• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ክብሩ የተነካው የክብር ዶክትሬት

July 12, 2015 07:16 am by Editor Leave a Comment

እንደብዙዎቹ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ዩኒቨርሲቲው በየጊዜው የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን በንግግር እንዲከፍቱ ለመረጣቸው ታላላቅ ሰዎች የክብር ዶክትሬት ይሰጣል፡፡ እ.ኤ.አ. 2009 ላይ ግን የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን በንግግር ለከፈቱት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የክብር ዶክትሬት ላለመስጠት መወሰኑን አስታወቀ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፕሬዚዳንቱ ልምድና የሥራ ውጤት ለክብር ዶክትሬት ጣሪያ አልደረሰም የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ ጉዳዩ በተወሰነ መልኩ ውዝግብ አስነስቶ የነበረ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የመክፈቻ ንግግር አድራጊዎችንና የክብር ዶክትሬት የሚሰጣቸውን ግለሰቦች የሚመርጥበት የራሱ ነፃ የሆነ ሒደት እንዳለው፤ የክብር ዶክትሬቱ የሚሰጠውም ለትልቅ ስኬት መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡ በወቅቱ ዲግሪው የክብር ከመሆኑ አንፃር ዩኒቨርሲቲው አሠራሩን መሠረት በማድረግ በውሳኔው መጽናቱ የብዙዎችን ይሁንታ አግኝቷል፡፡ ምንም እንኳ በብዙ ነገሮች አልፎ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መሆን በራሱ እንደ አንድ ትልቅ ስኬት መታየት አለበት የሚል ክርክር ያነሱ ቢኖሩም፡፡

ይህ የተለየ አጋጣሚ ላይሆን ይችላል፡፡ የክብር ዶክትሬት ብዙዎች ትልቅ ዋጋና ቦታ የሚሰጡት በመሆኑ ሰዎች ሁልጊዜም ለእገሌ የክብር ዶክትሬት ተሰጠ ሲባል ዲግሪው ለተሰጠው ሰው ይገባል አይገባም የሚል የራሳቸውን ምዘና ያካሂዳሉ፡፡ ከዚህ ሲያልፍም ሁለት ሦስት ሆነው ነገሩን ይነጋገሩበታል ይገመግሙታልም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎችም ለተለያዩ ሰዎች የክብር ዶክትሬት እየሰጡ ነው፡፡ ወቅቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የሚያስመርቁበት እንደመሆኑ ካለፉት ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ወዲህ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ይገባቸዋል ላሏቸው እያበረከቱ ያሉበት ጊዜ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል መቐለ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት ለድምፃዊ ኪሮስ ዓለማየሁ፣ ለሰር ቦብጊልዶፍና መቐለ ከተማ የሚገኘው ኒኮላስ ሮቢንሰን ትምህርት ቤት መሥራች ለሆኑት ጥንዶች ማክስና ካትሪና ሮቢንሰን ሲሰጥ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለሶል ሬብልሷ ቤተልሔም ጥላሁንና ለለማ ጉያ መስጠታቸው ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቢል ጌትስና ለቱርኩ ፕሬዚዳንት ጣይብ ኤርዶጋን የክብር ዶክትሬት መስጠቱም ይታወሳል፡፡

ባለፈው ዓመት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የሰጣቸው አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) የክብር ዶክትሬት ሊያገኙ ሲገባቸው የተረሱ፤ ዕውቅናው ሲሰጣቸውም ዘግይቶ የተሰጣቸው እንዳሉ ይናገራሉ፡፡ ለምሳሌ እሳቸው ይህን ዕውቅና ቀደም ሲል ማግኘት ይገባቸው እንደነበር አስተያየት የሰጧቸው ጥቂት እንዳልሆኑ ይናገራሉ፡፡

እሳቸው እንደሚሉት በየዘርፉ የሚመለከታቸው አካላት የመንግሥት ተቋማትና የሙያ ማኅበራት ዕውቅናው ይገባቸዋል የሚሏቸውን ፈልገው የማውጣትና ዕውቅና ለሚሰጠው አካል የማመልከት አሠራር ሊኖር ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የሚገባቸው ዕውቅናውን ለማግኘት ሊዘገዩ ከናካቴውም ሳያገኙ ሊቀሩ ይችላሉ፡፡ ‹‹አንገታቸውን ደፍተው በዝምታ የሚሠሩ ብዙ አሉ፡፡ እንደሸንኮራ ተመጥጠው የተጣሉም›› ይላሉ፡፡

በሌላ በኩል የክብር ዶክትሬት ዕውቅና ለማግኘት ዘገዩ ወይም ሳያገኙ ቀሩ ሳይሆን ዕውቅናው ለማይገባቸው እየተሰጠ መሆኑን በመግለጽ ዕውቅናውስ በምን መስፈርት እየተሰጠ እንደሆነ የሚጠይቁ ብዙዎች ናቸው፡፡

በማኅበራዊ ጥናት መድረክ (ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ) አጥኚ የሆኑት ዶ/ር ዘሪሁን መሀመድ በዩኒቨርሲቲዎቻችን የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ላይ ችግሮች አለ ብለው ያምናሉ፡፡ የመጀመርያው የክብር ዶክትሬቱ ለማን መሰጠት አለበት? የሚለውን በሚመለከት መስፈርቶች ግልፅ አይደሉም የሚል አስተያየት አላቸው፡፡ ‹‹ለሰዎች ዕውቅና መስጠት ይገባል፡፡ ግን የሚታየው የአገልግሎት ዘመን ነው? ስኬት? የታተሙ ሥራዎች ናቸው? ግልፅ የሆነ የመለኪያ መሠረት ያለን አይመስለኝም›› ይላሉ፡፡

በውጭ አገር በተሰማሩበት ሙያ ከስኬት ጫፍ የደረሱና ሥራቸውም በተጨባጭ ለሚታይ ሰዎች ዕውቅናው እንደሚሰጥ በመጥቀስ ዩኒቨርሲቲዎቻችን ግን በሙያቸው ገና ግማሽ መንገድ ለተጓዙ መስጠታቸው ጥያቄ ውስጥ የሚወድቅ መሆኑን ያመለክታሉ፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ዕውቅና መሰጠት ካለበት ዕውቅናው የግድ የክብር ዶክትሬት መሆን አለበት ወይ? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ እዚህ ላይም የተለያዩ አገሮችን በኒሻንና በተለያዩ ማዕረጎች ዕውቅና የመስጠት ተሞክሮ በማንሳት ዕውቅና ይገባቸዋል ለሚባሉ ሁሉ የግድ የክብር ዶክትሬት መሆን የለበትም የሚል ጠንካራ አቋማቸውን ያንፀባርቃሉ፡፡ በኒሻንና ለሌሎች ሽልማቶች ዕውቅና የመስጠት ነገር በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓት፣ ዘግይቶም ቢሆን በደርግም እንደነበር በማስታወስ ‹‹ለውጭ አገር ዜጋም፣ በዚህኛውም በዚያኛውም ዘርፍ ላሉ፣ ለዜጎችም የምንሰጠው የክብር ዶክትሬት ነው›› ይላሉ፡፡

በሌላ በኩል የክብር ዶክትሬት ብርቅዬ እንጂ በብዛት የሚሰጥ መሆን አለበት ወይ? የሚል ጥያቄ የሚያነሱም አሉ፡፡ ‹‹የክብር ዶክትሬትን እንዲሁ መስጠት ክብሩን መንካትና መንሳትም ነው›› የሚል አስተያየታቸውን የሰጡ አሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ቁጥራቸው በርካታ በሆነው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት በመስጠት ፉክክር ውስጥ የገቡ እስኪመስል ሩጫ እየታየ መሆኑን ለሪፖርተር የገለጹም አልታጡም፡፡ አንዳንዶች እውነትም ሥራቸው ብቻ ሳይሆን ቲፎዞ ጭምር ለክብር ዶክትሬት እንዳበቃቸውም አስተያየት ይሰነዝራል፡፡

ሌላው ከክብር ዶክትሬት ጋር በተያያዘ እንደ ችግር የሚነሳው ዲግሪው መጠሪያ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ዶ/ር ዘሪሁንን የመሰሉ ብዙዎች ዲግሪው በፍጹም መጠሪያ መሆን የለበትም የሚል አቋም ሲይዙ ይህን የሚቃወሙም አሉ፡፡ ዕውቅናው የጥረት የልፋት ዋጋ በመሆኑ መጠሪያ መሆን አለበት መጠሪያም ነው የሚሉት ባለፈው ዓመት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ባበረከተላቸው ዝግጀት ላይ ከዚያ ዕለት ጀምሮ ማንም ዶ/ር ብሎ ሊጠራቸው እንደሚገባ ያሳሰቡት አርቲስት ተስፋዬ አበበ ናቸው፡፡ ‹‹ብዙዎች ሲጠሩበት ኖረዋል፡፡ እንደዚሁ እንደ ሎተሪ ሳይሆን የሕይወት ታሪክና ስኬት ታይቶ የተሰጠ ነው›› ብለዋል፡፡

በተቃራኒው የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የተለያዩ የክብር ዶክትሬቶች ማግኘትን ነገር ግን ዶክተር ተብለው ተጠርተው እንደማያውቁ የሚያስታውሱት ዶ/ር ዘሪሁን የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው ዶ/ር ሲባሉ አቤት ማለት የሚዲያውም ይህን ዲግሪ እንደመጠሪያ መጠቀም አግባብ አይደለም ይላሉ፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለሆኑት ዶ/ር ፍቅሬ ለሜሳ የክብር ዶክትሬት ዕውቅና ሲሰጥ ዩኒቨርሲቲው ምንን መሠረት አድርጎ እንደሆነ በማስመልከት ጥያቄ አቅርበን ነበር፡፡ ዩኒቨርሲቲው ዕጩዎችን ከመምረጥ፣ የሕይወት ተሞክሮና የሥራ ልምዳቸውን መመርመርን ጨምሮ አጠቃላይ ሒደቱ የሚመራበት መመሪያ መኖሩን ይገልጻሉ፡፡ ሒደቱ ምስጢራዊ ሲሆን ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ዲኖች ይሳተፋሉ፡፡ ‹‹ዋናው መስፈርታችን ኅብረተሰብን በራስ ጥረት በመንቀሳቀስ መጥቀም ነው›› በማለት ምሳሌ መሆን መቻል፣ በሥራ የተመሰገኑ መሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ አገርን ማሳወቅ ከመስፈርቶቹ መካከል ናቸው፡፡ ዕጩዎች በዩኒቨርሲቲው፣ ከዩኒቨርሲቲው ውጪ ባሉ አካላትም ሊጠቆሙ ሲችሉ ዕጩዎችን የሚያቀርበው ፕሬዚዳንቱ ሲሆን በመጨረሻ የክብር ዶክትሬቱን የሚያፀድቀው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

ዶ/ር ፍቅሬ እንደሚሉት ዕጩዎች ላይ ጥናት የሚደረገው ምስጢራዊ በሆነ መንገድ ሲሆን የዕጩዎች ሥራና ስኬት ተጨባጭነት ይመዘናል፡፡ በሌላ በኩል መመሪያው ለመንግሥት ባለሥልጣናት ዕውቅናው እንዳይሰጥ ይከለክላል፡፡ ይህ የሆነው ባለሥልጣኑን ለመጥቀም ወይም ዩኒቨርሲቲው ራሱ ጥቅምን ታሳቢ በማድረግ ነው የሚል አመለካከት ይፈጥራል በሚል ሥጋት ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲያቸው በሰጠው የክብር ዶክትሬቶች ጥያቄ ተነስቶ ወይም ቅሬታ ቀርቦ ያውቅ እንደሆነ ለዶ/ር ፍቅሬ ጥያቄ አቀረብን፡፡ ‹‹ብዙ ቅሬታዎች ሊኖሩ ይችላሉ ግን ኦፊሻሊ በእኔ በኩል የመጣ ነገር የለም›› የሚል ነበር መልሳቸው፡፡ ዕውቅናው የሚገባቸው ብዙ እንደሚኖሩ ነገር ግን የግድ ከእነሱ ውስጥ ምርጥ የሚባሉትን መምረጥ የግድ መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬም የክብር ዶክትሬት የመስጠቱ ሒደት ሴኔት ባጸደቀው መመርያ የሚመራ ሲሆን ዕውቅናው በትክክል መመርያው ላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች መሠረት አድርጎ እንደሆነ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እሳቸው እንዳሉት ማንም የክብር ዶክትሬት ይገባዋል የሚለውን መጠቆም ይችላል፡፡ ይገባናል የሚሉም ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ዩኒቨርሲቲውም ይመርጣል፡፡ ለምሳሌ በመስፈርቶቹ መሠረት ለአንድ ሰው የክብር ዶክትሬት መስጠት ለዩኒቨርሲቲው ገፅታ ግንባታ አስተዋጽኦ ያበረክታል ወይ? የሚለው እንደ አንድ ነገር ይታያል፡፡ በቅርቡ ለቢል ጌትስና ለቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ከዚህ አንፃር ሲሆን ከራሳቸው በቀረበ ጥያቄ መሠረት እንደሆነ ደ/ር አድማሱ ገልጸዋል፡፡

እንደ ብርቅ መታየት ያለበት የክብር ዶክትሬት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየበዛ ነው ከዚህም ባለፈ ሁኔታው በኮታ እስኪመስል የክብር ዶክትሬትን ዋጋ የማጥፋት አካሄድ ነው የሚል አስተያየታቸውን የሰነዘሩ አሉ፡፡ ዶ/ር አድማሱ ግን የቁጥር ነገር እንደ ዩኒቨርሲቲዎች ሊለያይ እንደሚችል፤ ይህን ያህል ይሁን ብሎ መወሰን የዩኒቨርሲቲዎችን አካዴሚክ ነፃነት መጋፋት እንደሚሆንም ያስረዳሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲያቸውን በምሳሌነት በመጥቀስ በዚህ ዓመት ይህን ያህል የክብር ዶክትሬት እንሰጣለን የሚል ነገር በአሠራራቸው እንደሌለ፤ በዘንድሮው የምርቃት ሥነ ሥርዓትም ለአንድ ድርጅት ዕውቅና ከመስጠት ባሻገር ዩኒቨርሲቲያቸው የክብር ዶክትሬት ለግለሰብ እንደማይሰጥ አስታውቀዋል፡፡ ጊዜን በሚመለከት ደግሞ እንደ ጥያቄውና እንደ ሴኔቱ ውሳኔ በምርቃት ሥነ ሥርዓት ላይ ብቻም ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ (ለቢል ጌትስና ለኤርዶጋን እንደተሰጠው) የክብር ዶክትሬት በዓመቱ ማንኛውም ጊዜ ላይ ሊሰጥ ይችላል ብለዋል፡፡

የክብር ዶክትሬት መጠሪያ ይሆናል ወይ? ሌላው ለዶ/ር አድማሱ ያቀረብነው ጥያቄ ነበር፡፡ ‹‹እኛ ሊጠሩበት ይችላሉ ነው የምንለው፡፡ ነገር ግን ሊጠሩበት ይችላሉ አይችሉም የሚለው ነገር አሁን አሁን መነጋገሪያ እየሆነ በመሆኑ የሌሎችን የውጭ አገር ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮ በማየት በቅርቡ ውሳኔውን እናሳውቃለን›› የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ (ምንጭ: ሪፖርተር)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule