• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም

June 17, 2020 06:57 am by Editor Leave a Comment

ለዚህ ሃሳብ ማብራሪያ የሰጡት የህወሓት ሊቀ መንበርና የትግራይ ክልል መንግሥት ምክትል ርዕስ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ውይይቱ የተናጠል ሳይሆን ሁሉንም አካላት ማካተት እንዳለበት መናገራቸውን ጠቅሷል።

“የውውይት መድረክ መፈጠር ካለበት፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርጅቶች፣ ብሔር ብሔረሰቦችን የሚወክሉ ፌደራሊስት ኃይሎች የሚሳተፉበት አገራዊ መድረክ መዘጋጀት አለበት እንጂ ከህወሓት/ትግራይ መንግሥት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይት አንቀበልም፤ ትርጉምም አያመጣም” ማለታቸውን ቢሮው ገልጿል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ “ውይይቱ በመጨረሻ ሰዓት የተጀመረ ቢሆንም መሞከሩ ግን ጥሩ ነው” ያሉ ሲሆን ጨምረውም “የአገሪቱን ችግር ለመፍታት የሚንቀሳቀስ አካል ችግሩ የተፈጠረው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ በአገሪቱ አምባገናናዊ ሥርዓት ለመገንባት እየተሯሯጠ በሚገኘው ብልፅግና የተሰኘው ቡድንና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እንጂ በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል ብቻ የተፈጠረ አለመግባባት አድርጎ መመልከት አይገባም” ብለዋል።

የሐይማኖት አባቶቹና የአገር ሽማግሌዎች ስለጦርነት አላስፈላጊነት መስበካቸውና ስለሰላምና ውይይት መናገራቸው ልክ መሆኑን ያመለከቱት ደብረፅዮን (ዶ/ር)፣ ነገር ግን “ይህ መባል ያለበት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማክበር ምርጫ አድርጋለሁ ባለው ክልል ላይ የጦር አዋጅ ለሚያውጀው የፌደራል መንግስት ነው” ሲሉ ከሰዋል።

በዛሬው የሽምግልና ውይይት ላይ ስለተነሱ ጉዳዮች በተለይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ባነሷቸው ጉዳዮች ላይ አተኩሮ መግለጫ ያወጣው የትግራይ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እንዳለው፤ መፍትሔ ለማምጣት ተፈልጎ ከሆነ ቢያንስ በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ሌሎችም መሳተፍ እንደነበረባቸው መናገራቸውን ገልጿል።

ከዚሁ በተጨማሪም የመገናኛ ብዙሃን እንዳይገባ የተፈለገበት ምክንያትም ልክ እንዳልሆነ ተናግረዋል የተባሉት ደብረፅዮን (ዶ/ር) “ወደፊትም ቢሆን መደባበቁ ችግሩ ሊያባብሰው ካልሆነ መፍትሄ አይሆንም” ብለዋል።

በውይይቱ ወቅት በርካታ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ከተሳታፊዎቹ ለሽምግልና ቡድኑ መቅረቡ የተነገረ ሲሆን፤ እነሱም የተነሱ ጉዳዮችን ይዘው ወደ ፌደራሉ መንግሥት እንደሚቀርቡ ተናግረዋል ሲል የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ መግለጫ ጠቅሷል።

BBC

Filed Under: Left Column, News, Slider, Uncategorized

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule