• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከነጻነት ታጋዮች ጋር በቂሊንጦ

September 10, 2014 09:29 pm by Editor Leave a Comment

ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው “ጥቁር ሳምንት” (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት “አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር” በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል፡፡ ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል፡፡

ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ

“ሀገሬ ላይ እርግጠኛ የሆንሁበት ጉዳይ ቢኖር እኔን እንደ ዜጋ የሚጠብቀኝ መንግስት የሌለኝ መሆኑን ነው፡፡ ህገ-መንግስቱ አልጠበቀኝም፡፡ ህገ-መንግስቱ ጥሩ ቢሆንም አልተከበረም፡፡ ይህ ሁሌም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ነው፡፡

“ታስሬ ባለሁባቸው ቀናት ሁሉ የታዘብኩት ነገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት በሁሉም ዘርፍ መኖሩን ነው፡፡ አቅም ያላቸው ዜጎች ከስርዓቱ በመገፋታቸው ክፍተቱ እንዲሰፋ ሆኗል፡፡ በጣም ነው የሚያሳዝነው፤ የሚሰሩ ሰዎች በተገቢው ቦታ ላይ አለመኖራቸውን አይቻለሁ፡፡ የሚያሰራ ስርዓት ስለሌለ ብዙዎች ህሊናቸውን መርጠው በመራቃቸው ይመስለኛል አቅም ያላቸው ሰዎች የራቁት፡፡ ይህ ለሀገር አሳሳቢ ነው፡፡

Zone-9“የሚቆጨኝ ነገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ተቋማት በእንግሊዝኛ የተሰሩ የጥናት ስራዎችን በመምረጥ አሰባስበን በአማርኛ ቋንቋ በጆርናል መልክ ለመስራት አስበን ያን ሳንሰራ በመታሰራችን ነው፡፡

“አሁን በተለያዩ ሁኔታዎችና ጉዳዮች ላይ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያው በኩል የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ እኛን አስረው ሌላው ዝም እንዲል ፈልገው ኖሮ ከሆነ እንዳልተሳካላቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ለሀገር የሚያስቡ ብዙ ወጣቶች በየጊዜው ማበባቸው አይቀሬ ነው፡፡ እየታየ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ምንግዜም የሚበረቱ ሰዎች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አምናለሁ፡፡”

አይመዲን ጀበል፣ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል

“ልትጠይቁን ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ በተለይ ወጣቶቹ እያደረጋችሁ ያለው እንቅስቃሴ እንሰማለን፡፡ በጣም ደስ ይላል፡፡ እስካሁን በአገር ጉዳይ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የቆዩት የ1960ው ትውልድ አባላት ናቸው፡፡ አሁን ወጣቶች እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡ ይህ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ነገር ግን በቂ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስለሆነም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡”

ያሲን ኑሩ፣ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል

“እስር፣ እንግልትና ሌሎችም በደሎች የአምባገነኖች እርምጃ መለያ ባህሪያት ናቸው፡፡ አምባገነኖችን አንድ የሚያደርጓቸው እነዚህ ባህሪያት ናቸው፡፡ አምባገነኖች ከታሪክ አይማሩም፡፡ የዛሬ 20 አመትም ሆነ 50 አመት ወደ ስልጣን የሚወጣ አምባገነን ይህን ነው የሚደግመው፡፡ethiopian muslim

“መንግስት በኃይማኖቶች መካከል ልዩነት መፍጠር ይፈልጋል፡፡ እናንተ ክርስቲያኖች የኃይማኖት ድንበር ጥሳችሁ ከእኛ ከሙስሊም ወንድሞቻችሁ ጋር መቆማችሁን እናደንቃለን፡፡ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ መብት በመቆም የሚያደርገውን ጥረት እናደንቃለን፡፡ እኛን ለመጠየቅ እስር ቤት ድረስ ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ ትግሉ ከዚህም በላይ መስዋዕትነት ያስከፍላልና በርቱ፡፡”

ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ

“ማዕከላዊ የገባነውን የመጀመሪያ ሰሞን ለእኛ አስቸጋሪ ነበር፡፡ በማንኛውም ጊዜ እስር ሊኖር ይችላል በሚል ማዕከላዊ የሚደረጉትን ነገሮች ለማሳወቅ እንጥራለን፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የጻፍናቸው ጽሁፎች ለዚህ ያግዛሉ ብየ አምናለሁ፡፡ በመሆኑም በእኛ ላይ ከደረሱብን ነገሮች ሌሎች ይማሩባቸዋለን ብለን እናምናለን፡፡ ይህ ሲሆን የሚታሰሩ ሰዎች የሚደርስበት ችግር አዲስ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ ወደ ቂሊንጦ ከመጣን በኋላ የተሻለ ነገር ቢኖርም አሁንም ድረስ መጽሃፍና ጋዜጣ አይባልንም፡፡

“በጥቁሩ ሳምንት ዘመቻ ያደረጋችሁትን ነገር ሰምተናል፡፡ በጣም ደስ የሚል ስራ ሰርታችኋል፡፡ መጥታችሁ ስለጠየቃችሁን ደስ ብሎናል፡፡ እስሩ ቀጣይነት እንደሚኖረው ቢታወቅም፣ በየትኛውም ሁኔታ በርታትችሁ እንድትቀጥሉ እፈልጋለሁ፡፡

“በየቀኑ ጋዜጠኞች በሚደርስባቸው ጫና አገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን እንሰማለን፡፡ ይህ በጣም ያሳዝናል፡፡”

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ

“ከመታሰሬ በፊት ማዕከላዊ ውስጥ ስለሚፈጸሙ በደሎች በተለያዩ ሪፖርቶች ላይ ማንበብ ችዬ ነበር፡፡ ማዕከላዊ ከገባሁ በኋላ ያየሁት ግን ሰፊና ከጠበኩት በላይ ነው፡፡ በተለይ ትጥቅ ትግልን የመረጡ ተቃዋሚዎች አባላት ናቸው የተባሉ አሊያም በሚዲያው የማይታወቁና ጠያቂ የሌላቸው አካላት ላይ የሚደርሰው በደል ዘግናኝ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ተመሳሳይ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡ ድሮ ማዕከላዊ ውስጥ ይደረጉ እንደነበር ሰምቼ ነገር ግን ይሆናሉ ብዬ የማላምናቸውን ነገሮች ሁሉ እንደሚፈጸሙ ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡

kerry and nathnael“የማዕከላዊ መርማሪዎች አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ ምርመራ ማድረግ ሳይሆን ጥፋተኛ መሆናችንን እንድናምንላቸው ነው ሁሌም ተመሳሳይ ጥያቄ የሚያነሱልን፡፡ አንዳንዶቹ ጥያቄዎች በጣም የሚገርሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል በምርመራ ወቅት “እከሌ ጋር ሻይ እየጠጣን” ብለን የተናገርነውን ነገር እነሱ “ስብሰባ አድርገን” ብለው ይጽፉታል፡፡ ሻይ መጠጣት በእነሱ ስብሰባ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ አንድ ጋዜጠኛ የሚሰራው ህጋዊ ስራ ህገወጥ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለአብነት ያህል ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25/2004 ዓ.ም ባደረገው ሰልፍ ተገኝቼ ፎቶ አንስቼ ነበር፡፡ ይህ ፎቶግራፍ በክስ ቀርቦብኛል፡፡ አስቡት በዚህ ሰልፍ ኢቲቪና ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎችም ፎቶ አንስተዋል፣ ቪዲዮ ቀርጸዋል፡፡ መርማሪዎቹን “ይህ ስራዬ ነው፡፡ አያስወነጅለኝም” ብትል አያምኑልህም፡፡ ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስም ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ ተገኝተሃል የሚል ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡

“በተመሳሳይ ዩጋንዳ እያለሁ ባቋቋምኩት ጋዜጣ ላይ ሙሃመድ ሰልማን “ፒያሳ ሙሃመድ ጋ ጠብቂኝ” በሚል ከጻፈው መጽሃፍ ላይ ያሉ ጽሁፎችን ጋዜጣው ላይ አውጥቻቸው ነበር፡፡ ሆኖም ይህም በክስ ቀርቦብኛል፡፡ “መጽሃፍ ላይ ነው የወሰድኩት፡፡ መጽሃፉ ህጋዊ ሆኖ አገር ውስጥ ይሸጣል” ብትል ማንም አይሰማህም፡፡ ፖሊስ ህዝብን ለመጠበቅ የቆመ አካል ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡ ነገር ግን ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ ገና ሳይፈረድብን “እናንተስ ለምን ሽብር ትፈጥራላችሁ?” ያሉን ፖሊሶች አጋጥመውናል፡፡ ቀድመው ፈረዱብን ማለት ነው፡፡

prisoner  s“በምርመራ ወቅት በጣም የሚያስገርሙ ነገሮች ተነስተዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጆን ኬሪ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ወቅት መርማሪዎቹ የሚገርም ጥያቄ አንስተውልን ነበር፡፡ “ጆን ኬሪ ጓደኛችሁ ነው?” ብለው ጠይቀውናል፡፡ በጣም የሚገርም ነው፡፡ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን የእኛ ጓደኛ እንደሆነ አድርገው አቅርበውታል፡፡ ደግሞም ይህንንም ህገወጥ አድርገው ነው የሚያቀርቡት፡፡ በሌላ በኩል አንዴ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር፣ ሌላ ጊዜ ከግንቦት ሰባት ሌላ ጊዜ ደግሞ ከኦነግ ጋር ግንኙነት እንዳለን ይገልጹልናል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች በምንም መልኩ የሚገናኙ አይደሉም፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ጋዜጠኛ የሚከሰሰው በመጻፉ አይደለም፡፡ በጋዜጠኝነት ብትከሰስ አንድ ነገር ነው፡፡ እነሱ ግን የሚያነሱብህ ክስ ሌላ ነው፡፡

“ፌስቡክና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ የነበርን ሰዎች ያለመረጃ ስንቀመጥ ከባድ ነው፡፡ በተለይ በመጀመሪያዎቹ 75 ቀናት ነገሮች አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ ከዛ በኋላ ግን ቢያንስ ኢቲቪን መመልከት ችለናል፡፡ ኢቲቪ በሚያቀርባቸው ጉዳዮች ላይ የየራሳችን ትርጉም እየሰጠን አገራችን ውስጥ በጥቂቱም ቢሆን ምን እየተካሄደ እንዳለ መረዳት እንችላለን፡፡ ወደ ቂሊንጦ ከመጣን በኋላ ነገሮች የተሻሉ ናቸው፡፡ ከጠያቂዎቻችን መረጃዎችን ማግኘት እንችላለን፡፡” (የዜናው ምንጭ፤ የመግቢያውና የመጨረሻው ፎቶ፡ ነገረ ኢትዮጵያ)

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule