እንዳገኘ በልቶ እንዲህ ተነርቶ እንዲህ ሆዱ ሰፍቶ ቁርጡ ቀን ሲመጣ፥ ወያኔ ሲወገድ ገና መዋጮ አለ፥ ለልማታዊ ሆድ። … [Read more...] about … ለልማታዊ ሆድ
Archives for September 2014
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስር ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ (እንደተለመደው በየሳምንቱ መልሱን ተከታትለን ባለማቅረባችን ለአንባቢያን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን::) መልስ እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ፣ - እኔ ነኝ ተዘራ የማስደስታችሁ - ከክራሬ ጋራ ብለው የዘፈኑ - በገዛ ስማቸው ድምጻዊ ተዘራ - ማለት እኚህ ናቸው ላሁኑ ደግሞ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩
በአዲስ ዓመት ለተግባራዊ ዕርምጃ መዘጋጀት ይገባል
እንኳን ለ፪ሺ፯ ዓ.ም. አደረሠን፣ አደረሣችሁ! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፦ እኛ ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ የመስከረምን ወር የመጀመሪያ ቀን የዘመን መለወጫ ዕለት አድርገን ማክበር የጀመርነው በሺህዎች ለሚቆጠሩ ዘመናት እንደሆነ ይታወቃል። በረዥሙ ታሪካችን እንደየአመጣጣቸው፦ ደስታን እና ሐዘንን፣ መከራን እና ብሥራትን፣ ጦርነትን እና ሰላምን፣ መቆርቆዝን እና መበልፀግን፣ ረሃብን እና አንፃራዊ ጥጋብን፣ ወዘተርፈ አስተናግደናል። ያለፈውን ዘመን ሸኝተን አዲስ ዓመት ስንቀበል ዘወትር መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን። ስለዚህ ይህ መግለጫም የኢትዮጵያውያን የዘመናት ትውፊት አንዱ አካል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ያገባደድነውን ዓመት ዘመነ-ማርቆስን ስንሸኝ በዓመቱ ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባሮች መመዘን ጠቃሚ ይሆናል። ስለሆነም፦ «እኔ ለራሴ ነፃነት መከበር፣ እንዲሁም ወገኖቼ … [Read more...] about በአዲስ ዓመት ለተግባራዊ ዕርምጃ መዘጋጀት ይገባል
LONDON STREETS HOST ANGRY ETHIOPIANS FROM ALL OVER EUROPE
5th September 2014 will go down the history of Diaspora Ethiopians as a one of the great events in the struggle against the treacherous Woyyane regime. It was the third time that Ethiopians from all over Europe came together to raise a storm on the streets of London. The first was on 8th December 2005[i]. The 2nd was on 9th April 2009, when Meles Zenawi came to take part on the G20 London at Excel Business Centre. Now this one raising dust in London with a boom! It appears that the … [Read more...] about LONDON STREETS HOST ANGRY ETHIOPIANS FROM ALL OVER EUROPE
በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ
በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ በስደት አገራቸውን ጥለው የወጡ የኤርትራ ስደተኞችን እንደሚሰልል ተረጋገጠ። የስዊድን መንግሥት በደረሰው ጥቆማና ማስረጃ መሰረት ባደረገው ማጣራት ኤምባሲው በስለላ ስራ ተሰማርቶ ስዊድን ከለላ የሰጠቻቸውን የኤርትራ ተወላጆች አንደሚከታተልና እንደሚሰልል ማስረጃ ተይዞበታል። ተቀማጭነታቸው ስዊድን የሆነ የጎልጉል ተባባሪዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመነጋገር እንዳመለከቱት፣ የስዊድን ዜግነት ያላቸውንና ሻዕቢያን ለማስወገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን የሚደግፉ፣ አክቲቪስት የሆኑትን የኤርትራ አገዛዝ በኤምባሲው አማካይነት እንደሚስልላቸው የታወቀው በጥቆማ ነው። ውስን ቁጥር ያላቸው በስዊድን የሚኖሩ የኤርትራ ተወላጆች ባቀረቡት ጥቆማ መሰረት የስዊድን መንግሥት ባካሄደው ማጣራት የኤርትራ ኤምባሲ የተከሰሰበትን ተግባር እንደሚፈጽም ተረጋግጧል። የመረጃው … [Read more...] about በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ
የታገደው ድፍረት ፊልም የይገባኛል ጥያቄ አስነሳ
አንጀሊና ጆሊ ኤግዚኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር የሆነችበትና ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር ሊመረቅ የነበረው ድፍረት ፊልም፣ በፍርድ ቤት እግድ ከተቋረጠ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማስነሳቱ ታወቀ፡፡ በአሜሪካ በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ ከሆነ በኋላ የፊልሙ በአዲስ አበባ መመረቅ በብዙዎች በጉጉት እየተጠበቀ ነበር፡፡ እንዲህ የተጠበቀው ፊልም ሊመረቅ በታሰበበት ዕለት ከአሥራ አምስት ደቂቃዎች በላይ ሊታይ አልቻለም፡፡ በብሔራዊ ቴአትር እየታየ ፌደራል ፖሊስ ደርሶ ሊያቋርጠው የግድ ሆኗል፡፡ ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የሚያጠነጥነው አስገድዶ የደፈራትን የ29 ዓመት ወጣት በገደለችው የ14 ዓመት ታዳጊ አበራሽ በቀለ (በፊልሙ ሒሩት) ሕይወት ዙሪያ ነው፡፡ ደፋሪዋ … [Read more...] about የታገደው ድፍረት ፊልም የይገባኛል ጥያቄ አስነሳ
ደኅና ሁኝ ቤተክርስቲያን
ይሄንን ጽሑፍ የጻፍኩት ታች አምና አሁን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሆኘ እየመራሁ ነኝ የሚሉት አባ ማትያስ ለማወናበዱ እንዲመች እጣ መሆኑ ቀርቶ በይስሙላ ምርጫ ሐሙስ እንደተመረጡ ቅዳሜ በዕንቁ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፡፡ በወቅቱ በጽሑፉ ላይ ሁለት ነገሮችን ተንብየ ነበር፡፡ አንደኛው ፓትርያርክ ተብለው የተመረጡት ሰው እንደ አባ ጳውሎስ ሁሉ ለቤተክርስቲያን ደኅንነትና ህልውና አደጋ እንደሚሆኑ የሚናገረው ሲሆን፡፡ ሌላው ደግሞ የሰይጣን ጆሮው ይደፈንና ከአንድ ዐሥርት ዓመታት በኋላ የክርስቲያኖች (የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምእመናን) በመላዋ ሀገሪቱ የሚኖራቸው ብዛት እጅግ አሽቆልቁሎ ከአዲስ አበባ ሕዝብ ብዛት ያልበለጠ ይሆናል የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ ይሄንን ትንበያየን አለቅጥ የተጋነነ አድርገው የቆጠሩት ብዙ ነበሩ፡፡ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ በጥቂት ወራት ውስጥ አባ … [Read more...] about ደኅና ሁኝ ቤተክርስቲያን
“ሕወሀት ኢሕአዴግ” በቅርብ ጊዜ የብሔራዊ እርቅ ተማጻኝ!
ብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) በተለይ በእርስ በእርስ ግጭት ደም የተቃባንና የከፋ አደጋ የተጋረጠበትን ኅብረተሰብ ወይም የመበታተን አደጋ የተጋረጠባትን ሀገር በይቅር ለእግዚአብሔር ይቅር አባብሎ ሰላም ለማውረድና የቂም በቀልን ዶሴ ዘግቶ በአዲስ መንፈስ ብሔራዊ መግባባትን (National Consensus) ፈጥሮ የአንዲት ሀገርን ሕዝብ በአንድነት አስተባብሮ ለማንቀሳቀስና ህልውናውን ከመረጋጋቱ ጋራ ለማስቀጠል ዓይነተኛ መንገድ ነው፡፡ በሕወሀት ኢሕአዴግ የአገዛዝ ዘመን የዚህ የብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) ጥያቄ በተለያዩ አካላት በተደጋጋሚ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን የአገዛዝ ሥርዓቱ ይህ እርቅ ቢፈጸም የመጀመሪያውና ዋነኛው ተጠቃሚ እሱ መሆኑን እስከአሁንም ቢሆን መረዳት ባለመቻሉ ምክንያት የተለያዩ የእብሪት ኃይለ ቃሎችን … [Read more...] about “ሕወሀት ኢሕአዴግ” በቅርብ ጊዜ የብሔራዊ እርቅ ተማጻኝ!
ቱሪዝም ቢሮ የቀድሞ ውሳኔውን በመሻር ሎምባርዲያ የሚገኝበት ሕንፃ ቅርስ አይደለም አለ
የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጥንታዊው የሼክ አህመድ ሳለህ አልዛህሪ (ሎምባርዲያ ሬስቶራንት የሚገኝበት) ሕንፃ ቅርስ መሆኑን በባለሙያዎች አረጋግጦ ክብካቤና ጥበቃ እንዲደረግለት ሲያሳስብ ቢቆይም፣ ሰሞኑን ባወጣው ሰርኩላር ሕንፃው ቅርስ አይደለም በማለት የቀድሞውን ውሳኔ ሽሯል፡፡ ቢሮው ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ለአዲስ አበባና ዙርያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ጽፎ በነበረው ደብዳቤ፣ ሕንፃው ቅርስ መሆኑን ገልጾ በማስተር ፕላኑ በቅርስነት እንዲያዝ አስታውቆ ነበር፡፡ ቢሮው በጻፈው ደብዳቤ ከፌዴራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፣ ከቅርስ ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ደረጃ ማውጣት ዳይሬክቶሬትና ከቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት፣ እንዲሁም ከራሱ ቢሮ በተውጣጡ ባለሙያዎች በዝርዝር ተጠንቶ የቅርስ መሥፈርት እንደሚያሟላ … [Read more...] about ቱሪዝም ቢሮ የቀድሞ ውሳኔውን በመሻር ሎምባርዲያ የሚገኝበት ሕንፃ ቅርስ አይደለም አለ
የወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ላይ
ወያኔ በለስ ቀንቶት የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን ከተቆጣጠረ ጊዜ አንስቶ ከጫካ አዝሎት የመጣውን አብዮታዊ ዲሞክራሲና የአንድን ጎሳ ሁለንተናዊ የበላይነት የማስፈን ዓላማ ለማሳካት ባለው አቅም ሁሉ ሲሰራ ኖሯል። ዘረኛው ወያኔ የትግሬ ጎሳን በመሣሪያነት ለመጠቀም ሲል ጎሳውን በሞራል፤ በኢኮኖሚ፤ በጤናና በትምሕርት ከሌላው የላቀ ደረጃ ላይ ማድረስ በሚለው መርሁ መሠረት የሃገሪቱን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ወታደራዊና የደህንነቱን ዘርፍ ሁሉ በትግሬዎች ቁጥጥር ሥር እንዲውል በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓትን ዘርግቶ ይገኛል። ይህ ብቻም አይደለም የወያኔ አገዛዝ መሣሪያ ይሆነኛል ከሚለው ከትግሬ ህዝብና ከትግራይ ክልል በዘለለ ኢትዮጵያ ስለምትባል ሃገርም ሆነ ኢትዮጵያዊ ስለሚባል ሕዝብ ዘለቄታዊ ጥቅምና ጉዳት ባለማሰብ የሥልጣን ዘመኑን ዘለዓለማዊ ለማድረግ ያስችለኛል … [Read more...] about የወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ላይ