የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ቅደሚ!” በይፋ (officially) ለህዝብ የተበሰረውና በ“አብዮት አደባባይ” የተዘመረው ልክ የዛሬ 40 አመት ቅዳሜ መስከረም 2 ቀን 1968 ዓ.ም ነበር! በርካታ የቀድሞ ተማሪዎቼና ወዳጆቼ በተገናኘን ቁጥር “የምንወደው መዝሙር ግጥም እየተዘነጋን ነውና እባክህ ባመቸህ መንገድ እንደገና አውጣው” እያሉ ሲጠይቁኝና እኔም ቃል ስገባ ብዙ ጊዜ ሆነን። 40ኛ አመቱን ምክንያት በማድረግ ለታሪክ ማስታወሻ እንዲሆን እነሆ ግጥሙን በትህትና እያቀረብሁ፤ መዝሙሩ ብዙ ውጣ ውረድ ታሪክ ስላለው ወደፊት በሰፊው ይገለፃል። ፨ ፨ ፨ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ በኅብረሰባዊነት አብቢ ለምልሚ! ቃል ኪዳን ገብተዋል ጀግኖች ልጆችሽ ወንዞች ተራሮችሽ ድንግል መሬትሽ ለኢትዮጵያ … [Read more...] about “ኢትዮጵያ ቅደሚ!”
Literature
ጽፈኪን
መልካም አዲስ ዓመት!
የታሪክ አምድ ነባራዊ፣ ምድረ-ህይወት ፍልስፍና፣ መውጣት መውረድ፣ የዓለም ህግ፣ የተፈጥሮ ገጽ ሆነና፣ ጊዜ ክፉ፣ ጊዜ ደጉ..፣ እጥፍ-ዘርጋ፣ ዘመም-ቀና..፣ አንዴ ጽልመት..፣ አንዴ ብርሃን..፣ ባለታሪክ፣ ባለዝና፤ ስትወድቂ..፣ ስትነሺ..፣ በዘመናት ጉዞሽ ሂደት፣ ለዚህ ደረስሽ፤ እልልልል! ሁለት ሺ ሰባት ዓመት! (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about መልካም አዲስ ዓመት!
ጤፍ እንኳን ባቅሟ!
ትንሿ የ'ሕል ዘር፤ ዐይን እንኳ ብትገባ የማትቆረቁር፤ ድንገት ጠብ ብትል የማትገኝ ከምድር፤ ቁልቁል አሾልቃ በንቀት እያየች፤ በድሃው ወገኔ ከት ብላ ሳቀች! ........ እጅጉን አሾፈች:: አሹቅህን አውልቅ - ሽንብራህን ቆርጥም፤ ባቄላህን ጠርጥር - በቆሎህን ከርትም፤ እኔን ካሁን ወዲያ እንኳን ልትበላኝ፤ ድንገት በመንገድ ላይ ባይንህም አታየኝ፤ እያለች አፌዘች፤ በወገኔ ሳቀች !.......... በወገኔ አሾፈች !! አረም እንዳይውጣት - ወፎች እንዳይለቅሟት፤ ካቡን ዙሪያ ክቦ - ከብቶች እንዳይበሏት፤ አጭዶና ከምሮ - በሬዎች ለጉሞ፤ ሲወቃ እንዳልዋለ - ቀኑን ሙሉ ቆሞ_ _ _፤ በመንሽ አበጥሮ - በቁና ለክቶ፤ በሰፌድ አንፍሶ - በስልቻ ከቶ፤ ነቀዝ እንዳይበላት - ብርድ እንዳያጠቃት፤ ወቅቶ በጎተራ - እንዳላስቀመጣት_ _ _፤ አንተ አትቀምሰኝም! … [Read more...] about ጤፍ እንኳን ባቅሟ!
ትረገም ሆነብኝ!!
ልጇ ነፍሰ ገዳይ - ስለሆነ እርጉም እሱን የወለደች - እናቱ ትረገም ብለው ሲናገሩ እያሉ ሲያወሩ ... አትረገም ብዬ - ልጽፍ አሰብኩና ትረገም ሆነብኝ - “አ” እረሳሁና! … [Read more...] about ትረገም ሆነብኝ!!
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፱
ከአዘጋጆቹ፤ የጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ “እኚህ ሰው ማናቸው?” በሚል ዓምድ ሥር ለአገራቸው የለፉና የደከሙ ኢትዮጵያውያንን እንዲነሱ፣ እንዲወደሱ፣ እንዲከበሩ፣ … በማድረግ ግሩም ሥራ ሲሰሩ መቆየታቸውን ባለፈው ጠቅሰን ነበር፡፡ እርሳቸው ባለባቸው በርካታ ኃላፊነቶች ለተወሰኑ ጊዜያት ሳይመቻቸው ቢቀርም አሁንም ግን “እኒህ ሰው ማናቸው” ዓምድ በልባቸው ነው ያለው፡፡ በመሆኑም ሰሞኑን ከቀድሞ ፎቶዎች መካከል የሆነውን ይህንን በመላክ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን የካቢኔ አባላት የነበሩትን በቁጥር በማድረግ እነማን እንደሆኑ እንደተለመደው ቢቻል በግጥም አንባቢያን በማቅረብ እንዲሳተፉ በግጥም ጥሪ አድርገዋል፡፡ በጃንሆይ ዘመን የካቢኔ አባላት በመሆን ሰርተዋል እኒህ የሚታዩት እስቲ እነማናቸው ግለጹ በዝርዝር በፎቷቸው አንጻር በተሰጠው ቁጥር፡፡ … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፱
ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ
ለረጅም አመታት፣ ለብዙ ዘመናት፣ ፓርቲ ሲጠልዘኝ፣ መንግስት ሲረግጠኝ፣ ፖሊስ ሲነርተኝ፣ ሕጉ ሳይደግፈኝ፣ ዳኛው ቢፈርድብኝ፣ በቡድን ተካፍለው፣ በስም ተሸንሽነው፣ የሚጠልዟት ኳስ፣ የሚነርቷት ኳስ፣ ምትለጋዋ ኳስ፣ እኔ ራሴን መስላኝ፣ ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ። … [Read more...] about ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ
… አልሞት አለኝ
በስራው ላይ ልፈላሰፍ ቅኔ ልቀኝ ግጥም ልጽፍ ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ የማደንቀው ሰው ነበረኝ ሳይሞትማ ሳይቀበር ስሙን ማንሳት እሱን ማክበር መስሎ ታይቶኝ ልምድን መስበር የማደንቀው ሰው እያለኝ ልጽፍለት ተቸገርኩኝ አቤት! ዕውቀት አይ! ቁመና ብልህ ደፋር ቆራጥ ጀግና ሀይማኖቱን አጠንካሪ ደግ ለጋስ ሰው አክባሪ ብዬ ልለው ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ ታሞ እያየሁ ዛሬ ቢያጣ ዛሬ ቢርበው በቁም ሆኖ ከምረዳው ከማከብረው ከማደንቀው እደርሳለሁ ሲሞትልኝ ከምድር በታች ሲውልልኝ ያንጊዜ ነው ስሙ ገኖ የሚነሳው እሱን ሆኖ የብዕር ጫፍ የሚመዘዝ እንባ የሚረጭ የሚተከዝ ሚጻፍለት ሚደነቀው ታሪክ ገኖ ሚነበበው ገንዘብ ከኪስ ሚመዘዘው ለሟች በድን አካሉ ነው ያን አይቼ ልምድ አብቶኝ የቆየ ወግ አንቆ ይዞኝ የማደንቀው ሰው … [Read more...] about … አልሞት አለኝ
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፰
ከአዘጋጆቹ፤ ወዳጃችን ወለላዬ “እኚህ ሰው ማናቸው?” በሚል ዓምድ ሥር ለአገራቸው የለፉና የደከሙ ኢትዮጵያውያንን እንዲነሱ፣ እንዲወደሱ፣ እንዲከበሩ፣ ... በማድረግ ግሩም ሥራ ሲሰሩ ቆይተው ባለፈው ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት እናንተ አንባቢያን ታሪካቸው መነሳት አለበት የምትሉትን ከፎቶ ጋር እንድታቀርቡ ጥሪ አድርገው ነበር፡፡ የአገራችን ታሪክ በሚያስደነገጥ ፍጥነት እየወደመ ባለበት በአሁኑ ወቅት በህይወት ያሉትንም ሆነ የሌሉትን አንስተን ማወደስ ተገቢ ተግባር ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ልንሳተፍበት የሚገባ አገራዊ ጥሪ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ትኩረታችን እና ኃይላችንን የሚወስደው ነገር አንድ ብቻ መሆን የለበትም ምክንያቱም እየደረሰብን ያለው ጥቃት ከበርካታ አአቅጣጫ ነውና፡፡ ስለዚህ አሁንም ይህንን ዓምድ በከፈትንበት መልኩ ሥራቸውና ታሪካቸው እንዲነሳ የምትፈልጉት ሰው ካለ ፎቶውንና … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፰
የኢሕአዴግ ቁልቁለት
“ፋክት” መፅሔት ላይ ቋሚ አምደኛ በመሆን በየሳምንቱ በወቅታዊ ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ዙሪያ የሚያተኩሩ ፅሁፎችን ወደ አንባቢ ሲያደርስ የነበረው ሙሉዓለም ገ/መድኅን አዲስ መጽሐፍ ለኅትመት አብቅቷል፡፡ የመፅሃፉ ርዕስ፡- የኢሕአዴግ ቁልቁለት ደራሲ ፡- ሙሉዓለም ገ/መድህን የገፅ ብዛት፡- 235 ዋጋ ለአገር ውስጥ፡- 52 ብር ለውጪ አገር፡- 20 ዶላር አጠቃላይ ይዘት መፅሃፉ በአራት ክፍሎች እና በአስራ አራት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን፣ ክፍል አንድ ላይ “ቁልቁለቱን በኢሕአዴግ ጎዳና” በሚል አምስት ምዕራፎች ተካተዋል፡፡ በዚህ ክፍል ብሶት ወለደኝ የሚለው ህወሓት ተነሳሁለት የሚለውን የትግል ዓላማ እንዴት እየቀለበሰው እንደመጣ በዝርዝር ያስቃኛል፣ በመስመር መሀል ከጫካ ጀምሮ የህወሓት የፖለቲካ አሽከር ስለሆነው ኢህዴን/ብአዴን ፖለቲካዊ ክሽፈት ያነሳል፣ ለቁጥር ብቻ … [Read more...] about የኢሕአዴግ ቁልቁለት
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፯
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፮” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ ስድስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ መልስና አዲስ በታሪክ መዛግብት መጀመሪያ ምዕራፍ ስራ ታሪካቸው ምንም ሳይዛነፍ የተጻፈላቸው የሚነሱ ሁሌ እኚህ ስው ነበሩ ሸዋረገድ ገድሌ ሸዋረገድ ገድሌ ቆፍጣናዋ አርበኛ የተባሉ ናቸው የጦር ጥበበኛ ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፯” ደግሞ ወለላዬ ሃሳባቸውን ቀይረው አንባቢያንን ለማሳተፍ እንዲረዳ ከቀደምት ታሪካችን እስካሁን ያልተጠቀሱ ነገር ግን እናንተ አንባቢያን መታወቅ ይገባቸዋል የምትሉትን … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፯










