“… ሰው እያለ አጠገባችን፣
ቅንነቱን ማየት ሲያመን
ከኛው አብሮ በህይወት ቆሞ፣
መልካም ስሙን መጥራት ሲያንቀን፣
“ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይነሳም” እንላለን።
እንዲህ እያልን፣
ስንቱን ጠቢብ እየሸኘን፤
አበባውን ቀጥፈን ጥለን፣ አበባ እናስቀምጣለን!!”
መቼም ያለ-ግጥም ፍቅር መኖር የሚሆንልኝ አይመስለኝም። ዛሬ ግን ብዕሬን ያነሳሁት ግጥም ለመጻፍ ባለመሆኑ፣ እነሆ ! የነብይ መኮንን የሆነችውን ይህቺን ግጥም፣ ለተነሳሁለት የጽሁፍ ጭብጥ እንደ መግቢያ ሆና ታግዘኝ ዘንድ ተዋስኩ። ገጣሚ ነብይ መኮንን ይህቺን የቁጭት ስሜት አስተናጋጅ የሆነች ግጥም በመታሰቢያነት ያበረከተው፣ ለእውቁ ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ነው። ያ! ድንቅ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊና ገጣሚ ደግሞ በመጨረሻው የህይወት ዘመኑ፣ በስደት ባክኖ፣ በሰቀቀን ተጀቡኖ ያለፈው በአሜሪካ—ኦክላሆማ ግዛት ውስጥ ነው። (ነገርን ነገር ሲያነሳው፣ በጎረቤት ቴክሳስ ግዛት በኖርኩባቸው ጊዜያት፣ በኦክላሆማ የአብስትራክት ስዕል ሊቁ አጽም ያረፈበትን ቦታ ለማየት እንደጓጓሁ ሳይሳካልኝ ቀርቷል።) ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።
eunetu says
ምድራችን መቼ ለወገናቸው ጥቅም ተወልደው የሚኖሩና የኖሩ መልካም፣ ቅንና በሳል ሰዎች አጥታ ታውቃለች???
እኛው መልሰን በወሬና ባሉባልታ ጀምረን በመግደል አፈር ስለጫንባቸውና ስለምንጭንባቸው እንጂ!!!
ምሳሌ ካስፈለገ:
1) አለቃ ታዬ በቤተ ክህነትና በመንግሥት ጡንቻ
2) ደቂቀ እስጢፋኖስ በዘርአያእቆብ ተጨፈጨፉ ወዘተ
እውነቱ