(ርዕሰ አንቀጽ) ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታትና ከዚያም በፊት ስለዕርቅ ያልተናገረ የፖለቲካ ቡድን የለም ለማለት አይቻልም፡፡ ደርግ ስለ ዕርቅ ተጠይቆ አልሰማም አለ፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግም የአገዛዝ መንበሩ ላይ ከመቆናጠጡ ጀምሮ ስለ ዕርቅ ይወራል፡፡ አዳዲስ የሚፈለፈሉ የተቀናቃኝ ድርጅቶች በአገር ውስጥም ይሁን በውጪ ስለ ዕርቅ ያወራሉ፡፡ የገባውም ያልገባውም ስለ ዕርቅ ይናገራል፤ ይሰብካል፤ ያስተምራል፤ … ይህንን ሁሉ አልፎ “እኔም ያገባኛል” በማለት ህወሃትም ስለዕርቅ ያወራል፡፡ ከማውራትም አልፎ ያስተምራል፤ ያሠለጥናል፡፡ ሰላማዊ ጦርነት፤ ጥቁር ብርሃን፤ እንደሌለ ሁሉ ህወሃትና ዕርቅም እንደዚያው ናቸው፡፡ ስለ ድርድርም እንዲሁ ይወራል! አሸማጋይ፤ አደራዳሪ፤ አወያይ በሌለበት እንወያይ ይባላል፡፡ ሁሉንም የተቆጣጠረው ህወሃት የሚደራደሩ ተቃዋሚ ሳይሆኑ “ተጠቃሚ” ፓርቲዎችን … [Read more...] about ዕርቅና ድርድር ቢያይዋቸው፤ ቢያይዋቸው!
Archives for January 2017
በሚገዛው ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀ አገዛዝ – ተግባሩን “ስኬት” ሲል ገመገመ
ግድያ፣ አፈና፣ ቶርቸር፣ ረሃብ፣ የጅምላ ጭፋጨፋ - ስኬት በቅርቡ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ እርሱ “አሽከር” ለሚባለው የኢህአዴግ ሸንጎ ንግግር ሲያደርግ ኢህአዴግ የወሰዳቸውና እየወሰደ ያለው እጅግ አረመኔነት የተሞላበት አሠራር የሚደነቀ መሆኑን አስታውቋል። “መቶ በመቶ መርጦኛል፤ እመራዋለሁ” በሚለው ህዝብ ላይ ለታወጀው ክተት አስፈጻሚ መሆኑ፣ ንጹሃንን መጨፍጨፋቸው፣ መታሰራቸው፣ መታፈናቸው፣ ለስቃይ መዳረጋቸው “ስኬት” መሆኑንን ማመልከቱ “የዘመኑ አስገራሚ ትንግርት” እየተባለ ነው። በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖችን በግፍ አስሮ የሚያሰቃይ አገዛዝ ራሱን በጥንካሬ ሲፈርጅ መስማት አሳዛኝና አሳፋሪ እንደሆነ የሚጠቁሙ እንዳሉት “ግድያ፣ አፈና፣ ማሰቃየት፣ ረሃብ፣ የጅምላ ጭፋጨፋ ... ስኬት ተብሎ ሲቀርብ የሚያዳምጥና የሚያጨበጭብ ሸንጎ ህይወት የሌለው በድን ነው” ቢያንስ … [Read more...] about በሚገዛው ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀ አገዛዝ – ተግባሩን “ስኬት” ሲል ገመገመ
የማናውቀው ታሪካችን
ታሪካችንን ባለማወቃችን ሁሌም ወደኋላ በመገስገስ ላይ እንገኛለን፤ ሰሞኑን አንዳንድ ዜና መዋዕሎችን ማንበብ ጀምሬ እስካሁን አራት ያህል አንብቤአለሁ፤ ከዚህ በፊት እየተንገዳገድሁ በግዕዝ አንብቤአቸዋለሁ፤ ዛሬ የሲራክ አሳታሚ ድርጅት በአማርኛ እያሳተማቸው በመሆኑ ምስጋና ይድረሰውና ሳልንገዳገድ በአማርኛ እያነበብሁ ነው፤ በዚህ ንባቤ ውስጥ አንዳንድ ያገኘኋቸው ሀሳቦች ስለራሳችን ያለን እውቀት ምን ያህል ጎደሎ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው፤ ለዛሬው ሁለት ሀሳቦችን ከላሊበላ ዜና መዋዕል፤ አንድ ደግሞ ከሱስንዮስ መርጫለሁ፤ እኔን እንዳስደነቁኝ ሌሎችንም ያስደንቃሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ አንደኛ፤ ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በ1160 ዓ.ም. የነገሠው ገብረ መስቀል የሚባለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት "በነገሠ በአሥር ዓመቱ መራ ከተባለው አጠገብ የነበረውን ቤተ መንግሥት ወደሌላ ለማዛወር አስቦ … [Read more...] about የማናውቀው ታሪካችን
የአቦይ ስብሃት ነጋ የሙስና ወጎች
በአሜሪካ ሃገር፤ አንድ ባለስልጣን በሙስና ሲባልግ እስር ቤት ይገባል። በፊሊፒንስ አንድ ባልስልጣን የሙስና ወንጀል ቢፈጽም አሜሪካ ይገባል። የኛ ሃገር ባለግዜ ግን ሙስና ሲሰራ አሜሪካ እየተመላለሰ ይነግዳል። ለግዜው ልዩነቱ የዚህን ያህል ነው። ገለልተኛ የፍትህ አካል ባለበት ሃገር፤ ሙስና አፍ አውጥቶ አይናገርም፣ እግር አውጥቶም አይራመድም። አዲሱ ቀልድ፤ "ሙስና አለ፣ ማስረጃ የለም!" በያዝነው "ጥልቅ ተሃድሶ" ዘመን ሙስና ለሁለት ተከፍሎ እንዲታይ ተደርጓል። ማስረጃ ያለው ዘረፋ እና ማስረጃ የሌለው ዘረፋ። ልክ እንደ ግብር አከፋፈል። ግብር ከፋይ "ሀ" እና ግብር ከፋይ "ለ"። ምድቡ በዘረፋው መጠን እና በባለስልጣኑ ጉልበት ይወሰናል። የዘረፋው መጠን ከአስር ሺህ በር በታች ከሆነ እና ዘራፊው የድል አጥቢያ ታጋይ ከሆነ ማስረጃ ያለው፣ ሙስና ምድብ "ሀ" ይሆናል። መጠኑ … [Read more...] about የአቦይ ስብሃት ነጋ የሙስና ወጎች
አይደለም እንዴ? ዋሸን እንዴ?
ሰሞኑን የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ይመስላል ወያኔ/ኢሕአዴግ ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አማካኝነት ሰጥቷል። ዶላር እስካስገኘ ድረስ ሕፃናትንና ወጣት እህቶቻችንን በቁማቸው እየቸበቸበ ያለው ወያኔ ፀጉር መላጨት እንዳይጀምር ጠንቀቅ ነው። “አለና! ምንም አልሆንም! ምን ታመጣላችሁ! አሁንም ከማንም በላይ ነን” የሚለው የሰሞኑ የጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋዜጣዊ መግለጫ በሚገባ ለተረዳው ከሥልጣኑ አንፃር የወያኔን አቋምና የሀገሪቷን ቀጣይ ራዕይ መላሽ ነው። (ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about አይደለም እንዴ? ዋሸን እንዴ?
Is TPLF prison empire in Ethiopia silently approach towards half a century!?
Since TPLF fights for 17 years as a guerrilla fighter against the military junta Derg Mengistu Hailmariam here are facts about the prison cell and situation are it’s major characteristics features of the group. Tigray people liberation front from the grass roots history they have got a famous prison cell which is highly secret full know as bado shidishte which is used to arrest those who are against them and prisoners who are sundered, wounded or hijacked by TPLF. It is used to torture, harsh … [Read more...] about Is TPLF prison empire in Ethiopia silently approach towards half a century!?
የህወሃት ራስህን አድን “ጥልቅ ተሃድሶ” ሦስት ኦህዴድን ፈጠረ
ህወሃት በተለያዩ ጊዚያት አደጋ ሲገጥመው የሚዘይደው የማምለጫ ስልት በአካባቢው ባሉ “አጋሮቹ” ዘንድ “ዘመቻ ራስህን አድን” የሚል ስያሜ አለው። ይኸው ዘመቻ በኦሮሚያ ኦህዴድን እንዳራባው ነው የሚነገረው። የጎልጉል የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት ኦህዴድ ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ ችግር ተዳፈነ እንጂ አልበረደም። ይልቁኑም በድንገት አስተዳደራዊ መዋቅር ሊናጋ ይችላል የሚል ስጋት አለ። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) አንጋቾቹን አሰማርቶ በሺህ የሚቆጠሩ ኦሮሞ ወገኖችን መፍጀቱ፣ በየማጎሪያው ሰብስቦ ማሰቃየቱና በዚሁ ሳብያ የተፈጠረው ማኅበራዊ ቀውስ ከፍተኛ እንደሆነ የሚናገሩት የመረጃው ሰዎች፣ በዚሁ ሳቢያ ኦህዴድ ወደ ሦስት አካልነት መራባቱን፣ ይህ ድርጅታዊ መባዛት የ“ጥልቁ ተሃድሶ” ውጤት እንደሆነ ነው የሚናገሩት። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባሰባሰበው መረጃ መሰረት … [Read more...] about የህወሃት ራስህን አድን “ጥልቅ ተሃድሶ” ሦስት ኦህዴድን ፈጠረ
“[ሰዎች] አለሙያቸው ሙያ እየጫንባቸው አበላሽተናቸዋል” ወለላዬ
ሰላም ጎልጉሎች . . . እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ከኢትዮጵያ ዛሬ ጋር በግጥሞቼ ሳቢያ ቃለ መጠይቅ አድርጌ ነበር። እናንተም ግጥሞቼን በተገቢው ሁኔታ ያስተናገዳችሁልኝ ስለሆነ እናንተም (ዘንድ) ቢታተም እወዳለሁ። በድጋሚ መልካም በዓል ይሁንላችሁ። ወለላዬ መዝጊያ ትሁንልኝ መቶ ራት ግጥሞችን - ተሸክሜ ይዤ፤ ረብዕ ረቡዕ ስጥል - አንድ አንዷን መዝዤ በዚች ባሁኗ ቀን - በጨበጥናት ሳምንት፤ ወሩን ስደምረው - ሆነኝ ሁለት ዓመት፡፡ ዳግም በአዲስ ዓመት - እስከምንገናኝ፤ የዘንድሮው መዝጊያ - ይቺ ትሁንልኝ፡፡ (ወለላዬ) ወለላዬ በየሳምንቱ ረቡዕ ረቡዕ በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ላይ ለሁለት ዓመታት ያህል ሳያቋርጥ 104 ግጥሞች በመጻፍ አስነብቦናል። በነዚህ ግጥሞቹ እኛን ሆኖ ውስጣችን ገብቶ ያልተናገርነውን ተናግሮልናል። ታዝበን ያለፍነውን … [Read more...] about “[ሰዎች] አለሙያቸው ሙያ እየጫንባቸው አበላሽተናቸዋል” ወለላዬ
የዛ ሰውዬ ድምጽ . . .
ፊቱ አሸቦ መስሎ፣ እንደደነገጠ፣ ተጎልጉሎ ወጥቶ፣ ዓይኑ እንደፈጠጠ፣ ባንኮኒው ጋ ሄዶ፣ ቢራውን ጨበጠ። የሆነውን እንጃ! ሁኔታው ያስፈራል፣ እንባው በጉንጩ ላይ፣ አቋርጦ ይፈሳል አልቅሶ ሲበቃው፣ ውጪ እየሰለለ፤ ያየውን በውስጡ፣ እያሰላሰለ፣ ገድለው ሲጥሏቸው፣ በዓይኖቼ አየሁ አለ። ወደ ተናጋሪው፣ አፍጠን እያየን፤ እንደልማዳችን፣ ዝም ተባባልን። ሰውዬው ቀጠለ፣ ገድለው ሲጥሏቸው፣ በዓይኖቼ አየሁ አለ! ዘለው ያልጠገቡ፣ እህል የተራቡ፣ አገር የተቀሙ፣ ፍትሕ የተጠሙ፣ አንድ ፍሬ ናቸው! ገና እንዳገኟቸው፣ ከበው ይዘዋቸው፣ መሣሪያ አስጠግተው፣ ወደ ግንባራቸው፣ ጭንቅላታቸውን ... ፈረካከሷቸው። እያለ ሲናገር፣ ሰውዬው ሲቆጣ፣ ሲያለቅስ ሲያማርር፣ እኔም ልክ እንደሱው፣ በዓይኖቹ ገብቼ፣ አንገቴን አቅፌ፣ በሁለት እጆቼ፣ ጉልበቴ እየራደ፣ ነፍሴ … [Read more...] about የዛ ሰውዬ ድምጽ . . .
ለጀግናው አትሌት ስንብት!
. . . በዚያ ቀውጢ ጊዜ - በዚያ ቀውጢ ዘመን፣ ከአገር በራቀበት - የደስታ ሰመመን፤ ያገር ፍቅር ስሜት - መገለጫ ፈርጦች፣ ብቸኛው አማራጭ - የደስታችን ምንጮች፣ ነበሩን! ነበሩ! “አረንጓዴ ጎርፎች”. . .፤ እንዲህ እንደዛሬው - ሳይዘምን ዘመኑ፣ ያለም መገናኛ - ሳይራቀቅ ኪኑ፣ ዩ ቲዩብ፣ ኢንተርኔት፣ ስማርት ፎን..ሳይኖር፣ ዜና መቀበያው - ራድዮናችን ነበር፤ “. . . ክቡራትና ክቡራን ውድ አድማጮቻችን..”፣ የኦሎምፒክ ውጤት፣ ልክ እንደደረሰን፣ እናስደምጣለን...”፤ በለሆሳስ ሙዚቃ መሳሪያ ቅንብር መሻገሪያ ዜማ፣ ከተራራ ጫፍ ላይ፣ ወይ ከሰማየ-ሰማያት ከሩቅ እሚሰማ፣ “የኛ ነው ድሉ-ድሉ፣ የኛ ነው ድሉ-ድሉ፣ በርቱና ታገሉ..”፤ አገር ትንፋሽ አጥሮት - ጸጥ-ረጭ ብሎ፣ ዐይኖቹን ጎልጉሎ - ራድዮን ላይ … [Read more...] about ለጀግናው አትሌት ስንብት!