• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጄኔራል ታደሰ ብሩና ኮሎኔል ሀይሉ ረጋሳ

September 16, 2014 07:44 pm by Editor 1 Comment

ይህንን ፎቶግራፍ ሰሞኑን በኢንተርኔት ላይ ሲንሸራሸር ነው ያገኘሁት፡፡ ፎቶውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው በ1967 በመጋቢት ወር አጋማሽ የታተመ አንድ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ቅጂ ነው፡፡ ያ ጋዜጣ በደርግ ዘመን በድብቅ በከተማችን ይዘዋወር እንደነበረ ትዝ ይለኛል፡፡ በደርግ ውድቀት ማግስት ደግሞ የገለምሶ ከተማ ቀደምት ፎቶ ቤት የሆነው “ፎቶ አብደላ” የጋዜጣውን ኮፒና ይህንን ፎቶግራፍ ለየብቻቸው በማባዛት በሰፊው ሲያሰራጭ ቆይቷል (ፎቶ ቤቱ አንዱን ምስል በሶስት ብር ነው የሚሸጠው)፡፡

*****

በፎቶግራፉ ላይ የሚታዩት የሜጫና ቱለማ ማህበር አንጋፋ አባላት የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ታደሰ ብሩ እና ኮሎኔል ሀይሉ ረጋሳ ናቸው፡፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ የሁለቱን ሰዎች ፎቶግራፍ ያተመው “ታደሰ ብሩና ግብረ አበሮቹ tadese biru abd hailu regassaተያዙ” የሚል ርዕስ ከሰጠው የዜና ዘገባ ጋር ይመስለኛል (ሙሉ ርዕሱን ዘንግቼዋለሁ)፡፡ ይሁን እንጂ በዘገባው የቀረበው “የመሬት ላራሹን አዋጅ በመቃወም ሸፍተው ሀገር ሲያተራምሱ የነበሩት እነ ጄኔራል ታደሰ ብሩ በህዝብ ትብብር ተያዙ” የሚል ከእውነታ የራቀ ሐተታ ነው፡፡ እነ ጄኔራል ታደሰ ለኦሮሞ ህዝብ መብት መከበር ሲሉ ነው በጫካ የመሸጉት እንጂ የመሬት አዋጁን በመቃወም አይደለም፡፡ ይህ የነ ጄኔራል ታደሰ ብሩ የትጥቅ አመጽ ጥንቱ የሜጫና ቱለማ እንቅስቃሴ ቀጣይ ሆኖ ነው የተለኮሰው፡፡

ጀኔራል ታደሰ ብሩ በዚያን ጊዜ በምስራቅ ኦሮሚያ የተጀመረውን የትጥቅ ትግል ሁለተኛ ግንባር በማዕከላዊው ኦሮሚያ ለመክፈት ከአስራ አምስት ያልበለጡ ሰዎችን አስከትለው በጥር ወር 1967 ወደ ምዕራብ ሸዋ ጫካዎች ገቡ፡፡ ይሁንና ብዙም ሳይራመዱ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ በጸጥታ ሀይሎች ተያዙ፡፡ ደርጎችም ጀኔራል ታደሰንና ኮሎኔል ሀይሉን በይስሙላ ፍርድ ቤት ካቆሟቸው በኋላ በመጋቢት ወር 1969 ረሸኗቸው (በነገራችን ላይ “መለስ ተክሌ” የሚባለው የትግራይ ቀደምት ፋኖ “በማዘጋጃ ቤት ላይ ፈንጂ አጥምዷል” የሚል ክስ ቀርቦበት ከጄኔራል ታደሰ ብሩ ጋር በአንድ ላይ ተረሽኗል፡፡ በቅርቡ የሞቱት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ “መለስ” በሚለው የትግል ስም ራሳቸውን የጠሩት መለስ ተክሌን ለማስታወስ በሚል ነው፤ የአቶ መለስ ዜናዊ የልደት ስም “ለገሠ ዜናዊ” ነው)፡፡

*****

የሜጫና ቱለማ እንቅስቃሴንና የጄኔራል ታደሰ ብሩን አመጽ ደራሲ ኦላና ዞጋ “ግዝትና ግዞት” የሚል ርዕስ በሰጠው መጽሐፍ በሰፊው ጽፎልናል፡፡ ስለዚህ ሰፊውን ታሪክ ከዚያ ማንበብ ይቻላል፡፡ እኔም ለወደፊቱ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የመጻፍ እቅድ አለኝ፡፡ ለአሁኑ ግን የሜጫና ቱለማ ማህበርን በተመለከተ አንድ አስፈላጊ መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡

“ሜጫና ቱለማ” ከየትኛውም የፖለቲካና የሀይማኖት ቡድን ጋር ያልወገነ አንጋፋ ማህበር ነው፡፡ መላውን የኦሮሞ ህዝብ የሚያስማማና የሚያግባባ ማህበር ቢኖር እርሱ ብቻ ናቸው፡፡ ባለቤትነቱም የመላው ህዝብ ነው፡፡ አባላቱም በፖለቲካና በሀይማኖት የተገደቡ አልነበሩም፡፡ ታዋቂው የኢትዮጵያ የውትድርና ሊቅ ሌፍትናንት ጄኔራል ጃገማ ኬሎ፣ በቅርቡ ስልጣናቸውን ያስረከቡት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፣ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ነጋሦ ጊዲዳ፤ የኦፌዴን አባላት የነበሩት እነ ዶ/ር ሞጋ ፍረዲሳና ኃይሥላሤ ወልዲያ፣ የኦነግ መስራች አባላት የሆኑት አባቢያ አባጆብር፣ ገላሳ ዲልቦ፣ ሌንጮ ለታ ወዘተ … የማህበሩ አባላት ነበሩ፡፡ ሟቾቹ ባሮ ቱምሳ፣ ቄስ ጉዲና ቱምሳ፣ የድሬ ዳዋው ቀኛዝማች አብዱልዓዚዝ መሐመድ፣ የአርሲው ሃጂ ሮበሌ፤ ወዘተ ከማህበሩ አንጋፋ መካከል ነበሩ፡፡

ሜጫና ቱለማ በኦሮሞዎች መካከል አንድነትንና ፍቅርን ለማጎልበት በሰፊው ሰርቷል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋን ለማሳወቅም ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ ዛሬ ሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ሲቪክ ማህበራትና የባህል ቡድኖች እንደ መለያ አርማ የሚገለገሉበትን የ“ኦዳ” (የሾላ ዛፍ) ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀው የሜጫና ቱለማ ማክበር ነው፡፡ ይህ ማህበር በኦሮሞ ህዝብና በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል በጠላትነት የመተያየት ክፉ አባዜ እንዳይኖርም በሰፊው አስተምሯል፡፡ በመሆኑም ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የተወለዱ በርካታ አባላት ነበሩት፡፡

ምንጭ: OPride.com
ምንጭ: OPride.com

የሜጫና ቱለማ ማህበር ታሪክ በአዎንታዊነቱ የምንጊዜም ተጠቃሽ ነው፡፡ ከኦሮሞ ህዝብ ውጪ ያሉ የፖለቲካ ቡድኖችና ግለሰቦችም በታሪኩ ይኮሩበታል፡፡ ህወሐት፣ ኢህአፓ፣ ኦነግ፣ “ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ” እና ሌሎችም የፖለቲካ ድርጅቶችና አባላቶቻቸው የጻፏቸውን ድርሳናት ብታዩ ይህንን በቀላሉ መረዳት ትችላላችሁ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ (ሕወሐት)፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ (ግንቦት ሰባት)፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (ኦፌኮ-መድረክ)፣ አቶ አባዱላ ገመዳ (ኦህዴድ)፣ አቶ አረጋዊ በርሀ (ትዴን)፣ አቶ አንዳርጋቸው አሰግድ (መኢሶን)፣ አቶ ክፍሉ ታደሰ (ኢህአፓ)፣ ዶ/ር ታደሰ ኤባ (ኦነግ) የጻፏቸውን መጻሕፍትና ያደረጓቸውን ንግግሮች ብትመለከቱ ስለሜጫና ቱለማ ማህበር ቀናውን ሲናገሩ እንጂ አንድም የነቀፋ አስተያየት ሲሰነዝሩ አታገኙም፡፡

ታዲያ በብዙዎች አንደበት እንዲህ የተደነቀው ታሪካዊ ማህበር ባለፉት 10 ዓመታት ከኦነግ ጋር ንክኪ አለው በሚል ምክንያት አላግባብ ታግዶ ነው ያለው፡፡ ማህበሩ የታገደው የዛሬ አስር ዓመት ገደማ “የኦሮሚያ ዋና ከተማ ፊንፊኔ እንጂ አዳማ አይደለችም” የሚል የተቃውሞ ሰልፍ በመዘጋጀቱ ነው፡፡ መሪዎቹና በርካታ አባላቱም “ከሽብርተኞች ጋር ንክኪ አላችሁ” ተብለው ታስረው ነበር፡፡ መሪዎቹ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ባደረጉት ሽምግልና ተፈተዋል፡፡ ከአባላቱ መካከል ከፊሎቹ አሁንም እስር ቤት ነው ያሉት፡፡

ታዲያ የሚገርመው ነገር “የኦሮሚያ ዋና ከተማ አዳማ ናት” የሚል ውሳኔ ያሳለፉትና ውሳኔውን የተቃወመውን ሁሉ በጸረ-ሰላም ሲፈርጁ የነበሩት የኦህዴድ መሪዎች ከምርጫ-97 በኋላ ውሳኔያቸውን አጥፈው “የኦሮሚያ ዋና ከተማ ፊንፊኔ ናት” በማለት ወደ ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) መመለሳቸው ነው፡፡ ይህንን ጥያቄ በቀዳሚነት ያነሳው የሜጫና ቱለማ ማህበር ግን ከኦነግ ጋር ንክኪ አለው ተብሎ ታገደ፡፡ ያ ውሳኔ ዛሬም ድረስ እንደጸና ነው፡፡ ይህ ምን ዓይነት ፍትሕ ነው?

*****

እኛ ኦነግ አይደለንም፤ ኦህዴድም አይደለንም፤ ኦፌኮም አይደለንም፡፡ ፖለቲካው ውስጥ በጭራሽ የለንበትም፡፡ ሜጫና ቱለማ ግን የሁላችንም ነው፡፡ ኦሮሞ ነኝ የሚል ሰው በሙሉ ታሪኩን ይጋራዋል፡፡ ስለዚህ ይህ አንጋፋ ማህበር አላግባብ የተላለፈበት የእግድ ውሳኔ ተነስቶለት ታሪካዊ ሚናውን ይቀጥል ዘንድ እንዲፈቀድለት በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
——-
ግልባጭ
—-ለሚመለከተው ሁሉ …


Afendi Muteki is a researcher and author of ethnography, history and art with special focus on Eastern Ethiopia.

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Engida says

    September 25, 2014 03:22 pm at 3:22 pm

    Tebarek Afendi!

    Oromo bicha sayhonu lelochm Ethiopianoch endezih ayinet netsa tekuamat endinoru yebekulachin’n astewatso enadrg.

    Silezih Mechana Tulema lai yetetalewu egid ahununu yinesa!!!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule