• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ

May 10, 2023 09:25 am by Editor 3 Comments

የቴዎድሮስ ክፍል ጦር ጥሪውን ተቀበለ

በሕግ ወጥ መልኩ በዘመን ትህነግ በየክልሉ ተቋቁመው የነበሩና ልዩ ኃይሎች ፈርሰው ወደ መከላከያ ወይም ፖሊስ እንዲገቡ በተወሰነው መሠረት የቴዎድሮስ ክፍለ ጦር ጥሪውን ተቀበሎ ወደ ካምፕ ገብቷል።

መንግሥት ያቀረበውን የልዩ ኃይል ሪፎርም ተቀብለው ሰላምን መርጠው ወደ ሕጋዊ መንገድ የመጡ የቴዎድሮስ ክፍለ-ጦር የልዩ ኃይል አባላትን የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ደማቅ አቀባበል አደርጎላቸዋል። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደ ቤተሰቦቻቸው ተንጠባጥበው ለተበተኑ የልዩ ኃይል አባላትም በፈለጉት ማለትም የክልል ወይም የፌደራል ፖሊስ ወይም የመከላከያ ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

ዶ/ር ወንደሰን የተባለ ግለሰብ ከመስከረም አበራ ጋር ሲያወራ የተቀዳ ተብሎ በተሰራጨው የድምጽ ቅጂ ላይ እንደሚሰማው በጎንደር ያለውን ልዩ ኃይል ለማስካድ የተሠራው ሥራ መክሸፉን የሚገልጽ ነበር። ሤራውን እምቢ ብለው ወደ ካምፕ የገቡትን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩትን በተመለከተ ለምን እንደገቡ መስከረም ለጠየቀችው ወንደሰን ሲናገር “እንጃባታቸው” በማለት ነበር የመለሰው።

ጎንደር የቅርቡን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ማርሽ በመቀየር በተደጋጋሚ ወሳኝ ሚና ስትጫወት ቆይታለች፤ ይህ ሦስተኛዋ ነው።

ከለውጡ በፊት የነበረውን ኦሮሙማ እንቅስቃሴ “የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው” በሚል ገልብጦ ለውጡን አገር አቀፍ ይዘት እንዲኖረው ማርሻ የቀየረው ጎንደር፣ የፖለቲካውን ትግል እንዲነድና የትህነግ/ህወሃት መጥፊያ እንዲቃረብ በማድረጉ ሲጠቀስ እንደሚኖር ያወሱ ወገኖች፣ የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በምላሹ “የአማራ ደም የኔም ደም ነው” ሲሉ የትግሉን አቅጣጫ በመቀበልና በማስተጋባት፣ በትህነግ የተፈራውን የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ የትግል አንድነትን በማግነን ታሪክ መሠራቱን ገልጸዋል።

ሁለተኛው የዛሬ ሁለት ዓመት በወለጋ እና በሌሎች አካባቢዎች ማንነትን መሠረት ያደረገ የጅምላ ጭፈጨፋ ሲካሄድ የአማራ ክልል በሰላማዊ ሰልፍ መናወጥ ጀመረ። የዚህ ነውጥ ፊት አውራሪ ግን ከጀርባ ሆኖ ይዘውረው የነበረው በደርግ ጊዜ በተከሰተው ድርቅ የረሃብተኛውን ብር ሰርቆ ከአገር በኮበለለው ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ነበር።

በሁሉም የአማራ ክልል ቦታዎች እየተቀጣጠለ ይሄዳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት እንቅስቃሴ ጎንደር ሲደርስ ተነፈሰ። ኦሮሞን ወንጅሎና በኦሮሞ ላይ ጽንፈኛ አቋም ይዞ ይወጣል የተባለው ጎንደር የችግሩን ምንጭ ነቅሶ አወጣው፤ እንቅስቃሴውም በረደ። 

በሰሜን ሸዋ በተለይ አጣዬ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ዘር የለየ ጭፍጨፋ በመቃወም አደባባይ የወጡት የጎንደር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች “የከዳን ኦህዴድ እንጂ ወንድም የኦሮሞ ሕዝብ አይደለም” የሚል መፈክር አጉልተው በማሳየት ያሳዩት ተቃውሞ በወቅቱ “ሥልጡን” ተብሏል። ጽንፈኛ አመለካከት ላላቸው ደግሞ ታላቅ መልዕክት እንደሆነ ነው የተጠቆመው።

አሁን ለሦስተኛ ጊዜ ልዩ ኃይሉን መከታ በማድረግ፣ በወልቃይት በማስፈራራት ወደ አመጽ እንዲገባ ሲዋከብ የነበረው በተለይ የጎንደር ልዩ ኃይል ሁኔታዎችን አመዛዝኖ በውስጥና በውጪ ኃይሎች የተደገሰውን ሤራ አክሽፏል። ከልዩ ኃይል ውስጥ በስመጥር እንደሆን የሚነገርለት የቴዎድሮስ ክፍለ ጦር የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ካምፕ ገብቷል። ጎንደርም ታሪክ በመሥራት ኢትዮጵያን እየታደገች ትቀጥላለች።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ 

Filed Under: Left Column, News Tagged With: gondar, operation dismantle tplf, Special Force

Reader Interactions

Comments

  1. ሥርጉተ says

    May 10, 2023 09:32 am at 9:32 am

    ነገ እዬለቀመ ልክ ያስገባልኛል። ያገኛታል ሁሉም። ነገእዬለቀመልክያስገባልኛል።ያገኛታልሁሉም።ምርኮኝኑ ት የአመውም የአበውም የለብንም። ይህን ውርዴ ዜና ብላችሁ ስትዘግቡት ይገርመኛል። የሆነ ሆኖ ፈቃደ እግዚአብሄርን የሚጠብቁ ውሳኔወች የእዮር ይሆናሉ ። እግዜብሄር ይስጥልግ። መረጃውን ስለምታጋሩኝ። የቴወድሮስ ከሚባል የአቶ ጋሻው መርሻ ቢባል ጥሩ ነው። ምርኮኝነት ለተጠዬፈ ገናና ሥም አይሆንምና ሥሙ።

    Reply
  2. Tesfa says

    May 10, 2023 10:11 am at 10:11 am

    ይህ ድሪቶ መሳይ ሃሳብ በየስፍራው ተለቅሞ የተሰፋ በመሆኑ አርዕስቱ ከውስጥ ይዘቱ ጋር ይላተማል። ሲጀመር ጤናማ እይታ ያለው ሰው ልዪ ሃይል የሚባለው በመፍረሱና ወደ ዋናው ሰራዊት ወይም ወደሚፈልጉበት የሥራ መስክ መሰማራታቸው ተገቢ እንጂ ኡኡ የሚያሰኝ ነገር የለውም። ችግሩ በኦሮሚያና በትግራይ ያለውን ግፍና መከራ ሳይገቱ ትጥቅ አውርድ ተበተኑ መባሉ አማራውን ለቅስፈት እንደማመቻችት ይቆጠራል። ልብ ላለው ዘመቻው መሆን የነበረበት ቤትና ንብረትን በሚያቃጥሉና በሚያፈርሱ፤ ከክልሌ ውጡልኝ እያሉ በኦሮሞ ህዝብ ስም ደም በሚያፈሱት ላይ በሆነ ነበር። የተጣረሰው የጠ/ሚሩ አመራር በጅቡቲ መስመር በየጊዜው የኦሮሞ ጽንፈኞችና ሌሎች ታጣቂዎች በመንገድ ሰው ማገት፤ መግደል፤ መኪናዎችን ማቃጠልና ዘረፋን እየፈጸሙ ዘመቻው አማራ ላይ መሆኑ የፓለቲካውን መሽመድመድ አጉልቶ ያሳያል። ይህ ሲባል አማራው ፋኖም ሆነ የክልል ሃይሉ ጉድለት የለባቸውም ለማለት አይደለም። በመሰረቱ ጠበንጃ የታጠቀ ሁሉ ለግፍ የተጠጋ ድርቡሽ ነው። በዚህም የተነሳ ታጣቂ ሃይሎችን ሁልጊዜ የማያቸው በጥርጣሬ አይን ነው።
    “ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ” – የቱ ላይ ነው ታሪክ የሰራው? ነፍሴ አውጭኝ እያለ ራሱን በመከላከሉ? መንገዶችንና ሱቆችን ዘግቶ በአማራ ህዝብ ላይ እየሆነ ያለው ደባ ልክ አይደለም ማለቱ ነው ታሪክ ሰሪ ያስባለው? ሂድና አዲስ አበባና ኦሮሞ ክልል እስር ቤቶች በእነማን እንደሞላ አይተህ ንገረን። መስከረም አበራ ጋር እንዲህ ያለ ሰው በስልክ ሲነጋገር ተቀድቶ ገለ መሌ መባሉም የብልጽግናው የፈጠራ ወሬ እንጂ ልብ ያለውና እንዲህ ያለ ፓለቲካ ውስጥ ያለ ሰው ነገርን በስልክ ይፈጽማል ብዬ አላስብም። ግን ጊዜ ባዘመነው ስልት እየተጠቀሙ ያለፈና የአሁን ንግግሮችን በማገጣጠምና በማስመሰል ሰዎችን መወንጀል እንደ ስልጣኔ ስለሚቆጥሩት ለእነዚህ ድርቡሾች እውነትን ማሳየት ከቶውንም አይቻልም። የሰከሩት በራሳቸው የፓለቲካ ቅኝት በመሆኑ ከእነርሱ እሳቤ ውጭ የሌላው ፉርሽ ነው። ህዝብን የሚያንገላቱት፤ የሚዘርፉት ለመኖር በመሆኑ የመኖሪያ ብልሃታቸው ሲያከትም አወዳደቃቸው እንደ ሮም ይሆናል።
    የጎንደር ህዝብ “የኦሮሞ ደም የእኛ ደም ነው” ያለው በአብሮ መኖር የሚያምን፤ ኢትዪጵያን የሚወድ በመሆኑ ነው። ከኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች የተሰፈረለት ግን የመከራ ክምር ነው። በወለጋ የአማራ ደም እንደ ጎርፍ ሲፈስ ማን ተው አለ? ማን እንታደጋቸው አለ? እርግጥ ነው ዛሬም ወደፊትም በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ እናውቅልሃለን የሚሉትን የጠበንጃ አንጋች መንጋን በመጋፈጥ ጥቂት አማራዎችን ሊያድን ቢሞክርም እድል ፈንታም አብሮ መገደል ሆኗል። እነዚህ አውሬዎች ናቸው በኦሮሞ ህዝብ ስም 50 ዓመት የነገድበትና አሁንም በስሙ ስልጣን ላይ ሆነው ከወገኑ ጋር እያቃቃሩ ደም እያቃቡት ያሉት። ታሪክ ያለፈ የህዝቦች ተግባር ስብስብ ነው። ታሪክ በአንድ ጀምበር አይሰራም። ታሪክ እንደ ጸሃፊውና እንደሚተረክለት ህዝብና ግለሰብ ይወሰናል። ታሪክ በባህሪው ሙሉዕ ሆኖ አያውቅም። ሲልለት ይለጠጣል፤ ያለሆነ ነገርን ፈጥሮ ያወራል፤ አልፎ ተርፎም የታሪኩን ዋና ተዋናኞች ከሥፍራው ባልነበሩ ሰዎች ተክቶ ይወሸክታል። ስለሆነም ሚዛናዊ የሆነ የታሪክ ስብስብ ለማቅረብ የታሪክ ተመራማሪዎች በብዙ ይቸገራሉ። ጎንደር የታሪክ ሃገር ነው። ይህም የሚታይ፤ የሚዳሰስ አልፎ ተርፎም የተዘከረው ሁሉ አስረግጦ ያሳያል። ለህልውናው ቆሞ ነፍሴ አውጭኝ፤ ድረሱልኝ የሚል ወገን ግን ገና ታሪክ አልሰራም። እንዲያውም ምድሪቱ በስርዓት አልበኞችና በኦነግ ታጣቂዎች እየታመሰች በሰላም ገብቶ መውጣት አዳጋች ሆነባት እንጂ። ያው የሩቅ አታኳሽ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ አያውቅምና ጎንደር ታሪክ ሰራች መባሉ ፌዝ እንጂ እውነትነት የለውም። ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ – ጸሃፊ በሥፍራው ሂዶ/ዳ ነገሮችን በራሱ/ሷ አይን ማየቱ እንዲህ ያለ የተወላገደና የተለጣጠፈ ጽሁፍ ባልተጻፈም ነበር። የምድሪቱ ችግር ከቀን ወደ ቀን እየባሰ፤ ፍትህ ያለቅጥ እየተወላገደ፤ በፈጠራ ትረካ የአማራ ህዝብ በየስፍራው እየተፈናቀለና እየተገደለ፤ መሪዎቹ በወረፋ በሴራ እየተገደሉና በፍርሃት ውስጥ እያሉ ጎንደር ታሪክ ሰራ ማለት ማፌዝ ነው። በቃኝ!

    Reply
  3. Abatabor says

    May 12, 2023 05:20 pm at 5:20 pm

    Trying to divide Amhara forces as presented in your statement is futile and provocative. Amhara is united than ever before and will never abandon its core principles, such as equality, peace and justice for all. The central point here is Abiy Ahmed’s scheme to eliminate Amhara might in his making of NEW ETHIOPIA. It is a pity that the PM doesn’t know the socio economic and political stand of that war faring nation. To remind him in simple terms, Amhara is as populous (or more) as Oromo and that cannot be ignored. If Abiy continues ruling this ancient country obnoxiously and carelessly, he will face catastrophic end like other irresponsible dictators.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule