ሰው በሕይወት ሳለ መቼም ማድነቅ አንወድ
ማሻሻል አለብን ይሄን ነገር የግድ
እኚህ ጠንካራ ሰው ፕሮፌሠር መስፍን
ለራሳቸው ቢሆን የለፉት እስካሁን
ሀብት ከሥልጣን ጋር በእጃቸው ጨብጠው
በታዩ ነበረ ከሁሉ ሰው በልጠው
ነገር ግን እኚህ ሰው ለሀገር ሲለፉ
ሆኖም እንደሳቸው ከህሊናው አድሮ
መኖር ክብር አለው እየበሉ ሽሮ
ጥንትም ሆነ አሁን በተሳሳተ ሀገር
መቼም ድኖ አያውቅም አዋቂ ከችግር
ገዢን የማይፈሩት በዕድሜ ዘመናቸው
እኮ ለምንድነው ብለውም ቢሏችሁ
ህሊናው የጸዳ ያልፈጸመ በደል
እስከዛሬ ድረስ መቼ ፈርቶ ያውቃል
ብላችሁ መልሱ ይሄን ተናገሩ
ሌላ ምንም አይደል አትጠራጠሩ
እኚህን ታላቅ ሰው እንያዛቸው በወግ
በዕድሜ ዘመናቸው ክብርን አንንፈግ
የሳቸው ብቸኛ ህዝብ ነው ሿሚያቸው
ማዕረጋቸው ላይ ማዕረግ እንስጣቸው
******
ለፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም 86ኛ የልደት በዓል መታሰቢያ የተጻፈ
eunetu says
ወለላዬ እኔም ተስማምቻለሁ፤
በጎ ሃሳብሽን እጋራለሁ፤
ለእኒህ ሰው ጤናን እመኛለሁ፤
የማያልፍ ሥራ ላገር ሲሠሩ አይቻለሁ፤
አጨራረሳቸው እንዲያምር አጥብቄ እጸልያለሁ፤
መሀሪው ጌታም ይሰማኛል ብዬ አምናለሁ፤
በእውነት አሜን በይ እኔ ከልብ ብያለሁ።
በዘመናቸው ለራሳቸው ያልኖሩ፤
ላገር ለወገን ብቻ ሲጮሁ የኖሩ፤
እንደ እኔ እንኳን ጎጆ ለመቀለስ ያልሞከሩ፤
አቅቷቸው ሳይሆን ቅድሚያ በመስጠት ላገር ለምድሩ፤
የከበረ ሰው ነኝ በል/ሉ በማለት ሁሉም ሲሮጥ ወደ ዘር ማንዘሩ፤
ነው!ናቸው እንበል ዛሬ፣ ነገን ጠብቀን ከማለት ነበሩ፤
ስለዚ ዛሬውኑ ተስማምተን መልካም ስም እናውጣላቸውና ይክበሩ፤
ሰው የዘራውን ያጭዳል እንደሚል ቃሉ፤
እኔ ግን ቀድሜ ብያቸዋለሁ፣
ያለመጽሀፍ ቅዱስ ወንጌል ሰባኪ!!!
እውነቱ ነኝ
koster says
We should respect and appreciate all those who are voice for the voiceless Ethiopians when they are alive.
eunetu says
Golgule?????
I can not understand why you are waiting for my comment to post????
Eunetu
ሸመልስይማም says
ኢትዮጵያሀገሬምኝነሽተላላየምተልሽቀርቶየገደለሸበላ
ተብላል::
ሸመልስከደሴ