• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ቴዲ አፍሮ – በሁለት ጽንፎች

September 1, 2014 10:11 pm by Editor 10 Comments

ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጽሞ ሊተቹ የማይችሉ ሶስት ግዝፍ ነገሮች አሉ። እነዚህም

1ኛ – ሃይማኖት
2ኛ – መንግስት
3ኛ – ቴዲ አፍሮ

ናቸው።

ከእንግዲህ ቴዲ አፍሮ ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ መቆራቆዣ ተቋም ሆኗል። ይህን አስመልክቶ ወዳጃችን Girmabbaacabsaa Guutamaa እንዲህ ይላል….

“ቴውድሮስ ካሳሁን aka ቴዲ ኣፍሮ ዘፋኝ ብቻ ኣይደለም። በሃገሪቱ ውስጥ ካሉት ይልቁንም ባብዛኛው ሊታረቁ የማይችሉ (divergent) ማህበረ-ፖለቲካዊ እሳቤዎችን በሚያራምዱ ኤሊቶች ከሚመሩት የተለያዩ ቡድኖች መካከል የኣንዱ ግሩፕ political ideologue ነው ቴዲ።”

ይህ ብያኔ (Definition) የተለጠጠ ቢሆንም ውሸት ግን አይደለም። ቴዲ በሁለት ጽንፍ የቆሙ የፖለቲካ ወገኖች መቆራቆዣ አእማድ (Pillar) ሆኗል።

የቴዲን ዘፈኖች መተቸት ችግር ያስከትላል። የቴዲ ስራ ላይ ሂስ ማቅረብ “ሃራም” ሆኗል። ለምን ቢባል — ቴዲ ለደጋፊዎቹ የማይሳሳት እና ሁሉን አወቅ ነው። የቴዲን ስራዎች መንካት ያሰድባል፤ ያስዘልፋል፤ ባስ ሲል ደግሞ የኢትዮጵያን አንድነት እና “ኢትዮጵያዊነትን” እንደመካድ ያስቆጥራል። የቴዲን አዲሱ ነጠላ ዜማ የተቹ ሰዎች ብዙ ስድብ ሲቀምሱ ታዝቤያለሁ።

በተመሳሳይም የቴዲን ዘፈኖች ማድነቅ ችግር ያስከትላል። ቴዲ በነቃፊዎቹ ዘንድ ሁሌ ስህተት ነው። ስለዚህ የቴዲን ስራዎች ማድነቅ ብሄር ብሄረሰቦችን እንደ መጨቆን፤ የቀድሞ ስርዓትን እንደመናፈቅ እና ገፋ ሲል ደግሞ መንግስትን በ17 መርፌ እንደ መውጋት ተደርጎ ይቆጠራል። “ጥቁር ሰው” የወጣ ጊዜ የኦሮሞ ልሂቃን እና የመንግስት ደጋፊዎች ለምን የአጼ ምኒልክ ስም ተጠራ በሚል የስድብ መዓት ሲያወርዱ አስተውያለሁ።

የሆነው ሆኖ ቴዲ ከእንግዲህ ተራ ዘፋኝ ብቻ አይደለም።

በሰባ ደረጃ

“በሰባ ደረጃ የተባለው ነጠላ ዜማ ቴዲን የሚመጥን ነው ወይስ አይደለም?” የሚለው ክርክር መቋጫ አልባ ይመስላል። ይሄን ዘፈን ሌላ ዘፋኝ ቢጫወተው እንዲህ አይነት አቧራ ያስነሳ ነበር? መልሱ ግልጽ ነው። በእርግጥ ሙዚቃ የስሜት ጉዳይ ነው። ሆኖም ግን በእውቀት የሚተች ጥበብም ነው።

— ለምሳሌ

አስቴር አወቀ በአንዱ ዘፍኗ ውስጥ እንዲህ የሚል ስንኝ አላት።

አዳራሽ
በብዛት ይገኛል
ሽንኩርት እና ፍራሽ

ይሄ ግጥም በሁለት መልኩ እጅግ ደካማ ነው።

1ኛ አዳራሽ ውስጥ ሽንኩርት እና ፍራሽ በጭራሽ አይሸጥም።
2ኛ ከአጠቃላይ የዘፈኑ አውድ (Context) አንጻር ይሄ ስንኝ ምንም ግንኙነት የለውም።

ይሄ አዝማሪዎች የሚታወቁበት የግጥም አይነት ሲሆን የላይኛው እና የታችኛው ሃሳብ ፍጹም አይገጥምም። በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት የዘፈን ግጥም ከትችት አያመልጥም።

የቴዲ አፍሮ “በሰባ ደረጃ” ሃሳቡ በጣም ግሩም ነው። ሆኖም ግን ግጥሙ ውስጥ ልክ በድሮ ጊዜ አዝማሪዎች እንደሚያደርጉት የላይኛውና የታችኛው ስታንዛ የማይገናኝ እና ከአውዱ ውጪ የሆነ ግጥሞች መኖራቸው ዘፈኑን እንዲተች ምክኒያት ሆኗል። ይሄን ሃሳብ ለማጠናከር ብዙዎች የሚከተለውን አንጓ ከግጥሙ ውስጥ ይመዛሉ።

“አምጧት ከጎኔ ትቀመጥ
እንጀራ አይቀርብም ካለ ወጥ”

ጋዜጠኛና ገጣሚ Demeke Kebede ይሄ አይነት ግጥም ለቴዲ አፍሮ አይመጥንም በማለት ይከራከራል። ከዚህም በተጨማሪ “አርምዴ ሜሪ” ብሎ ስሟን ማዟዟሩ ተገቢ እንዳልሆነ ያሰምርበታል።

ታዋቂው ገጣሚና የወግ ጸሃፊ Bewketu Seyoum ግን በዚህ ሃሳብ አይስማማም። እንዲያውም ቴዲ አፍሮ ከዳግማዊ አጼ ቴውድሮስ ቀጥሎ የተነሳ “ሳልሳዊ ቴዎድሮስ” ነው በማለት አሞካሽቶት ሲያበቃ “አርምዴ መሪ ብሎ መጥራት የገጣሚነት ነጻነቱ ይፈቅድለታል” በማለት በተለየ መንገድ ተንትኖታል።

እርግጥ በእወቀቱ እንዳለው ቴዲ የባህል ዘፈን ለመዝፈን ግዴታ በእንኮዬ መስክ እና በኳሊ በር ወይም በጃን ተከል ዋርካ ስር እያለ መዝፈን አይጠበቅበትም። ሆኖም ግን “አርምዴ ሜሪ” ተብሎ ለትውልድ ሲተላለፍ የሚያመጣውን ጉዳት እንዴት እንደተመለከተው አልገለጸም። እስኪ አስቡት አስቴር አወቀ በአንድ ዘፈን ውስጥ “አወቀ አስቴር” ተብላ ብትጠቀስ የወደፊቱ ትውልድ አወቀ የሚባል ወንድ ዘፋኝ ነበር ብሎ ሊተረጉመው ቢችልስ? ቴዲ በጥቁር ሰው ውስጥ “ባልቻ አባቱ ነፍሶ” ያልኩት አውቄ ነው ማለቱ ብዙዎችን አሳዝኗል። የሚስራ ሰው መሳሳቱ የሚጠበቅ ስለሆነ ማመኑ አይከፋም ነበር።

የሜሪን ስም ጉዳይ ብንቀበለው እንኳን እነዚህን ግን ማለፍ አይቻልም። ሴይቼንቶ የሚለውን አጠራር ቴዲ “ሴሼንቶ” ብሎ ገድፎታል። ሴሼንቶ የሚባል መኪና አልነበረም። መውዜር የተባለውን ጠመንጃም መውዜሬ እንደማለት “መውዘሬ” ሲል አንሻፎታል።

በሰባ ደረጃ እነዚህ አይነት ህጸጾች ቢኖሩበትም በርካታ የጠፉ ቃላትን በማምጣት አዲሱን ትውልድ ታሪክ በማስተማሩ ቴዲያችን ሊመሰገን ይገባዋል።

መግቢያው ላይ ያለው የክራር ድምጽ ከሜሪ አርምዴ አገራረፍ ጋር የሚመሳል መሆኑ ጥሩ ቢሆንም በኪቦርድ ተከትፎ መሰራቱ ጥራቱን ደካማ አድርጎታል። የሙዚቃው ምት 6 በ 8 (በተለምዶ ችክችካ የሚባለው) ሲሆን ማስጨፈሪያ አይነት ስለሆነ ቴዲ ከፊታችን ላለበት የአሜሪካ ኮንሰርት ጥሩ መሳቢያ ይሆንለታል።

ቅኔ የመፈለግ በሽታ

በሰባ ደረጃ ቅኔ አለው በማለት በርካታ ሰዎች የተለያየ ትርጉም ሰጥተውታል።

— ግርማ “ቴዲ ኣፍሮና እሱ የሚወክለው ኤሊት የፒያሳውን ሰባ ደረጃ እንደመውጣት ኣድካሚ ነው ያለውን ኢትዮጵያን የማዳን ሃላፊነት በፍቃደኝነት ወስደዋል” በማለት ተንትኖታል።

— ሌላኛው አስተያየት ሰጪ “ቴዲ ለፍቅር እንጂ ለብር እንደማይንበረከክ “ብርም አይገዛሽ – ኬረዳሽ” በማለት ኮንሰርቱ ላሰረዙበት ሰዎች ነገራቸው” ብሏል።

“አቅፎ ገልዋን አልጠግብ ያለው
ማነው ካላችሁ ማነው ማነው?”

— “ያለው እኮ ለወያኔዎች ልክ ልካቸው ሲነግራቸው ነው” ብሎ የጻፈም አለ።

ጋዜጠኛ ደመቀ ግን “ሰባ ደረጃን ደግሜ ደጋግሜ ብሰማውም አንዳችም የፖለቲካ ሰበዝ ተሰብዞበት አላገኘሁትም” በማለት ዘፈኑ የፍቅር እንጂ የፖለቲካ እንዳልሆነ ተከራክሯል።

እኔም ከደመቀ ጋር በብዙ መልኩ እስማማለሁ። ለምን ከተባለ አንዲት ምሳሌ ሰጥቼ ልሰናበት።

ሶስቱ አልማዞች

በደርግ መጀመሪያ ዘመን ህዝቡ ዘፈኖችን እና ስነጽሁፍን ሁሉ ቅኔ ማላበስ ፋሽን አድርጎት ነበር። አፈና ሲኖር እንዲህ አይነት የህዝብ አስተያየት (Public opinion) የተለመደ ነው። የሆነው ሆነ ጥላሁን ገሰሰ ሶስቱ አልማዞች የሚል አንድ ሸክላ አሳተመ። የዘፈኑ አዝማች እንዲህ የሚል ነው

አልማዝን አይቼ አልማዝን ባያት
ሶስተኛዋ አልማዝ ብትመጣ ድንገት
ሁለቱን አልማዞች ስላስረሳችኝ
ምርጫዬ ከምርጫ ተበላሸብኝ

ይሄ ዘፈን የተዘፈነው በወቅቱ የደርጉ ሊቀመናብርት ለሆኑት ለብ/ጄነራል ተፈሪ በንቲ፤ ለሻለቃ መንግስቱ ኃይለማሪያም እና ለሻለቃ አጥናፉ አባተ ነው ተብሎ ተወራ። ልክ ልካቸውን ነገራቸው እያለ ሕዝቡ ወሬውን አስተጋባው። ይሄ ወሬ እነ መንጌ ጆሮ ሲደርስ ወዲያው ሸክላው ታገደ። ደራሲው ተስፋዬ ለማ በቁጥጥር ስር ዋለ። ጥሌም ሁለት ጥፊ ቀምሶ ሁለት ቀን ታስረ።

ደራሲ ተስፋዬ ለማ ከረጅም ጊዜ እስር በኋላ ሲፈታ ወደ ውጪ አገር ተሰደደ። በቅርቡ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት እንዴት እንደጻፈው ተረከ። እንዲህ በማለት….

አንድ ቀን ከሰዓት ላይ ማኪያቶ ለመጠጣት ጆሊ ባር ገባሁ። የታዘዘችን አሻሻጭ (ባር ሌዲ) በጣም ውብ ነበረች። ታዛኝ ስትሄድ እንዴት ቆንጆ ነች … ይህቺስ አልማዝ ነች ብዬ ከጀልኳት። ማኪያቶውን ይዛ የመጣችው ግን ሌላ አስተናጋጅ ነበረች። የሚገርመው ይህቺኛዋም በጣም ውብ ሆና ታየችኝ። መጨረሻ ሂሳብ ስጠይቅ ደግሞ ሌላ ሞንዳላ አልማዝ ስትመጣ ወዲያው ከሁለቱ የበለጠ ውብ ሆና ታየችኝ። ወዲያው እስክሪብቶ አውጥቼ ማስታወሻዬ ላይ “ሶስቱ አልማዞች” ብዬ ጻፍኩ። ግጥሙን እዛው ቁጭ ብዬ ጨርሼው ጥላሁን ዘፈነው።

አይገርምም?

**ማሳሰቢያ
——————
የስድብ (አስተያየት) ፈጽሞ የተከለከለ ነው። ቴዲ እራሱ እንኳን በፍቅር እንጂ መች በስድብ ያምናል?

** ጉደኛው ሰባ ደረጃ በፎቶው ላይ የሚታየው ነው።

(ምንጭ: Yona Bir ፌስቡክ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Dereje Mengesha says

    September 2, 2014 08:38 pm at 8:38 pm

    አበሻ በሙሉ ምን ያጉመተምታል
    አባ ታጠቅ ካሳ ገና ባሕር ይዘምታል፣
    አለ አዝማሪው፣ ይኼ ቅኔ ነው። የአባ ታጠቅን የሩቅ እሳቤ ጠቁዋሚ።በቴዲ አፍሮ ዘፈኖችና የግጥሙ ስንኞች ላይ ግን አዲስ ዘፈን ባወጣ ቁጥር የሚቀርቡት የቅኔ ፈለቀቅን ባይ ትርጉሞች በምንም መልኩ የቴዲን ምናብ ተርጉመውም ይሁን በጥሬው ገላጭ አይደሉም።ብዙዎች የራሳቸውን አለም ምልከታ እንጂ ያሳዩን በገሃዱ አለም የምናቀውን ራሱ ሲተረጎም ፍቅር የሆነውን ቴዲ አፍሮን አይደለም በፍፁም።የቴዲ ልብ ቂም አርግዞ አንደበቱ በወገኖቹ ላይ መርዝ የሚተፋ አይደለም።ስብዕናው የሚጠየፈውን በግድ ሊጭኑበት የሚግደራደሩት እነማን መሆናቸውን ለማወቅ ታምራት ገለታን መካደም አያስፈልግም። ስብዕናው ላላደፈ ሁሉ ገሃድ ነውና።ስለዚህ እንደ ቴዲ አይነቶቹን በፋኖስ የሚፈለጉ የጥበብ ሰዎችን ለማስመታት ለጥበቡም ለቅኔውም ትርጉዋሜውም ያልተፈጠሩ ብዙ ባይሉበት ደስ ይለኛል። ቴዲ ፍቅር ነው።ቴዲ ለበቀልም ለአሽሙርም አልተፈጠረም።ተረረም

    ትርጉዋሜውም ያልተፈጠሩ ብዙ ባይሉበት ደስ ይለኛል። ቴዲ ፍቅር ነው።ቴዲ ለበቀልም ለአሽሙርም አልተፈጠረም።ተረረም
    ተረረም ተግባባን

    Reply
  2. habiba redi says

    September 3, 2014 01:14 am at 1:14 am

    ሲጀምር አንድ ዘፋኝ የፈለገውን መዝፈን አለበት ይህ ጠበብ ነው ተዲ ሆነ ሌላ ዘፋኝ ይሄን ዝፈን ይሄን አትዝፈን መለት አይቻልም ግን ግን ቴዲ በርግጥም የፖሎቲካ ሰው ነው አይደለም ብለን እራሳችንን ከሰላታለልን በስተቀር በትነሹ እንይ የሀይሌስላሴ ደጋፊ ነው ሁሌ የሳቸውን ለበስ ለበሶ መድረክ ላይ ሳይወጣ የቀረበት ቀን የለም ሀሌስላሴን ተቃዋሚ ብዙ አሉ እሱ የሳቸውን አገዛዝ ሚመኝ ሰው ነው ኑግሳዊ አገዛዝ እሳቸው ለሀገራቸው ምን ጠቀሙ ሰለዚህ ተፀዲ በርግጥም የፖለቲካ ሰው ነው።ዘፋኝ መለት ከፖለቲካ የነፃ ከሆነ ምንም አይነት አርማ አዞትሮ መጠቀም የለበትም ግን የፈለገውን መዝፈን መብቱ ነው

    Reply
  3. Ayele says

    September 3, 2014 04:16 am at 4:16 am

    Mendenew leande tera azemari yehen yahl bota mestet.ya yededeboch agezaze endegena yemetal belo maseb yewhent new,bezhe zemen yehn yarege astesaseb yezo megegnet erasu legem keayatu almeshalun ysayal. Zare lay honen yeyanewn menaseb kehne egnam betetenkek eyetebknachehu new

    Reply
  4. EnaAstewul says

    September 3, 2014 06:43 pm at 6:43 pm

    አዳራሽ
    በብዛት ይገኛል
    ሽንኩርት እና ፍራሽ:

    ሽንኩርት የተባለውን ሳታውቅ እንዴት ለትችት ቸኮልክ? ወጣት ሴቶች ማለት ነው አቶ ገምጋሚው:: ዶሮ ማነቂያ ሲባል ሴተኛ አዳሪዎችን ለማለት ነው:: በዘመናችን ወደክለብ/ ኮንሰርት ልሂድና ችክ ልጥበስ ብትል: በእውነት ዶሮ ልትጠብስ ተዘጋጅተህ ነው የምትሄደው? መልሱን ላንት:: በድሮው ጊዜም ታዋቂ ሴቶችን እንዲሁ አይደለም የሚጠሩት:: አርምዴ ሜሪ (የአርምዴ ልጅ ሜሪ) : የድሮው ዘመን አጻጻፍ እንደሆነም በዚሁ እንድታውቅ ልንገርህ::

    Reply
  5. EnaAstewul says

    September 3, 2014 06:47 pm at 6:47 pm

    ከበደ ብዙነሽ የሚባሉ የሴት አርበኛን ታውቃለህ/ሰምተሃል? አርምዴ ሜሪም እንደዛ ነው::

    Reply
  6. Tulu forza says

    September 3, 2014 09:56 pm at 9:56 pm

    “አምጧት ከጎኔ ትቀመጥ
    እንጀራ አይቀርብም ካለ ወጥ” ከዚህ በላይ መንቶ ግጥም ምን ፈለግህ? በአነጻጻሪ ዘይቤ የተከሸነ፡፡ እንጀራ ካለ ወጥ፥ አሱም ካለ እሷ!
    የአርምዴ ሜሪም `ሂስ’ አንደዚሁ፡ `ከመጠምጠም መማር ይቅደም’ የሚለውን ጥንታዊ ብሂል ያስታውሳል፡፡

    Reply
  7. senu says

    September 3, 2014 10:37 pm at 10:37 pm

    abet abet,,!! yehe bedemachin yale Mikegnenet !! kkkk

    Reply
  8. bibi says

    September 4, 2014 10:52 am at 10:52 am

    እኔ የምለው የቴዲ ዘፈን ስለሆነ እኮ ነው አንተም ለመተቸት ብዕርህን ያሾልከው:: ይሄ ዘፈን በJossy ወይም በተመስገን ተዘፍኖ ቢሆን ኖሮ በጣም አሪፍ ዘፈን ነው እያልክ ትኮመኩም ነበር::

    ለምን የዚህ ልጅ ሥራ እና ድርጊት እንደዚህ እንደሚያገበግባችሁ አላውቅም::

    Leave him alone and let us enjoy his music.

    Reply
  9. Tselot says

    September 4, 2014 03:19 pm at 3:19 pm

    I heard his music. The music is matured as usual beyond his age. I believe, the issue is not about the poem; it is about the nationalism that he is praising Ethiopia and past patriots, which is becoming big problem to hear for many that have a project to destroy that country in the name of “Biher Bihereseb?” First of all, it is just music; second, “Enjera yal Wot” is good comparison for the idea he is addressing in that music; third, Armde Mary is same as Mary Armde, same as English speakers call us. Simply, the problem of the writer and supporters is current disease going on in the country (Ethiopia), among Ethnic cleansing planner’s “Tsegur Mesentek.”

    Reply
  10. በለው ! says

    September 9, 2014 06:38 pm at 6:38 pm

    ////ክራር ወዲህ በል! ታንታራራም ታራራም ታራራም! …አዎን የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ…በሁሉን አናጥፋው ዘመን “የማፍረስ አባዜ” ይህ ወጣት ከታሪክ…አስክታሪካዊ ቦታና የፍቅር ሠፈር ሸገርን አስጎበኘን…ክብረት ይስጥልን ብለናል!።መቼም በግጥምም (አማርኛን በአማርእኛ)በትርጓሜና በትችት የሚችለን የለም ግን ሁሉን ቻይ አምላክ ለሁሉ ማሰብ፣ ክህሎት፣ ድምፅን ሲለግስ አንዳንዶች ያልተወለዱበትን ያላደጉበትን ባሕላና ቋንቋ መስለው ለመገኘት ብዙ ይጥራሉ። ያም ቢሆን ከማን አንሼ ያ..ብሄርና ሰፈርና ህዝቡ የአኔም ነው እኔም ያገባኛል አዘምርለታለሁ እቀኝለታለሁ አውቄው እቀውቅና ይሰጠኛል ብለው ነው መልካም ነው በልዩነታችን ውበታችንን ማሳየት ሳይሆን አንድነታችን ኅብረታችን ጥንካሬአችን ነው ታፍረንም ተከብረን የኖርነው ለዚያም ነው!እንግዲህ ሣልሳዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፸ ደረጃን ወረደበት ! እናንት የቀበና፣ የሽሮ ሜዳም፣ የውቤ በረሃ፣ካዛንችስ፣ለገሃር አራት ኪሎ፣ሽሮ ሜዳ፣ ጃልሜዳ፣አፍንጮ በር፣ እሪ በከንቱ እያላችሁ ውረዱበት ! /////>>>ክራር ወዲህ በል! ታንታራራም ታራራም ታራራም!ተቀበል በለው!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule