• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሳዑዲው አልጋወራሽ ሞተዋል? ወይስ በህይወት አሉ? ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አላሙዲንን “ያስፈቱት” ማንን አነጋግረው ነው?

June 1, 2018 11:47 am by Editor 3 Comments

በሙስና ወንጀል በሚል በርካታ የሳዑዲ ባለሃብቶችን ዘብጥያ የጣሉት የዙፋን ተስፈኛው የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን በሳዑዲ ሚዲያ ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል። በአንዳንዶች ግምት በቤተመንግሥት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል ይባላል። አልጋወራሹ በህይወት ከሌሉ ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አህመድ አላሙዲንን “አስፈትተው” የመጡት ማንን አነጋግረው ነው የሚል ጥያቄ ተነስቷል። የሳዑዲ መንግሥት አልጋወራሹ በሥራቸው ላይ እንዳሉ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል።

የሳዑዲ የዙፋን ተስፈኛ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን 11 ልዑላንን እና 38 የመንግሥት ባለሥልጣናትን (የቀድሞውን ጨምሮ) እንዲሁም የንግድ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን፤ ደላላ (ተጠሪ ወይም front man) ባለሃብት እንደሆነ የሚነገርለት በግማሽ ኢትዮጵያዊ የሆነው ሞሐመድ አላሙዲ (አል-አሙዲ) በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል መሆኑን በኅዳር ወር ጎልጉል አረጋግጦ መዘገቡ ይታወሳል።

ይህ “በሳዑዲ አረቢያ ታሪክ ተፈጽሞ አያውቅም” ተብሎ የሚነገርለትን የጸረ ሙስና ዘመቻ የሚያካሂደው ኮሚቴ “ማንኛውንም የማሰር፣ የመያዝ፣ ወዘተ ሥልጣን” እንደተሰጠውና ይህንንም በኃላፊነት የሚመሩት አልጋወራሹ መሆናቸውን አስመልክተው ንጉሥ ሳልማን በሳዑዲ ቲቪ ላይ እንደተናገሩት፤ “የሕዝብን ገንዘብ በነካ፣ በመዘበረ፣ ወይም እንዳይሰረቅ ባልተከላከለ ወይም ሥልጣኑን ተጠቅሞ (ይህንን ዓይነት ተግባር በፈጸመ) በማንኛውም ግለሰብ ላይ ሕጉ በጽናት ተግባራዊ ይደረጋል። ይህ የሚፈጸመው በትልልቆቹም ሆነ በትንንሾቹም ላይ ይሆናል፤ ማንንም አንፈራም” ማለታቸውን የጎልጉል ዘገባ በወቅቱ ትንታኔ የሰጠበት ነበር።

በዚህ ዓይነት ከፍተኛ ሥልጣንና ተስፋ የፊት መሪ የተደረጉት አልጋወራሽ ሳልማን ከኤፕሪል 21 ወዲህ በሳዑዲ ሚዲያ ፈጽሞ ያልታዩ መሆናቸውን በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የሚዲያ ዘገባዎች ሰሞኑን ጠቅሰዋል። ይህንንም ተከትሎ የምዕራቡ የዜና ዘገባዎች ሁልጊዜ የሚዲያውን ትኩረት የሚሹት አልጋወራሽ ለሕዝብ ሳይታዩ የመቆየታቸውን ሁኔታ በማንሳት ሲዘግቡ ሰንብተዋል።

ከሳዑዲ አረቢያ ጋር በጠላትነት የምትተያየው ኢራን ግን አልጋወራሹ በቤተመንግሥት አካባቢ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ቆስለዋል ወይም ሞተዋል በማለት በርግጠኝነት ትናገራለች። የጸረ ሙስናውን ዘመቻ እና የአገሪቱን ሥልጣን ለብቻቸው ጠቅልለው በመያዛቸው በሳዑድ ቤተሰብ በተከፈተው ጠላትነትና የሥልጣን ሽኩቻ ኤፕሪል 21 ቀን ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ እንደነበር የኢራን ጋዜጣ ዘገባ ያመለክታል።

ካይሃን የተባለው የኢራን ጋዜጣ የስለላና የመረጃ ምንጮች ዘገባ ጠቅሶ እንደሚለው ከሆነ በተኩስ ልውውጡ ወቅት አልጋወራሹ “ቢያንስ በሁለት ጥይት ተመትተዋል፤ በዚህም ሳቢያ ሞተዋል” ይላል። በመቀጠልም አልጋወራሹ በህይወት ካሉ ለምን የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ በሳዑዲ ጉብኝት ሲያደርጉ ከአልጋወራሹ ጋር የተነሱት ፎቶ ይፋ አልተደረገም በማለት ይጠይቃል።

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ግን ይህንን አቋም በግልጽ ይቃወማል። አልጋወራሹ በህይወት እንዳሉና መንግሥታዊ ሥራቸውንም በሥርኣት እያከናወኑ መሆናቸውን ይናገራል። ለዚህም የተለያዩ ፎቶዎችንና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በዋቢነት ያቀርባል። ሆኖም የትኞቹም ምስሎች ቀን የሌላቸው ከመሆናቸው በላይ በየትኛውም ምንጭ ማረጋገጥ እንዳልቻለ ሲኤንኤን ዘግቧል።

በኤፕሪል 21 የተካሄደውን የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ የሳዑዲ መንግሥት ተኩስ አልተሰማም በማለት አይክድም። ሁኔታው የተከሰተው ለመዝናኛ የሚውል ሰው አልባ በራሪ (ድሮን) ሳይፈቀድለት በቤተመንግሥቱ ሰማይ ሲበር በመታየቱ ያንን ለማክሸፍ የተወሰደ እርምጃ ነው በማለት ያስተባብላል።

አልጋወራሹ ከፊፋው ፕሬዚዳንት ጋር (ፎቶ፤ አረብ ኒውስ ፋይል)

የምዕራብ ዜና ወኪሎች በተለይም ሲኤንኤን የአልጋወራሹን በህይወት አለመኖር አጽንዖት ሰጥቶ ከዘገበ የተወሰኑ ሰዓታት በኋላ የሳዑዲ መንግሥት መቼ እንደተከሰተ የማይታወቅ አልጋወራሹ የንግድ ልማት ስብሰባ ሲመሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል። የሳዑዲ መንግሥት ስብሰባው ከሁለት ቀን በፊት የተካሄደ ነው ቢልም ሲኤንኤን ግን ስብሰባው በቅርቡ ወይም ከኤፕሪል 21 በኋላ ለመቀረጹ ማረጋግጥ አልቻልኩም ብሏል።  ከዚህ በተጨማሪም የሳዑዲ መንግሥት አልጋወራሹ  የየመኑን ፕሬዚዳንት ሲቀበሉ የሚያሳይ ተጨማሪ ቪዲዮ ለቋል። በሌላ በኩል አልጋወራሹ የፊፋውን ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ባለፈው አርብ አነጋግረዋል በማለት አረብ ኒውስ ቢዘግብም የተጠቀመው ፎቶ ግን ከፋይል ክምችቱ እንደሆነ አልካደም።

አልጋወራሹ በህይወት አሉ፤ ይህ የሳዑዲና የምዕራቡ ዓለም ጠላት የሆነችው ኢራን አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ነው የሚሉ የአሜሪካና የአውሮፓ የፖለቲካ ተንታኞች ልዑሉ ከጸረ ሙስናው ዘመቻ ጋር በተያያዘ ምናልባት በብዛት በሚዲያ ሲታዩ ስለነበሩ አሁን ለመቀነስ የወሰዱት እርምጃ ነው ይላሉ። ይህንንም እንደሽፋን አድርጋ ኢራን በሳዑዲ አለመረጋጋት መኖሩን በመጠቆም የራሷን የፖለቲካ ፍላጎት ለማሟላት እየተጠቀመችበት ነው ሲሉ ይሟገታሉ።

ከጸረሙስናው ጋር በተያያዘ አላሙዲንን ለውርደትና በሌብነት ክስ ለእስራት የዳረጉት አልጋወራሽ በህይወት ከሌሉ ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አህመድ ባለፈው ወደ ሳዑዲ በሄዱ ጊዜ በርግጥ አልጋወራሹን አግኝተዋቸዋል የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነው። በኢትዮጵያ ህወሓት/ኢህአዴግ የሚቆጣጠራቸው የሚዲያ ውጤቶች ጠ/ሚ/ሩ ከአልጋወራሹ ጋር መገናኘታቸውን በስፋት ቢዘግቡም ያሳዩት ቪዲዮም ሆነ ፎቶ ግን አልነበረም።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ጠ/ሚ/ሩ ከሳዑዲ እንደተመለሱ በፍጥነት በሚሊኒየም አዳራሽ በመገኘት በሌብነትና ዝርፊያ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለውን አላሙዲንን ለማስፈታት ስምምነት ላይ መደረሱን ለተሰብሳቢው ይፋ አደረጉ። ከመስመርም አለፍ ብለው አላሙዲንን በተዋቡ ቃላት አሞካሹት፣ አወደሱት፣ አመሰገኑት። ምንም እንኳን በወቅቱ ጠ/ሚ/ር ዓቢይ በአገራችን ሕግ በተገቢው አላሙዲንን እንጠይቃለን ቢሉም ትርፍ የሄዱበት መንገድ ሳዑዲ ሄደው ያከናወኗቸው ሌሎች ተግባራት የበለጠ ሚዛን በመድፋታቸው እንጂ ስለ አላሙዲን የተናገሩት ኢትዮጵውያን አሳዝኗል፤ አስቆጥቷል።

ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንደሚሉት በርግጥ አልጋወራሹ በህይወት ከሌሉ የአላሙዲን “ተፈትተዋል” መባል፤ “ከተፈቱም ወደ አገር ሳይመጡ መቅረታቸው” ከዚህ ውስብስብ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምክንያት ሊሆን ይችላል ይላሉ።

ለበርካታ ዓመታት ግብር ባለመክፈል፣ እጅግ ሰፋፊ የመሬት ይዞታዎችን (በተለይ ከኦሮሚያ)  አጥሮ ያለ ሥራ በማስቀመጥ፣ እስካሁን ያልተከፈለ ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር በመውሰድ፣ ወዘተ በርካታ ጥያቄዎች የሚቀርብበት አላሙዲ ወደ አገር እንዲመጣ የተፈለገው ከዚህ ጋር በተያያዘ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ።

ከእነዚህ ያልተወራዱ ሒሳቦች በተጨማሪ የአላሙዲ ሚድሮክ በስሙ የያዛቸውና ኢትዮጵያ ከዓለምአቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ ዋስትና የገባችባቸው፣ ያልተጠናቀቁ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ይገኛሉ። የእነዚህንም ሒሳብ ማወራረድ የፌዴራሉ ብቻ ሳይሆን የኦሮሚያም ከፍተኛ ፍላጎት ነው ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች።

ስለዚህ ይህንን ጉዳይ በቶሎ ወደፍጻሜ በማድረስ በሚድሮክ ሥር የሚገኙትን ሃምሳ ሺህ ሠራተኞች ኅልውና መታደግ ያልተፈለገ ችግር ከመግባት የሚያድን ነው የሚሉ ወገኖች፤ ሁኔታዎች ከፈቀዱም በሕጋዊ መልኩ ንብረቶቹን እስከመውረስ ለመሄድ እንዲቻል በጠ/ሚ/ሩ ቀጥተኛ ተሳትፎ አላሙዲንን ለማስፈታት የተፈለገው ለዚህ ነው የሚለው አስተያየት በርካታዎችን የሚያሳምን ነው።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ የአልጋወራሹ በህይወት መኖርም ሆነ አለመኖር በተጨባጭ አልተረጋገጠም።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Filed Under: News Tagged With: abiy, alamoudi, corruption, crown prince salman, Ethiopia, Full Width Top, Middle Column, saudi arabia

Reader Interactions

Comments

  1. እዝራ says

    June 2, 2018 01:28 am at 1:28 am

    ጎልጉሎች በጣም ነው የማደነቃችሁ።
    ሁሌም ውኃ ያልነካው ጮማ ዜና ይዛችሁ ስለምትመጡ በጣም ነው የማደንቃችሁ፡የማከበራችሁ።
    ፕሮፌሽናል ጋዜጠኞች ናችሁ። በርቱ

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    June 2, 2018 11:48 pm at 11:48 pm

    ጎልጉሎች!! በጣም ነው የናቅኋችሁ!!

    Reply
  3. Belhu says

    June 4, 2018 10:08 am at 10:08 am

    Always hate.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule