
እንኳን ለ፪ሺ፯ ዓ.ም. አደረሠን፣ አደረሣችሁ!
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፦
እኛ ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ የመስከረምን ወር የመጀመሪያ ቀን የዘመን መለወጫ ዕለት አድርገን ማክበር የጀመርነው በሺህዎች ለሚቆጠሩ ዘመናት እንደሆነ ይታወቃል። በረዥሙ ታሪካችን እንደየአመጣጣቸው፦ ደስታን እና ሐዘንን፣ መከራን እና ብሥራትን፣ ጦርነትን እና ሰላምን፣ መቆርቆዝን እና መበልፀግን፣ ረሃብን እና አንፃራዊ ጥጋብን፣ ወዘተርፈ አስተናግደናል። ያለፈውን ዘመን ሸኝተን አዲስ ዓመት ስንቀበል ዘወትር መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን። ስለዚህ ይህ መግለጫም የኢትዮጵያውያን የዘመናት ትውፊት አንዱ አካል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
ያገባደድነውን ዓመት ዘመነ-ማርቆስን ስንሸኝ በዓመቱ ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባሮች መመዘን ጠቃሚ ይሆናል። ስለሆነም፦
«እኔ ለራሴ ነፃነት መከበር፣ እንዲሁም ወገኖቼ ኢትዮጵያውያንም ከአረመኔያዊው የትግሬ-ወያኔ ናዚያዊ አገዛዝ ነፃ እንዲወጡ የድርሻዬን ምን አከናውኛለሁ?»
ብለን እያንዳንዳችን ራሣችንን መጠዬቅ ይገባናል። ያለበለዚያ ግን ዓመት ቆጥሮ፣ ለይስሙላ ብቻ «እንኳን አደረሰህ፣ አደረሰሽ፣ አደረሳችሁ!» መባባሉ ብቻ ፋይዳ የለውም።
ነገ የምንቀበለው ዘመነ-ሉቃስ፣ እያንዳንዳችን ለአገራችን ለኢትዮጵያ ዳግማዊ ትንሣኤ ታላቅ ታሪካዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ከወሬ ባለፈ የመጀመሪያውን ተግባራዊ ዕርምጃ «ሀ» ብለን የምንጀምርበት ዕለት ሊሆን ይገባል። የዘመናዊ ቅኝ ገዢዎች ወኪሎች ሆነው፣ አገራችንን እና ወገኖቻችንን የመከራ ፍዳ የሚያስከፍሉትን የትግሬ-ወያኔዎችን እና መሠል ተባባሪዎቻቸውን ድል መንሣት የምንችለው፣ ከማንም የውጭ ኃይል በሚጣልልን ዳረጎት እና የዕርዳታ አሽክላ ሣይሆን፣ በራሣችን ኃይል ተማምነን ስንቆም መሆኑን ለአፍታም መጠራጠር የለብንም። ለዚህ ደግሞ «አንድነት ኃይል ነው!» የሚለውን ዕድሜ-ጠገብ ብሂል ልንከተል ይገባል።
በተለይ ለዐማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን፦ ጥንትም ሆነ ዛሬ ነፃነታችንን አስከብረን የኖርነው በራሣችን ተጋድሎ እንጂ በውጭ ኃይሎች በጎ ፈቃን ያለመሆኑን አንዘንጋ። ስለዚህም በእኛ ላይ የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ከፍቶ የኅልውና መጥፋት አደጋ ላይ ያደረሰንን የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ እንደ ንብ ሠራዊት «ሆ» ብለን በአንድነት እንዝመትበት። «መጀመሪያ የመቀመጫዬን» እንዳለችዋ ብልህ እንስሣ፣ እኛም በያለንበት የሚገኙትን ወንጀለኛ የወያኔ-ናዚዎች ነባራዊ ሁኔታው በሚፈቅድልን መንገድ እንታገላቸው። ይህንን በማድረግ የጥንታዊት አገራችንን የኢትዮጵያን ዳግም ትንሣኤ እናረጋግጥ!
መልካም አዲስ ዓመት!
ረቡዕ ጳጉሜን ፭ ቀን ፪ሺ፮ ዓ.ም.
ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደግ!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በታማኝ እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!
Leave a Reply