ብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) በተለይ በእርስ በእርስ ግጭት ደም የተቃባንና የከፋ አደጋ የተጋረጠበትን ኅብረተሰብ ወይም የመበታተን አደጋ የተጋረጠባትን ሀገር በይቅር ለእግዚአብሔር ይቅር አባብሎ ሰላም ለማውረድና የቂም በቀልን ዶሴ ዘግቶ በአዲስ መንፈስ ብሔራዊ መግባባትን (National Consensus) ፈጥሮ የአንዲት ሀገርን ሕዝብ በአንድነት አስተባብሮ ለማንቀሳቀስና ህልውናውን ከመረጋጋቱ ጋራ ለማስቀጠል ዓይነተኛ መንገድ ነው፡፡
በሕወሀት ኢሕአዴግ የአገዛዝ ዘመን የዚህ የብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) ጥያቄ በተለያዩ አካላት በተደጋጋሚ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን የአገዛዝ ሥርዓቱ ይህ እርቅ ቢፈጸም የመጀመሪያውና ዋነኛው ተጠቃሚ እሱ መሆኑን እስከአሁንም ቢሆን መረዳት ባለመቻሉ ምክንያት የተለያዩ የእብሪት ኃይለ ቃሎችን በመሰንዘር ከተለያዩ ወገኖች ለሚቀርብለት ጥያቄ ቀና ምላሽ መስጠት ሳይችል ቀርቷል፡፡ የዚህም ምክንያቱ አንደኛ የሥርዓቱ ባለሥልጣናት የሌላው ጉድፍ እንጅ የራሳቸው ግንድ ስላልታያቸው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ቀኑ ለእነሱ “ሁልጊዜም ፋሲካ” እንደሆነላቸው የሚኖርና አይቀሬው ነገር ማለትም ቀን ተለውጦ ትላንት በሌላው እጅ የነበረው ዛሬ በእነሱ እጅ ያለው ነገ ደግሞ በሌላው እጅ እንደሚገባ ያለመረዳትና ዘለዓለም በእነሱ እጅ የሚኖር ስለመሰላቸው የፈጠረባቸው መዘናጋት ናቸው፡፡
በእኔ እምነት ይህ ትንሽዬ አገዛዝ የቀረበለትን ወርቃማ እድል ሊጠቀምበት ሳይችል ቀርቶ በማባከኑ ከጉዳዩ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችልበትን እድል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳመለጠው አስባለሁ፡፡ አርቀው ማሰብ ቢችሉ ወይም የያዙትን የኃላፊነት ቦታ የሚመጥን ጭንቅላት ቢኖራቸውና ነገ ሌላ ቀን ነው ብለው ጥያቄውን በቀናነት ተቀብለው አስተናግደውት ቢሆን ኖሮ ለሁሉም መልካም ተአማኒ ሰላም ለሀገርም የጸና መሠረት ያለውና ትክክለኛ የዲሞክራሲ (የበይነ-ሕዝብ) ሥርዓት ለመመሥረት በተቻለ ነበር፡፡
ይህ እድል በወያኔም ባይሆን በሌላ ለሀገሪቱና ለሕዝቧ እንደሚኖር አትጠራጠሩ፡፡ ለወያኔ ግን ኃጢአቱን ሊያሥተሰርይለትና በኢትዮጵያ ታሪክ መልካም ስም ሊያሰጠው የሚችለውን መልካም ታሪክ ሠርቶ ማለፍ የሚችልበት ቀን አለፈ፡፡ እስከዛሬ ይህ ትንሽዬ አገዛዝ ተለማኝ ሌሎች ወገኖች ማለትም የሲቢክ (ሕዝባዊ) ማኅበራትና ፖለቲካዊ (እምነተ-አሥተዳደራዊ) ማኅበራት ደግሞ ለማኝ ነበሩ፡፡ እመኑኝ አትጠራጠሩ ከዚህ በኋላ ግን ለማኙ ወያኔ ተለማኙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሆናል፡፡ አዲሱን ዓመት 2007ዓ.ምን ጨምሮ ቀጣዩ ዓመት ለወያኔ ጭንቅና ጥብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ ተስፋን ይዘው መጥተዋል፡፡
ከዚህም የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወያኔ ይሄንን ብሔራዊ እርቅ እሱ በሚመቸው መንገድ አጠናቆ ከጉድ ከውርደትና ሞት ለመዳን የሚችልበትን ስልት በመንደፍና ጭንቅ በገጠመው ቁጥር እየሰበሰበ የሚያሠማራቸውን ከጭንቁ የሚታደጉትን “የሀገር ሽማግሌ” ተብየዎችን ቀሳጢ ጉዳይ አስፈጻሚዎች በማሠማራት ውትወታውን እንደሚያጧጡፈው “ምናለ አምሳሉ በሉኝ” ጠብቁ፡፡ በእኔ እምነት ሕወሀት ኢሕአዴግ ይሄንን ታላቅ ብሔራዊ ቁምነገር መከወን የሚችልበት አቅም ትከሻ ቅድስናና ሰብእና ቅንጣቱ እንኳን የለውም፡፡ በሕወሀት ኢሕአዴግ ከዋኝነት አስተናጋጅነት ኃላፊነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሊመጣ ሊገኝ የሚችል መሠረት ያለው እውነተኛና ትክክለኛ ሰላምና እርቅ አይኖርም፡፡ ምክንያቱም አንዴ ሁለቴ ሦስቴ ብቻም አይደል ለቁጥር ለሚያዳግት ጊዜ መንግሥት ነኝ ከሚል አካል ፈጽሞ በማይጠበቅ ነውረኛነት ብልግና እብለትና ክህደት ማጭበርበር ማወናበድም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተደጋጋሚ ጊዜያት ስለተካደና ስለተሞኘ ስለተወናበደና ስለተጭበረበረ ወያኔ መታመንን መልሶ ላያገኘው አጥቶታልና ብቻ ሳይሆን ወያኔ ይሄንን ማድረግ የሚችልበት ተፈጥሮ ወይም ሰብእና እንደሌለው ሕዝቡ በሚገባ ያውቃልና ነው፡፡
አሁንም እርግጠኛ ነኝ ወያኔ ይሄንን አስመሳይ እንቅስቃሴ በሚጀምርበት ጊዜ በተቃውሞና በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያሉ የሥልጣን ጥማት ያስቸገራቸው ዜጎች በአገዛዙ በመደለል የእንቅስቃሴው አባሪ ተባባሪ ሆነው በመራኮት በሀገርና በሕዝብ ዘላቂ ጥቅም ላይ ከባድ ስሕተትና በደል የሚፈጽሙ ግለሰቦችና ቡድኖች እንደሚኖሩ አትጠራጠሩ፡፡ ምን አለፋቹህ የምታዩት ታላቅ ድራማ ይኖራል፡፡ ከዚህ በኋላ ከምሁራንም በሉ ከፖለቲከኞች እንዲሁም ከሀገር ሽማግሌዎች ባጠቃላይ ከሀገሪቱ ልኂቃን የብሔራዊ እርቅን ጥያቄ ለወያኔ አቀረቡ የሚባሉ ዜጎች ቢኖሩ ያለውንና የነበረውን የተፈጠረውንና የሚፈጠረውን ሁሉ ጨርሰው የማያውቁ ያልተረዱና የማይረዱ የዋሀን እንደሆኑ ልነግራቸው እወዳለሁ፡፡
ይሄንን ሐሳብ ያለ ምንም ግላዊና ከሀገር ጥቅም ጋር ከማይቃረን ምክንያት ከቀናነት ብቻ የሚያስቡ ዜጎች ካሉ እንደምኞታቸው ቢሆን ምንኛ መልካም በሆነ ነበር፡፡ ያለው ሀቅ ግን ከሚያስቡት እጅግ የራቀና የተለየ ነው፡፡ የሥርዓቱ ባለሥልጣናት በብዙ ቢሊዮን (ብልፍ) የሚቆጠረውን ከሀገሪቱ የመዘበሩትን ገንዘብ ቢመልሱም እንኳ፣ ለሀገር ለወገን በተቆጩ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት በታተሩ እየታፈኑ ተወስደውባቸው ልጆቻቸው ወላጆቻቸው በግፍ ተገለውባቸው ለመቅበር እንዲችሉ አይደለም ሞታቸውን እንኳን እንዳያውቁ ተደርገው እርማቸውን እንዲበሉ የተደረጉ ወገኖችን “ግድ የላቹህም ከሁሉም ነገር ሀገር ትበልጣለችና ስለ ሀገር ብላቹህ ይቅር በሉ” ብለን ማሰመን ብንችልም እንኳ፣ “በገደሉኝ በተሻለኝ” የሚያሰኙ ግፍና በደል የተፈጸመባቸውን ወገኖችንም እንደዚያው ማሳመን ብንችልም እንኳ፤ ሀገር ይቅር የማትለው ለይቅርታ የማይመች በርካታ የሀገር ክህደት ወንጀሎች አሉና ይህ የብሔራዊ እርቅ ሐሳብ ከወያኔ ጋራ ምንም የሚሆን አይደለም፡፡ በወያኔ የተደለሉ የተወሰኑ ወገኖች ተወናብደውና አወናብደው እንዲሆን ቢያደርጉ ግን ሀገሪቱ በኢፍትሐዊ መንገድ በወያኔ ያጣቻቸውን ብሔራዊ ጥቅሞቿን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀን በወጣለት ጊዜ ሥልጣንን በእጁ ባደረገ ጊዜ እንዲመለሱለት ጥያቄ የማቅረብና ማስመለስ የሚችልበትን መብት እንዲያጣ ያደርገዋልና ከወያኔ ጋራ በዚህ መልኩ መሸኛኘት የማይታሰብ ነው፡፡
በየዋህነት እንደሚያስቡት ወገኖች በወያኔ እጅ ይሄ ቢፈጸም በኋላ ላይ ለማይወጣላቸው ጸጸት እንደሚዳረጉ ነገሩ እርግጥ ነውና ከወዲሁ መጠቀሚያ ከመሆን እንዲቆጠቡ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ለነገሩ የፈለገውን ያህል ቢባል በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በወያኔ ተሹመው እያገለገሉ እንደምናያቸው የትምህርታቸውንና የእድሜያቸውን ያህል የማያስቡ እንደ እንስሳ ያለ ሆዳቸው ምንም ነገር የማይታያቸው፤ ካለባቸው የአድር ባይነት ርካሽና ወራዳ ሰብእናቸው የተነሣ የዐፄ ኃይለሥላሴን የደርግን አሁንም ደግሞ የወያኔን ሥርዓት ወይም ደግሞ ደርግን ሲያገለግሉ ቆይተው አሁን ደግሞ የወያኔ ሹመኛ ሆነው ያለ አንዳች የአቋም ችግር እንደሚያገለግሉት ሆዳቸው አምላካቸው ክብራቸው በነውራቸው የሆኑ ግልሰቦችን እንደባዶ ብርጭቆ የሞሉባቸውን ሁሉ የሚሞሉ፣ በዚህ ርካሽና ወራዳ ማንነታቸውም ከሰው ፊት ሲቀርቡ ቅንጣትም እንኳን ሐፍረትና መሸማቀቅ የማይታይባቸውን ግለሰቦች አግኝቶ መንቀሳቀሱ አይቀርም፡፡ ምን ቢሠራ ምን ቢያደርግ ግን የሕዝብ አመኔታን አያገኝም እንጅ፡፡
ነገር ግን አገዛዙ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንቅሮ እንደተፋው አውቆ ምንም ቢያደርግ ተአማኒነት አግኝቶ ተጠቃሚ በሚሆንበት መንገድ የሚያደርገውን አስመሳይ ብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) መከወን እንደማይችል ከተረዳ ግን ጡንቻው ሊያቆየው እስከቻለለት ጊዜ ድረስ እየተንገታገተ ይቆይና የፍጻሜው ሰዓቱ ሲደርስ በየመቀመጫችን የቀበረብንን የዘርና የሃይማኖት የሰዓት ፈንጅዎች (Time Bombs) በማፈንዳትና ሀገሪቱን በማፈራረስ ለፍርድ የሚያቀርብ ጠያቂና ከሳሽ አካል እንዳይኖርበት ለማድረግ እንደሚሞክር ካላቸውና ከምናውቀው “ከእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ተፈጥሯቸውና ከእስከዛሬው ፀረ ኢትዮጵያ ሸራቸው በመነሣት መረዳት ይቻላል፡፡ ወያኔ ሁለቴና ሦስቴ አይደለም ሽህ ጊዜ እንኳን በምርጫ ቢሸነፍም ተሸንፌያለሁ ብሎ ሥልጣን የማያስረክብበትም ዋነኛው ምክንያት ይሄ ነው፡፡ ሥልጣን በለቀቀ ማግሥት በፈጸመው ግፍ፣ ሙስና፣ ወንጀልና የሀገር ክህደት ሁሉ እየታነቀ ለፍርድ እንደሚቀርም አሳምሮ ስለሚያውቅ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ወያኔ ከደገሰበት የጥፋት ድግስ አንጻር ሊጠነቀቃቸው የሚገቡ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ይህ የወያኔ ሀገሪቱን አፈራርሶ የመጥፋት ሰይጣናዊ ተግባር እውን ይሆናል ብሎ ግን ቅንጣት ታክል እንኳን እንዳይጠራጠርና ሥጋት እንዳያድርበት ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ይህች ሀገር መቸም ጊዜ ቢሆን ባላት የሠራዊት ብዛትና ኃይል ብቻ በመመካት ከጥፋት የዳነችበት ወይም የተረፈችበት ዘመን ኖሮ አያውቅም፡፡ ይልቁንም በየበረሀው በየገዳሙ በየዋሻው በየፍርኩታው በየበዓታቸው ጤዛ ልሰው ቅጠል ቀምሰው ዳዋ ጥሰው ድንጋይ ተንተርሰው ግርምዓ ሌሊቱን ፀብአ አጋንንቱን ታግሰው በአስጨናቂ ጾም ጸሎት ሥግደትና የተለያዩ የመከራ ትሩፋት ስለ ተወዳጅ ሀገራቸውና ሕዝባቸው መከራ በመቀበል በሚያለቅሱት በቅዱሳኖቿ ጸሎትና ምልጃ እንጅ፡፡ ይሄንን ያህልም የተፈተነውና መከራ እያየን ያለነውም የእነሱን ጸሎት ፈጣሪ ስላልሰማ ወይም ስለማይሰማ አይደለም፡፡
የዚህ ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በዕብ. 12፤5-11 ላይ ይገኛል “ልጀ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቃልል በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል፡፡ ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታቹሀል፡፡ ለመቀጣት ታገሡ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርጋቹሀልና፡፡ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኗልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃሎች እንጅ ልጆች አይደላቹህም፡፡ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይዎት ልንኖር በተገባን? እነሱ መልካም ሆኖ እንደታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል፡፡ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጅ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል” ይላል ቃሉ፡፡ “የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላቹህምን? ይላል እግዚአብሔር” ትን. አሞ. 9፤7 በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ልጆች እንጅ ዲቃሎች አይደለንምና ምንም ቢበድሉ የቱንም ያህል ቢረክሱ ቢያምፁበትም ምንም እንደማይላቸው እንደ ሌሎች ሀገራትና ሕዝቦች ዝም አይለንም እሽ እስክንልና እስክንመለስ ድረስ ይቀጣናል፡፡
ትናንትና በቅዱሳኖቿ ጸሎትና ልመና እንደሚመጣባትና እንደሚደርስባት የፈተናና የመከራ ክብደትና ብዛት ሳያደርግባት እንደአመጣጡ እየመለሰ ከብዙ መከራና ጥፋት የታደጋት አምላክ ዛሬም አለ፡፡ በእርግጥ ቃሉ “እሽ ብትሉ ለኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላቹህ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላቹሀል” ትን.ኢሳ. 1፤19-20 እንዳለው ይህ ሁሉ ጉድ የመጣብንና የተሰበርነው እንቢ በማለታችን መሆኑን ሁሉም እያንዳንዱ ወደሌላው ሳይሆን ወደ ራሱ ወደ ውስጡ በመመልከት ምን ያህል እንዳመፅን እንደረከስን እንደበደልን ከውስጡ ከሚያገኘው መልስ የሚረዳው ነገር ቢሆንም ምን ብንበድለው ምን ብናሳዝነው እንዲህ ወያኔ ላሰበብን ለደገሰብን ዓይነት ጥፋት አሳልፎ ይሰጠናል ብላቹህ ቅንጣት ታክል እንኳን እንዳትሠጉ፡፡ “እመኑ እንጂ አትፍሩ”
ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በእግዚአብሔር ቸርነትና በራሱ በልጆቹ ጥረት ቀድሞ በመንቃት ከጫፍ እስከ ጫፍ ወያኔ የተከለብንን የዘርና የሃይማኖት ፈንጅዎቹን በማምከን ሌሎች እሾሆቻችንም በመንቀል በአዲስ መንፈስ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆኖ በመነሣት ከጥፋት ይድናል የሚል የጸና እምነት አለኝ፡፡ ለወያኔ የምንሰጠው ወይም የማንነፍገው ነገር ቢኖር ፍትሕና ሕትህ ብቻ ነው፡፡ ሁሉም የዘራውን ማጨዱ ግድ ነው፡፡ ቃሉም እንደሚል “ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና” ገላ 6፤7 ፡፡ እናም በብዙ ነገር የቆሰለውን የደማውን ያመረቀዘውን የሀገር አንጀት የሚያጠግገው ቂም በቀልን የሚሽረው ፍትሕ ብቻ ነው፡፡ ለዚህች ከቅርብ እርቀት ላለች ትንሣኤያችንን ለምታረጋግጠው ብሩህ ቀናችንም ታጋዩ አርበኛው ወታደሩም በጽናት ይታገል፣ ሁሉም ዓይነት ሠራተኛ በትጋት ይሥራ፣ ገበሬውም በብርታት ይረስ፣ ካህኑም በንጽሕና ይጸልይ ይቀድስ፣ እናቶችም ያለ እረፍት ይማለሉ፣ ሁሉም ዜጋ እጁ ላይ ባለው ነገር ሁሉ የመጨረሻ ይበርታ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
Kebede Zemach Zewdie says
ፌዴራሊዝም ለዘላለም ይቀጥላል የስልጣን ጥመኞች በአንድነት ስም የብሔር ጭቆና ለማስፈን ቀን በቀን ይለፍፋሉ! ሁሉም በገዛ ሃገሩ ኢትዮጵያ እኩል ማንነቱ ተከብሮ ባህሉ ታዉቆለት በቁዋንቁዋዉ ተናግሮ በሰላም የመኖር እንጂ ማንም ጌታ ሌላዉ ሎሌ የሚሆንበት ስርዓት አብቅቶለታል!
koster says
National Reconcilation works in a “civilized society”. For TPLF fascists National Reconcilation means “Shinfet” and for a group of people who claimed to be super warriors, golden race etc. to admit mistakes and ask excuse is unthinkable. Besides if they loose power, there are lots of things they loose so they prefer to loot and kill until the last minute until they will be killed or overthrown by a united Ethiopian force.
DASSENNECH says
የህወሃት ፍላጎትም ሆነ ቋሚ አላማ መግዛት ነው። ብሄራዊ እርቅ የሚፈልግ ደግሞ አገር ማስተዳደር የሚፈልግ ነው; ስለዚህ በምን መልኩ ነው ህወሃት ብሄራዊ እርቅ ይፈልጋል ተብሎ የሚታሰው? ካሸነፈው፤ ከናቀው፤ ረግጦ ከሚገዛው ህዝብ ጋር መታረቅ በዕብሪት ለተወጠረው ህወሃት ውርደት ነው፡ ጥያቄውም ድፍረት ነው የሚሆንበት; ለእርቅ ጤነኛ አእምሮ ያስፈልጋል፡፤ በጥላቻ፤ በቂም በቀል፤ በአፍቅሮተ ነዋይ ከሁሉም በላይ ደግሞ በበታችንት ስሜት የተወመጠረና የበላይነቱን በመግደል፤ በማሰር፤ በማንገላታትና በማዋረድ ማሳየት የሚፈልግ ቡድን እንዴት ሆኖ ነው እርቅ የሚያስበው? የህወሃት ያለቀለት ነገር ነው ስለዚህ ከህወሃት በሗላ ስለምትፈጠረው የጋራ ሃገር ማሰቡ ይሻላል እንጂ ከህወሃት ጋር ብሄራዊ እርቅ ሸንጎ የሚሉት ከማዘናጋት ያለፈ ፋይዳ የላቸውም ብየ አምናለሁ።
አንተነህ ጌትነት says
ወንድም ዓለም ሠዓሊ አምሳሉ ጽሁፍሕ ለሀገሩ እጅግ ከሚቆረቆር ዜጋ የሚጠበቅ ጽሁፍ ነው። በመሆኑም ጽሁፍህ እጅግ እጅግ ያስደስተኛል፤ስሜተንም ይገልጽልኛል።ጀግናም ነህ ኢትዮጵያ ተቀምጠህ እንደዚህ ያለ ጹሁፍ የምትጽፍ ስለሆነ። ጎልጉሎችም ብዙን ጊዜ የምታወጧቸው ጽሁፎች ሚዛናዊ በመሆናቸው እጅግ ያስመሰግናችኋል።ሌሎቹ ድህረ ገፆች በሌላ ኃይል ስለሚነዱ ነጻ ጽሁፍ ስለማያወጡ ለነፃነት የሚደረገውን ትግል እየገደሉት ስለሆነ የናንተ ድህረ ገጽ ሐላፊነቱን በትክክል እየተወጣ ስለሆነ በዚህ ልትመሰገኑ ይገባል።
ሥላሴ ረጅም ዕድሜ ይስጥህ።
ወንድምህ አንተነህ ጌትነት ( ከባዕዳን ምድር አውስትራሊያ)
Mamo says
I really agree in what you said, there is no stone that the current regime digs up to stay on power. They know very well it is improbable to continue in the current situation: oppressive, devoid of democracy, absence of freedom of speech, unfair wealth distribution, controlling the military, security service, desperate to be part of everything etc. Hence they would attempt a fake National reconciliation as anticipated, if so,we have to do every thing possible to make the reconciliation genuine and legitimate with that very small spark of hope just to avoid crisis and other destructive means.
Amsalu Gebrekidan says
በመሠረቱ በሕዝቡ ላይ ዘረኛ ግፍ እየፈጸመ ሕዝቡን እንዲህ በተሳሳተ አቅጣጫ እንዲያስብ ያደረገው ማን ሆነና? ስለዚህ እኔ “የሕወሀት ባለሥልጣናት የኢትዮጵያና የሕዝቧ የወደፊት ሁኔታ በእጅጉ አሳስቧቸዋል” የተባለውን አባባል በፍጹም አላምንም፡፡ ምክንያቱም እንዲህ እንዲሆን ለ23 ዓመታት አሁንም በዚህ ወቅት የደከሙበትና እየደከሙበት ያሉበት ዓላማቸው ነውና፡፡ ስለሆነም ያገሬ ልጆች ሆይ! የወያኔ ባለሥልጣናትን አስመሳይ ወሬ በፍጹም በፍጹም አትመኑ፡፡ ሲጀመር እነሱ እንዲህ ዓይነት ሰብእና ጨርሶ የላቸውም፡፡ ከአካላቸው በስተቀር የሰው ተፈጥሮ የላቸውም፡፡ ፖለቲከኞቹ ብቻ ሳይሆኑ የሃይማኖት መሪዎቻቸውም ጭምር እንጅ፡፡ ይሄ አታላይ ሐሳብ የመጣው መጨረሻቸው ከደጃቸው ቆሞ እያንኳኳ ከመሆኑ የተነሣ ስለጨነቃቸው ነው፡፡ ይልቁንስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይህ የሚጠቁመው ውጥን ትግልህ ለእነሱ አስጊ መሠረት መያዙን ሥር መስደዱን ነውና ግፋ! በርታ! በአጭር ጊዜ ውስጥ ነጻነትህል ታረጋግጣለህ፡፡ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን!!!
Substantially, who is the one makes the people to think in the wrong direction with their racist injustice activities? So, I never believe that “ Woyyanes are worried highly about the feature of the Country and the People of Ethiopia” never. Because that is their objective, their business they worked hard for the last 23 years and current time as well. So my compatriots never believe the Woyyanes officials talk never! First of all they never have that kind of personality. They have no Human nature except their body. Not only their politicians but also their religious leaders. This cheating is comes from their distress, because their last is stand and knocking out of their door. On the contrary People of Ethiopia, That indicates your scheme struggle is entrenched and it has a base that makes them so worried. Hence, Go forward! Cheer up! You will assure your Independent in a short period of time. God be with you!