• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአረብ ሃገሩ ክፉ ስደት!

September 1, 2014 10:48 pm by Editor 1 Comment

ገና ረፋዱ ላይ ጸሃዩ ናላን ያዞራል … የቢሮ የቤት ማቀዝቀዣዎች እንኳ ሙቀቱን ተቋቁመው የማብረድ ስራቸውን እንዳይከውኑ የሳውዲ ጅዳ በጋ ሃሩር ጸሃይ ፈተና ሆኖባቸዋል! … በዚህ የቀለጠ የበርሃ ሃሩር ጤነኛ መቋቋም ያልቻለው  ሙቀት በአንዲት ሰውነቷ የደቀቀ እህት ይወርድባታል … ቦታውም ከጅዳ ቆንስል ግቢ የቅርብ ርቀት በሚገኝ የአንድ አረብ ግቢ በር ላይ ነው  …. ስለዛሬው የማለዳ አሳዛኝ አጋጣሚ ላጫውታችሁ…! ያሻችሁ ተከተሉኝ!

የኩባንያ ስራየን በመከዎን ላይ እንዳለሁ እግረ መንገዴን ቀዝቃዛ ውሃና ማኪያቶዋን ለመነቃቂያ ፉት ልበል ለማለት በጅዳ ቆንስል ቅጽር ግቢ ውስጥ ወደሚገኘው የኮሚኒቲ ካፍቴርያ ብቅ ብየ ያችኑ ማኪያቶ አዘዝኩ … ማኪያቶየን እየቀማመስኩ እንደኔው የካፍቴሪያ ታዋቂ ደንበኞች ከሆኑ ወዳጆቸ ጋር ስንጨዋወት አንድ ሌላው ወዳጃችን ግዙፍ ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ ገባ ! … ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ በቆመበት “አንዲት እህት በር ላይ ወድቃለች ፣ ማን ይሆን የሚረዳኝ?” እያለ እኛን ትቶ ሌላ ሰው በአይኑ መፈለግ ያዘ፣ ብዙም ሳይቆይ ወጥቶ ሄደ። የካፍቴሪያው ደንበኞች እኛ ከደቂቃዎች በፊት አድምቀን ስንረባረብበት የነበረውን ያህል ወሬ ወንድማችን ስለሰጠን መረጃ ግድ የሰጠን አንመስልም ለማለት ደረቅ ቢልም ችግሩን ለምደነው ጉዳያችን ብለን ማንሳት ሳይገደን ቀረና ዝም ብለን ተፋጠጥን …

ብዙም ሳልቆይ ወደ ወደቀችው እህት አመራሁ! ብዙ ኢትዮጵያንውያን ለጉዳይ በሚመላለሱበት የቅርብ ርቀት የወደቀችውን እህት ጠጋ ብለው የሚጠይቃት አይስተዋልም። ይልቁንም እያየን ከንፈር እየመጠጥን ከምናልፈው የነገ ተረኞች ይልቅ አረቦች ቀረብ ብለው “ምነው?  ምን ሆና ነው? ለምን ወደ ቆንስላው አታስጠጓትም? ለምን አንቡላንስ አትጠሩላትም?” እያሉ ወድቃ ባዩዋት የእኛ እህት ሲጨነቁ ተመልክቻለሁ! እኛ ይህን ቀርቦ መጠየቅና መርዳት ባይቻለን ይህች እህት ቢያንስ ቀዝቃዛ ውሃ የምታገኝበትንም ሆነ ማቀዝቀዣ ወዳለው የቆንስሉ መጠለያ የአፍታ እረፍት እንድታገኝ ሙከራ ማድረግ አልቻልንም። እኔና ያ ወዳጀ ሰብሰብ እያሉ ለመጡትና ጉዳዩን በቅርብ ላዩ ለቆንስሉ ባለሟሎች ሳይቀር “ለምን ወደ መጠለያው አናስገባትም?” አልናቸው ባለሟሎቹም  “መጀመሪያ ፍቃድ ማግኘት ያስፈልጋል” ሲሉ መለሱልን ፣ “ታዲያ እናንተው ግቡና እንደ ቀረቤታችሁ የቆንስሉን ሃላፊዎች አስፈቅዱልን” የሚል ጎታጉታችን አቀረብን፣ ሃሳባችን ተቀብለው ሊያስፈቅዱ ወደ ቆንስሉ ሃላፊዎች ቢሮ ሄዱ። ተሎ አስፈቅደው ይመጣሉ ብለን በተስፋ ጠበቅናቸው፣ አልመጡም፣ ለምን ወደ ኃላፊዎች አልደውልም የሚል ሃሳብ መጥቶልኝ ወደ ቆንስል ሸሪፍና ቆንስል ሙንትሃ ደወልኩ፣ ስልኩ ይጠራል ግን አያነሱም!…eth arabia

እኔና ወዳጀ እኛው ራሳችን መጠየቁ ሳይሻለን አይቀርም በሚል ስንንቀሳቀስ ፈቃድ ሊጠይቁ የላክናቸው ወንድሞች የቁራ መልዕክተኛ ሆነዋልና  በላይኛው በር ገብተው በታችኛው በር ሲወጡ በማያርፈው አይኔ አሳዛኙን ሂደት ታዘብኩ! …ቢገርመኝ በንዴት ተቁለጭልጨ ቀረሁ! ወዳጀን በአይኔ በላይኛው ገብተው በታችኛው ወደ ሾለኩት ወንድሞች አቅጣጫ እያመላከትኩ ራሴን በመነቅነቅ “ይህን ጉድ እያየህ ነው!” አይነት ጠቆምኩት፣  እሱም አይኑን ፈጠጥ ራሱን በአንድ በኩል ሽቅብ ነቅነቅ እያደረገ “እነሱ ድሮውንም እንዲህ ናቸው!” የሚል የሚመስለውን ምላሽ መለሰልኝ…

ወደ ቆንስሉ ሃላፊዎች ቢሮ አቀናሁ፣ ሰው የቢሮውን በር ግጥም አድርጎታል። ቆንስሉን እናነጋግር ስንላቸው “ማን ይሰማናል ብለህ ነው?” የሚል ድፍን ያለ ምላሽ የሰጡኝ አንዳንዶች በቦታው የነበሩ ወገኖች ጉዳያቸውን ሊያስፈጽሙ ወረፋ ይዘው ተመለከትኩ። የሚያውቁትን ጉዳይ ደግሜ አስረድቸ በወረፋው እንዲያስቀድሙኝ ብማጸናቸውም ምን ሲባል አሉኝ፣ ግራ ተጋብቸ ተንደርድሬ የሃላፊዋን ቢሮ ከፍቸ ገባሁ! ሃላፊዋ የሉም፣ ተፈናቃዮችና የመጠለያው ጉዳይ የሚያገባቸውን ወንድም አገኘሁና ጉዳዩን በማስረዳት ይህች እህት ወደ መጠለያው ወይም የጸሃይ ከለላ ወደምታገኝበት የቆንስል ወይም የኮሚኒቲው ግቢ እንድትገባ ይተባበሩን ዘንድ ተማጸንኩት! ከሁሉ በማስቀደም ልጅቱን ለመርዳት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በስብሰባ ላይ  ከነበሩት ከቆንስል ሙንትሃ ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ጉዳይ ፈጻሚው አሰረዱኝ። እኔ፣ ወዳጀና የቀረነው ያገባናል ያልን ይህች ምስኪን የተጣለች እህት ከሙቀት ላይ እስካሁን የቆየችውን ያህል ከአሁን በኋላ ብትቆይ እንደማትተርፍ ተረድተናልና አፋጣኝ እርምጃ ይገኝ ዘንድ ወደ ቆንሰሉ ሃላፊ ወደ ቆንስል ሸሪፍ ከይሩ ቢሮ አመራሁ።

ቆንስሉ ሃላፊ ሞቅ ባለ ሰላምታ ተቀብለውኝ ሰላምታ ተለዋወጥን።  ከምጣቴ አስቀድሜ ስልክ ደውየ ምላሽ ሳጣ ወደ ቢሯቸው ለመምጣት መገደዴን አስረድቸ የወደቀቸውን እህት ጉዳይ ለቆንስል ሸሪፍ አስረዳኋቸው። ቆንስል ሃላፊው አቶ ሸሪፍ ስብሰባ ላይ ስለነበሩ ስልኬን በጊዜው  አለማንሳታቸውን ገልጸውልኝ ከታችኛው ቢሮ “ፈቃድ ላግኝ ” ወዳሉኝ ጉዳይ ፈጻሚ ሰራተኛ ደውለው የወደቀችውን እህት ከወደቀችበት ወደ መጠለያ እንዲያስገቡ ጠየቋቸው።  አሁንም ጉዳይ ፈጻሚው ወንድም ቆንስል ሙንተሃን ለማስፈቀድ እየጠበቋቸው መሆኑን ለሃላፊው ገለጹላቸው። ሃላፊው “መጀመሪያ እያትና የሚረዳ ነገር ካለ ትረዳ ፣ ወደ ግቢ አስገቧት፣ ይህን ለማድረግ ምንም ፈቃድ አያስፈልገውም!” ብለው ትዕዛዝ ሰጥተው ስልኩን ዘጉት፣ እኔንም ስለመረጃው አመስግነውኝ፣ እኔም ለትብብራቸው አመስግኛቸው ተለያየን…

ትዕዛዝ የተቀበሉትን ጉዳይ ፈጻሚ ይዠ ወደ ወደቀችው እህት ስንደርስ ከተጣለችበት ወደ ተሻለው የቆንስሉ ግቢ ፊት ለፊት ካለ አንድ ግቢ ታዛ አምጥተዋት ተመለከትን! በቦታው ቆንስል ሙንትሃ ሰውነቷ በውስጥ ደዌ የረገፈውን አህት ውሃ እያጠጡና እያነጋገሯት ደረስን! ቆየት ብየም ከዚህ ቀደም ቆንስሉ በትብብር ሆስፒታል አስገብቷት እንደነበር ለመረዳት ችያለሁ። ያም ሆኖ ውሃ በአፏ ላይ ስታደርግ መናገር የጀመረችው እህት ከሆስፒታል አውጥተው እንደጣሏት ተናግራለች ….

ወደ ዝርዝሩ አንገባም … ከሁሉም በላይ “አይ የሰው ነገር፣ አይ ቁንጅናና ረጋፊው የሰው ገላ! ለይላ! አንች እንዲህ ሆንሽ?!” በማለት በአይኑ አንባ ግጥም እያለ የሚያደርገው የጠፋው “ሃገር ቤት አውቃታለሁ!” ያለን ወንድም ለይላ ለ15 ዓመታት ሳውዲ እንደቆየች አጫውቶኛል …ተሰባስበን “አንቡላንስ አዘናል!” ያሉንን የቆንስል ሃላፊና ምስኪኗን እህት ከበናል …ትክዝ ብየ የአረብ ሃገር ስደት መጨረሻ አሰብኩት …መጨረሻችን ይህው መሆኑ ቢያመኝ “የአረቡ ሃገር ክፉ ስደት … ስደት ክፉ ነገር ነው!” አልኩ ለራሴ በውስጤ በማልጎምጎም ዝም አልኩ! … ድንገት “ኤሽ እንደክ?” “ምን አላችሁ?” ሲል ቆንስሉን ከሚጠብቁት የሳውዲ ልዩ ኮማንዶዎች አንዱ ወደየስራችን እንድንሰማራ አዘዘን  …  ወታደሩ አዞናልና ተበታተንን… !

“ያገባናል!” ብላችሁ ለደከማችሁ ፈጣሪ ዋጋውን ይክፈላችሁ! ዝምታን ለመረጣችሁ፣ ለሸሻችሁ፣ አይታችሁ ላላያችሁ፣ ሰምታችሁ “የዝሆን ጀሮ ይስጠን” ላላችሁ ልቦና ይስጣችሁ! ሌላ የምለው የለም!

ብቻ …  እውነት እላችኋለሁ ወደ አረብ ሃገር አትሰደዱ! ክፉው የአረብ ሃገር ስደት መጨረሻው አያምርም፣ ስንቱን ወገኔን በላው?

እስኪ ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. habiba redi says

    September 3, 2014 12:40 am at 12:40 am

    ወድ የተከበርክው እወነተኛ ልበለው ታሪኩ ልብ ወለድ በቻ ጥሩ ነው ግን ብቻ ገጠመኝ ይባል ለምን ሲቆቃውን ብቻ ማውራት ትወዳላቸው 2ሚሎዎን የበለጠ የኢትዮጲያ ህዝብ እየኖረበት ነው ቤተሰብን እራሱን ከችግር ከረሀብ እህት ወንደሙን እያስተማረ ነው እኔ የድሃ ልጅ ነኝ 16 አመት እያለው እናቴን ማሳከሚያ አጥቼ ስንከራተት ነበር በደህነት ምክንየት በዙ ስቀይ አየን 17 አመቴ ሳውዲ መጣው እናቴን በከፈተኛ ወጭ አሳከመን 2ወንደሜን አስተማርን ቢሆንም የኢትዮ ወሰጥ ሰራ የለም ነፃነት የለም 2ወንደሞቼ ገንዘብ ከወጣለት ትመህርተ ቡሀላ በህጋዊ ሳውዲ መተው እየሰሩ ነው እኔ እዚህ 10 አመቴ ነው ብዙ ኢትዮጲያ አውቃለው እንደኔ ነው ያሉት ትግስት አርገው አንገዳቸውን ደፍተው እየሰሩ ነው ያሉት ሰቆቃ ብቻ አታውሩ 30%የኢትዩጲያ ልጅ አረብ ሀገር ነው ሚኖረው መከራውን ችግሩን ችለን እየሰራን ነው ሰቆቃ አታውሩ ላትጠቅሙን ሆረር አትልቀቁበን እንካን እናንተ መንግስት እንካ እየረዳን አይደለም ሀገር መኖሪያ ፍቃድ ገብተን ተንሽ ነግድ ሰንከፈት የቫት የግድግዳ የንግደ ፍቃድ የጣሪያ እያለ ገዘባችንን ሙጥጥ ያረጋል መርዳት ሲገባው ከስደት ነው የመጡት እስኪደራጁ ትንሽ ዝም ለበላቸው አይልም እንደገና ተቆጥተክ ስተናገር አሸባሪ ብሎክ እስር ቤት ከዛ በባህር እንመጣለን ተመለሰን። እና ዝም በሉ አተዝፈኑ ሰቆቃ ብቻ ግን ለምን ስርተን እየተለወጥን የለውን አትናገርም። በቃ በቃ ወሬ ጠላን እወነት ካዘክላት ወደ ቤትህ አትወሰዳትም ነበር ለአረብ ያላቹ ደፍን ጥላቻ ብቻ ስትሉ ሰቆቃ ብቻ ወሬ ጠላን ነቃንባቹ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm
  • “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት August 1, 2023 09:25 am
  • ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው July 31, 2023 09:27 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule