ራሳቸውን ራስ ገዝ አገር አድርገው በማስተዳደር ላይ ያሉት ሶማሌላንድና ፑንትላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ውህደት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ማቅረባቸው ተሰማ። ሰነዱ ለእንግሊዝና ለሌሎች የአውሮፓ ሃያል አገራት መቅረቡም ታውቋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች "እንሰጋለን" ሲሉ የውህደት ጥያቄው ሊተገበር የሚገባው እንዳልሆነ አመልክተዋል። ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ጥያቄ ያቀረቡት ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች የተጠቀሰውን ሰነድ ማቅረባቸውን የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የሰነዱን ዝርዝርና ውህደቱ በምን መልኩ ሊከናወን እንደሚችል ዝርዝር መረጃ ለጊዜው ከመስጠት ተቆጥበዋል። ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ራሳቸውን ከተበጠበጠችው እናት አገራቸው ነጥለው አገር ማስተዳደር ከጀመሩ ዓመታት ቢያስቆጥሩም እስካሁን ድረስ በአገርነት እውቅና … [Read more...] about ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ
Archives for September 2014
ምሽት ዳንኪራ ከዲያስፖራ
ያለሁት ካናዳ፤ ቶሮንቶ ነው፡፡ ከጥቂት ሳምንታት ቆይታ በኋላ ትላንት ማታ አንዱ የኢትዮጵያ ምግብና ዳንኪራ ቤት ለማምሸት ከዘመድ እና ሰሞኑን ከተዋውቅኳቸው ጥቂት ሰዎች ጋር ሄድኩ፡፡ ቤቱ በአንድ ሰሞን በአንድ ዜማ እጅግ ታዋቂ ሆኖ በነበረ ወጣት ድምፃዊ የሚተዳደር ነው፡፡ ስገባ ወጣቱን ድምፃዊ አየሁት፡፡ እንግዶቹን ዞር ዞር እያለ ሰላም ይላል፡፡ ከማውቀው ወፍሯል፡፡ ዘመናዊም ባህላዊም ዘፈን በዲጄ ሲለቀቀቅ ጠባቧ ቤት ንዝረቷ ይጨምራል፡፡ ከምሽቱ አምስት ሰአት ገደማ ቤቷ ሞላች፡፡ ከሀበሻ ውጪ ሌላ ዘር ያለው ሰው ግን አላየሁም፡፡ ስድስት ሆነን ከተቀመጥንበት ጠረጴዛ ጀርባ ባለጌ ወንበርና ጠረጴዛ ላይ አንዲት በህንድ ዘዬ የተሰራ “እዩኝ እዩኝ” ሆደ- ግልብ ብልጭልጭ ልብስ የለበሰች ረጅምና ቀጭን፣ ቆንጅዬ ልጅ ተቀምጣ ቢራ ትጠጣለች፡፡ አላግባብ ተከምሮ ሳር ከጫነ መኪና … [Read more...] about ምሽት ዳንኪራ ከዲያስፖራ
የዛፍ ጥላ ስር ትምህርት ቤቶች
ጠመዝማዛ ባላዎች ላይ የቆመው ክፍል በደደሆ ዛፍ ቅጠል የተሠራ ጣሪያ አለው፡፡ ክፍሉ ውስጥ ከ20 የማይበልጡ ትንንሽ ድንጋዮች ላይ ኩርምት ኩርምት ብለው የተቀመጡ ተማሪዎች ይታያሉ፡፡ ደብተሮቻቸውን በየጉልበታቸው ላይ አድርገው ከፊት ለፊታቸው ያለውን መምህር ያዳምጣሉ፡፡ ከመሬት ብዙም የማይርቀው የክፍሉ ጣሪያ መምህሩን ጐንበስ ብሎ እንዲያስተምር ግድ ብሎታል፡፡ መምህሩ ለማለቅ በተቃረበ ነጭ ጠመኔ ያረጀ ሰሌዳ ላይ ቁጥሮች እየጻፈ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሒሳብ ያስተምራል፡፡ የክፍሉ ጣሪያ በሳሳበት አቅጣጫ የተቀመጡ ተማሪዎች ጸሐይ ይመታቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ድንጋዩ ጐርበጥ ሲያደርጋቸው ወደ አንድ ወገን ገደድ እያሉ ለመመቻቸት ይጣጣራሉ፡፡ እነዚህ በዛፍ ጥላ ስርና በዳስ የሚማሩ ተማሪዎች የመኪና ድምጽ በሰሙ ቁጥር አንገታቸውን አጠማዘው ይመለከታሉ፡፡ ግድግዳ በሌለው ክፍላቸው አቅራቢያ … [Read more...] about የዛፍ ጥላ ስር ትምህርት ቤቶች
የአረብ ሃገሩ ክፉ ስደት!
ገና ረፋዱ ላይ ጸሃዩ ናላን ያዞራል ... የቢሮ የቤት ማቀዝቀዣዎች እንኳ ሙቀቱን ተቋቁመው የማብረድ ስራቸውን እንዳይከውኑ የሳውዲ ጅዳ በጋ ሃሩር ጸሃይ ፈተና ሆኖባቸዋል! ... በዚህ የቀለጠ የበርሃ ሃሩር ጤነኛ መቋቋም ያልቻለው ሙቀት በአንዲት ሰውነቷ የደቀቀ እህት ይወርድባታል ... ቦታውም ከጅዳ ቆንስል ግቢ የቅርብ ርቀት በሚገኝ የአንድ አረብ ግቢ በር ላይ ነው .... ስለዛሬው የማለዳ አሳዛኝ አጋጣሚ ላጫውታችሁ...! ያሻችሁ ተከተሉኝ! የኩባንያ ስራየን በመከዎን ላይ እንዳለሁ እግረ መንገዴን ቀዝቃዛ ውሃና ማኪያቶዋን ለመነቃቂያ ፉት ልበል ለማለት በጅዳ ቆንስል ቅጽር ግቢ ውስጥ ወደሚገኘው የኮሚኒቲ ካፍቴርያ ብቅ ብየ ያችኑ ማኪያቶ አዘዝኩ ... ማኪያቶየን እየቀማመስኩ እንደኔው የካፍቴሪያ ታዋቂ ደንበኞች ከሆኑ ወዳጆቸ ጋር ስንጨዋወት አንድ ሌላው ወዳጃችን ግዙፍ ሰውነቱ … [Read more...] about የአረብ ሃገሩ ክፉ ስደት!
ቴዲ አፍሮ – በሁለት ጽንፎች
ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጽሞ ሊተቹ የማይችሉ ሶስት ግዝፍ ነገሮች አሉ። እነዚህም 1ኛ - ሃይማኖት 2ኛ - መንግስት 3ኛ - ቴዲ አፍሮ ናቸው። ከእንግዲህ ቴዲ አፍሮ ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ መቆራቆዣ ተቋም ሆኗል። ይህን አስመልክቶ ወዳጃችን Girmabbaacabsaa Guutamaa እንዲህ ይላል.... "ቴውድሮስ ካሳሁን aka ቴዲ ኣፍሮ ዘፋኝ ብቻ ኣይደለም። በሃገሪቱ ውስጥ ካሉት ይልቁንም ባብዛኛው ሊታረቁ የማይችሉ (divergent) ማህበረ-ፖለቲካዊ እሳቤዎችን በሚያራምዱ ኤሊቶች ከሚመሩት የተለያዩ ቡድኖች መካከል የኣንዱ ግሩፕ political ideologue ነው ቴዲ።" ይህ ብያኔ (Definition) የተለጠጠ ቢሆንም ውሸት ግን አይደለም። ቴዲ በሁለት ጽንፍ የቆሙ የፖለቲካ ወገኖች መቆራቆዣ አእማድ (Pillar) ሆኗል። የቴዲን ዘፈኖች መተቸት … [Read more...] about ቴዲ አፍሮ – በሁለት ጽንፎች