• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ

September 8, 2014 01:24 am by Editor 1 Comment

በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ በስደት አገራቸውን ጥለው የወጡ የኤርትራ ስደተኞችን እንደሚሰልል ተረጋገጠ። የስዊድን መንግሥት በደረሰው ጥቆማና ማስረጃ መሰረት ባደረገው ማጣራት ኤምባሲው በስለላ ስራ ተሰማርቶ ስዊድን ከለላ የሰጠቻቸውን የኤርትራ ተወላጆች አንደሚከታተልና እንደሚሰልል ማስረጃ ተይዞበታል።

ተቀማጭነታቸው ስዊድን የሆነ የጎልጉል ተባባሪዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመነጋገር እንዳመለከቱት፣ የስዊድን ዜግነት ያላቸውንና ሻዕቢያን ለማስወገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን የሚደግፉ፣ አክቲቪስት የሆኑትን የኤርትራ አገዛዝ በኤምባሲው አማካይነት እንደሚስልላቸው የታወቀው በጥቆማ ነው።

ውስን ቁጥር ያላቸው በስዊድን የሚኖሩ የኤርትራ ተወላጆች ባቀረቡት ጥቆማ መሰረት የስዊድን መንግሥት ባካሄደው ማጣራት የኤርትራ ኤምባሲ የተከሰሰበትን ተግባር እንደሚፈጽም ተረጋግጧል። የመረጃው ባለቤቶች እንዳሉት ስደተን ሸሽተው የሚኖሩበት አገር ድረስ እየተከታተሉ መሰለል በህግ የተከለከለ በመሆኑ የኤርትራ ኤምባሲ ሊዘጋ እንደሚችል ፍንጭ ማግኘታቸውን አመልክተዋል።

ዳዊት ይስሃቅ
ዳዊት ይስሃቅ

ይህንኑ የተረዳው የሻዕቢያ አገዛዝ ከውሳኔው በፊት የምርመራውን ውጤት ለማስገልበጥ የበኩሉን እየሰራ መሆኑንን ከመረጃው አጠናካሪዎች ለመረዳት ተችሏል። የስዊድን መንግሥት በኤርትራ እስር ቤት ታስሮ ይሙት ይዳን በይፋ በማይታቀወቀው ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ ጉዳይ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር ሲወዛገብ እንደነበርና ጉዳዩ እስካሁን እልባት እንዳላገኘ የመረጃው አቀባዮች አመልክተዋል።

በተለያዩ አገራት በትውልድ አገራቸው ያለውን አገዛዝ ኮንነው የጥገኛነት ማመልከቻ የሚያስገቡ፣ ከለላ ከተሰጣቸው በኋላ “በደለን” ለሚሉት አገዛዝ ሲላላኩና ሲሰሩ ባደባባይ እንደሚታይ በመጠቆም አስተያየት የሰጡ፣ ይህ የኤርትራ ተወላጆች መረጃ ላይ ያተኮረ ክስ ለኢትዮጵያዊያን ታላቅ ትምህርት እንደሚሆን ተናግረዋል።

በአሜሪካና በተለያዩ የአውሮጳ አገሮች ኢህአዴግ ዜጎችን እየተከታተለ እንደሚሰልል፣ በአፍሪካ ድንበር አቋርጦ የፈለገውን ከመሰለል አልፎ እንደሚያስርና እንደሚገድል ያስታወሱት አስተያያት ሰጪ “ተቃዋሚዎች የኢህአዴግ ኤምባሲዎች የስለላ ስራ እንደሚሰሩ ማስረጃ በመሰብሰብ ክስ ሊመሰርቱ ይገባል” ብለዋል።ali and isayas

ጋዜጠኛ ዳዊት የስዊድን ዜግነት ያለው ሲሆን 2001 ላይ ነበር የታሰረው። በኤርትራ የመጀመሪያዋ “ሴቲት” ጋዜጣ ሪፖርተርና ሸሪክ ባለቤት የነበረው ዳዊት በመስከረም 2001 ከመኖሪያ ቤቱ ታፍኖ ሲወሰድ በተመሳሳይ 10 የሚሆኑ ጋዜጠኞችም መታሰራቸው በወቅቱ ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ ድርጅት (ሲፒጄ) ዘግቦ ነበር። ከነሱም በተጨማሪ ተለምዶ G15 የሚባሉት የለውጥ አራማጅ ባለስልጣኖች አብረው ታስረዋል። ዳዊት የት እንደታሰረ ባለስልጣናት እንኳን እንደማያውቁ አቶ አሊ አብዶ የቀድሞው የማስታወቂያ ሚኒስትር ኢሳያስን ከድተው ከኮበለሉ በኋላ መግለጻቸውን በስዊድን የሚገኙ መገናኛዎች ወንድማቸውን ጠቅሰው መዘገባቸው ይታወሳል።

“የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ልጅ” የሚባሉት አቶ አሊ፣ ዳዊት በህይወት እንደሌለ ፍንጭ በመስጠት ቀዳሚው ባለስልጣን ሆነዋል። የሆነ ሆኖ ሻዕቢያ በጋዜጠኛ ዳዊት ጉዳይ በግልጽ እምነት ክህደት አላካሄደም። ጋዜጣ ከኤርትራ ምድር እንዲታገድ መደረጉን በወቅቱ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። (ፎቶ: የኤምባሲው ድረገጽ)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. aradaw says

    September 11, 2014 01:52 am at 1:52 am

    የእኛን ጉድ ማን ይናገር ማን ያውራ
    የእኛዎቹ ከመሰለል ኣልፎ ያፍናሉ ይገድላሉ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule