ወርቅነህ ገበየሁ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን በህወሃት ተሹሟል። ይህ ከታማኝ ምንጭ የደረሰን መረጃ ነው። መረጃው እንደሚጠቁመው፤ እነ ዶ/ር ደብረጽዮን ሹመቱን ያጸደቁለት፤ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገና በስልጣን ላይ እንዳሉ ነበር። የህወሃት ሰዎች፤ "የኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ሃገሪቱ አሁን የገባችበትን አስከፊ ችግር ይፈታል" የሚል ቅኝት ይዘው ወደ ምዕራቡ አለም እንዲሰማሩም ተደርጓል። ከሀገሬው ሕዝብ ይልቅ የአሜሪካ እና የአውሮፓን ልብ መግዛት ከቻሉ ለተለመደው የበጀት ድጎማ ዋስትና ያገኛሉ። ሁሉም ወገኖች ሳይስማሙበት በሸፍጥ የተፈጸመው ይህን ሹመት ከአሜሪካ ባለስልጣናት ይሁንታ አግኝቷል ተብሏል። የአሜሪካ መንግስት ይህንን ሹመት ለመቀበል ሁለት ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ምክንያት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሮሞ ስለሆነ የተቀሰቀሰውን የቄሮ አመጽ ሊያስቆም ይችላል በሚል … [Read more...] about ወርቅነህ ገበየሁ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን ህወሃት ወስኗል
Archives for February 2018
የከረረው የአሜሪካና የህወሓት “ወዳጅነት ተበጥሷል”
አጋራችን ብትሆኑ ኤምባሲችን ወደየሩሳሌም እንዲዛወር ድምፅ ትሰጡ ነበር - አሜሪካ ለህወሓት ህወሓት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳያውጅ በጌቶቹ ከተነገረው በኋላ በራሱ መንገድ መሄዱ የግንኙነት “ገመዱን እንደበጠሰው” ተነገረ። አሜሪካ ኤምባሲዋ ወደየሩሳሌም እንዳይሄድ የተቃወሙ አገራትን ዋጋ ትከፍላላችሁ ያለችውን በህወሓት ላይ ተግብራዋለች። አውሮጳውያን የጠነከረ ተቃውሟቸውን በህወሓት ላይ በዚህ ሳምንት ውስጥ እንደሚያሰሙ ይጠበቃል። በባራክ ኦባማ አስተዳደር የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር የነበሩት ቶም ማሊኖውስኪ ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ የአገሪቱን ሁኔታ የገለጹበትን አስመልክቶ ጎልጉል ይህንን መዘገቡ ይታወሳል። “ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቸኛ ሃላፊነት ነው፤ … በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚፈለገው ለውጥ … [Read more...] about የከረረው የአሜሪካና የህወሓት “ወዳጅነት ተበጥሷል”
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የግል አስተያየት
የሃገራችን ፖለቲካ በፍጥነት በሚለዋወጡና አቅጣጫቸውን ለመተመን በሚከብዱ ሁኔታዎች ውስጥ ይዋኛል። ለእነዚህ በፍጥነት ለሚለዋወጡ ፖለቲካዊ ክስተቶች ገፊው ነገር (driving force የምንለው) ምንድን ነው? ካለን በተለይም ላለፉት ሶስት ዓመታት በተከታታይ በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ኣመጽ ነው። ይህ ኣመጽ በከፍተኛ ሁኔታ በፖለቲካው ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው። በብዙ ሃገራት ህዝቦች በአምባገነን ስርዓት ላይ ሲያምጹ 5 ዋና ዋና ክስተቶች ይፈጠራሉ። ህዝብ እምቢኝ ሲል አገዛዙ መረረኝ ብሎ ሲያምጽ አመጹ ተጽእኖ ፈጥሮበት የሚከሰቱት እነዚህ 5 ጉዳዮች፦ በገዢው ፓርቲ ውስጥ መሰንጠቅ፣ መፈረካከስና አለመረጋጋትን ያመጣል። ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያጠነክራል፣ ያበረታታል፣ ያደራጃል፣ ወኔ ይሰጣል። አዳዲስ መሪዎችን ከአመጹ መሃል ያወጣል:: የለሂቁን ልዩነት ያጠባል። … [Read more...] about በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የግል አስተያየት
ብሔራዊ የመረጋጋትና የሰላም ጥሪ፤ ከሕጋዊው ሲኖዶስ
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ብሔራዊ የመረጋጋትና የሰላም ጥሪ፤ ከሕጋዊው ሲኖዶስ
ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የትኛው ኦህዴድ?
በደም ወይስ በድርጅት አባልነት? ወርቅነህ ገበየሁ ወዴት ወዴት? ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን ፍላጎት መኖሩን፣ እሱም ቦታውን እንደሚፈልገው የጎልጉል የመረጃ አቀባዮች ጠቆሙ። ወርቅነህ ቀደም ሲል ከነበረው ሃላፊነት፣ ኦሮሞ አይደለም በሚል የሚቀርብበት ክስ፣ በ1997 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለተካሄደው ግድያ ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው በሚል ስለሚወነጀል ኢህአዴግ ራሱ የበጠሰውን የሕዝብ እምነት ሊቀጥል አይችልም የሚል ስጋት መኖሩንም አመላክተዋል። ቀደም ሲል በጄኔራል ማዕረግ የፌደራል ፖሊስ አዛዥ የነበረው፣ ከዚያም በጁነዲን ሳዶ እግር ተተክቶ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር የሆነው በኦሮሚያ ማሊያ ለትግራይ የሚጫወተው ወርቅነህ፣ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነትም የታጨው የኦሮሞን ሕዝብ ለማባባበል ነበር። እንደታሰበው ሳይሆን ግን በተሾመ ማግስት … [Read more...] about ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የትኛው ኦህዴድ?
ኃይለማርያም ደሳለኝ ለምን ለቀቁ?
ኢ.ቢ.ሲ. በሰበር ያስተናግደውን የኃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ፤ ዞምቢዎቹ ተሯሩጠው ለማጽደቅ ግዜ አልወሰደባቸውም። እሳቸውም ልክ ስልጣን እንደነበረው ጠቅላይ ሚኒስትር "ስልጣን አስረክቢያለሁ" ሲሉ እፍረት የሚባል ነገር ፊታቸው ላይ አይታይባቸውም ነበር። ሹመት እንጂ ሕገ-መንግስቱ የሚፈቅደው ስልጣን እጃቸው ላይ እንዳልነበር ሕጻናትም ያውቁታል። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መልቀቅያቸውን በብርሃን ፍጥነት ሲያጸድቀው፤ ድርጊትዋን ከደቡብ አፍሪካው ጃኮብ ዙማ ክስተት ጋር ለማመሳሰል የተተወነች ድራማም አስመስሏታል። ስልጣን ሳይኖር “ሰላማዊ ሽግግር” የሚሏት ፌዝ … ኃይለማርያም ደሳለኝ ተሸክመውት የነበረው ሹመት ይሁን ስልጣን ሲለቅቁ፤ "ከደሙ ነጻ ነኝ" ብለው ለተሰራው ወንጀል ሁሉ እንደ ጲላጦስ እጃቸውን ሊታጠቡ እንደማይችሉ ግን እርግጥ ነው። ከዚህ ባለፈ ግን የእሳቸው መውረድ … [Read more...] about ኃይለማርያም ደሳለኝ ለምን ለቀቁ?
ዘብረቅራቃው የባህር ዳር “ቅጠል ሰፈር” ጉድ!
ልብ-ወለድ ታሪኮችን አብዝቶ መጻፍ፣ ዕውነታዉን በግማሹም ቢሆን አስቶ፣ በራስህ የህልም ዓለም ዉስጥ እንድትዋኝ ያደርግሃል፡፡ የCreative writing ኪኑ ከአምላክ ቢሰጥህም፣ ጭቆናንና መገፋትን-ድህነትንና መቆራመድን በጠራ-ገለጥለጥ ባለ አማርኛ ከመግለጽ ግን አትታጎልም፡፡ የኔ ሁለት የሃሳብ ጽንፎች እንደዚህ ሲጓተቱ ቆይተው፣ በስተመጨረሻ "ዕውነታን በኪነት" አሉና ተስማሙ፡፡ ሰፈሬ ከከተማዋ (ከባህር ዳር) አንዷ ክፍል ሆና በመጠራት ትታወቃለች፡፡ በአሁኑ የቀበሌ አወቃቀር፣ "ክፍለ-ከተማ" ተባለች፤ "ሽምብጥ ክፍለ-ከተማ"! አብዛኛው ነዋሪዎቿ በዝቅተኛ የአኗኗር መደብ ዉስጥ ይካተታሉ፡፡ ጠላና አረቄ በመሸጥ የሚተዳደሩ ባልቴቶች በእልፍዓእላፋት መዝገብ ውስጥ ሊመዘገቡ አንድ ሃሙስ የቀራቸው ናቸው፡፡ የህወሃት "እያደኸዩ መግዛት" ፖሊሲ በትክክል ውጤት ያመጣው (በባህርዳር ደረጃ) … [Read more...] about ዘብረቅራቃው የባህር ዳር “ቅጠል ሰፈር” ጉድ!
በኢትዮጵያ የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው ወታደራዊ አገዛዝ ሊታወጅ ነው!
በኢትዮጵያ በተከታታይ የዘለቀውን ሕዝባዊ ተቃውሞ መቆጣጠር የተሳነው ህወሓት በኢትዮጵያ በአስቸኳይ አዋጅ ስም አገሪቷን በወታደራዊ አስተዳደር ስር ለማስተዳደር ኣዋጅ አንደሚያወጣ ተሰማ። የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው አዋጅ ምናልባትም ዛሬ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ያለፈው የኢህአዴግ ስብሰባ ወቅት ስምምነት ተደርሶበት የነበረው ሁሉንም ያሳተፈ የሽግግር መንግስት ምስረታ ህወሓት ኣልቀበለውም ብሏል፥ ይህንን ተከትሎ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣኑ እንዲወርድ በህወሓት ግፊት ሲደረግበት ቆይቷል፤ የሃይለማርያም በፈቃዱ ከስልጣን መውረድ ለህወሓት የደኢህዴንን ስጋት እንዲቀንስለት ታስቦ የተደረገ ግፊት ነው፥ የኦህዴድ መክዳትና የብአዴን መከተል ላይ ደኢህዴን ከተጨመረ የህወሓትን ህልውና አደጋ ላይ መጣሉ ስላሰጋው ነው ህወሓት ሃይለማርያም በፈቃዱ ለቀቀ ማስባል … [Read more...] about በኢትዮጵያ የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው ወታደራዊ አገዛዝ ሊታወጅ ነው!
ሕዝባዊ ጽናትና የHR 128 ጡንቻ “እስረኞች”ን አስፈቱ
አገሪቱን ከሁሉም አቅጣጫዎች ለዓመታት ሲያናውጥ የቆየው ሕዝባዊ ዓመጽ ከHR 128 ጋር ተዳምሮበት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የገባው ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” እያለ በግፍ ያሰራቸውን እየፈታ ነው። የተፈቱት ተመልሰው ላለመታሰራቸው ምንም ዋስትና የለም ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዚዳንትነቱን መንበር ከተረከቡ ጊዜ ጀምሮ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) የተባለው አሸባሪ የበረሃ ወንበዴዎች ቡድን ስሉሱ እንደዞረበት አስተውሎ የራሱን ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል። በጣም ይተማመንባቸው የነበሩትን “ነጭ ወያኔዎች” ህወሓት መናፈቅ የጀመረው ኦባማ የሥልጣን መንበሩን በሚያስረክቡበት የመጨረሻ ዓመት መገባደጃ ላይ ነበር። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ October 3, 2017 ባቀረበው የዜና ዘገባ ላይ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ይህንን ማለቱ ይታወሳል፤ ባራክ ኦባማ የሥልጣን ዘመናቸውን … [Read more...] about ሕዝባዊ ጽናትና የHR 128 ጡንቻ “እስረኞች”ን አስፈቱ
ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!
የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል። አቶ ገብረመድኅን … [Read more...] about ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!