በዚህ ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ ከጅማ ዞንና ከከተማዋ የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት የተሳተፉበትና በህዝቦች አብሮነት እሴት ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊዎች ምን አሉ? የህዝቡን አብሮ የመኖር እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተነቅፈዋል። የኦሮሞ ህዝብ በሰላም የመኖር እሴትና አኩሪ ባህል እንዳለው ተብራርቷል። በመሰዳደብ፣ ጥላቻና ነቀፋ ላይ ያተኮሩ ተግባራትን ሊወገዙ እንደሚገባቸው ሀሳብ ተሰጥቷል። ህዝቡን እንወክላለን የሚሉ አካላት እየተፈፀሙ ያሉ የህዝቡን አብሮነት እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተወግዘዋል። የተወሰኑ የውይይት ተሳታፊዎች ሀሳብ፦ "ከየትኛውም ብሄርም ይሁን ሃይማኖትም ይሁን ክልል ተንኮል የሚያስብ ሰው የትም አይደርስም። በመሳደብ የሚመጣ ለውጥ የለም።" "አዋቂና ለኦሮሞ ተስፋ ናቸው ከምንላቸው ሰዎች … [Read more...] about “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ
Left Column
“ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል”
የዚህች ሃገር ችግር የሴራ ፓለቲካ ነው። ጀዋር ሞሃመድ ዛሬ (ሰኞ) ለማየት የሚሰቀጥጥ አንድ ቪዲዮ ለጠፈ። በጣም አንጀት የሚበላ ጥቁርም ሆነ ነጭ ኦሮሞም ሆነ አማራ፤ የሰውን ልጅ እንደዛ በጭካኔ ማሰቃየት ከባድ የሰብዓዊነት ጥሰት ነው። የህግ ተጠያቂነት ደግሞ ግድ ነው፤ ግን ደግሞ ማነው ይህን ወንጀል የፈጸመው? ዋናው ነገር ይህንን ወንጀል የፈጸመውን እና ያስፈጸመውን ለይቶ ለህግ ማቅረብ ነው። ቪዲዮው ልጁ ግፍ ሲፈጸምበት እንጂ ግፍ የፈጸሙትን አያሳይም ለምን ወንጀለኞችን መደበቅ አስፈለገ? ታስቦበት ስለተፈጸመ ነው። በሴራ ከመዘፈቅ ይልቅ ወንጀሉን የፈጸሙትን በማጋለጥ ለህግ የበላይነት መተባበር ነበር። ግን ያንን ትተው ግፍ የተፈጸመበትን በማሳየት ህዝብን ማበሳጨት ነበር የተፈለገ። ወንጀሉን የፈጸመውን በመደበቅ አማራ ኦሮሞን አሰቃየ ማለት የፖለቲካ ሴራ ነው። ነገሩ … [Read more...] about “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል”
ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ
የውሃ ሃብት ባለሙያ ነኝ፤ የግድቡ ጉዳይ ቀጥታ ከሙያዬ ጋር ባይገናኝም እንደዜጋ ሁኔታውን በቅርብ እከታተላለሁ፤ ፖለቲካንም እንዲሁ። የዋዜማን ሰዎች ዋዜማ ሳትሆኑ ነው የማውቃችሁ፤ ካገር ከመውጣታችሁ በፊት ማለቴ ነው። የማውቃችሁም በግል ሳይሆን እንደማንኛውም የሚዲያ ተጠቃሚ ነው፤ ስለዚህ እናንተ አታውቁኝም። አሁንም ዋዜማን እከታተላለሁ። ከዳያስፖራ ከሚመነጩት የዜና ዘገባዎችና መረጃዎች የእናንተ በተሻለ መጠን ተዓማኒነትና ሥርዓት የያዘ ነው ብዬ ስለማምን አነባችኋለሁ። “ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግስት የመፈረም ፍላጎት እያሳየ ነው” በሚል ርዕስ ያወጣችሁትን ዘገባ አንብቤዋለሁ። ዘገባው እንደሚለው ለረጅም ጊዜ የተጠበቀውን ሰነድ ስምምነት እንድትፈርም ኢትዮጵያ ግፊት እየተደረገባት እንደሆነ፤ ይህም “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ … [Read more...] about ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ



