ህወሃት የሚጠላውን ነገር ሁሉ “አማራ ነህ” ይለዋል። ዶ/ር ዐቢይ ኦሮሞ እንደሆነ ስለማያውቁ ሳይሆን የጠሉትን ሁሉ አማራ ብለው መጥራት ስለሚፈልጉ ነው። ይኸውም ለነሱ አማራ ማለት ጠላት ማለት ነው። “በነገራችን ላይ ነፍጠኛና ትምክህተኛ ማለት ለአማራ ህዝብ የሰጡት የብዕር ስም ነው”። አማራ ጠላት ነው የሚለውን ትርክት ይዘህ ስታያቸው ቃላቶቹ አንድን ህዝብ ለማጥፋት የተሰሩ እንደሆኑ ይገባሀል። ... ህወሃት ማለትኮ አገር እየመራ አገራዊ ተቃርኖዎችን የሚተነትን አስማተኛ ድርጅት ነው። የትም ዓለም አገር እየመራ አገሪቱን የሚመራበት አካሄድ ትክክል ባለመሆኑ ሊፈርስ ይችል ይሆናል እንጂ መሪው አገር እንድትፈርስ የሠራ የለም - ከህወሃት ውጭ። አሁንም አይደለም ከግብጽ ህውሃት ከየትኛውም ኃይል ይሁን ኢትዮጵያን የሚያጠፋለት ከሆነ አይተባበርም ማለት ሃሰት ነው።... ሙስጠፌ … [Read more...] about “… በዓለም እስካሁን ብቸኛው በጣም የሚጠላትን አገር የመራ ፓርቲ ህወሃት ብቻ ነው” ሙስጠፌ ዑመር
Politics
አወዛጋቢው የሽመልስ አብዲሳ ሙሉ ንግግር ትርጉም
ኢህአዴግ የተሰራው ለህወሃት ነውና የተሰራበት ምክንያት ደግሞ ስልጣን ላይ ለመቆየት ነው። እኛም ብልፅግናን የሰራነው ከስልጣን ለመውረድ አይደለም። ብልፅግና ደግሞ ወደዳችሁም ጠላችሁም የኛ ነው። እኛ ነን የሰራነው። ለእኛ እንደሚሆነን አድርገን። በተመሳሳይ መንገድ ህወሃት ኢህአዴግ እንዲመቸው አድርጎ ነበር የሰራው። ኢህአዴግ ገና ሲፈጠር የቀድሞዎቹ የኦህዴድ መስራች ሰዎች ለመታገል ሞክረዋል። ግን አልቻሉም። ያልቻሉበት ምክንያት ደግሞ ጠብመንጃ ስለሌላቸው፣ ሀይል ስለሌላቸው ነበር። ኢህአዴግ ሳይመሰረት በፊት አሁን የምናወራውን ነገር አንስተው ነበር። አሁን ዶ/ር ቢቂላ ያነሳውን ነገር ሁሉ አንስተው ነበር። እነ ኢብራሂም መልካ ተገምግመው የተባረሩት በዚህ ነው። ስለ ውክልና እና ስለ ፍትሃዊነት ስለ ጠየቁ። ግን majorityን minority የሚያደርጉበት instrument ስለሆነ፤ … [Read more...] about አወዛጋቢው የሽመልስ አብዲሳ ሙሉ ንግግር ትርጉም
“በትግራይ ያለውን የወጣቶች እንቅስቃሴ ሕዝቡ … መደገፍ ይኖርበታል” ዶ/ር አብርሃም
ካልተወም በግፊት እንዲተው ማስገደድ ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ በትግራይ እያታየ ያለው የወጣቶች እንቅስቃሴ ህዝባዊ ዓላማ እስከአለው ድረስ ህዝቡ የእኔ ነው ብሎ መደገፍና ሥርዓት ይዘው እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ አስታወቁ። የህወሀት ጥገኛ ቡድን እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት በተለይ ደግሞ የትግራይን ህዝብ የማይመጥን እንደሆነም አመለከቱ። ህዝቡ የወጣቶቹን እንቅስቃሴ ሊቀበልና ሊደግፍ እንደሚገባ ዶክተር አብርሃም ጠቅሰው፣ በትግራይ ያለው አፋኝ አገዛዝ ወይም ፓርቲ ወጣቶችን እንዳያሰቃያቸው ከለላ መሆን ያለበትም ህዝቡ መሆኑን አስገንዝበዋል። ለህዝብ ጥያቄ የተንቀሳቀሰ ወጣት ሲገደል እንዲሁም ለምን ተናገርክ ተብሎ ሲጨፈጨፍና ሲታሰር ካየ፤ ለህዝብ ብሎ … [Read more...] about “በትግራይ ያለውን የወጣቶች እንቅስቃሴ ሕዝቡ … መደገፍ ይኖርበታል” ዶ/ር አብርሃም
“የፌዴራል መንግሥት በትግራይ የሆነ ዕርምጃ እወስዳለሁ ካለ ራሱ ያደርገዋል”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት በፋና ቴሌቪዥን በትግርኛ ቋንቋ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። ከተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ለውጡና የትግራይ ክልል ሁኔታ፣ የድምፂ ወያነና የትግራይ ቴሌቪዥን መዘጋት፣ ምርጫን በተመለከተ፣ የኤርትራ ጉዳይና የፌዴራል መንግሥት ትግራይን ሊያጠቃ ነው ስለመባሉ ይገኙበታል። በማብራሪያቸው የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሚከተለው ተጠናቅረዋል። ለውጡና የትግራይ ክልል ሁኔታ “የትግራይ ሕዝብ የማይሳተፍበት ፖለቲካ በኢትዮጵያ ይኖራል የሚል እምነት የለኝም። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ በአሁኑ ወቅት ሦስት ችግሮች አሉ። እነዚህ ሦስት ችግሮችን በግልጽ መገንዘብ ያስፈልጋል። የመጀመርያው ችግር ከለውጥ ጋር የተያያዘ ነው። አገራችን ከለውጥ ጋር በተያያዘ ፈተና ውስጥ ነው … [Read more...] about “የፌዴራል መንግሥት በትግራይ የሆነ ዕርምጃ እወስዳለሁ ካለ ራሱ ያደርገዋል”
የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ማጣራት እና ስለ ታሳሪዎች አያያዝ
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን አሳዛኝ ግድያ ተከትሎ በተለይ በኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎችም አንዳንድ ቦታዎች የተከሰተውን መጠነ ሰፊ የጸጥታ ችግር ፣ የሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት በሚመለከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከመነሻው ጀምሮ በቅርብ መከታተሉን የቀጠለ ሲሆን፤ እስከ አሁን የተካሄዱትና በመካሄድ ላይ ያሉት ዋና ዋና ሥራዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡- 1. የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በፈጣን ምርመራ ማጣራትና መዘገብ ምንም እንኳን የደረሰውን አደጋ በተመለከተ በተወሰነ መጠን በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃንና ድርጅቶች እንዲሁም የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የተዘገበ ቢሆንም፤ ኢሰመኮ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የምርመራ ስልት ላይ የተመሰረተና በበቂ ማስረጃዎች የተደገፈ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አይነት በተገቢው መጠን የሚያጣራና የሚመዘግብ … [Read more...] about የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ማጣራት እና ስለ ታሳሪዎች አያያዝ
“ኦነግ ሸኔ የህወሓት መጠቀሚያ ዕቃ ነው” ታዬ ደንደኣ
የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ትልቁ ተግዳሮት የነበረው ኦነግ ሸኔ መሆኑን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ አስታወቁ። ህወሓት ኦነግ ሸኔን በአደባባይ እንደ ጠላት እየፈረጀ በተግባር ግን የኦሮሞን ትግል ለማክሰም እንደ መሣሪያ ይጠቀምበት እንደነበረም አመለከቱ። አቶ ታዬ ደንደኣ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ያካሄደው የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ፍሬያማ እንዳይሆን ኦነግ ሸኔ ከህወሃት ጋር የነበረው ከሕዝብ የተሰወረ ህብረት ዋንኛ ምክንያት ነው ብለዋል። ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ታጋዮች አንድ ወጥመድ ሆኖ ለህወሃት ሲያገለግል እንደነበርም አመልክተዋል። ብዙዎች ኦነግ ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ እያለው የዚህ ድርጅት ትግል ለምንድን ነው ወደፊት ገፍቶ የማይመጣው? የሚል ጥያቄ ነበራቸው። … [Read more...] about “ኦነግ ሸኔ የህወሓት መጠቀሚያ ዕቃ ነው” ታዬ ደንደኣ
ከውጭ ሃይል ጋር የሚሰሩ ፓርቲዎች ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል
ከውጭ ሃይል ጋር ተቀናጅተው የአገር ሉኣላዊነትንና አንድነትን ለመናድ የሚሰሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተለይተው በህግ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ። አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያነጋገራቸው አንዳንድ ፓርቲዎች እንደተናገሩት፤ መንግስት በቅርቡ በአገሪቱ ለተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት የሆኑና ከውጭ ሃይሎች ጋር የሚሰሩ ፓርቲዎች ስለመኖራቸው ከመግለፅ ባለፈ ድርጊቱ በሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ በመሆኑ በአገር ክህደት ወንጀል ተጠያቂ ሊያደርጋቸው ይገባል። የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንደተናገሩት፤ ማንኛውም በህጋዊ መንገድ ለመስራት የተመዘገበ ፓርቲ የአገሪቱን ህገ መንግስት አክብሮ የመስራት ግዴታ አለበት። የፖለቲካ ፓርቲ በመሆኑ ብቻ ከተጠያቂነት ሊያመልጥ … [Read more...] about ከውጭ ሃይል ጋር የሚሰሩ ፓርቲዎች ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል
ኦኤምኤን ሕጋዊ ክስ ተከፈተበት፤ ለጊዜውም ሊታገድ ይችላል
በአሜሪካ አገር በትርፍ አልባ ድርጅትነት የተቋቋመውና ለበርካታዎች ሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ተጠያቂ ነው የሚባለው ኦኤምኤን (የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ) ክስ ተመሥርቶበታል። ከሚዲያው ጋር ታደለ ኪታባ (የሚዲያው ሹም እንደመሆኑ)፤ እንዲሁም አያንቱ በከቾ በግል የክስ ተመሥርቶባቸዋል። ክሱን ያቀረቡት ጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ እንደሚሉት ይህ ፋይል የማስከፈት ዓይነት ተግባር ነው እንጂ በትክክል በዐቃቤ ሕግ ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ክስ አልተመሠረተባቸውም። የጉዳዩ ባቤት የሆኑት አቶ ጥበበ ሳሙኤል እንዲህ ይላሉ፤ ከበርካታ ሰዎች እና የሚድያ አውታሮች፤ 'OMN and its employees are Charged in District Court የሚል የዜና ዘገባ እየተራገበ መሆኑ እና እንዳብራራ ጥያቄ እየተጠየቅኩ ነው። በአጭሩ ለማብራራት "they are sued not … [Read more...] about ኦኤምኤን ሕጋዊ ክስ ተከፈተበት፤ ለጊዜውም ሊታገድ ይችላል
ህወሃት “የመጨረሻ” ያለው ሤራ መክሸፉን መቀበል አቅቶታል
መንግሥት ህወሃትን ቀስ በቀስ ሥሩን እየቆራረጠ ቢቆይም አብዛኞች ባለመረዳትና በተገዙ ኃይሎች ውዥንብር ዕድሜው ሊራዘም እንደቻለ ለህወሃት ቅርበት ያላቸው እየገለጹ ነው። በተቀነባበረ ዕቅድ ሃጫሉ እንዲገደል ተደርጎ መንግሥትን ለመገልበጥ የታቀደውና የመጨረሻ የተባለው ሤራ መክሸፉ ህወሃት መንደር ግራ መጋባት መፍጠሩ ተስምቷል። የዐቢይ አስተዳደር እንደሚባለው ደካማ እንዳልሆነም አንዳንዶቹ በይፋ ሲናገሩ ተደምጧል። ለውጡን ተክትሎ ከህወሃት አሰልቺ የስብሰባና የግምገማ (ምይይጥ) ባህል በተቃራኒው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፍጥነት መጓዛቸውና ለህወሃቶች ከጅምሩ የማሰቢያ ጊዜ የከለከለ ነበር። የጎልጉል ታማኝ የመረጃ ምንጭ እንደሚሉት፤ የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ሲነጋ ልክ እንደማንኛውም ተራ ዜጋ ከፍተኛና አዳዲስ ውሳኔዎችን ይሰማሉ። በዚህም እነርሱ ለአንዱ ጉዳይ አንድ ወር ሲሰበሰቡና … [Read more...] about ህወሃት “የመጨረሻ” ያለው ሤራ መክሸፉን መቀበል አቅቶታል
አርቲስት ሃጫሉ ለምን ተገደለ?
https://www.facebook.com/goolgule16/videos/856526528088415 … [Read more...] about አርቲስት ሃጫሉ ለምን ተገደለ?










