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በጀግነትና በጽናት እየታገሉ ነው።

ይህ ትግል በባርነትና በነፃነት መካከል የሚደረግ ወሳኝ ትግል ነው። የዚህ ትግል ውጤት የእኛ የዚህ ዘመን ትውልድ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የወደፊት ታሪክ፤ የልጅ ልጆቻችንን ሕይወት ይወስናል። በዚህም ምክንያት ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ለነፃነት ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጎናችን ሊቆም ይገባል።

አርበኞች ግንቦት 7 አመራሩን ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን እና ትግሉ በሚጠይቀው ቦታ እንዲገኙ የሚያደርግ መሆኑ ሲገልጽ ቆይቷል። አሁን ትግሉ በደረሰበት ደረጃ የአመራሩ በትግሉ ሜዳ ውስጥ መገኘት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ሊቀመንበሩን ጨምሮ አመራሩን ወደ ትግሉ ሜዳ አንቀሳቅሷል። በዚህም መሠረት የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትግል ሜዳ ወርዷል።

ትግሉ መሯል። ወሳኝ የሆነ ትግል ውስጥ ገብተናል። የትግሉ መሪዎች የሕይወት መስዋዕትነት እሚከፈልበት ቦታ ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት የንቅናቄው አመራር በተሟላ ሁኔታ በትግሉ ሜዳ ውስጥ እንዲገኝ ማድረግ ተችሏል። ኢትዮጵያዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ዘረኛው የህወሓት አገዛዝን ከጫንቃችን ለማስወገድ ቆርጠን እንድንነሳ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።

ኢትዮጵያን ከህወሓት አገዛዝ ነፃ የሚያወጣው አርበኞች ግንቦት 7 ብቻ አይደለም። ስለሆነም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚደረገው ትብብር ቀዳሚ ትኩረት ከተሰጣቸው ሥራዎች አንዱ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ለድል እንዲበቃ ይታገላል። ኢትዮጵያዊያንም በያሉበትም በተመሳሳይ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው በህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ ላይ ክንዳቸውን እንዲያነሱ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።

እነሆ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በአካል ትግል ሜዳ ውስጥ ይገኛል። የሚችል ሁሉ እንዲከተል፤ መከተል የማይችል በያለበት ሁኖ ሁለገብ ትግሉን እንዲያጧጥፍ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Israel n. says

    July 21, 2015 03:29 pm at 3:29 pm

    Im proud of u guys indeed war was not an alternative but some times even God also chose it.may God be wt u.

    Reply
    • Ewnetu says

      July 26, 2015 05:39 am at 5:39 am

      I scoured many web sites about Birhanu Nega’s move to the front. It seems a summer vacation for him since his college is closed now. Few bloggers estimate the fighters’ number to 150. Is the photo a merely photo-op? First, why do we see limited number of fighters on the photo. The guy who held Ethiopian flag is an Eritrean army and why? Only 4 memebrs are from patriotic army (EPPF). Be real. Put your emotion aside, are we brainwashed by ESAT and G7. Think rationally. This is a merely joke.

      Reply
  2. Firew Ayenachew says

    July 25, 2015 06:56 pm at 6:56 pm

    I hop your strugle will be succesfule

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule