የቴዎድሮስ ክፍል ጦር ጥሪውን ተቀበለ በሕግ ወጥ መልኩ በዘመን ትህነግ በየክልሉ ተቋቁመው የነበሩና ልዩ ኃይሎች ፈርሰው ወደ መከላከያ ወይም ፖሊስ እንዲገቡ በተወሰነው መሠረት የቴዎድሮስ ክፍለ ጦር ጥሪውን ተቀበሎ ወደ ካምፕ ገብቷል። መንግሥት ያቀረበውን የልዩ ኃይል ሪፎርም ተቀብለው ሰላምን መርጠው ወደ ሕጋዊ መንገድ የመጡ የቴዎድሮስ ክፍለ-ጦር የልዩ ኃይል አባላትን የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ደማቅ አቀባበል አደርጎላቸዋል። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደ ቤተሰቦቻቸው ተንጠባጥበው ለተበተኑ የልዩ ኃይል አባላትም በፈለጉት ማለትም የክልል ወይም የፌደራል ፖሊስ ወይም የመከላከያ ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ዶ/ር ወንደሰን የተባለ ግለሰብ ከመስከረም አበራ ጋር ሲያወራ የተቀዳ ተብሎ በተሰራጨው የድምጽ ቅጂ ላይ እንደሚሰማው በጎንደር ያለውን ልዩ ኃይል … [Read more...] about ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ
Archives for May 2023
ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል
ኢትዮጵያ ማር ለማምረት የሚያስችል ያላትን ከፍተኛ ጸጋ በሚገባ እየተጠቀመች እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡ ሃገሪቱ በአመት 500 ሚሊዮን ቶን ማር የማምረት አቅም ቢኖራትም እያመረተች ያለችው ግን 10 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ሆኖ የምትመረተዋ አነስተኛ የማር ምርት በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ እየወጣች መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡ በተለያዩ የሃገሪቷ አካባቢዎች ገበሬዎች የሚያመርቱት የማር ምርት በትክክለኛው መንገድ ወደ ገበያ እየቀረበ ባለመሆኑ እና በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ ስለሚወጣ ሃገሪቷን ገቢ እያሳጣት ይገኛል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳሬክተር አቶ ታሪኩ ተካ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ደላሎች አዛዥ በሆኑበት የማር ምርት ሃገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል ብለዋል፡፡ የማር ምርት እና ግብይትን የሚመለከት … [Read more...] about ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል
ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ
በመንግሥትና በኦነግ ሸኔ ወይም ኦነግ መካከል ሲካሄድ የከረመው የመጀመሪያ ምዕራፍ የተባለ ንግግር መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሑሴን ቅድሚያ ወስደው ይፋ አድርገዋል። የጎልጉል ታማኝ የመረጃ አቀባዮች እንደሰሙት መንግሥት “አልቀበልም” ያለውና ያላስማማው ጉዳይ ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ ያቀረበው ጥያቄ ዋናው ነው። ከመንግሥት ተደራዳሪዎች በኩል ቃል በቃል ምን ምላሽ እንደተሰጠ ባይገልጹም ዜናውን ያቀበሉን እንዳሉት ከሆነ መንግሥትም ሆነ አቀራራቢዎቹ አካላት በዚህ ጉዳይ ላይ የያዙት አቋም ተመሳሳይ ሆኗል። ጥያቄው ሚዛን የሚደፋና አሁን ላይ ሊነሳ የማይችል እንደሆነ ቀደም ሲል የኦነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። የኦፌኮው ሊቀመንበር መረራ ጉዲና ገና ከጅምሩ ኦነግን በሚቃወሙት አፍላ ጊዜያቸው “ኦሮሞ … [Read more...] about ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ
መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ
ከ698,000 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Mereja TV’ የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ ከነገ ጀምሮ “በአማራ ክልል ለ10 ቀናት የሚቆይ ዘመቻ የኮቪድ ክትባት በሚል ምንነቱ ያልታወቀ ክትባት ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል” የሚል መረጃ ማሰራጨቱን ተመልክተናል። ገጹ በተጨማሪም ህብረተሰቡ ክትባቱን እንዳይወስድ የሚያሳስብ መልዕክት ማከሉን አስተውለናል። መረጃ ቲቪ የተባለው ይህ የፌስቡክ ገጽ ይህን ይበል እንጅ በአማራ ክልል እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ለ10 ቀናት ሊሰጥ ስለታቀደው ክትባት የአማራ ክልል ጤና ቢሮና የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ባለፉት ቀናት በተናጠል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ መስጠታቸውን ተመልክተናል። በመግለጫዎቹም የክትባቶቹ ምንነት የተገልጸ ሲሆን ዘመቻ አገር አቀፍ ስለመሆኑን ተብራርቷል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በትናትናው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ … [Read more...] about መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ