የአይሲል (Islamic State of Iraq and the Levant - ISIL) እንቅስቃሴ ከሰማይ ዱብ ያለ አዲስ ክስተት አይደለም። አይሲል ( አንዳንዶቹ ISIS ይሉታል - Islamic State of Iraq and Syria ) በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው የፖለቲካ ውጥንቅጥ ሀቅ ውጤት ነው። ለአነሳሱ፣ ለዕድገቱና ለሂደቱ ብዙ ነባሪ ምክንያቶች አሉት። በርግጥ የአይሲልን እንቅስቃሴ ከሀይማኖትና ከዘይት ሀብት ለይቶ ማየት አይቻልም። በፍልጥዔማውያንና በእስራዔላውያን መካከል ያለው ማብቂያ የለሽ ያልተቋረጠ ጦርነት አንዱ ምክንያቱ ነው። በኋላ ቀር የአረብ ነገሥታትና በሥራቸው የሚሰቃየው ሕዝብ የኑሮና የሀብት ሥምሪት መራራቅ ሌላው ምክንያቱ ነው። በእስልምና አጥባቂዎችና ለዘብተኛ ተከታዮች መካከል ያለው የግንዛቤ ልዩነት ሌላው ምክንያቱ ነው። አሜሪካኖች የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ … [Read more...] about የአይሲል (ISIL) እንቅስቃሴ ምንነትና አንደምታው (ከአንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ዕይታ)
Archives for September 2014
ቶክ ሾው (ትዕይንተ-ወግ) ከያኔያንና ጥበብ በሀገራችን
ይሄንን ጽሑፍ ለመጻፍ ምክንያት የሆነኝ “ጆሲ ኢን ዘ ሀውስ” የተሰኘው በዮሴፍ ገብሬ እየተዘጋጀ ኢ.ቢ.ኤስ በሚባል የኬብል ቴሌቪዥን (የመስመር ምርዓየ-ኩነት) የሚቀርበው የጥዕይንተ ወግ ዝግጅት ነው፡፡ ወደዚህ ትዕንተ ወግ ጉዳይ ወደ ኋላ እመለስበታለሁ፡፡ በብዙኃን መገናኛዎች ከሚቀርቡ ዝግጅቶች ውስጥ የትዕይንተ ወጎችን (Talk shows) ያህል የመወያያ፣ የመገናኛ፣ የመቀራረቢያ፣ የመደማመጫ፣ የመተዋወቂያ እንዲሁም አሳታፊ ዐቢይ መድረክ የለም፡፡ እነዚህ መድረኮች ጠቀሜታቸውና ሚናቸው ጎልቶ የመታየት ዕድል የሚያገኙት ግን ካለው ምቹ የአሥተዳደር ሥርዓት የተነሣ በምእራቡ ዓለም ሀገራት ነው፡፡ መቸም ከመወያየት የማይገኝ ጥቅም የማይፈታ ችግር የለምና እነዚህ ዝግጅቶች በእነዚህ ሀገራት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እያበረከቱ የማይተካ ሚናቸውንም እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ ከጠቀሜታቸው ጥቂቶቹን … [Read more...] about ቶክ ሾው (ትዕይንተ-ወግ) ከያኔያንና ጥበብ በሀገራችን
ቅኔና አዘማሪ
መግቢያ ለአዘማሪ ሙያ ተስማሚ የግብር መግለጫ መሆን ያለበት የቱ ነው? አዘማሪ ወይስ አርቲስት? በሚል በአቶ ዓለም ነጻነት ሬድዮ የቀረበው ውይይት ለዚህች ጦማር መነሻ ሆኖኛል። ከቀደሙ አባቶች እንደሰማሁት አዘማሪ ብቻውን የቆመ አይደለም። ከብዙ ነገሮች ጋራ ከቅኔያችን፣ ከዜማችንና ከስሜታችን ጋራ የተያያዘ ነው። አዘማሪ የሚለውን ቃል ከነዚህ ነጥሎ ለማቅረብ መሞከር ያዘማሪን ክብርና ቦታ ዝቅ ያደርገዋል የሚል ስጋት አለኝ። ስለዚህ አዘማሪ ወደሚለው ቃል ዘው ብለን ከመግባታችን በፊት የአዘማሪን ተልእኮ መዳሰስ ሊኖርብን ነው። አዘማሪ የሚለው ቃል የግብሩ (የተልእኮው) መግለጫ ነው። ተልእኮውም ራሱ አዘማሪ ተቀኝቶም ሆነ ገጥሞ ወይም ሌላ የተቀኘውን በዝማሬው ቅላጼ ከጉሮሮውና ከመሳሪያ ጋራ አስማምቶ፣ ቀምሞና አስወድዶ አስውቦ ለህዝብ ማቅረብ ነው። ህዝቡንም ከባህሉ ከታሪኩ … [Read more...] about ቅኔና አዘማሪ
“ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ”
መግቢያ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ። መባል ስላለበት ነው። ያለፈውማ ዓመት አንደኛውን ጥቁር ዓመት ተብሏል። ሲያንሰው ነው። ወያኔ ከመቼው በበለጠ ጥቃቷን በኢትዮጵያ ልጆች ላይ በሁሉም አቅጣጫ ያጧጧፈችበት ዓመት ነበር። ነጻውን መገናኛ ብዙሀን ከጨዋታ ውጪ አድርጋለች። ብዙ ጋዜጠኞች በማሠሯ ወህኔ ቤቱ ጠቧል መሰለኝ፣ አሁን አሁን የያዘችው ዜዴ፣ በቁጥጥሯ ሥር ከሌሉ፣የፋሺን ጋዜጠኞችም ሳይቀሩ ማዘዣ ሳይደርሳቸው፣ በሬዲዮዋና በጋዜጦቿ “ከስሼአቸዋለሁ!” በማለት፣ ነጭ ሽብር እየነዛችባቸው በርግገው ከአገር እንዲጠፉ ማሳደዷን በሰፊው ተያይዛቸዋለች። በዓመቱ መጨረሻ ወር ብቻ 21 ጋዜጠኞች ተደናብረው አገር ጥለው እግሬ አውጪኝ ብለዋል። ሲሸሹም እያየች አታስቆማቸውም። ብቻ ሲወጡላት፣ “እስየው ተሰደዱልኝ!” ብላ “ደቁሴ ንሬ፣ ተባራብሬ!”ዋን ትደልቃልች! ወንድማችን እስክንድር ነጋ፣ … [Read more...] about “ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ”
The Ethiopian Diaspora and consciousness
The Bay Area that currently is home away from home for thousands of Ethiopians is nothing like any other place that I have known. I was born in a small village on the southern part of Ethiopia and have resided in Addis Abeba, Oregon and Seattle Washington before moving here. The Bay Area is unique. I thank the Gods and celebrate my luck whenever I have a chance. The place where I originated from is not known for such movement of people from one location to another. As much as I remember the … [Read more...] about The Ethiopian Diaspora and consciousness
“ክልክል ነው”
ማጨስ ክልክል ነው ማፍዋጨት ክልክል ነው መሽናት ክልክል ነው ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል የቱ ነው ትክክል? ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ኃይል ባደለኝ "መከልከል ክልክል ነው"፤ የሚል ትዕዛዝ አለኝ፡፡ (በእውቀቱ ስዩም፣ የ፣ሣት ዳር ሐሳቦች፣ 2000) … [Read more...] about “ክልክል ነው”
ጄኔራል ታደሰ ብሩና ኮሎኔል ሀይሉ ረጋሳ
ይህንን ፎቶግራፍ ሰሞኑን በኢንተርኔት ላይ ሲንሸራሸር ነው ያገኘሁት፡፡ ፎቶውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው በ1967 በመጋቢት ወር አጋማሽ የታተመ አንድ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ቅጂ ነው፡፡ ያ ጋዜጣ በደርግ ዘመን በድብቅ በከተማችን ይዘዋወር እንደነበረ ትዝ ይለኛል፡፡ በደርግ ውድቀት ማግስት ደግሞ የገለምሶ ከተማ ቀደምት ፎቶ ቤት የሆነው “ፎቶ አብደላ” የጋዜጣውን ኮፒና ይህንን ፎቶግራፍ ለየብቻቸው በማባዛት በሰፊው ሲያሰራጭ ቆይቷል (ፎቶ ቤቱ አንዱን ምስል በሶስት ብር ነው የሚሸጠው)፡፡ ***** በፎቶግራፉ ላይ የሚታዩት የሜጫና ቱለማ ማህበር አንጋፋ አባላት የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ታደሰ ብሩ እና ኮሎኔል ሀይሉ ረጋሳ ናቸው፡፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ የሁለቱን ሰዎች ፎቶግራፍ ያተመው “ታደሰ ብሩና ግብረ አበሮቹ ተያዙ” የሚል ርዕስ ከሰጠው የዜና ዘገባ ጋር ይመስለኛል (ሙሉ ርዕሱን … [Read more...] about ጄኔራል ታደሰ ብሩና ኮሎኔል ሀይሉ ረጋሳ
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ አንድ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ከምንጊዜም በላይ - ብዙ ሰው ተሳትፎ ማንነታቸውን - እንዳሳየን ጽፎ በጀግንነታቸው - መቼም ያልተረሱ እኚህ ስው ነበሩ - ደጃዝማች ገረሱ ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡ ጥያቄ ድጋሚ ተወልደው - በህይወት ቢኖሩ የምንፈልጋቸው - ብዙዎች … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪
በጎደሬ ወረዳ የዘር ግጭት ተነሳ፤ መከላከያ ገብቷል
በጋምቤላ ዞን በጎደሬ ወረዳ ነጋዴዎችና ሰፋሪዎች ከአካባቢው ተወላጅ የመዠንገር ጎሳ አባላት ጋር ተጋጩ። በግጭቱ ከ17 ሰባት በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በግጭቱ የመዠንገር ዞን አስተዳዳሪና የጎደሬ ወረዳ ዳኛ ከነቤተሰቦቻቸው የግጭቱ ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። ግጭቱን ለማብረድ የመከላከያ ሠራዊት የገባ ሲሆን፣ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል ግጭቱን ለማብረድ በጉዞ ላይ እንዳለ በተሰጠ መመሪያ እንዲመለስ ተደርጓል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለጎልጉል እንደገለጹት በወረዳው በመሬት ባለቤትነትና በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ከመሀል አገር በመጡ ሰፋሪዎችና ነጋዴዎች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ዓመታትን አስቆጥሯል። የፌዴራል አገዛዙም ሆነ የክልሉ አመራሮች ችግሩ ሳይሰፋ ሰላማዊ መፍትሄ ባለማፈላለጋቸው ችግሩ ሊካረር ችሏል። ኢህአዴግ የሚከተለው በዘር ከፋፍሎ የመግዛት ፖሊሲ ለችግሩ … [Read more...] about በጎደሬ ወረዳ የዘር ግጭት ተነሳ፤ መከላከያ ገብቷል
የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድህ ምንድነው?
ከአኝዋክ ጀስቲስ ካውንስል የተሰጠ መግለጫ የህወሃት ፍጹም ታማኝ ነበር። በተለያዩ ሃላፊነቶች በህጻናት፣ በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በሰራው ወንጀል በህግ ይፈለጋል፣ በህግ የሚፈልጉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም አቀፍ የፍትህና የመብት ተሟጋቾች ናቸው። ህወሃትን ክዶ በስደት ከሚገኝበት አገር እጁን እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቦለታል። ይህ "ሰው" በጋምቤላ ክልል የፖሊስና የጸጥታ ሃላፊ የነበረ። የደህንነት አመራር ነበረ። ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ለዓመታት የመራ፣ በጅምላ ለተጨፈጨፉት የአኝዋክ ንጹሃን ደም ቀዳሚ ተጠያቂ ነው - ኦሞት ኦባንግ !! ኦሞት በዴሰምበር 13/2003 በጅምላ ጄኖሳይድ ለተፈጸመባቸው ከ424 በላይ የአኝዋክ ንጹሃን ዜጎች፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ስደት፣ መሬታቸው በግፍ ለተነጠቁና በጠመንጃ ለተፈናቀሉ ዜጎች … [Read more...] about የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድህ ምንድነው?