ሁሉም የፌዴራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሥርዓትን ሊጠቀሙ ነው በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ሁሉም የፌዴራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሥርዓትን ይጠቀማሉ ሲል የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ የባለሥልጣኑ የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሲስተም ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ታደሰ ከበደ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ በሲስተሙ ከ25 በላይ የሚሆኑ ጫረታዎች ወጥተዋል፡፡ በቀጣይ ሁለት ዓመታት የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ ይሰራል፡፡ በቀጣይ ሥርዓቱን ወደ ክልሎች በማውረድ ይሰራል ያሉት አቶ ታደሰ፤ በ2015ና 2016 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ጨረታዎችን የሚያወጡትና ግዥዎችን የሚያከናውኑት ሲስተሙን በመጠቀም ይሆናል ብለዋል፡፡ በዚህም እንደ አገር ያለውን … [Read more...] about ከመንግሥት ግዢ ጋር በተያያዘ የሚፈጸመው ሌብነት ሊታነቅ ነው
corruption
በሙስና ተመዝብሮ በአገር ውስጥና በውጭ 130 ቢሊዮን ብር ተደብቆ እንደሚገኝ ተጠቆመ
መንግሥት በተለያዩ ሁኔታዎች በሙስና ወንጀል የተመዘበሩ ሀብቶችን ለማስመለስ ጥረት እያደረገ ቢሆንም፣ እስካሁን በተደረገ ጥናት በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ተደብቆ የሚገኝ ከ130 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት እንዳለ ተጠቆመ። የአመራር ለውጥ ከተደረገ ከሁለት ዓመታት ወዲህ ሙስናን ለመዋጋት መንግሥት የአገሪቱ ተቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየተንቀሳቀሰ፣ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትም በተወሰነ ሁኔታ እየቀነሰና አጋር መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍና ተነሳሽነት የጨመረ ቢሆንም፣ በአገሪቱ ያለውን አለመረጋጋት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ የሙስና ወንጀል በተደራጀ መልኩ እየተፈጸመ መሆኑም ተገልጿል። ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ በተደራጀ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተነገረው፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢሊሌ ሆቴል ለሁለት ቀናት … [Read more...] about በሙስና ተመዝብሮ በአገር ውስጥና በውጭ 130 ቢሊዮን ብር ተደብቆ እንደሚገኝ ተጠቆመ
በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን
በሌብነት የተጠረጠሩት በረከት ስምኦንና ታደሰ ካሣ አርብ በባህር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በዕለቱ ሁለቱም ግለሰቦች ያሉባቸውን ችግሮች ያስረዱ ሲሆን በተለይ በረከት ስምዖን በእስርቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲል ማማረሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ኮምፒውተር ያስፈልገናልም ብለዋል። በዕለቱ የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ባለፈው በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ማስረጃዎችን ማየቱንና የምስክሮችን ቃል መቀበሉን አሳውቋል። ሆኖም ጉዳዩ ከባድ፣ ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ምስክሮች እና ሰነዶች በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መገኘታቸውን አስታውሶ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። በወቅቱ የቀረበውን ማራዘሚያ ቀን በረከት የተቃወመ ሲሆን ያቀረበው ምክንያትም የሕግ ሥልጣን በሌለው አካል መከሰሰሱን ነው። ይህ ሕጋዊነት … [Read more...] about በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን
“የጥላቻና የምቀኝነት አስተሳሰብ መገረዝ አለበት፤ አደገኛ በሽታ ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የአስፈጻሚውን አካል የሥራ ክንውን በተመለከተ ያቀረቡት ሪፖርትና ለጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ። ሙሉውን ለመመልከት የቪዲዮው ምስል ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about “የጥላቻና የምቀኝነት አስተሳሰብ መገረዝ አለበት፤ አደገኛ በሽታ ነው”
የሳዑዲው አልጋወራሽ ሞተዋል? ወይስ በህይወት አሉ? ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አላሙዲንን “ያስፈቱት” ማንን አነጋግረው ነው?
በሙስና ወንጀል በሚል በርካታ የሳዑዲ ባለሃብቶችን ዘብጥያ የጣሉት የዙፋን ተስፈኛው የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን በሳዑዲ ሚዲያ ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል። በአንዳንዶች ግምት በቤተመንግሥት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል ይባላል። አልጋወራሹ በህይወት ከሌሉ ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አህመድ አላሙዲንን “አስፈትተው” የመጡት ማንን አነጋግረው ነው የሚል ጥያቄ ተነስቷል። የሳዑዲ መንግሥት አልጋወራሹ በሥራቸው ላይ እንዳሉ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል። የሳዑዲ የዙፋን ተስፈኛ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን 11 ልዑላንን እና 38 የመንግሥት ባለሥልጣናትን (የቀድሞውን ጨምሮ) እንዲሁም የንግድ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን፤ ደላላ (ተጠሪ ወይም front man) ባለሃብት እንደሆነ የሚነገርለት በግማሽ ኢትዮጵያዊ የሆነው ሞሐመድ አላሙዲ (አል-አሙዲ) በቁጥጥር ሥር ከዋሉት … [Read more...] about የሳዑዲው አልጋወራሽ ሞተዋል? ወይስ በህይወት አሉ? ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አላሙዲንን “ያስፈቱት” ማንን አነጋግረው ነው?