“በሰባ (ሳባ) ፈረጃ” ሰሞኑን ከያኔ ቴዎድሮስ ካሳሁን የለቀቀው ነጠላ ዜማ ነው፡፡ የዘፈኑ (የሙዚቃው) በነገራችን ላይ ሙዚቃ የአማርኛ ቃል አይደለም ሚውዚክ የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል በሀገርኛ አማርኛ ሲጠራ ነው ልክ school አስኳላ እንደተባለው ማለቴ ነው፡፡ እናም ቴዲ ይሄንን ነጠላ ዘፈን እንደለቀቀ ያው እንደሚታወቀው ቴዲ ዝም ብሎ ዘፋኝ አይደለምና ማለትም የሥነ-ኪንን ዓላማና የዜግነት ግዴታን ጠንቅቆ የሚያውቅ የተረዳ በሥራዎቹም ላይ በተደጋጋሚ ይሄንን ያሳየ ከያኔ ነውና በዚህ ነጠላ ዜማው “ምን ብሎ ይሆን?” በሚል ጉጉት አድማጩ ያተኮረው በስንኞቹና መልእክታቸው ላይ ነበር፡፡
ለሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ይህ ነጠላ ዜማ ቴዲን የማይመጥን ብላሽ ዓይነት ዘፈን ነው የሆነበት፡፡ አንዳንዶችማ ጭራሽ “ቴዲ እንዴት ቢንቀን ነው እንዲህ ዓይነት ፍሬ ፈርስኪ የሆነ ዘፈን በነጠላ ዜማ የቆየውን ያህል ቆይቶ ያውም በአዲስ ዓመት ዋዜማ ወርውሮ የጣለብን? እኛ እሱ የቀበጣጠረውን ሁሉ የግድ መቀበል አለብን እንዴ?” ያሉ አሉ፡፡ ሌሎቹም የቴዲን ችሎታ እስከመጠራጠር በመሄድና ቴዲን በዚህ “ብላሽ” ባሉት ሥራ በመለካት የባልደራሱና የኡኡታየ ደራሲ እሱ አለመሆኑን ለራሳቸው እርግጠኛ የሆኑ አሉ፡፡ ምክንያቱም ይሉና “ያንን የመሰለ የድርሰት ችሎታ ያለው ጭንቅላት እንዲህ ዓይነት ብላሽ ዘፈን አይጽፍም ይላሉ”
ነገሩ ግን ወዲህ ነው ወገኖቸ ቴዲ ከነበረበት ችሎታና አቅም የበለጠ መጠቀ ረቀቀ እንጅ አልወረደም አልተንሸራተተምም፡፡ የእውነቴን ነው የምላቹህ ቴዲ በዚህ ዘፈኑ ቀላል አልተቀኘም፡፡ በእርግጥ የዚህ ዜማ ቅኔ ከዚህ በፊት እንደተቀኘባቸው ዘፈኖቹ እንደ ባለደራሱና ኡኡታየ ዳህላክንና ያሥተሰርያልን ያልጨመርኳቸው ቴዲ በእነዚህኞቹ ማለት የፈለገውን በቅኔ ሳይኖን በግልጽ ያለ በመሆኑ ነው፡፡ እናም እንደ ሁለቱ ማለትን እንደ ባልደራሱና ኡኡታየ ለብዙው ሰው የሚገባ ቅኔ ባለመሆኑ ይህ “በሰባ ደረጃ” የተሰኘው ነጠላ ዜማው ለሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ግልጽ አልሆነለትም፡፡ እንኳን ለሁሉም አድማጭ ለከያኔያን (ገጣሚያን፣ ባለቅኔዎችና ጸሐፍት) እንኳን ግልጽ ስላልሆነላቸው ስላልገባቸው “እልም ያለ የፍቅር ዘፈን” እንደሆነ አድርገው ነበር ለመሔስ የሞከሩት፡፡
ሌላው ዜጋ ባይረዳው እንኳን ከያኔያኑ ግን ሊረዱት በተገባ ነበር፡፡ ይሄ እንግዲህ ስንኞቹ ምን ያህል የጠጠሩ የረቀቁ እንደሆኑ ነው የሚያሳየው፡፡ እውነቴን ነው የምላቹህ ቴዲ ሊሠራው የፈለገው ዘፈን የፍቅር ዘፈን ቢሆን ኖሮ ለየት ባለ መልኩ ከዚህ በላቀ መልኩ አሳምሮ ጽፎ ባቀነቀነልን ነበር፡፡ ዘፈኑ ሁሉም ሰው ነው እንደሚለው “የፍቅር” ሳይሆን “የሀገር” ስለሆነ ግን ሊያስተላልፈው የፈለገው መልእክትና ሐሳብ ቀይዶ ስለያዘው ዘፈኑ የፍቅር ዘፈንን ያህል አሰኛኘት፣ ቀለም፣ ቃና፣ ድምቀትና ጣእም እንዳይኖረው ሊያደርገው ችሏል፡፡
መቶ በመቶ እግጠኛ ባልሆንም ቴዲ የዚህን ዘፈን ቅኔ ትርጉም ይሄ ይሄ ነው ብሎ እንኳን ለሌላ ሰው ለባለቤቱም እንኳን ነግሯታል ወይም ይነግራታል ለማለት እቸገራለሁ፡፡ ከእሷ ለመደበቅ ፈልጎ ማለቴ ሳይሆን አለ አይደል ተመራምራ ትድረስበት ብሎ እሷን ለማመራመር፡፡
የዚህን ዘፈን ቅኔ ትርጉም ከመተርጎሜ በፊት ቴዲን ይቅርታ ልጠይቅ እወዳለሁ፡፡ እንደሚመስለኝ ቴዲ የዚህን ዘፈን ቅኔ ትርጉም ሊነግረን የሚሻው የሚችለውም ፍትሕ የተረጋገጠባት ዲሞክራሲያዊ (በይነ-ሕዝባዊ) የመንግሥት አሥተዳደር ባገኘን ጊዜ ይሄ ማለት ይሄ ነው እያለ ለመተርጎም ከራሱ ጋር እንደተቃጠረ እገምታለሁ፡፡ በመሆኑም አሁን በዚህ ጊዜ በማንም ቢሆን መተርጎሙን ይወደዋል ብየ አልገምትም፡፡
ከዚህ አንጻር መተርጎሜ ቅር ሊያሰኘው እንደሚችል ስገምት አስቀድሜ ይቅርታ ልጠይቀው እንደሚገባኝ አመንኩ እናም ቴዲሾ ይቅርታ! መቸም አንድ የሥነ-ኪን ሥራ ለአደባባይ ከበቃ በኋላ አትሒሱብኝ አትተርጉሙብኝ ማለት አይቻልምና ብየ ነው፡፡ ቆይ! ቆይ! ወይም እንዲህ ብናደርግስ? ዝርዝሩን ልተወውና ምሳሌያዊ አገላለጹን (It’s Metaphorical expression) ብቻ ብጠቃቅስስ? አዎ ይሄ ሐሳብ የሚያስማማን ይመስለኛል፡፡
ጥሩ እንግዲህ በዚህም መሠረት በዘፈኑ ውስጥ ያለችው ሴት ገጸ-ባሕርይ (character) ኢትዮጵያ ናት፣ ለገጸ ባሕርይዋ ያለው ፍቅር የሀገር ፍቅር ነው፣ ገጸ-ባሕርይዋ ግድ የለሽ (ኬሬዳሽ) መሆኗ ሀገሪቱ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ አልሰማት ማለቱን በቃ ማለት አለመቻሏን ለማጠየቅ ነው፣ ሰባ (ሳባ) ደረጃ ከሳባ ከቀዳማዊ ምኒልክ እናት እስከ ራስ መኮነን ልጅ ተፈሪ (ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ) ድረስ ያለውን ረጅሙን የሀገራችንን የመንግሥት አሥተዳደር እና አድካሚውን የሥልጣኔን ዳገታማ ጉዞ ይወክላል፣ ክራሩ እንደሚታወቀው ክራር ንዋዬ-ሐቅል ነው (የሽፍታ ንብረት) የእነፋኖ የአርበኞቹ መሸነጫ መቀስቀሻ ማንጎራጎሪያ መሣሪያ ነው እናም ክራሩ የወከለው አርበኝነትን ነው፡፡ ቴዲ ይሄንንም ለማስገንዘብ ሲል “ሄዶ ከኮሪያ ዘማች ሲመለስ፤ ያወሳል ናፍቆቱን በክራሩ ድምጽ” በማለት እነ ካሳ ተሰማን የሚያህል በክራር አንጎራጓሪ የአርበኛ ዘፈን አንጎራጓሪን እፊታችን እንዳለ ያህል እንዲሰማን በማድረግ ሥዕላዊ ትውስታን እንድናይ ያደርገናል፡፡
በሉ “ለአዋቂ አንዲት ቃል ትበቃለች” እንዲሉ በተስማማነው መሠረት በዚሁ ይብቃቹህ፡፡ ስንኞቹ ይሄ ማለት ይሄ ነው እንዲህ ማለት እንዲህ ነው እያሉ ለመተርጎም እንዴት ይመቹ ነበር መሰላቹህ፡፡ ነገር ግን ይሄንን ለማድረግ ሁኔታዎች አይፈቅዱምና እያዘንኩ በዚሁ እቋጨዋለሁ፡፡ አንድ የምነግራቹህ ነገር ቢኖር ግን ቴዲ ያለትርጉም ያስገባት አንዲትም ቃል አለመኖሯን ነው፡፡ ለማንኛውም ነግቶልን በነጻነት እንዲህ ያለው እንዲህ ለማለት ነበር እያልን ለመጨዋወት ያብቃን አሜን!
በመጨረሻም ቴዲቲ ተሳክቶልሀል እጅ ይባርክ ብያለሁ ተባረክ ከያኔ (Artist) ማለት እንዲህ ነው፡፡ በእርግጥ የዚህን ያህል አክብደህ ቅኔውን በማራቅህ ቢከፋኝም ከነዚሁ ቅሬታየ በጣም አደንቅሀለሁ፡፡ በእርግጥ አንድ ከያኔ ነገርን በቅኔ የሚገልጽበት አራት ምክንያቶች ቢኖሩም እኔ ግን በግሌ ሸፋፍኖ መናገር አልወድም በእርግጥ በእኔም ግጥሞችና ጽሑፎች ላይ ቅኔ የለባቸውም ማለቴ አይደለም፡፡ ከአራቱ ምክንያቶች በአንደኛው ምክንያት ማለቴ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ግን እኔ አንጀቴ የሚርሰው በግልጽ ልክ ልኩን በነገርኩት ጊዜ ነው፡፡ ምክንያቱም የነገሩን ቅኔ በጣም በሰወርነው ጊዜ እንዲደርስ የተፈለገው መልእክት እንዲደርሰውና እንዲገነዘበው ለፈለግነው አካል ሳይደርስና ሳይረዳው ይቀራል ብየ ስለማስብ ነው፡፡ እንዲህ ሲሆን ያ የኪነት ሥራ ግቡን ሳይመታ ይቀራል፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
shimon says
ቀስተ ደመና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ልጁ የተወለደበት ነበር .. እናልሀ ባለፈው ዓመት አራሱን ሰፋ ሲያደርግ ውስጥ የነበሩ ነዋሪዎችን አስወጥቶዋል .. የቴዲ ዘመዶች ቤቱን ሲለቁ ድሮ ካሳሁን ግርማሞ የፃፋት ግጥም ተገኘች ተዘፈነች .. አንተ የሌለ ቅኔ ለመዝረፍ ዳዴ ትላለህ .. ግጥሙ የድምፃዊና ጋዜጠኛ አባቱ ካሳሁን ግርማሞ ነው አትቀባጥር .. ዳንትል!!
Abe says
TedyAfro fesun bifesam QINE new yemitilut…..bishqoch
asefa korench says
@abe you are bull and u are an ordinary person ,empty mind don’t post as such down graded ideas keshim
Woy Zendro says
Qoy golguloch gin min nekachihu? Ahun yihen yemesele dingay ras endezih aynet worQ guday lay enditsf tadergalachihu? Be-Teddy “70 dereja” wust Qine ale bilo yelem bilew yetekerakerutin BewQetun yemesaselu TalalaQ bale Qinewochin keneQore bihuala….Qinewun yinegrenal bilen sintebiQ ziba-zinke tantararam yileQibinal ende! Zim billo si’ilun ayisilim! Azimam chibba 😉
Amsalu Gebrekidan says
ለአስተያየታቹህ አመሰግናለሁ አብዛኞቻቹህ አልገባቹህም እንጅ እኮ ያስቀረሁት ነገር የለም፡፡ ቁልፉ ከተሰጣቹህ በኋላ ከፍቶ መግባት ያቅታቹሀል እንዴ? እስኪ እንዲህ አድርጉ የነገርኳቹህን ቁልፍ ቁልፍ ነገሮች ያዙና ዘፈኑን አድምጡት ተስፋ አደርጋለሁ ሁላቹህንም ባይሆን ይገባቹሃል፡፡ ሁላቹህንም ለማለት ያልደፈርኩት አንዳንድ ታሪካዊ ኩነቶችን የማያውቁ ሰዎች ዘፈኑን ሽ ጊዜ ቢያደምጡትም ለመረዳት ስለማይቻላቸው ነው፡፡ አስቀድሜ እንደተናገርኩት ከዚህ በላይ እያንዳንዷን ቃል እንዲህ እንዲህ ነው እያልኩ አብራርቸ መተንተኑ አደጋ ስላለውና ቴዲን ለጅቦች አሳልፎ መስጠት ስለሆነ ነው፡፡ አመሰግናለሁ
ተስፋየ says
Le ato amsalu ge/kidan
It looks like that you want to praise Teddy. as far as I am concerned, you are not praise him insteade you want to send him to jail and being languished in Woyanies prison for the second time. What ever he said, we love his him for his lyrics and also for his messages. The way how you said it for those who are naive enough to fallow what you say, it seemed you love his works. But from what you have said you want woyane cadres to check him out about the massage of his new clip. Please, please let us get out from such rut. Stop it. Don’t tel me you love him. We all understand Amharic well. I don’t think we need some self appointed “Turjumans.” We have been paid dare price already. If you love him just tell him “we love you Teddy, keep up the good job”, this will be fine for one who live under AGAZI’s Administration.