• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Literature
ጽፈኪን

“ሰው አይደለም ! …” አለኝ

July 2, 2016 07:07 am by Editor Leave a Comment

“ሰው አይደለም ! …” አለኝ

ገና ቁጭ እንዳልኩኝ ቀጥሮኝ እንዳገኘኝ እከሌ ጨርሶ «ሰው አይደለም!»  አለኝ ምነው? ምን አ’ረገህ ? «ሰው አይደለም!» ስልህ እኮ! ምን አ’ረገህ? «ሰው አይደለም!» አልኩህ። ቢራችንን አዘን በዝምታ ቆየን እንደገና ደግሞ ሳሉን እየሳለ አንገቱን ነቅንቆ «ሰው አይደለም!» አለ። ሰው ይመስላል አልኩኝ ስሜቱን ልረዳ ፊቱን መረመርኩኝ ባ’ይኑ እየገረፈኝ አይምሰልህ! አለኝ ግንባሩ ታጠፈ ጥርሶቹን ነከሰ ጠረጴዛ መታ፣ ቢራችን ፈሰሰ ልጠራርግ መጥታ -  ልጅት እያየችኝ በፊቷ ምልክት ምን ሆኗል? አለችኝ መዳፌን አሳየሁ፣ ከንፈሬን አስረዘምኩ እኔም ልክ እንደሷው በምልክት መለስኩ እሱ ግን ቀጠለ «ሰው አይደለም» ማለት «ሰው አይደለም!» አልኩኝ እኔም ተመቸሁት በቢራ ተራጨን በውስኪ ታጠብን ስሙን እያነሳን «ሰው አይደለም!» አልን። ልጅትም … [Read more...] about “ሰው አይደለም ! …” አለኝ

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

አባቱን ነገረኝ

June 22, 2016 08:22 am by Editor Leave a Comment

አባቱን ነገረኝ

በአባቱ ወንበር ላይ ሳሎን ተቀምጦ በባዶ ግድግዳ ተግ ብሎ አፋጦ የፊቱን ሁኔታ እየለዋወጠ ትካዜ ተጭኖት ቃላት እያማጠ ዓይኑን አጨንቁሮ እየመረመረኝ እንደዚህ እያለ አባቱን ነገረኝ አባቴ... አባባ ኤጭ! አለ ፊቱን አጨማዶ ሁሉን ነገር ጠልቷል ውስጡ ሆኗል ባዶ በምሬት ኮምትሯል ... በጥላቻ በግኗል ... አስሬ ኤጭ! ይላል አባባ ኤጭ! አለ እንደገና ደግሞ በሳሎኑ መሀል ተገትሮ ቆሞ እንደገና ደግሞ ቁጭ አለ አንገት ደፋ ካፍጫው አወጣ እምቅ አየር ተፋ ኤጭ! አለ እንደገና ተነሳና ቆመ ሽቅብ አንጋጠጠ ጣሪያው ላይ ቆዘመ የአባባን ንዴት ይቺን አላውቃትም ከወትሮው ተለየች ብዙ አልወደድኳትም አባባ አሳዘነኝ አዝኜም ፈራሁት ምን ሆንክ? አይባልም በንዲህ ያለ ንዴት አባባ ዓይኑ ቀላ ስሩ ተገተረ በአንድ ጊዜ አረጀ ሀያ ዓመት ጨመረ እንደዛ … [Read more...] about አባቱን ነገረኝ

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

አማኒ ኢብራሂም — “ያልታወቀው” የጥበብ ሰው!

June 20, 2016 05:26 am by Editor 1 Comment

አማኒ ኢብራሂም — “ያልታወቀው” የጥበብ ሰው!

“... ሰው እያለ አጠገባችን፣ ቅንነቱን ማየት ሲያመን ከኛው አብሮ በህይወት ቆሞ፣ መልካም ስሙን መጥራት ሲያንቀን፣ “ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይነሳም” እንላለን። እንዲህ እያልን፣ ስንቱን ጠቢብ እየሸኘን፤ አበባውን ቀጥፈን ጥለን፣ አበባ እናስቀምጣለን!!” መቼም ያለ-ግጥም ፍቅር መኖር የሚሆንልኝ አይመስለኝም። ዛሬ ግን ብዕሬን ያነሳሁት ግጥም ለመጻፍ ባለመሆኑ፣ እነሆ ! የነብይ መኮንን የሆነችውን ይህቺን ግጥም፣ ለተነሳሁለት የጽሁፍ ጭብጥ እንደ መግቢያ ሆና ታግዘኝ ዘንድ ተዋስኩ። ገጣሚ ነብይ መኮንን ይህቺን የቁጭት ስሜት አስተናጋጅ የሆነች ግጥም በመታሰቢያነት ያበረከተው፣ ለእውቁ ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ነው። ያ! ድንቅ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊና ገጣሚ ደግሞ በመጨረሻው የህይወት ዘመኑ፣ በስደት ባክኖ፣ በሰቀቀን ተጀቡኖ ያለፈው በአሜሪካ—ኦክላሆማ ግዛት ውስጥ … [Read more...] about አማኒ ኢብራሂም — “ያልታወቀው” የጥበብ ሰው!

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

አስርቱ አምባገነናዊ ትዛዛት!

June 14, 2016 04:17 am by Editor 2 Comments

አስርቱ አምባገነናዊ ትዛዛት!

"እኔ ስላንተ በበረሐ ደሜን አፍስሻለሁና ከእኔና ከአጋሮቼ በቀር ሌላ የፖለቲካ ፖርቲ በቃልህ አትስበክ በልብህም አትመን"፤ "መንግስት የኛ ናትና ወደ መንግስት አትመልከት ስልጣኑንም አትመኝ"፤ "የባለስልጣናትን ጥፋት ... የዜግነት መብቱንም በሶሻል ሚዲያ የተቸ እሱ ወዮለት፤ የባለስልጣን ሚስትም ቅምጥም ሃብትም የማይነኩ፤ የማይደፈሩ "ቅዱስ" ናቸውና ትንፍሽ እንዳትል!! ...." "ከደርግ ጨካኝ አገዛዝ አውጥቼሃለሁና... በፍፁም ልብህ በፍፁም ሃሳብህ ለእኔ ብቻ ተገዛ"፤ "ብሰርቅም፤ ባስርም፤ ብገድልም እንዳለየ እለፍ ... መብራት ቢጠፋ፤ ውሃ ቢቋረጥ ... አርፈህ ተቀመጥ"፤ "እኔ ልማታዊ መንግስትህ በስራዬ ፍፁም የማልሳሳት ነኝና በማስተዳድራት አገር ለሚደርስ ጥፋት ሁሉ የኤርትራን መንግስት ርገም"፤ "ከእኔ አርማ በስተቀር በሰማይ ይሁን በምድር እንዲሁም … [Read more...] about አስርቱ አምባገነናዊ ትዛዛት!

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

ስለቴክኖሎጂ ሊያነጋግር የከጀለ መጽሀፍ

June 1, 2016 02:34 am by Editor Leave a Comment

ስለቴክኖሎጂ ሊያነጋግር የከጀለ መጽሀፍ

የዛሬዋ ዓለማችን በደረሰችበት የእድገት ደረጃ ስልጣኔን ወይም ብልጽግናን ከቴክኖሎጂ ለይቶ ማየት ያስቸግራል። የሰለጠነ ህብረተሰብ ማለት ቴክኖሎጂን ያዳበረ ህብረተሰብ ማለት ነው። ባንጻሩም ቴክኖሎጂን ያላዳበረ ህብረተሰብ ማለት ደግሞ ያልበለጸገ ህብረተሰብ ነው። የሰለጠነ ህብረተሰብ ስንል ደግሞ ድኅነት የተረታበት፤ በሽታ የመነመንበት፤ ትምህርት የተስፋፋበት (እውቀት የለመለመበት)፤ ዲሞክራሲ የሰፈነበት፤ የመገናኛና ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በስፋት የተንሰራፋበትና ህግ የበላይ የሆነበት ህብረተሰብ ማለታችን ነው። ቴክኖሎጂ እላይ ለተጠቀሱት ለሰው ልጆች አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አዎንታዊ የሆነ ቀጥተኛ አስተዋጽኦ አለው። ይሄን ሲይደርግ ግን ቴክኖሎጂ ከህብረተሰብ ውጪ ሆኖ በታዓምር ወይም ትእዛዝ በመስጠት ሳይሆን በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች የሚተገብሩት፤ ሌሎች የህብረተሰብ … [Read more...] about ስለቴክኖሎጂ ሊያነጋግር የከጀለ መጽሀፍ

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

ልዩ ጥበብ ገንባ

May 25, 2016 12:53 am by Editor Leave a Comment

ልዩ ጥበብ ገንባ

ፍቅር ታሞ ከርሞ አልጋ ላይ እንደሰው ብዙ ዘመን ሆነ ሞቶ ከቀበርነው ይሄ ሆኖ እያለ ሞቱን እያወቅን ለአያሌ ዓመታት ዘፋኞች በዘፈን አሁንም እንዳለ ህይወት እስትንፋሱ ጨርሶ እንዳልሞተ እንዳልወጣች ነፍሱ አድርገው ሲዘፍኑ ሲያቀብሉን ውሸት ነገሩን ዋጥ አድርገን አብረን ጨፈርንበት ከሁሉ ‘ሚገርመው የሚደንቀው ነገር አለ የሚባለው የአሁን ዘመን ፍቅር ገንዘብን ውሃልክ አ’ርጎ ተመስርቶ በዓይናችን እያየን መካካዱ ከፍቶ ዘፋኙ ተነስቶ ሲለን ፍቅር ፍቅር በሆታ በስክስታ የኛ አብሮ ማጫፈር ከ «እማትበላ ወፍ»«እዘበናኝ» ድረስ ሆዴ አንጀቴ እያለ ተሸክሞ እንደ ውርስ ወጣቱም ያንኑ ሲያማስል ሲያቁላላ ስለከረመበት ሳይቀይር በሌላ ያወጣው ሙዚቃ ሳይሰማ ጣፍጦ ዘፈኑ ይሞታል ዘፋኙ ተቀምጦ ይህ ሁሉ ሲሰራ ይህ ሁሉ ሲፈጠር እስከዛሬ ቆየን ምንም … [Read more...] about ልዩ ጥበብ ገንባ

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

እግርና ጫማ

May 17, 2016 05:53 am by Editor Leave a Comment

እግርና ጫማ

እግርና ጫማ ተጣብቀው አንድ ላይ በክር ተሳስረው አብረው ውለው ስታይ እውነት አይምሰልህ ያ ሁሉ ፍቅራቸው ሲመሽ ወደማታ ሄደህ ብታያቸው በአንሶላ መካከል እግር ተዘርግቶ ጫማ በራፉ ላይ ወድቋል አፉን ከፍቶ! … [Read more...] about እግርና ጫማ

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

ማዕረግ እንስጣቸው!

April 27, 2016 06:52 am by Editor 4 Comments

ማዕረግ እንስጣቸው!

ሰው በሕይወት ሳለ መቼም ማድነቅ አንወድ ማሻሻል አለብን ይሄን ነገር የግድ እኚህ ጠንካራ ሰው ፕሮፌሠር መስፍን ለራሳቸው ቢሆን የለፉት እስካሁን ሀብት ከሥልጣን ጋር በእጃቸው ጨብጠው በታዩ ነበረ ከሁሉ ሰው በልጠው ነገር ግን እኚህ ሰው ለሀገር ሲለፉ ምንም ሳይኖራቸው ዕድሜአቸውን ገፉ ሆኖም እንደሳቸው ከህሊናው አድሮ መኖር ክብር አለው እየበሉ ሽሮ ጥንትም ሆነ አሁን በተሳሳተ ሀገር መቼም ድኖ አያውቅም አዋቂ ከችግር ገዢን የማይፈሩት በዕድሜ ዘመናቸው እኮ ለምንድነው ብለውም ቢሏችሁ ህሊናው የጸዳ ያልፈጸመ በደል እስከዛሬ ድረስ መቼ ፈርቶ ያውቃል ብላችሁ መልሱ ይሄን ተናገሩ ሌላ ምንም አይደል አትጠራጠሩ እኚህን ታላቅ ሰው እንያዛቸው በወግ በዕድሜ ዘመናቸው ክብርን አንንፈግ የሳቸው ብቸኛ … [Read more...] about ማዕረግ እንስጣቸው!

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ለንቅልፍህ አትሳሳ

April 21, 2016 01:49 am by Editor Leave a Comment

ለንቅልፍህ አትሳሳ

የእንቅልፍ ምቀኛ (ከዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ) እወራረዳለሁ በአንድ ሚሊዮን ብር ሸለብ ሲያደርግህ ነው ስልክህ የሚል ቅርርር! ሚያዝያ 9፣ 2008 ዓ.ም. (አፕሪል 17፣ 2016 እ.ኤ.አ.)፤ ምንጭ፡- ፌስቡክ ምላሽ ለዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ለንቅልፍህ አትሳሳ ወለላዬ ይከሰታል አዎን! ልክ ነህ ዶክተሬ የት ይጠፋል ብለህ የሚል ፍቅሬ ፍቅሬ ደግሞም ትክክል ነው እንዳተ ለሚጽፍ በዚህ በአሁን ጊዜ ምን ይሠራል እንቅልፍ ላገራችን ችግር ስላለው አበሳ ካልተጻፈ በቀር በፍቅሬ ቶሎሳ ማን ይመጣል ብለህ ሁሉም እኮ አለቁ ካገሪቷ ጠፉ በሞት ተነጠቁ ቢቻልማ ኖሮ እነሱን መቀስቀስ እንኳን ስልክ ማጮህ ባናወጥነው በተኩስ ቢነሳማ ኖሮ ስልክ በማንጫረር በአሉን በጠራን ከዋጠችው ምድር ባስነሳነው ነበር ፀጋዬን … [Read more...] about ለንቅልፍህ አትሳሳ

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳፩

February 25, 2016 03:14 am by Editor 1 Comment

እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳፩

ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሃያ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ በጌምድርና - ሰላሌን በመግዛት ጠቅላይ አዛዥ ሆነው - በጣሊያን ጦርነት በተንቤን ግንባር - ላይ ሌሎች የመሩ ልዑል (ራስ) ካሣ ኃይሉ - እኚህ ሰው ነበሩ ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳፩” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡ ጥያቄ ብዙዎች ነበሩን - እጅግ ጀግና ሰዎች የህዝብ … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳፩

Filed Under: Who is This Person Tagged With: Left Column

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 7
  • Page 8
  • Page 9
  • Page 10
  • Page 11
  • …
  • Page 27
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule