
ወያኔ በለስ ቀንቶት የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን ከተቆጣጠረ ጊዜ አንስቶ ከጫካ አዝሎት የመጣውን አብዮታዊ ዲሞክራሲና የአንድን ጎሳ ሁለንተናዊ የበላይነት የማስፈን ዓላማ ለማሳካት ባለው አቅም ሁሉ ሲሰራ ኖሯል።
ዘረኛው ወያኔ የትግሬ ጎሳን በመሣሪያነት ለመጠቀም ሲል ጎሳውን በሞራል፤ በኢኮኖሚ፤ በጤናና በትምሕርት ከሌላው የላቀ ደረጃ ላይ ማድረስ በሚለው መርሁ መሠረት የሃገሪቱን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ወታደራዊና የደህንነቱን ዘርፍ ሁሉ በትግሬዎች ቁጥጥር ሥር እንዲውል በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓትን ዘርግቶ ይገኛል።
ይህ ብቻም አይደለም የወያኔ አገዛዝ መሣሪያ ይሆነኛል ከሚለው ከትግሬ ህዝብና ከትግራይ ክልል በዘለለ ኢትዮጵያ ስለምትባል ሃገርም ሆነ ኢትዮጵያዊ ስለሚባል ሕዝብ ዘለቄታዊ ጥቅምና ጉዳት ባለማሰብ የሥልጣን ዘመኑን ዘለዓለማዊ ለማድረግ ያስችለኛል በሚለው ጊዚያዊ ጥቅም ላይ ብቻ በማተኮር የሃገሪቱን መሬትና ዳር ድንበር ሳይቀር ለባዕዳን አሳልፎ በመስጠት የጊዚያዊ ፖለቲካና የንዋይ ጥቅም ማጋበሻው እያደረገው ይገኛል።
ሌላው ቀርቶ የሃይማኖት ተቋሙ እንኳ ከትግሬ ጎሳ የበላይነትና ቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን ወያኔ ገና ሥልጣን ላይ ከመውጣቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ የነበሩትን አቡነ መርቆሪዎስን ከመንበራቸው አሽቀንጥሮ በመወርወር በብዙ ሺህ ኪሎሜትር ተጉዞ ባህር ማዶ ድረስ በመሻገር በሃይማኖት ህንጸጽ ተወግዘው በመሰደድ ከኦርቶዶክስ እምነት ይልቅ ወደ ካቶሊኩ እምነት አዘንብለው የነበሩትን አባ ጳውሎስን ትግሬ በመሆናቸው ብቻ መርጦ ፓትርያርክ አድርጎ ሊሾማቸው ችሏል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply