ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፮” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ ስድስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
መልስ
መልስና አዲስ
ስራ ታሪካቸው ምንም ሳይዛነፍ
የተጻፈላቸው የሚነሱ ሁሌ
እኚህ ስው ነበሩ ሸዋረገድ ገድሌ
ሸዋረገድ ገድሌ ቆፍጣናዋ አርበኛ
የተባሉ ናቸው የጦር ጥበበኛ
ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፯” ደግሞ ወለላዬ ሃሳባቸውን ቀይረው አንባቢያንን ለማሳተፍ እንዲረዳ ከቀደምት ታሪካችን እስካሁን ያልተጠቀሱ ነገር ግን እናንተ አንባቢያን መታወቅ ይገባቸዋል የምትሉትን ከፎቶና ታሪክ ጋር እንድትጠቁሙ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን ለዝግጅት ክፍላችን በኢሜል (editor@goolgule.com) ወይም በፌስቡክ ገጻችን በኩል እንድትልኩልን ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ “የኋላው ከሌለ የፊቱ” የሚሄድበት አይታወቅምና ይህንን በዚህ የመሳተፍ የሁላችንም ሃላፊነት ይሁን፡፡
ጥያቄ
ታዋቂ የነበር በስራው የጎላ
አስታዋሽ በማጣት አሁን የተጉላላ
አጥቶ የሚሰቃይ ያን ሁሉ መአረግ
ተረስቶ የቀረ አንድ ብቻ አይደለም
እስቲ ምታውቁት አስታውቁን እናንተም
ምስልም ያላችሁ የዛ ሰው ገጽታ
እንወቅ አሳዩን ቀርቦ በዚህ ቦታ
ማወቁ ይጠቅማል አያመጣም ጉዳት
እንችልም ይሆናል ባቅማችን ለመርዳት
የዛሬው ማናቸው ጥያቄና ምስል
እንደዚህ ተደርጎ ወደ አንባቢ ዞሯል
chalatumsa says
ለሃገር የሠሩ ለወገናቸዉ የጠቀሙ የታሪክ ሰዎችን እንዲታወሱ ማድረግ የሚበረታታ ተግባር ነዉ፡፡