
ከአዘጋጆቹ፤
ወዳጃችን ወለላዬ “እኚህ ሰው ማናቸው?” በሚል ዓምድ ሥር ለአገራቸው የለፉና የደከሙ ኢትዮጵያውያንን እንዲነሱ፣ እንዲወደሱ፣ እንዲከበሩ፣ … በማድረግ ግሩም ሥራ ሲሰሩ ቆይተው ባለፈው ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት እናንተ አንባቢያን ታሪካቸው መነሳት አለበት የምትሉትን ከፎቶ ጋር እንድታቀርቡ ጥሪ አድርገው ነበር፡፡
የአገራችን ታሪክ በሚያስደነገጥ ፍጥነት እየወደመ ባለበት በአሁኑ ወቅት በህይወት ያሉትንም ሆነ የሌሉትን አንስተን ማወደስ ተገቢ ተግባር ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ልንሳተፍበት የሚገባ አገራዊ ጥሪ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ትኩረታችን እና ኃይላችንን የሚወስደው ነገር አንድ ብቻ መሆን የለበትም ምክንያቱም እየደረሰብን ያለው ጥቃት ከበርካታ አአቅጣጫ ነውና፡፡
ስለዚህ አሁንም ይህንን ዓምድ በከፈትንበት መልኩ ሥራቸውና ታሪካቸው እንዲነሳ የምትፈልጉት ሰው ካለ ፎቶውንና ታሪኩን በግጥማዊ ጥያቄ የማቅረቡ ጊዜ ያላለፈ በመሆኑ አንባቢዎቻችንን አሁንም እንድታስቡበት እንወዳለን፡፡ በግጥም ማቅረብ የማትችሉም ከሆነ ፎቶውንና አጭር የሕይወት ታሪክ ከላካችሁልን መላ እንፈልግለታለን፡፡ በዚህ አድራሻ ይላኩልን (editor@goolgule.com)፡፡
ይህንን ዓምድ ለጀመሩትና እስካሁንም ሳይሰለቹ የቀጠሉትን ወዳጃችንን ወለላዬን ከልብ እናመሰግናቸዋለን፡፡ እኛ በሥራ መብዛትና በሌሎች ጉዳዮች እንኳን የላኩልንን አዘግይተን ብናትምም እንኳን ተስፋ ሳይቆርጡ በዚሁ መቀጠላቸው ሊታወቅና ሊመሰገኑበት የሚገባ ነው፡፡ ማን ያውቃል ወደፊት “እኚህ ሰው ማናቸው?” ብለን የርሳቸውንም ሥራ እናወድሳቸው ይሆናል?
“የኋላው ከሌለ የፊቱ” የሚሄድበት አይታወቅምና ይህንን በዚህ መሳተፍ የሁላችንም ሃላፊነት ይሁን፡፡
ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፰” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
ጥያቄ
መቼም ሀገራችን በያንዳንዱ ዘመን
አላጣችም ጀግና ደጀኗ የሚሆን
እኚህ የሚታዩት ለናት ሀገራችው
ዳር ድንበር መከበር የተዋጉ ናቸው
በሉ ተናገሩ ማነው የሚባሉት
በምን ይገለጻል የሳቸው ጀግንነት
Welelaye please tell us who is he?
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአፓርታይዱ የትግራይ ቡድን እራሱን ነፃ ማውጣት
ሚደረገው ትግል ማንኛችንም ትዮጵያውያን በሚችለው አቅምና በተለያዩ
መንገዶች ለራሱ ነፃነት ሲልመታገል እንዳለበትና ካለፈው ስርዓት
ት/ርት መውሰድ የሚታገለው ለራሱና ለቤተሰቡ እንዲሁም ለአዲሲቷ
ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጽያ መሆኑን አምኖ ከሕብረቱጋር መታገል አለበት
እላለሁኝ።