• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሙስና ተመዝብሮ በአገር ውስጥና በውጭ 130 ቢሊዮን ብር ተደብቆ እንደሚገኝ ተጠቆመ

September 29, 2020 09:39 pm by Editor Leave a Comment

መንግሥት በተለያዩ ሁኔታዎች በሙስና ወንጀል የተመዘበሩ ሀብቶችን ለማስመለስ ጥረት እያደረገ ቢሆንም፣ እስካሁን በተደረገ ጥናት በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ተደብቆ የሚገኝ ከ130 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት እንዳለ ተጠቆመ።

የአመራር ለውጥ ከተደረገ ከሁለት ዓመታት ወዲህ ሙስናን ለመዋጋት መንግሥት የአገሪቱ ተቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየተንቀሳቀሰ፣ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትም በተወሰነ ሁኔታ እየቀነሰና አጋር መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍና ተነሳሽነት የጨመረ ቢሆንም፣ በአገሪቱ ያለውን አለመረጋጋት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ የሙስና ወንጀል በተደራጀ መልኩ እየተፈጸመ መሆኑም ተገልጿል።

ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ በተደራጀ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተነገረው፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢሊሌ ሆቴል ለሁለት ቀናት ባዘጋጀው የጋራ የውይይት መክፈቻ መድረክ ላይ ነው።

በተቋሙ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዘለዓለም ፈቃዱ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሐሳብ ላይ እንደገለጹት፣ ሙስናን ከመዋጋት አንፃር መንግሥት ተቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሠራበት ነው። የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትም በተወሰነ መልኩ የመቀነስ አዝማሚያ አለው፣ አጋር መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፋቸውና ተነሳሽነታቸው ጨምሯል። ምንም እንኳን እንዲህ ዓይነት ተግባራት ያሉ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ ያለውን አለመረጋጋት በመጠቀም የሙስና ሁኔታ በተደራጀ መልኩ እየተፈጸመ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከመሬት ወረራ፣ ከባንክ ገንዘብ ማጭበርበር፣ ሐሰተኛ ሰነዶችን ከመጠቀምና ሕገወጥ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ከማቅረብ ጋር በተያያዘ፣ የሙስና ወንጀሎች በስፋት እየጨመሩ መምጣታቸውን ምክትል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ባለፈው ዓመት የተከሰተው ዓለም አቀፍ የኮሮና ወረርሽኝ ለሙስና ወንጀል ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። ሙስና በግሉ ዘርፍም (Private Sector Corruption) ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንም ተናግረዋል።

በሙስና ወንጀል የተመዘበረ ሀብትን ከማስመለስ አንፃር ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም፣ በወንጀሉ የተገኘውን በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ተደብቆ የሚገኝን ከ130 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ማስመለስ አለመቻሉንም ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በ2012 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥቱን የፀረ ሙስና ሕጎችን ከማስፈጸምና መፈጸማቸውን ከመከታተል አንፃር የሠራውን እንዳብራሩት፣ የሙስና ወንጀል ምርመራን አስጀምሯል። ይመራልም። በሙስና ወንጀል የክስ መዛግብትን በሚመለከት 582 መዛግብት ለዓቃቤ ሕግ ቀርበው በ400ዎቹ ላይ ምርመራና ድጋፍ ክትትል ማድረጉንና 466 መዛግብት ውሳኔ ማግኘታቸውን አብራርተዋል።

በ2012 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ የተመዘበረ ሀብት ማስመለስ መቻሉን፣ በተለያዩ ወንጀሎች የተመዘበሩ ሀብቶችን የሚያስመልስ ዳይሬክቶሬት በማቋቋም፣ በአገር ውስጥ የተደበቁና ወደ ውጭ አገሮች የሸሹ ሀብቶችን በተመለከተ የማጥናት (Tracing) እና አገሪቱን የመለየት ሥራ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል።  

በበጀት ዓመቱ ከመንግሥትና ከግል ባንኮች ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የተወሰደባቸው ከ40 በላይ የክስ መዛግብት ወደ ፍርድ ቤት ቀርበው በክርክር ላይ መሆናቸውን፣ በርካታ ሚሊዮን ብሮች እንዲታገዱና የውርስ አቤቱታ እንዲቀርብባቸው መደረጉን፣ ከሜቴክና ከሌሎች ትልልቅ የሙስና ወንጀሎች ጋር በተያያዘም ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የያዙ የክስ መዝገቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ክርክር መደረጉን ምክትል ዳይሬክተሩ አብራርተዋል። በመደበኛ መዝገቦች ላይ የአፈጻጸም ክፍተት ቢኖርም፣ በትልልቅ መዝገቦች ላይ ግን የተሻለ ውሳኔና የችሎት ክርክር አፈጻጸም መመዝገቡን አክሏል።

ምክትል ዳይሬክተሩ ስለቀጣይ አሥር ዓመታት ዕቅድ አፈጻጸምና በ2013 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ እንዳብራሩት፣ በማስረጃ አለመሟላት ምክንያት በርካታ የተከማቸ መዛግብት ላይ ማስረጃዎችን በማሟላት ውሳኔ እንደሚያሰጡ፣ ‹‹ለምርመራ›› በሚል ተመላሽ የተደረጉ መዛግብትን ከመከታተል ባለፈ፣ በከባድና ውስብስብ ወንጀሎች ምርመራ ላይ በቀጥታ እንደሚሳተፉ ማቀዳቸውን አስረድተዋል።

ከፍተኛ የሕዝብና የመንግሥት ጥቅም ያላቸው ትልልቅ የሙስና ወንጀል ጉዳዮችን ከምርመራ ጀምሮ ቅድሚያና ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሠሩ፣ በዋና ኦዲተር የኦዲት ሥራ የተሠራባቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በተያያዘ ያልተወራረደ ሒሳብ እንዲወራረድና በሕግ የመጠቀም ተግባር በስፋት እንደሚከናወን መታቀዱን ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ዳይሬክቶሬቱ የተለያዩ ተግዳሮቶች እንደገጠሙት የጠቆሙ ምክትል ዳይሬክተሩ፣ ማስረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በተገቢው ፍጥነት ለማግኘት አለመቻሉ፣ በማስረጃዎች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን፣ አግባብነት የሌላቸው ማስረጃዎችን መስጠት፣ ሙስና የሚፈጸምባቸው ተቋማት ቢኖሩም የሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት አለማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

የኦዲት ሥራ የሚሠሩ አካላት በመደበኛነት ከሚሠሩ ኦዲት ውጪ ከወንጀል ምርመራ ጋር የተያያዙ ኦዲቶችን በአፋጣኝ ሠርቶ ለመላክ ውስንነት እንዳለባቸው ጠቁመው፣ ጥፋተኛውን በግልጽ ከማሳየት አንፃር ጉድለት እንደሚታይባቸውና በሠሩት ኦዲት ላይ ምስክርነት ሲጠየቁ ፈቃደኛ ለመሆን ተግዳሮቶች እየገጠማቸው መሆኑንም አስረድተዋል።

ሚዲዎችም ሙስናን ከማጋለጥ አንፃር ያላቸው ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑን፣ የሙስና ወንጀል ጉዳዮችን በወቅቱ ለሕዝብ ከማሳወቅ አንፃር ችግሮች መኖራቸውንም ምክትል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። በፋይናንስ ተቋማትና ሌሎች ተቋማትም በርካታ ተግዳሮቶች መኖራቸውንና በተለይም በግሉ ዘርፍ ከሚፈጸም ሙስና ጋር በተያያዘ ምርመራ የሚያደርግ አካል አለመኖሩን አሳውቀዋል።

የአስተዳደር አካላት፣ የልማት ድርጅቶች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የፍትሕ አካላት፣ ዋና ኦዲተር፣ ሚዲያና ኅብረተሰቡ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ግንኙነት ችግር እንዳለበት ጠቁመው፣ በመንግሥትም ሆነ በግሉ ዘርፍ የሚፈጸም ሙስናን በማጋለጥ ረገድ ተባብሮ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኦዲት ተቋማት የተረጋገጡ ጥፋቶችን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ አንፃር አስፈጻሚ ተቋማት ላይ ተፅዕኖ መፍጠር፣ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ደግሞ ከበደል ጋር በተያያዘ በትብብር መሥራት፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሥነ ምግባር ትምህርቶችን አጠናቅሮ በመስጠትና ሚዲዎችም የምርመራ ጋዜጠኝነት ሥራ በማናወን ሙስናን እንዲያጋልጡ ጥሪ አቅርበዋል። (ታምሩ ጽጌ፤ ሪፖርተር)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Law, News, Right Column Tagged With: corruption, new birr notes, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
Copyright © 2026 · Goolgule