I listened to VOA Amharic interviews with the ESFNA’s four voting board members (BMs) online, which aired in mid August 2014 and again late August 2014. Afterwards I formed an idea about their readiness for good governance (GV). First off for creating the forum, I appreciated VOA Amharic, and in turn, Journalists and Broadcasters Addisu Abebe and Alula Kebede. I considered the generous airtime VOA gave to the BMs as a favor to strengthen the federation. Also, I appreciated the BMs who shared … [Read more...] about ESFNA’s Board Members Opinion Poll Report
Archives for September 2014
ለሁላችንም የሚበጅ የተባረከ የእርቅ አስተሳሰብ
እንግዲህ ያረጀ የአመፅ ታሪክ ከመድገም፤ ከውጭ አገር መፍትሔ ከመኮረጅና፤ እልከኛና አንገተ ደንዳና ሆነን ለአዲሱ ጤናማ ኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ የማንመች ከመሆን ይጠብቀን። በአይነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነውንና የኛው በኛው ለኛው ሆኖ የሚያኮራንን አዲስ የእርቅና የመግባባት ስሌትን መፍጠር እንችላለን የሚል አስተሳሰብ ይኑረን። እንቆቅልሻችንን እንፍታና የአገር ልጅነት ግዴታችንን በታማኝነት እንወጣ። በተቃራኒ የፖለቲካ አስተሳሰብ የተከፋፈልን ህዝብ ብንሆንም፦ ጥላቻና ንቀትን አስወግደን፤ ሁለቱም ጎራ (መንግስትና ተቃዋሚ) በጡንቻ መጠቀምን እንደ ኋላቀርነት ለመቁጠር የሚያስችል ብስለትና ድፍረት ይታይብን። በብዙ የተለያየ ባህልና ቋንቋ የበለፀግን ህዝብ ነን። የምንከባበርበትና በእኩልነት የምንተያይባት አዲሲቷን ኢትዮጵያ በልዩነታችን እንደ አንድ ቤተሰብ በመሆን ለመገንባት እንድንችል … [Read more...] about ለሁላችንም የሚበጅ የተባረከ የእርቅ አስተሳሰብ
ናፍቆት (በኑሬ)
ስጋዬ ሲበላኝ በጥርሴ ነከስኩት፤ ቆዳዬ ሲበላኝ በጥፍሬ ፎከትኩት፤ እፎይ አስታገስኩት፤ ፀጥ ረጭ አረ'ኩት። የውስጥ አጥንቴ ግን ሲበላኝ ነዝንዞ፣ ሲነክሰኝ ጠዝጥዞ፣ ምንም አላረ'ኩት፤ ምንም አላከኩት፤ ላልችል ችየ ቻልኩት። አልፎክተው ነገር ቆዳዬን መንቅሬ፣ አላኝከው ነገር ስጋዬን ሰርስሬ፣ ይሔው እስከዛሬ፣ አጥንቴ እየበላኝ፣ አለሁልሽ ፍቅሬ። ኑረዲን ዒሳ (ዒሻራ) 14/02/1995 ዓ.ም … [Read more...] about ናፍቆት (በኑሬ)
በግ አሳራጅና አራጅ
አቶ ኑሮ ውድነህ አምና የአዲስ ዘመን በዓልን አስመልክቶ ቤተሰባቸውን ለማስደሰት በማሰብ ያላቸውን ገንዘብ አሰባስበው ገበያ ይሄዱና የበግ ዋጋ ይጠይቃሉ። ሆኖም የበጎቹን ዋጋ ሲሰሙ የሚሮጡት የርቀት መጠን በሜትር እየተነገራቸው እንጂ መሸጫ ዋጋቸው አልመስል እስኪላቸው ድረስ አስደንጋጭ ይሆንባቸዋል። አውጥተው አውርደው ግን ለቤተሰባቸው መጠነኛም ብትሆን በግ በመግዛት ሃሳባቸው ላይ ፀንተው ረከስ ባለ ዋጋ እጅግ ቀጫጫ የሆነች ግልገል በግ ተከራክረው ይገዛሉ። እናም ወደቤታቸው እየሄዱ እያለ በግ አራጅ ይመለከታሉ። እሳቸውም ወጉ እንዳይቀርባቸው: አቶ ኑሮ ውድነህ: ኮራ ጀነን ብለው "ስማ አንተ በግ አራጅ . . . እስኪ ና ወዲህ" ይሉታል። በግ አራጅ: ወደ ሰውየው እየተጠጋ "አቤት?" አቶ ኑሮ ውድነህ: በኩራት እንድ ሁለቴ ካገሱ በኋላ "ይህቺን በግ ስንት ትገፍልኛለህ?" … [Read more...] about በግ አሳራጅና አራጅ
ወያኔ፣ ሽብር እና እኛ
በአለም አቀፍ ደረጃ ስለ ሽብርተኝነት ያለው አረዳድ እና ወያኔ ሽብርተኝነትን የሚተረጉምበት መንገድ ለየቅል ናቸው። በአለም አቀፍ ደረጃ የሽብርተኝነት ጉዳይ እንደ ዋና አጀንዳ ተይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ መነጋገሪያ የሆነው በ1934 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ነው። በዛሬው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተተካው የሊግ ኦፍ ኔሽን በሽብርተኝነት ዙሪያ ሲመክር ቆይቶ በ1937 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና ለመቅጣት የሚያስችል አንድ ድንጋጌ (Convention for the prevention and punishment of terrorism) አጽድቋል። ከዚህ ድንጋጌም በኋላ ከ14 የሚበልጡ አለም አቀፍ ድንጋጌዎችና ስምምነቶች በተባበሩት መንግስታት ጸድቀዋል። የእነዚህ ሕጎች ዋነኛ አላማም መንግሥታት ሽብርተኝነትን በተናጠልም ሆነ በጋራ እንዲዋጉ ለማስተባበር ብቻ ሳይሆን ሽብርተኝነትን … [Read more...] about ወያኔ፣ ሽብር እና እኛ
የከያኔ ቴዎድሮስ ካሳሁን በሰባ (ሳባ) ደረጃና ቅኔው
“በሰባ (ሳባ) ፈረጃ” ሰሞኑን ከያኔ ቴዎድሮስ ካሳሁን የለቀቀው ነጠላ ዜማ ነው፡፡ የዘፈኑ (የሙዚቃው) በነገራችን ላይ ሙዚቃ የአማርኛ ቃል አይደለም ሚውዚክ የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል በሀገርኛ አማርኛ ሲጠራ ነው ልክ school አስኳላ እንደተባለው ማለቴ ነው፡፡ እናም ቴዲ ይሄንን ነጠላ ዘፈን እንደለቀቀ ያው እንደሚታወቀው ቴዲ ዝም ብሎ ዘፋኝ አይደለምና ማለትም የሥነ-ኪንን ዓላማና የዜግነት ግዴታን ጠንቅቆ የሚያውቅ የተረዳ በሥራዎቹም ላይ በተደጋጋሚ ይሄንን ያሳየ ከያኔ ነውና በዚህ ነጠላ ዜማው “ምን ብሎ ይሆን?” በሚል ጉጉት አድማጩ ያተኮረው በስንኞቹና መልእክታቸው ላይ ነበር፡፡ ለሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ይህ ነጠላ ዜማ ቴዲን የማይመጥን ብላሽ ዓይነት ዘፈን ነው የሆነበት፡፡ አንዳንዶችማ ጭራሽ “ቴዲ እንዴት ቢንቀን ነው እንዲህ ዓይነት ፍሬ ፈርስኪ የሆነ ዘፈን በነጠላ ዜማ … [Read more...] about የከያኔ ቴዎድሮስ ካሳሁን በሰባ (ሳባ) ደረጃና ቅኔው
ህወሃት “በህወሃት ወዳጆች” ለእርቅ እንዲነሳሳ እየተሸመገለ ነው!
በኢትዮጵያ ከቀን ወደ ቀን እየከረረ የሚሄደው የጥላቻ ደረጃ ያሳሰባቸው “የህወሃት ወዳጆች” ህወሃት ለእርቅ እንዲነሳሳ የማግባባት ስራ እየሰሩ መሆናቸው ተሰማ። የአቶ መለስና “የህወሃት ወዳጅ” ወይም ቅርብ ናቸው የሚባሉት ራስ መንገሻ ስዩም ጉልህ ሚና ይዘዋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪዎች እንደዘገቡት ከሆነ በህወሃት መንደር እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያምኑ ወገኖች በህወሃትና በተቀረው ህዝብ መካከል እየሰፋ የሄደው ጥላቻ መልኩን እንዳይቀይር ከፍተኛ ስጋት አላቸው። በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚሰማው ቅሬታና የተቋጠረው ቂም ማየሉ ያሳሰባቸው እኚህ ወገኖች ህወሃት ደጁን ለእርቅ መክፈት እንዳለበት በማሳሰብ መጎትጎታቸው እንጂ የእርቁ መሰረትና እርቁ የሚያካትታቸውን ወገኖች በዝርዝር አልገለጹም። “ኢህአዴግ ናቸው” በሚል የሚታሙት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅና ፓስተር ዳንኤል … [Read more...] about ህወሃት “በህወሃት ወዳጆች” ለእርቅ እንዲነሳሳ እየተሸመገለ ነው!
2007-A year of decision
Happy New Year Ethiopia (መልካም እንቁጣጣሸ) Meskerem is a special month. We love and honor Meskerem so much that we name our children by it signifying a new beginning for the long journey ahead. Meskerem is the end of the rainy season and our high mountains and valleys adorn themselves in bright yellow flowers as far as the eye can see, totally overwhelming our senses. For a Diaspora, Meskerem in a strange land, is another hard pill to swallow as an exile from a precious homeland. The physical … [Read more...] about 2007-A year of decision
የስደት እፍታ – ፋሲል አየር ወለድ
ጥርስ ያልነቀለበት እትብቱ ዘመዱ ያልተቀበረበት ባዕድ መሬት ባዕድ ዓይኑ ውሃ ኹኖ ቦታው ጭጋግ ለብሶ ባሳብ እየዋኘ ሄደ ተመልሶ አገሩ ናፈቀው አሁን ይህን ጊዜ ዓደይ አበባ ነው ደማቅ ሰማያዊ ወሩ መስከረም ነው አጭር ነበር ጉዞው የሄደው ባሳቡ ወዲያው ተመለሰ ተመለሰ ዓይኑ እምባ አቀረረ። (ግጥም ገብረክርስቶስ ደስታ) ስደት ከወጣሁ ሦስት ወራት አልፎኛል። በቀጥታ የገባሁት ወንድሜ ቤት ነበር። ሚስትና ሁለት ህጻናት ልጆች አሉት። ሆኖም የራሴ የሆነ አንድ መኝታ ክፍል አላጣሁም። ተዋበ በፊት የማውቀውን አይነት ሆኖ አላገኘሁትም። ሳቁ ደርቋል፣ አጫጭር ነገሮች ተናጋሪ ሆኗል። ነገሮች የሰለቹት አይነት ነው። ሊያውራ የጀመረውን እንኳን አይጨርሰውም። በእንጥልጥል እያለ ወደሌላ ይሸጋገራል። የሌላን ሰው ንግግር የሚሰማው ከፊሉን ነው። የገባው ስለሚመስለው አይፈልገውም፤ … [Read more...] about የስደት እፍታ – ፋሲል አየር ወለድ
ከነጻነት ታጋዮች ጋር በቂሊንጦ
ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው “ጥቁር ሳምንት” (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት “አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር” በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል፡፡ ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል፡፡ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ “ሀገሬ ላይ እርግጠኛ የሆንሁበት ጉዳይ ቢኖር እኔን እንደ ዜጋ የሚጠብቀኝ መንግስት የሌለኝ መሆኑን ነው፡፡ … [Read more...] about ከነጻነት ታጋዮች ጋር በቂሊንጦ