
የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል። አቶ ገብረመድኅን አርአያ “ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው” በሚል ርዕስ ያቀናበሩትን ዳጎስ ያለ ሠነድ በድረገጻችን ላይ እንድናትመው በላኩልን መሠረት ከጥቂት ወራት በፊት ክፍል አንድን አቅርበን ነበር። (ይህንን ዕትም ለመረዳት ክፍል አንድን ማንበብ አስፈላጊ በመሆኑ እዚህ ላይ በመጫን እንዲያነቡ እናሳስባለን)። ስማቸው የግድ መገለጽ ስላለበት ስማቸው የወጣ ለዚህ ጽሁፍ ምላሽ መስጠት ለሚፈልጉ በራችን ክፍት ነው። የዝግጅት ክፍላችን ለአቶ ገብረመድኅን ምስጋናውን እያቀረበ ሌሎችም የህወሓት የቀድሞ አባላት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱና በዚህ መልኩ ከሕዝብ ጋር እንዲታረቁ ሃሳብ እንሰጣለን። ያለ እውነት ዕርቅ የለም፤ ያለ ዕርቅ አብሮ መኖር የለም።
ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው!
ወያኔዎች በትግራይ ህዝብ የጥቃት ዘመቻ የከፈቱበት ምክንያት የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ እምነቱ ከፋፋይና ዘረኛው ወያኔ ፤ በእውቅና አለመቀበሉ ቀጥሎ ያለውን ዋና ምክንያቶች እንመልከት።
1. አማራ ደመኛ ጠላትህ ሲሉት አይደለም ወንድሜ ወገኔ ኢትዮጵያዊ ነው በማለቱ፣
2. ተሓህት የትግራይን ሕዝብ አይወክልም አናውቃችሁም በማለቱ፣
3. ተሓህት የነጠቀውን የሰሜን ጎንደርና የሰሜን ወሎ ለም መሬቶች አንቀበልም፣ የሰሜን ጎንደሩ የጎንደር ጠ/ግዛት ነው፣ የሰሜን ወሎ የወሎ ጠ/ግዛት ነው፣ ከትግራይ ግንኙነት የላቸውም፤ በጎንደር በኩል የሚያዋስነን ተከዜ ወንዝ ነው። በወሎ በኩል ማይጨው ችንኮማጂ ነው፤ ሲሆን በምን መልኩ ነው የትግራይ የሚሆነው በማለቱ፣ ከወንድሞቻችን ጥላቻና ቅራኔ አትፍጠሩብን ብሎ ጮሆ በመናገሩ፤ ሸዋዊ የትግራይ አማራ ተብሎ የግድያ ኖህ የወረደበት።
4. የተሓህትን ፕሮግራም አንቀበልም 1ኛ ትግራይ የኢትዮጵያ የታሪክ አስኳል የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ የሚመካ ነው፤ ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ግዛት እንጂ ቅኝ ተገዢ አይደለችም፤ አማራው ኢትዮጵያዊ፤ ትግራይም ኢትዮጵያዊ ፤ ምንም ልዩነት የለንም በማለት ጮሆ በመናገሩ።
5. በጣሊያን ጊዜ የተዋጉና በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩ የትግራይ ልጆችን የህ.ወ.ሓ.ት.ን መርህ የሚያጨናግፉ ናቸው ብሎ በማሰብ ህ.ወ.ሓ.ት አጥፍትዋቸዋል። በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የታሪክ አዋቂዎች አዛውንት ሊቃውንት የአምስት ዓመት ከወራሪው ጣልያን የተዋጉ አርበኞች በመብራት እየፈለገ የወያኔው መሪዎች የገደልዋችው ያጠፍዋችው፤ ተገድለውም ሃብት ንብረታቸው ህ.ወ.ሓ.ት ወርሶታል። እነዚህ የሃገርና የህዝብ አለኝታዋች ሙሉ በሙሉ በትግሉ ጊዜ አጠፉዋቸው፤ ገደልዋቸው። ዛሬ ስለ ትግራይም ሆነ አጠቃላይ ስለ ነበረው ጥንታዊ ታሪክ በትግራይ ውስጥ የሚያውቅ ተፈልጎ አንድም አይገኝም።
ትግራይ በ17ቱ የህ.ወ.ሓ.ት. የትግሉ ዘመን ወድማለች። የታሪክ አዋቂ በኢትዮጵያዊነቱ የሚቆረቆር በትግሉ ዘመን ተመልሶ እንዳያንሰራራ ተመልሶ እንዳይፈጠር አድርገው በመምታት አጥፍተዉታል። በጣም የሚያስገርም ሁኔታም የተፈፀመው በወልቃይት፤ ጠለምት፤ ጠገዴ ብቻ በሰሜን ጎንደር አማራው በተመሳሳይ ሁኔታ አዛውንቶች እየተፈለጉ በስውር እየታፈኑ፣ የት እንደገቡ የማይታወቁ ማን ተያዘ ማን ተገደለ የሚለው በግልጽ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም ብዙ የሰሜን ጎንደር አዋቂ ሽማግሌዎች የውሃ ሽታ ሆነው የቀሩ አሉ፤ ይህን ለማወቅ የሚችሉት የየአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው። የታሪክ አዋቂ ሲጠፋም ተተኪው ትውልድ ይቸገራል። የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች ይህ እንደፖሊያሳቸው የሚጠቀሙበትም የቆየው ታሪክ ለማጥፋትና ለማክሰም ነው።
በእነዚህ ንጹሃን የትግራይ እና የሰሜን ጎንደር ኢትዮጵያውያን የፈሰሰሰው ደም ተጠያቂው ማነው? ማነውስ ሃላፊነቱ የሚቀበለው? ምንስ አጥፍተው ነው? ወደ ትግራይ ስንመለስ፤ የተናገሩት እውነት ነው፤ ትግራይ የአማራው ቅኝ ተገዢ አይደለችም፤ ሰሜን ጎንደር፤ ወልቃይት፤ ጠገዴ ጠለምት፤ ቃፍታ (ሰቲት) ሁመራ የሰሜን ወሎን መሬቶች የትግራይ አይደሉም፤ አልነበሩም፤ ይህም ታሪክ የሚያውቀው ሃቅ ነው። የትግራይ ህዝብ ምን አጠፋ ህ.ወ.ሓ.ት የገደለው የረሸነው ያጠፋው። ማንኛውም ህዝብ አስተዋይና አርቆም ሃሳቢ እንደሆነ ሁሉ የትግራይ ህዝብም ከዚሁ ተነስቶ ነበር እውነቱን የተናገረው። ይህ ህ.ወ.ሓ.ት. የጀመረው በትግራይ ህብረተሰብ ማጥቃትና መግደል የንጹሃን ዜጎችን ደም በከንቱ የፈሰሰው ይህ ደም አሁንም በእግዚአብሔር ፊት እየጮኸ ይኖራል። መሬትና ሰማይ የፈጠረ ጌታም ፍርዱን ይሰጣል፤ የማይቀር ነው። የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች የአማራው ጎንደሬው ለምና ሰፊ መሬት በሕገ ወጥ በጉልበት ለመንጠቅ፤ የአማራው ደም የንጹሁን ኢትዮጵያውያን ዜጎች ደማቸው በትውልድ መንደራቸው እንደጎርፍ ካለምንም ጥፋትና ሃጥያት ፈሰዋል፤ ዘራቸው አጥፍተዋል፤ ህፃን፣ አራስ፣ እርጉዝ፣ ሽማግሌ፣ ወጣት፣ ተገድለዋል፣ በስዉር ጠፍተዋል። የእነዚህ ንጹሃን ኢትዮጵያዊ ዜጎችም ፈጣሪ አምላክ ፊት ደማቸው እየጮኸ ነው። ቀሪዎቹ በሂወት ያመለጡም በስደት እየተንከራተቱ ይኖራሉ።
ይህን አሳዛኝ ታሪክ ያነሳሁት የትግራይ ሕዝብ ነፃአውጪ ህ.ወ.ሓ.ት.፤ ማ.ገ.ብ.ት ተብሎ ሲፈጠር ቀጥሎም ደደቢት በርሃ ወርዶ ተ.ሓ.ህ.ት. (ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ) ከዛም ስሙን ለውጦ ህ.ወ.ሓ.ት. (ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) ቢልም እውቅና ያልሰጠው በአንጻሩ ግን የትግራይ ሕብረተስብ ፀረ ወያኔ አምርሮ የታገለው ህዝብ ነበር። ፀረ ወያኔ ሆኖ መታገሉ ከባድ መስዋእትነት በሂወቱ በንብረቱ በሃብቱ ከፍሎ ነው ያለፈው። ሁሉ ኢትዮጵያዊም ይህን በእምነት ሁሉ ኢትዮጵያዊ ያምንበታል። ለዚሁም ተጠያቂዎቹ አረጋዊ በርሄ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ ስዩም መስፍን፤ መለስ ዜናዊ ሲሆኑ፣ እነዚህ በዋና የንፁሃን ደም በሰሜን ጎንደር በትግራይ በኢትዮጵያውያን ንፁህ ደም በፈጸሙት ወንጀል ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው። ቀጥሎ ደግሞ፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ አርከበ ዕቁባይ ገብሩ አስራት በዋናነት ግንባር ቀደም ይጠቀሳሉ።የኢትዮጵያ ህዝብ ክስ ሲመሰርትም መነሻው ከዚሁ ነው። የህ.ወ.ሓ.ት. ፋሺስት ድርጅት ለብዙ ዓመታት የመሩትም እነዚህ፤ ተከታትለው ወደ ሥልጣን የመጡ እንደሆነ እንመለክታለን።
ይህ የትግራይ ሕዝብ በማጥፋት የተሰማራው የህወሓት አመራር ሕዝብ በመግደሉ በተሰማራበት ወቅት በተሓህት ውስጥ የነበርው ታጋይ በዝምታ አልተመለከተውም ነበር። ከዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችእና በህዝቡ እየተፈጽሙት ያሉትን ግፍን ሰቆቃ ድርጅቱ ከምን ተነስቶ በምን ምክንያት ሰላማዊ ህዝብ እያሰረና እያሰቃየ ሽማግሌዎች ወጣቱን ወንድ ሴት ይፈጃል የሚሉና ተዛማች ብዙ ጥያቄዎች ተነሱ። አመራሩ በታጋዩ የተነሱ የዲሞክራሲ ጥያቄዎች ተቀብሎ በሰላም ከመፍታት ይልቅ ታጋዩን በመወንጀል፤ ይህ ፀረ ተ.ሓ.ህ.ት እንቅስቃሴ ነው በማለት ራሱ አመራሩ ለተነሱ የዲሞክራሲ ጥያቄ በመወንጀል ሕንፍሽፍሽ የሚል ስም በመስጠት፣ በበዙ ታጋዮችና ሰላማዊ ዜጋውም በሕንፍሽፍሽ ተመርዘዋል ተብሎ ሰላማዊ ዜጋው ከየቤቱ እየተለቀመ፤ ታጋዩ ከትግል ሜዳው እየተለቀመ፣ እየታፈነ፣ በቶርቸርና በእሳት እየተቃጠለ፣ በእሳት የጋለ ፍም ሳንጃ ሆድ እቃው እየገባ ተገደል፣ ጠፋ፣ የተገደሉት ሰላማዊ ዜጎችም ሙሉ ንብትና ሃብታቸው በህወሓት ተወረሰ። የብዙዎች ቤት ፈረሰ።
የትግራይ ሕብረተሰብ ለዚሁ ሁሉ መጥፎ ጥቃት የተዳረገበት ዋና ምክንያት ከላይ የተጠቀሱ ሲሆኑ ሌላው ደግሞ ጣልያን ኢትዮጵያ በ1928 በወረረበት ጊዜ በአርበኝነት የተዋጉ ሁሉ የተሓህት-ህወሓት አመራርን በመኮነናቸው ነበር። ይህ ሲሆን አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ መለስ ዜናዊ ያሳለፉት መመሪያ እነዚህ የትግራይ ሸዋ አማራ በአጭሩ አነጋገር ሸዋዊ ትግራዋይ በሙሉ በየትም ትግራይ መሬት የሚኖሩ በሕዝብ ግንኙነት እየተለቀሙ ታስረው ሃለዋ ወያኔ (06) በሚስጢር እንዲገቡ በማለት በሰጡት የትእዛዝ መመሪያ ሁሉም ከያሉበት ተለቅመው ሃለዋ ወያኔ እየገቡ ተገድለዋል፣ ንብረታቸውን ተወርሰዋል። ዛሬ በትግራይ እንኳንስ ከጣልያን የተዋጋ በወቅቱ ሕጻናት የነበሩትም አንድም ሰው አይገኝም፣ ተገድለዋል። ዋና የተገደሉበት ምክንያት፤
- የህ.ወ.ሓ.ት የፖለቲካ አቋም ወይም ፕሮግራም አንቀበልም ብለው በማውገዛቸው
- አማራ የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ስለሆነ አብረን እንምታው እናጥቃው ሲባሉ፤ አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት አይደለም፤ ሁላችን አንድ ኢትዮጵያ ወንድማሞች ነን፤ አማራ የፈጸመብን በደል ጥቃት የለም፤ አማራው የኛ፤ እኛም የሱ ነን በማለታቸው፤
- የሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን ወሎ መሬት የትግራይ ነው የምትሉን የትግራይ አይደለም፤ በታሪክም አልነበረም፤ የወንድሞቻችን በጉልበት የምትወሩት ያላችሁ ርስተ መሬት አንቀበልም በማለቱ
- ጣልያን ጣልያን የምትሉት በየቦታ ከጣልያን የተዋጋነው ሃገራችን ኢትዮጵያ ለመውረር በቅኝ አገዛዝ ስርአቱ ሊገዛን የመጣው፤ ወራሪ ቅኝ ገዢ ጠላት ነው፤ የሃገራችን ኢትዮጵያ አንድነትና ሏላዊነት አሳልፈን አንሰጥም በማለት ጣልያን መታነው አሸነፍነው፤ ኢትዮጵያን ነፃ አወጣን፤ በማለት ፀረ ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት አቅዋም በመያዛቸው ነበር።
ሆኖም ይህንን መቀበል ያቃታቸውና ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት ከላይ በተጠቀሱ የወያኔ መሪዎች ከባድ ጥቃት በመሰንዘር ህዝቡን ጨረሱት፤ ህጻናትም ሳይቀሩ አብረው ተጨፈጨፉ። ዛሬ ታሪክ ነጋሪ በትግራይ ፈጽሞ አይገኝም። የታሪክ ፈላስፋዎች የታሪክ አዋቂዎች የሆኑት የወያኔው መስራቶችና አሁንም በሥልጣን ያሉት ደንቆሮች የወያኔ መሪዎች በሥልጣን ኮረቻ የተንጠለጠሉ ቅኝ ገዢዎች የህ.ወ.ሓ.ት. ባንዳዎች ናቸው።
ይህ በዚሁ እንዳለ፣ የትሓህት-ህወሓት መሪዎች በትግራይ ሕብረተሰብ የጀመሩትን ጥቃት እንደቀጠለ ሁኖ የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ሰቲት ሁመራን፤ በጉልበትና በማንአለብኝነት በካርታቸው የተካተተው በፕሮግራማቸው ውስጥ የትግራይ መሬት ነው በማለት ሰፊዉን የጎንደር ክፍለ ሃገር መሬት የሰሜን ወሎ መሬት በማካተት (ፀሃፊና አዘጋጅ አረጋዊ በርሄ ነው) ሕገ ወጥ የለም ሰፊ መሬት ወረራ ፈጽመዋል። ይህን ወረራ ለማስፈጸም የተካሄድ ቅድመ ዝግጅት በሰሜን ቤገምድር (ሰሜን ጎንደር)፤ መኮንን ዘለለው የተባለው ነገር ግን አካባቢውን የማያውቀው በስመ ተወላጅ በአባቱ በኩል ተወላጅ የሆነውን ታጋይና በህዝብ ግኑኝነት ክፍል የተመደበ በሱ የሚመራ ቡድን በወልቃይት፤ በጠገዴ፤ በጠለምት ጥናት እንዲያካሂድ በ1969 ዓ.ም ውስጥ ተላከ። ይህ ከሃዲ ግለሰብ ከግለሰው እስከ ቡድን ከቡድን በየበአላቱ እሁድ ወ.ዘ.ተ. በየቤተክርስትያኑ እየተንቀሳቀሰ ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ቃፍታ ሁመራ የትግራይ መሬት መሆኑ የሰሜን ጎንደር ህዝብም ሁሉ ትግራዋይ መሆኑ የታሪክ ሃቅነት በጎደለው ለማሳመን ባካሄደው መፍጨርጨር ሳይሳካለት በሙሉ የሰሜን ጎንደር ህዝብ በልበ ሙሉነት ወድቅ አደረገው። በግልጽም እናንተ ወራሪ የጣልያን አሽከሮች ውላጅ ናችሁ በማለት አሸማቀቃችው። ይህ የጎንደር ግዛት በማንም ያልተደፈረ በእናንተ ከሃዲዎች እይፈፈርም ብሎ ህዝቡ በግልጽ የተናገረበት ጊዜም ነው። ከዚያም ተዋርዶ ተደብዶቦ፤ ህዝቡም ወደ ማንም ቤት ዝር እንዳይሉ በማስጠንቀቅ በርሃብ ጠውልገው ወደመጡበት እንዲመለሱ አደረጋቸው። ነገር ግን መኮንን ዘለለውና ቡድኑ ሲያደርጉት የነበረው ሤራ ህዝቡ ሁሉ ቢቃወምም ትልልቅ ሰዎች የታሪክ አዋቂዎች የበሰሉ ጠንካራ ሰዎች በብዛት በሚስጢር እየመዘገቡ፤ እነዚህ ሰዎች በሂወት ካሉ ነገሩ አይሳካም በማለት በድብቅ ስማቸው ወደ ወያኔ መሪዎች በየእለቱ በማስተላለፍ ለክፉ ሞት ዳረጉዋቸው።
የህ.ወ.ሓ.ት . መሪዎች አሁን የገጠማቸው ክሽፈትና ወርደት አጸፋውን ለመመለስ ዝግጅታቸውአሰቀመጡ። ቀደም በማለት በትግራይ ሕብረተሰብ የአፈና ዘዴ በመጠቀም አነስተኛ ሀይል አፋኝ ጉጅሌ በማደራጀት ክፉና አረመኔው ጨካኞች አፋኝ ቡድን ሶስት አቅጥጫ ተሰማራ። ይህ ጊዜም በ1969 ዓ.ም. ወደ መጨረሻው አካባቢ በሶስት አቅጣጫ በማሰማራት
- ወልቃይት፣
- ጠለምት፣
- ጠገዴ
ውስጥ ሲገቡ ጉጅሌያቸውን ይዘው በሶስቱ ቦታዎች ተሰማርተው ቀደም ሲል ከመኮነን ዘለለው የነበሩ የህዝብ ግኑኝነት መሪነት በድብቅ በዘዴ የተቃወሙት የሰሜን ጎንደር አማሮች አንድ በአንድ በተናጠል እያፈኑ ሰውን በመልቀም ያፈኑዋቸውን ሓለዋ ወያኔ በማስገባት ወንድ፣ ሴት ሳይሉ ገደሉዋቸው። ሃብት ንብረታቸውም እየተወረሰ ዝርፍያው ቀጠለ ቀስ በቀስም የጀመሩት ጥቃት እየተስፋፋ ሄደ።
ተ.ሓ.ህ.ት. ለ1ኛው ጉባኤ ይዘጋጅም ስለነበረ 1ኛ ጉባኤው የካቲት 5 ቀን 1971 ዓ.ም. ዓዲ ዳዕሮ አካባቢ ማይ አባይ በተባለው ቦታ ተካሂዶ የአመራር ቦታ ለውጥም ተደረገ። በዚሁ መሰረት እንደሚከተለው ተደላደሉ።በዚሁ ጉባኤ የተመረጡ አመራሮች አምስቱ የቆዩ ፖሊት ቢሮ (ሥራ አስፈጻሚ) እንዳሉ ተመልሰው ሥልጣናቸው ሲይዙ ቀሪዎቹም ዝርዝር የሚከተለው ነው፤
1ኛ. አረጋዊ በርሄ፤ ወታደራዊ አዛዥ፤ ፖሊት ቢሮ
2ኛ. ስብሃት ነጋ፤ የህ.ወ.ሓት ሊቀ መንበር፤ ፖሊት ቢሮ
3ኛ. ግደይ ዘራፅዮን፤ የህ.ወ.ሓ.ት ም/ሊቀመንበር፤ ፖሊት ቢሮ
4ኛ. አባይ ፀሃየ፤ የፕሮፓጋንዳ ክፍል ዋና ሃላፊ፤ ፖሊት ቢሮ
5ኛ. ስዩም መስፍን፤ የውጭ ጉዳይ ዋና ሃላፊ፤ ፖሊት ቢሮ
6ኛ. ገብሩ አስራት፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ
7ኛ. መለስ ዜናዊ፤ የፕሮፓጋንዳ ጽ/ቤት ም/ሃላፊ፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ
8ኛ. አስፍሃ ሓጎስ፤፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ
9ኛ. አርከበ (ዮሓንስ) እቁባይ፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ
10ኛ. ፃድቃን ገብረተንሳይ፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ
11ኛ. ስየ አብርሃ፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ
12ኛ. አታክልት ቀፀላ፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ፤ ግንቦት ወር 1971 ዓ.ም በስብሃት ነጋና በአባይ ፀሃየ እንዲሁም በመለስ ዜናዊ የተገደለ። ገዳይ ሳሞራ (መሓመድ) የኑስ በሲሞኖቭ ባልር መነጽር ጠመንጃ።
13ኛ. ዘርአይ አስገዶም፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ
14ኛ. አውዓሎም ወልዱ፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ
15ኛ. ተወልደ ወ/ማርያም፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ ብዙም ሳይቆይ በህመም ምክንያት ሱዳን ሂዶ 1975 ዓ.ም የተመለሰ ነው።
የነዚህን ስም ዝርዝር ያስቀመጥኩበት ካለ ምክንያት አይደለም፤ በተለይ በአማራው ላይ የዘር ማፅዳት ከባድ ወንጀል በመፈጸማቸው ነው። አማራው ያፈራው ሃብት ንብረት ወ.ዘ.ተ. መርፌም ሳትቀር ለህ.ወ.ሓ.ት. ውርስ እንዲሆን ብለው የህዝብ ሃብት ንብረት የዘረፉ፤ የአማራው ህዝብ የገደሉ፤ የግድያውም ቀንደኛ ተባባሪዎችና ፈፃሚዎች የነበሩ ናቸው። እነዚህ ተሰባስበው ነው በንጹሃን ዜጎች ላይ እልቂትና ሰቆቃ እያደረሱ የመጡ፤ ከአምስቱ ፖሊት ቢሮ ስድስተኛው መለስ ዜናዊ አብረው ሊጠየቁና ሊከሰሱ የሚገባቸውናቸው። የሰሜን ጎንደር ህዝብ በአረጋዊ በርሄ የሚመራው የህ.ወ.ሓ.ት ሰራዊት ቀሪው አራቱ ፖሊት ቢሮ በየቦታው ተሰማርተው ትዕዛዝና አመራር በመስጠት ማእከላዊ ኮሚቴውም ይበልጥ በዘር ማጥፋቱ ተሰማርተው የነበሩ፤
1. አዋአሎም ወልዱ፤ 2. ስየ አብርሃ፤ 3. መለስ ዜናዊ ከስየ አብርሃ ተደራቢ በመሆን፤ 4. ዘራይ አስገዶም፤ 5. ፃድቃን ገብረ ተንሳይ፤ 6. ገብሩ አስራት፤ 7. አርከብ እቁባይ፤ 8. አስፍሃ ሓጎስ ናቸው።
ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ በየተዋጊው ሰራዊት ተመድበው ትእዛዝ በመስጠት በአማራው ላይ ጥቃት በመክፈት የአማራ ዘር ማጥፋት ከባድ እርምጃ በመውሰድ፤ አማራው ሊቋቋመው በማይችል ሁኔታ ሰላማዊው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ዘሩን ለማጥፋት ያለው የሌው ሃይላቸው አጠናክረው ግፍ የፈጸሙ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች፤ 1. አረጋዊ በርሄ፤ 2. ግደይ ዘራጽዮን፤ 3. ስብሃት ነጋ፤ 4. አባይ ጸሃየ፤ 5. ሥዩም መስፍን፤ 6. መለስ ዜናዊ፤ በሰሜን ጎንደር አማራ በትንሹ ከ1969ዓ.ም. የጀመረው ጥቃት በክፉ መልኩ ተጠናክሮ ከታህሣስ ወር 1972 ዓ. ም. የተጀመረው የአማራ ዘር ማጥፋት ዘመቻ እስከ 1977 ዓ .ም. በቀጠለበት ጊዜ በዋናነት የዘር ማጥፋት ወንጀሉን በአማራው ላይ የፈጸሙ ዋናዎቹ እነዚህ ናቸው። በዚሁ የወያኔ ጥቃት ከ2 ሚልዮን በላይ ነብሰ ጡር አራስ ህፃናት ሽማግሌዎች ወጣቶች ወንድ ሴት ልዩነት በሌለው በወያኔ እጅ ተገድለዋል። አገዳደሉም በተለያየ ስልትና ዘዴ ተፈጽሞባቸውል። ቀሪው ለስደት ተዳርጓል፤ የመጣ ይምጣ ከቤቴ ወጥቸ አልንገላታም ያለም አለ።
ከማ.ገ.ብ.ት ምስረታ እስከ የካቲት ወር 1967 ዓ.ም. የማገብት ሊቀ መንበር፤ ቀጥሎም በትግሉ ሜዳ ከየካቲት ወር 11ቀን 1967 ዓ.ም እስከ የካቲት ወር 1971 ዓ፣ም ሊቀ መንበርና ወታደራዊ አዛዥ የነበረው አረጋዊ በርሄ ነው። በምን ምክንያት ሊቀ መንበርነቱን ለቀቀ ለሚል ጥያቄ አጭር መልስ።
አረጋዊ በርሄ፤ ስብሃት ነጋ፤ መለስ ዜናዊ ስብሰባዎች በሚካሄዱባቸው ጊዜያት ገና ወደ ጉባኤው ሳይገባ ሶስቱ እየተደበቁ የሚያደርጉት ስምምነት ነበራቸው። ድርጅቱን በሞኖፖል ለመቆጣጠር የሚያስችላቸው ሶስቱን የተስማሙበት አረጋዊ ሊቀመንበርነቱን ለስብሃት ነጋ ሊሰጠው አረጋዊ በወታደራዊ አዛዥነቱ እንዲወሰን መለስ ዜናዊ የማርክሲስት ሌኒንስት፤ በሌኒናዊ መርሀግብር የካድሬዎች አሰልጣኝና አደራጅ ኮሚሽን እንዲሆን በተስማሙት መሰረት ነበር። 1ኛው ጉባኤው ተካሂዶ 15 አመራር ተመርጠው የሥራ አስፈፃሚው ምርጫ በሚመረጥበት ጊዜ በሁሉም ተሰብሳቢ በሙሉ ድምጽ የተመረጠው አረጋዊ በርሄ የህ.ወ.ሓ.ት. ሊቀመንበር ቢመረጥም ብሞትም አልቀበልም ስብሃት ነጋ ነው ብቁ ለሱ ይስጠው ብሎ አንገቴን ለካራ አለ። የተመረጡ አመራር ስብሃት ለዚሁ ብቃት የለውም እባክህ ተቀበለን ቢሉቱም በፍፁም አልቀበልም በማለቱ ለስብሃት ነጋ ሰጡት። መለስ የተሰጠውን ቦታ አደላድሎ ያዘ፤ አረጋዊም ድሮም የራሱ የነበረው ወታደራዊ አዛዥነቱን ያዘ፤ቀሪው በየቦታው ተደላደለ። በአጭሩ ነው የገለፅኩት እንጂ ብዙ ታሪክ አለው፤ ለወደፊቱ ራሱን በቻለ ርዕስ ለህዝብ አሳውቃለሁ፤ ለአሁኑ ይህ ይበቃል። አረጋዊ በርሄ ደግሞ በታጋዩ እንዲጠላ እንዲናቅ ያደረገው ዋናው ይህ ነው። ስብሃት ነጋ ማለት አእምሮው የዞሮበት ደፍድፍ ደንቆሮ ገዳይ ጨካኝ አውሬ ነው።

ህወሓት ከኢህአፓ ጦርነት ስለአጋጠመው ደፍሮ ሰሜን ጎንደር ሕዝብ ለማጥቃት ሁኔታውና ጊዜው አልፈቀደለትም ነበር። ከኢህአፓ ጋር በተካሄደው ጦርነት ኢህአፓ ጥቃት ደርሶበት ሰሜን ጎንደርን ለቆ በመውጣቱ ምክንያት በአረጋዊ በርሄ ወታደራዊ አዛዥ የሚመራው የወያኔ ሰራዊት ጠቅላላ ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት(‘ሰሜን ጎንደር’) በመውረር ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጸመ። ስብሃት ነጋ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀህየ፣ ስየ አብርሃ፣ ስዩም መስፍንና መለስ ዜናዊ የወያኔውን ሰራዊት ተከፋፍለው በመያዝ ሰሜን ጎንደር የንጹሃን ዜጎች አማራ የሬሳ ክምር መሬት አደረጉት። እነዚህ ሁሉ አመራር በቀጥታ ትእዛዝ የሚቀበሉት፣ የሚንቀሳቀሱት፣ ጥቃት የሚፈጽሙበት ቦታዎች ከአረጋዊ በርሄ በሚሰጣቸው መመሪያ ነበር። በዚሁ ጊዜም ተጨማሪ (06) ሃለዋ ወያነ በስፋት እንዲዘጋጁ አመራሩ ስላመነበት በምክትል ሊቀመንበሩ ግደይ ዘርአጽዮን ቁጥጥር ተጨማሪ ሃለዋ ወያን እንዲዘጋጅ በታዘዘው መሠረት በርሱ ኃላፊነት ተጨማሪ ከመሬት በታች 12 ሜትር ጥልቀት ትንሽ ጠባብ መስኮት 150 እስከ 200 እስረኞች የሚይዙ ሆነው እንዲሰሩ ወስኖ የነበሩትም እንዲሰፉ አድርጎ አሰራው። የሚሰሩበትም ቦታዎቹም፣ ግህነብ (ቃሌማ)፣ ፍየል ውሃ፣ ባኽላ ሳምረ፣ ሱር እስር ቤት ሲሆን፣ እንዲሰፋ የተደረጉባቸው ቦታዎች ደግሞ አዲ በቅሎ፣ ወርዒን ፃኢ ጨምሮ በስፋትና በብዛት ከመሬት በታች ሃለዋ ወያኔ ተሰሩ። በዚሁ ጊዜ አማራዎች፣ ሽማግሌ፣ ወጣት፣ ህፃን፣ ሴት፣ ወንድ ሳይለዩ ወደነዚህ ሃለዋ ወያኔ እየታፈሱ ታጋዙ። እዛው እንደገቡም በተለያዩ የጭካኔ ግፍ ተገደሉ። በጢስ እየታፈኑ የሞቱት አማራዎች ብዙ ናቸው። በጅምላ ጉድጓድ በጥይት እየተደበደበ ያለቀው አማራ ብዙ ነው። ወህኒ ቤት ውስጥ በገባው ተላላፊ በሽታ ምክንያት ኮሌራን ሌላ በሽታዎች በመተላለፍ ሕዝብ አለቀ። በቶርቸር፣ በመርዝ፣ በእሳት፣ የጋለ ብረት ወደ ሆዱ በመክተት አሰቃይተው ንጹህ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አጠፉት። የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች በአማራው ያልፈጸሙት ግፍ የለም ። እነዚህ አረመኔ ግፈኞች በአንድ ህዝብ ላይ አማራ ጠላታች ብለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካሂደዋል። የሞተም በሂወት ያሉትና የሞቱትም እንደነ መለስ ዜናዊ በከባድ ወንጀል
1. ዘር በማጥፋት፤
2. ሃገር ለባእዳን መሸጥ (ለሱዳን)፤
3. የመሬት ወረራ መፈጸም (ሰሜን ጎንደር፤ ሰሜን ወሎ) የታላቅዋን ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ የትግራይ መንግሥት ማስፋት የሌላው ክፍለ ሃገር ለምና ሰፊ መሬት በመንጠቅ የህዝቡ ማንነት፣ ባህሉን፣ ወጉን፣ ፀረ ዲሞክራሲ፣ ፀረ ህልውና፣ በመሆነ መልኩ የፈጸሙት ከባድ የወንጀል ተግባር ነው። አሁንም ህ.ወ.ሓ.ት በዚሁ እየቀጠለበት ሲሆን እንዲያውም በከፋ መልኩ በግማሹ ወደ ትግራይ በማካለል ግማሹ ለሱዳን መንግሥት በመሸጥ በአማራው ላይ የሚፈጸመው ግፍ አባብሶታል።
በአማራው እየተፈጸመ ያለው ግፍ አማራን ብቻ የሚመለክት አይደለም፤ የሁሉ ኢትዮጵያዊ ጥቃት ነው፤ አማራው ዘሩ ሲጠፋ አማራው ብቻ አይደለም ዘሩ የሚጠፋው ያለ ሁሉ ኢትዮጵያው ነው ዘሩ የሚጠፋ ያለው፤ የጎንደር ለምና ሰፊ መሬት ለሱዳን እየተሸጠ ያለው የጎንደር ብቻ አይደለም የሁሉ ኢትዮጵያዊ ነው፤ የኢትዮጵያ የታሪክ ቦታዎች፤ ቴዎድሮስ በመቅደላ፤ ዮሃንስ በመተማ እምቢ ለጠላት ብለው የተሰዉበት መሬት ወያኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ለሆነው የሱዳን መንግሥት አሳልፎ መሸጥ ታሪካችንም አሳልፎ እየሸጠው ይገኛል።ስለሆነም የጎንደር ህዝባዊ ትግል የሁሉ ኢትዮጵያዊ ትግልም ነው። የምንታገልበትም ጊዜው አሁን ነው። ጎንደርና ትግራይ፤ ጎንደርና ሲዳሞ፤ ጎንደርና ሓረር፤ ጎንደርና አፋር፤ ጎንደርና ኦጋዴን፤ ጎንደርና ጋምቤላ፤ ወ.ዘ.ተ ምንም ልዩነት የለንም! ሁላችን የኢትዮጵያ ልጆች ነን፤ ኢትዮጵያ የሁላችን ሃገር መመክያ ናት፤ ሁላችን ሃገራችን ከወያኔው ፋሽሽት ስርአት ከሃዲ ባንዳ ተባብረን ኢትዮጵያን እናድን።
የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ሌላውም አማራ በህ.ወ.ሓ.ት.፤ የወረደበት ከባድ የጥቃት ዘመቻ በዝምታ ወይም እየተገደለ አልቀረም። ተወልዶ ያደገበት የትውልድ ቦታው ስለሆነ መግቢያው መውጫው ስለሚያውቀው፤መሳሪያ ያለው ታጥቆ፤ የሌለው በቤቱ ያገኘው ጎራዴ፤ ፋስ፤ ገጀራ፤ ወ.ዘ.ተ. እናቶች ወጣት ሴቶች ወንድም ሳይቀር በርበሬ በመያዝ ወያኔን በሚገባ በሁሉ አቅማቸው ገድለዉታል፤ አጥቅተዋል። በአንዳንድ ቦታዎችም ሙሉ በሙሉ ለማለት የሚቻለው የወያኔ ሠራዊት ደምሠዉታል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በታሪክ የተመሰከረለት አርበኛ ተዋጊ፤ ሙሉ ወኔ ያለው ህዝብ ከመሆኑ የተነሳ ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. እንደፈለገው ኢትዮጵያን እንዲያፈርስ ህዝብ ሊበታትን በደም ሊያቃባ እድል አልሰጠዉም። የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት ህዝብ ቆለኛም ደገኛም ህዝብ ነው። የመሬቱ ነፋስ የተስማማ ከመሆኑ የተነሳ ወያኔ ይህ ህዝብ በቀላሉ ሊያጠቃው ጠራርጎ ሊያባርረው አልቻለም። ሌላው አማራ ቶሎ ብሎ በመቻኮል ወደ በቀል አርምጃ አይሸጋገርም፤ ከተነሳ ግን ወደ ኋላ አይታጠፍም፤ በአማራ ጥርስ የገባ ጠላት የመጨረሻ እጣ ፈንታው ውድቀት ምርኮ ናት። አማራ ለኢትዮጵያ አንድነት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ዋልታና ማገር፤ የሃገሩ ድንበር በመጠበቅ፤የእስልምና፤ የክርስትና ሃይማናት ባለቤት በመሆኑም እነዚህ ሁሉ ተዳምረው በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ህዝብ፤በባንዴራው አረንጓዴ፤ ብጫ፤ ቀይ የሚኮራ ህዝብ ነው። ይህ አማራ የሚባለው ህዝብ ዘሩን ካልጠፋ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር በአፄ ምኒሊክ የተፈጠረች ናት፤ ከተፈጠረችም ከ100 ዓመት ያነሰ ዕድሜ ያላት ታሪክ-አልባ ሃገር ናት፤ ከዓለም ካርታ ለመፋቅ ይቻላል፤ ብሎ የተነሳው የባእዳን ቅጥረኛ ባንዳ ወያኔ፤ የአማራው ወኔ ጥንካሬ ጀግንነት አይቶታል፤ አሁን እያየው ነው።
ህ.ወ.ሓ.ት አማራውን ሲያጠቃ አብሮም የተጠቃው የኢትዮጵያ ተዋህዶ ክርስትናም ነው። ቀደም ሲል በ1971 ዓም በአክሱም አውራጃ እንዳባ ጴንጦሌን (ብዙ አክሱማዊም እንዳባ ፍሬሚናጦስ) እያለ የሚጠራው ከአክሱም ከተማ የ5 ኪሎሜትር ርቀት ያለው አካባቢው የሚጠራበት ስም ደግሞ እንዳየሱስ በተባለው ቦታ ጥንታዊው ገዳም እንዳ አባ ጴንጦለን ብዙ ጥንታዊ ቅርሶች፤ ብዙ ጥንታዊ የታሪክ መጻህፍት፤ ጥንታዊ የብራና ጽሁፎች የሚገኝበት ገዳም ለመዝረፍ ህ.ወ.ሓ.ት በሰነዘረው ጥቃት ሳይሳካለት ቀርቷል። ቀጥሎም በአድዋ ውስጥ የሚገኘው እንዳሥላሴ ገዳም ላይ ቢሞክርም አልተሳካለትም። ይህ ኦፐረሽን የተመራው በአረጋዊ በርሄ ነበር፤ቀጥሎ ወያኔ የዘመተው ወደ ዋልድባ ገዳም፤ በዚሁ ገዳም ተልእኮው ሙሉ ለሙሉ ተሳካለት፤ በህ.ወ..ሓ.ቱ ሊቀ መንበር ስብሃት ነጋና በህ.ወ.ሓ.ቱ ም/ሊቀመንበር ግደይ ዘራጽዮን መሪነት ዋልድባ ገዳም ሙሉ በሙሉ ተዘርፈዋል። ብዙ ብጹዓን ባህታውያን፤ ቀሳውስት፤ አባዎች ተገድለዋል፤ ታሪካዊ ቅርሶች መጻህፍት ብራናዎች ሃብቱ ንብረቱ ወ.ዘ.ተ. ተዘርፈዋል። አሁንም ዋልድባ ገዳም እየተጠቃ ይገኛል፤ ባለታሪክ ጥንታዊ ገዳም እየወደመ ለህልፈቱም ገደል አፋፍ ነው ያለው፤ ይህ ገዳም አማራን ብቻ አይመለከትም የሁሉ ኢትዮጵያዊነው፤ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይና ዋልድባ ገዳም በሚል ርእስ ለሁሉ ኢትዮጵያዊ ስለ አሰራጨሁት የዚሁ ቅዱስ ዋልድባ ገዳም በህ.ወ.ሓ.ት. የደረሰበትና እየደረሰበት ያለው ጥቃት በዝርዝር ስለፃፍኩት ጽሁፉ በየዌብ ሳይቱ ስለሚገኝ እዛው ፈልገን እንመልከት።
በአማራው የተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ደግሞ ከሁሉ የከፋ በአርከበ እቁባይ፣ ዘርአይ አስገዶም፣ ሳሞራ የኑስ፣ ታደሰ ወረደ፣ ሃየሎም አርአያ ወዘተ የሚመሩ የገዳይ ቡድን ሕዝቡን እየሰበሰቡ በሳር ቤት ውስጥ በማስገብት ቤቱን በእሳት በማቃጠል ያለቅው ሰው ቁጥር ብዙ ነው። እኔ ራሴ ያየሁት አርከብ እቁባይ 12 ቤተሰቦችን ሰብስቦ በገዛ ቤታቸው፣ አባት፣ እናት፣ ልጆች፣ የተዳሩ ሴቶች ልጆቻቸውን ጨምሮ ከነህፃናቱ ሰብስቦ ሳር ቤት አዳራሽ አስገብቶና ቤቱን ዘግቶ እሳት ለቀቀባቸው። ሁሉም ቤተሰብ በእሳቱ አለቁ። በዚሁ በሰሜን ጎንደር የተካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል በተጨማሪ ሁሉም ንብረታቸው ሃብታቸው፣ በሬ፣ ላም፣ ፍየል፣ በግ፣ አጋሰስ ጠቅላላ የቤት እንሣት ሁሉ በህወሓት ተዘርፈው ተወርሰው ተወሰደዋል።
ከ1972 ዓ.ም. ታህሳስ ወር ይህ ሁሉ ጥቃት የተጀመረው አጠቃላይ የጠገዴ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት አማራ ዘሩ ሲጠፋ ቀሪው ደግሞ ወደ ሱዳን ተሰደደ፤ ጫካ ውስጥ ገብቶ ፀረ ወያኔ በሽምቅ ውጊያም የተሰማራ ጥቂት አልነበረም። ህዝብም ባገኘው መንገድ ሁሉ ወያኔን ከማጥቃት አላቆመም፤ የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ሴቶች በርበሬ በትንሽ ከረጢት ቋጥረው ከወገባቸው አትለይም በቤታቸው ውስጥም የተዘጋጀ አለ የወያኔ ታጋይ በመንገድ ሲገኙት አቁመው ለማነጋገር በመሰለ መልኩ ከያዝዋት በርበሬ ዘግነው በማውጣት አይኑ ላይ በመርጨት እዛው ሲደናበር መሣሪያ ማርከው ብዙ የወያኔ ታጋይ ገድለዋል። ወደ ቤታቸው የሚመጣ ታጋይም በርበሬ በውሃ በጥብጠው የሚበላ የሚጠጣ አቅርበው ደህና ነው ብሎ ሆዱን ሲሞላ፤ የበጠበጡት በርበሬ አይኑ ላይ በመድፋት የታጠቀው መሳሪያ ማርከው ታጋዩም በድምፅ አልባ መሳሪያ ይገድሉታ፤ በዚሁም ተገድሎ የጠፋ የወያኔ ታጋይ ብዙ ነው።
በ1973 ዓ.ም . በተለያየ መንገድ የተገደሉ ከማስታውሳቸው ውስጥ፤ በህዝብ ግንኙነት የነበሩት፤ አለማየሁ፤ብርሃነ፤ ፍስሃ፤ ገብረተንሳይ፤ ነጋሽ፤ አማረ፤ ደስታ የተባሉና ሌሎችም ብዙ ተገድለዋል። እነዚህን የጠቀስኩት ከማውቃቸው ነው። በወያኔ ታጋይ ሰራዊትም በተለያዩ መንገዶች በህዝቡ የተገደሉም ብዙ ናቸው ከማስታውሳቸው ለመጥቀስ ገብረ ሥላሴ፤ በላይ፤ ፍጹም፤ ካህሳይ፤ ነጋሽ፤ ገረግዚሄር፤ አባይ፤ አበበ፤ ጸጋይ፤ የሚባሉ ህዝቡን ለመግደል በቡድን በቡድን ተከፋፍለው ሲንቀሳቀሱ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብም በየጫካው ተደብቆ በማድፈጥ የገደላቸው እነዚህን አስታውሳለሁ። የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት ህዝብ የሚቻለውን ሁሉ አቅሙ በፈቀደለት መጠን ህ.ወ.ሓ.ት. ወያኔን ከማጥቃት ባለው መሣሪያ እየተጠቀመ ወደ ኋላ ሳይል ጀግንነቱን ያስመሰከረና ያሳየ ህዝብ ነው። እኔ ባለኝ እምነት ይህ ኩሩ ጀግና ህዝብ ከወያኔ ፋሽሽት ቅኝ ገዢ አረመኔ ስርአት እየታገለ የመጣና ባለኝ እምነት መሠረት እውነትም የኢትዮጵያ መድህን ጠባቂም ነው። ተስፋ ሳይቆርጥ ከ1972 ዓ ም. አንስቶ እስከ ዛሬዋ ዕለት የማንነት ጥያቄው አድማሱን በማስፋት ወያኔ በማጥቃት ተሰማርቶ ይገኛል። በመሬቴ ላይ እሞታለሁ እንጂ ትወልድ ቦታየ አለቀም ያለው በ1969 ግንቦት ወር የተጀመረው ጥቃት እስከ ዛሬ ድረስ ቀጥሏል። ይህ የሰሜን ጎንደር ህዝብ በወያኔ እየሞተ እየተገደለ ማንነቴን አሳልፌ አልሰጥም ብሎ 42 ዓመት ሙሉ ከተሓህት-ህወሓት ዘራችንም ብታጠፉ አንድ ሰወ እስኪቀር ማንነታችን አሳልፈን አንሰጥም እኛ አማራ ጎንደሬዎች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም፤ ብሎ እስከ አሁን ድረስ በማንነቱ የማይደራደር ማንነቱን አሳልፎ የማይሰጥ ኩሩ ኢትዮጵያዊ አማራ ነው።
በምሬት እየታገለ የሚገኝ የጎንደሩ ህዝብ ከቀን ወደ ቀን ጥንካሬው በግልጽ እየታየ ነው። በየትም ቦታ የተገኘ አማራ እንዲገደል ህ.ወ.ሓ.ት. ያወጀው በ1969 ሲሆን፣ በትግራይ ውስጥ የሚኖሩ አማራዎችም ከየቦታው እየተለቀሙ እንዲገደሉ አምስቱ የተሓህት አመራሮች፣ አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ ስብሃት ነጋ አድርገዋል። ትግራይ የትግራዮች እንጂ የሌላው መጤ ቦታ አይደለችም፣ ስለሆነም ማንም የትግራይ ተወላጅ ያልሆነ ከትግራይ ይውጣ ተብሎ እንዲታወጅም ያደረጉት እነዚሁ ናቸው። በአዋጁ መሰረትም አማራው በነቂስ እየተፈለገ ተገደለ፣ እነዚህ ይህ ውሳኔ የተላለፈባቸው ከትግራይ ተጋብተው ልጆች ወልደው ያሳደጉም ናቸው፤ ያመለጠውም ሂወቱና ቤተሰቦቹን ይዞ የሸሸም ብዙ ነው። ይህ የተመለከተና ያየ የትግራይ ህዝብም ወያኔን አወገዘ፤ መሬታቸው ነው አይወጡም፤ ይህ የኢትዮጵያ ቦታ ነው፤ ማነው ወጪ ማነውስ አስወጪ፤ ከፈለጋቹህ ወያኔዎች ውጡ እያለ ከአማራው ወንድሙ ጋር ቆመ። በየቦታው ፀረ ወያኔ እንቅስቃሴ ተነሳ፤ ወያኔም በየቦታው ይህ እንቅስቃሴ የታዩባቸው ቦታዎችን በህዝብ ግንኙነት ክፍል በኩል በፀረ ወያኔ ፖሊሲ ተንቀሳቅሰዋል ያላቸውን የትግራይ ሰዎች አንድ በአንድ እየለቀመ ሓለዋ ወያነ በማስገባት ደብዛቸው አጠፋቸው፤ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
ተሓህት-ህወሓት ይህን ሁሉ በሰሜን ጎንደር አማራው ኅብረተሰብ ላይ ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈጽም እጃቸውን ለወያኔ የሰጡ የኢህአፓ አባላት የነበሩ፤ ታምራት ላይኔ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ በረከት ስምኦን፣ ዮሴፍ ረታ፣ መለሰ ጥላሁን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ታደሰ ካሳ፣ ሙሉአለም አበበ፣ ወዘተ ይገኙበታል። ከወያኔ ህወሓት ጋር በመተባባር የሰሜን ጎንደር፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት ወዘተ የቀድሞዎቹ ኢ.ህ.ዴ.ን. በህ.ወ.ሓ.ት. አምሳልና ቡራኬ ተጠፍጥፈው የተሰሩ ተላላኪዎች የዛሬዎቹ ብአዴን አካባቢው ለብዙ ጊዜ የቆዩበትና የሚመሩበት ስለነበሩ ሕዝቡን በነቂስ ስለሚያውቁት አካባቢ እየመሩ ለወያኔ ጥቃትና የዘር ማጥፋት ወንጀልም ተባባሪ ሆነዋል። ወያኔን እየመሩ የሰሜን ጎንደሬውን አማራ አጥቅተውታል። ስለሆነም በማራው ላይ የደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል በተለያዩ የጥቃት ዘዴዎች በህወሓት የተፈጸመው እነዚህ የብአዴን አመራር ከህወሓት አመራር ጋር አብረው ተጠያቂ ናቸው።
በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ጥቃት፤ ሃብት ንብረት ዘረፋ፤ ለሚደርሰው ማንገላታት ሰላማዊ ዜጋው ተይዞ ለእስር የሚዳረገው በሕዝብ ግንኙነት በኩል ጥናትና ሪፖርት ነው። መኮንን ዘለለው ለመጀመሪያ ጊዜ በህ.ወ.ሓ.ት በኩል ወደ ወልቃይት ጠገዴ የተሰማራው እሱ ነበር፤ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግን አልተቀበለውም። ሪፖርቱ ሲያስተላልፍም ሁሉም ፀረ ተ.ሓ.ህ.ት./ህ.ወ.ሓ.ት ናቸው በማለት ከነስም ዝርዝራቸው ለወያኔ ፖሊት ቢሮ (ከ100 በላይ ሰዎች ሴቶችም አሉበት) ቀስ በቀስ አንድ በአንድ ብስራት አማረ በሚመራው አፋኝ ቡድን ተለቅመው በቡምበትና ሱር ሓለዋ ወያነ ገብተው ጠፍተዋል፤ ንብረታቸውም ሙሉ በሙሉ በወያኔ ተዘርፎ ባዶ ቤት ቀርቶዋል። የዚህ ሁሉ ተጠያቂው ስንመለከት፣ መኮንን ዘለለው ነው። በዚህም ላይ የሚጠየቁ መረሳ ረዳ፣ አጽብሃ ሃይለማሪያም፣ ፀጋይ በርሄ (ሃለቃ)፣ መኮንን የአዲረመጽ ሕዝብ ግንኙነት፣ አርአያ ወርቅነህ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ቀሺ ታደሰ፣ መሃሪ ግብርገርግስ፤ ሃለቃ ታደለ አለምሰገድ፤ መብራት በየነ፤ ወዘተ ናቸው። እነዚህም አንኳር ተጠያቂ ናቸው።
ገብረመድህን አርአያ፣ ፐርዝ፣ አውስትራሊያ
በሚቀጥለው ዕትም “የህወሓት ፕሮግራም” በሚል ርዕስ ሃተታ እናቀርባለን።
ሰዎች!! የንባቡን ርዕስ ተመልከቱ!! ወይን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከመጀመርያውም ቢሆን ዓላማው ኣልነበረም፣ ባይሆን ሻቢያ እንጂ!! የኣሁኑ የሃገራችን ሁኔታን ስናስተውል፣ ዕውን ወይን ናት ወይ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሳች??? ከሆነስ፣ ምን ላይ ታየ?? በሻቢያስ?? ሕዝብ ይፍረድ!!! ይህ ከላይ ያለው ትንታኔ ከሻቢያ የቀረበ የማባበያ ወይም የመሸንገያ የዱቄት ከረጢት ነው። እንጎቻውን የተቀማ እረኛ የሆነብን ሻቢያ እንጂ ወይን ኣይደለችም!! የሻቢያ ቅጥፈት፣ ሰሞኑን እያየን ያለውን በሱዳን ድንበር መቀበል ያቃታት ሻቢያ ሸክሟን ወይም የበጋ ያረጀ ልብሷን ልትወረውርልን ትፈልጋለች።
ጥንትም እኛ ነበርን ባቀብ ቁልቁለቱ
ዛሬ ዘመኑብን (ተነሱብን) ወሬ ሊያካትቱ!!
የአገራችን ችግር ምንጩ በቅድሚያ ህወሓት ነው። ቀጥሎ፣ የህወሓትን ስውር ደባ መቋቋምና ሕዝቡን በአገራዊ ራእይ ዙሪያ ማስተባበር የቻለ መሪ አለመገኘቱ ነው። በመጨረሻም፣ አድሎአዊ አስተዳደር ነው። ከላይ የተዘረዘረው የሥልጣን ሽሚያ ያመለክታል። ሆኖም ሥልጣንና ጥቅም በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ብቻ አይደለምና፣ በየሚንስቴር መ/ቤት፣ በሁሉም ደረጃ ይፋ ተደርጎ ይህን ለማስቆም ብሔራዊ አካል መቋቋም ይኖርበታል። በአየር መንገድ። በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር። ወዘተ። በኢትዮጵያ ስም በዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በየቆንስላዎች ብቃት ያለው ዜጋ ሳይወዳደር የህወሓት ሰዎች ብቻ መመደባቸው መቆም አለበት። ቴድሮስ አድሃኖም፣ ሙሉ ቀጸላ፣ ሐዲስ ታደሰ፣ መሐሪ ታደሰ፣ አበበ አእምሮ ሥላሴ፣ ወዘተ፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ለውድድር እድሉ ሳይሰጣቸው የተሾሙ ናቸው። ብቃት ካለውና ለሌላውም እድሉ እስካልተነፈገ ትግሬ አማራ ኦሮሞ መሆን ቁምነገር አይደለም። ቴድሮስ ጤና ጥበቃና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የሆነው በችሎታና በልምድ ከርሱ የላቁ ጠፍተው አይደለም። የዓለም አቀፍ ጤና ዳይሬክተርነቱን ለማግኘት ከመንግሥት ካዝና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠር ገንዘብ ወጥቶ ነው።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለምሳሌ፣ በአማራ ወይም በኦሮምያ ክልል ኗሪ የሆነ ንግድ መክፈት አይፈቀድም። ለትግራይ ኗሪ ግን ይፈቀዳል። ማንም ትግራይ ሄዶ ንግድ ማቋቋም አይችልም። ይኸ መቅረት ይገባል። በአሁኑ ወቅት በተለይ ከ18 ዓመት ወዲህ ብዙ የትግራይ ተወላጆች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ኢኮኖሚውንና ፖለቲካውን ተቆጣጥረውታል። ይህ መቆም አለበት። ለሁሉም እኩል እድል መሰጠት አለበት። በጋምቤላም ይኸው ነው። ጥቅም ባለበት ሁሉ። የአካባቢው ኗሪ ግን ከነበረበት ብዙም ፈቅ አላለም። የሚገርመው፣ የትግራይ ተወላጆች የሰበሰቡትን ሃብት እዚያው ክልል እንደማልማት ትግራይና አዲስ አበባ ቤት ይሠራሉ፣ ወደ ውጭ በውጭ ምንዛሪ ያሸሻሉ። ሥራ ፈጥረናል ይላሉ፤ ከሚያሸሹት ሃብት አንጻር ይኸ ኢምንት እንደ ሆነ መገመት አያዳግትም።
አንዳንድ ሰዎች፣ ይህማ አንድ ዘር (ትግራይን) መጥላት ነው ይላሉ። አይደለም። በዘር አስተዳደር ክልል የጀመረው ህወሓት መሆኑን አንርሳ። ስለዚህ እርሱ ባመጣው አሠራር መጫወት ተገቢ ነው። የትግራይን ሰው መጥላት ልክ አይደለም። ማንንም በጎሳው የተነሳ መጥላት አግባብ አይደለም።
ሰላም አውቶቡስ እንመልከት። ድሮ አንበሳ አውቶቡስ በደንብ ከተማውንና ክፍለ ሃገሩን ያዳርስ ነበር። ህወሓት የክፍለ ሃገሩን አስቁሞ በራሱ ድርጅቶች በኩል ተቆጣጠረው። ሰላም አውቶቡስ የሚገጣጠመው በሜቴክ ነው። ሜቴክ ሌላ የህወሓት ድርጅት ነው። መሆን ያለበት፣ ቢያንስ ቢያንስ፣ ሰላም አውቶቡስ ወደ አማራ ክልል ወይም ኦሮምያ፣ ወይም ቤንሻንጉል መስመር ሲሠማራና ክልሉን ሲሻገር ለአውራ መንገዱ ቀረጥ መክፈል ይኖርበታል፤ የክልሉ ኗሪዎች በሾፌርነት፣ በቲኬት ቆራጭነት መቅጠር ይገባል።
ህወሓት የሚደጋግመው ተረት አለው። ከደርግ እሥራት መስዋእት ከፍዬ ሕዝቡን ነጻ ያወጣሁት እኔ ነኝ እያለ። ስድሳ ሺህ የሚደርስ የትግራይ ወጣት መስዋእት አድርጌ ይላል። እውነት ነው? ስንቱ የትግራይ ወጣት በህንፍሽፍሽ እና ከትግራይ ሊግ፣ ከሻቢያ፣ ከጀብሃ፣ ከኢሕአፓ ጋር በተካሄደው የርስበርስ ጦርነት ተማገደ? ደግሞስ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ሳይሆን ለትግራይ ሪፑብሊክ ሲዋጋ ከርሞ በለስ ሲቀና በአሜሪካኖች ድጋፍ ሥልጣን ያዘና ለማረሳሳት ይሞክራል። ለማንኛውም፣ ለነጻነት ታገለ እንኳ ቢባል አሁን ይከፈለኝ፣ ብዘርፍ በወንጀል ብሰማራ መብቴ ነው ማለት ምን ትርጉም አለው?
አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ቂም በቀል ትተው፣ ጦር መማዘዝ ትተው፣ ለእኩልነት መታገል አለባቸው። እነ ለማ መገርሳ በወከላቸው ህዝብ ፊት የክልላቸውን ጥቅም ማስከበር መብታቸው ነው። በጠራራ ፀሐይ ህወሓት ቡናውን ወርቁን ከሰሉን የጋማ ከብቱን ጫቱን ዐረብ አገር የሚላኩ እህቶቻችንን፣ ለጉዲፈቻ ህጻናትን፣ ምኑን ሲያጋግዙ ዝም ተብለው ከርመዋል። ከንግዲህ መቆም አለበት።
በአዲስ አበባ እና አካባቢው በልማት ስም ሕዝብ አፈናቅለው ለህወሓት መሪዎች (እንደ ቴዎድሮስ፣ ተስፋሚካኤል፣ ወዘተ) የተላለፈው መሬት መመለስ አለበት። አላሙዲ በጠራራ ፀሐይ ህወሓትን እየቀለበ የዘረፈው መቆም አለበት። አላሙዲን ባለበት ክልል ያለው መስተዳድር ውሎችን እንደ ገና መርምሮ ለአካባቢው ሕዝብ በሚጠቅም መንገድ ማቃናት አለበት። “ፌዴራል” ነው በሚል ሰበብ የሚካሄደው ሌብነት መቆም አለበት።
ኦሮምያ ከአማራ ጋር ያለውን ቁርኝት የበለጠ ማጠናከር አለበት። ወደ ኋላ መመለስ የማንችለውን የድሮ ወሬና ቂም ትተን የዛሬውንና የነገን ትግል ማሸነፍ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። የኦሮምያ መሪዎች እነ ሌንጮ ለታ ካለማስተዋላቸው የተነሳ የህወሓትና የሻቢያን ምክር ሰምተው አንድ ትውልድ ለድንቁርና ማግደዋል። አማርኛ ሆነ እንግሊዝኛ ቋንቋ መማር ለመግባቢያና በአካባቢው ሥራና ፖለቲካ ለማሳተፍ ቁልፍ ሆኖ ሳለ፣ አማርኛ የጨቋኝ ቋንቋ ነው በሚል ወሬ ትውልዱን አራቁተዋል። ሌንጮ ራሱ በኦሮምኛ እንጂ በአማርኛ አልናገርም ያለበትን የጥጋብ ዘመን አስታውሳለሁ። የአማርኛ ቋንቋ እውቀቱ ከአማራ ያላነሰ ሆኖ ሳለ። ትግሉ በሁሉም መስክ በእኩልነት ዙርያ መሆን አለበት። ለዚህ የሚያስፈልገው መስዋእት የሚከፍሉ፣ ለጥቅማቸው የማያጎበድዱ መሪዎች ነው። ከዚህ ቀደም ያልታየው የሕዝቡ ከዳር ዳር መነሳት ነው። ህወሓት ሳያስበው የራሱን ጉድጓድ ቆፍሯል። ሕዝብ ከተንቀሳቀሰ የጦር መሳሪያ ብዛት አይገድበውም። ይኸ በታሪክ የተመሠከረ ነው። ህወሓት በፍርሃት መግዛት ሞከረ፣ አሁን ግን ተጋልጧል። በኦሮምያ ደም አፈሰሰ፣ በአማራ ደም አፈሰሰ፣ በወሎ ደም አፈሰሰ። የፈሰሰው ደም ሕዝቡን አስተሳሰረ። አሁን መመለስ አይቻልም። አርባ ጄኔራሎችን ሲሾም ህዝቡ አንተ ሞላጫ አጭበርባሪ ማንን ታጭበረብራለህ? አለው። ለማ መገርሳ እንዳለው፣ 6 ሚሊዮን ቄሮ ምን ልታደርግ ትችላለህ? የትግራይ ህዝብ ቢቆጠር 4 ተኩል ሚሊዮን ነው! አማራ ቴዲ አፍሮን ጋበዘ። የቴዎድሮስን ሐውልት አስመረቀ። ሕዝብ መመለስ አይቻልም። ኢሳት ሆነ አገር ወዳድ ድርጅቶች ከላይ የዘረዘርኩትንና ሌላም ማስረጃ በአጣዳፊ መሰብሰብ መጀመር አለበት። ለታሪክና ጊዜው ሲፈቅድ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀት ጊዜው አሁን ነው። ኢኮኖሚክስ ችሎታ ያላቸው በዚያ መስክ ይሰማሩ። ፖለቲካ፣ ፋይናንስ፣ ትምህርት፣ ወዘተ ሁሉም በየፊናው ተደራጅቶና ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ አለበት።
I like Gebremedihin Araya,what he wrote about the situations,I know Ataklti Ketsela from Mekelle,his younger sister was my classmate before the family left to gonder at the end years of the 1950,she was very claver,compating with the clever students of the class,she became important person,that is what I heard,she was about 13 at the time.They were from the most outstanding family in the town.
Tadesse,
Do you know Hailemariam Ketsela too who now lives in Dallas, Texas? I believe he is the younger brother of the late Dr. Ataklti. He told me that he grew up in the Chewa Sefer area of Gonder. Their father was an aristocrat from Aksum and I am not sure what took them to Gonder.
Gebremedhin Araya is a patriotic man and I am an eyewitness to some of the killings disappearances that he is talking about. I have always tried to tell people that TPLF is an embodiment of Satan but no one believes it. I am from Tigrai but I have never ever ever ever supported Woyane because I knew how diabolical they are. I was very young during the time when TPLF raided the little town In which I was born and shortly, they started rounding up people from all walks of life; young and old. Once they have been placed in the underground dungeon, those victims never returned. The reason for the arrest is usually that the victims were found to be “collaborators” or “spies” Not true. The real reason behind the disappearance is in fact, in order to instill fear among the people. Can you imagine innocent people being rounded up and murdered just to set the stage hat Woyane is a power to be feared and reckoned with. I left the town within a year and went to Mekelle and although none of the victims were my relatives, I never recovered from the tragedy. I was so subdued and still cry for to this day. God of Ethiopia is about to pronounce his judgment over these satanic group of bandits called Woyane.
May be also 9/10 like me.
የሚገረመው እኮ አቶ ገብረ መድህን ከላይ ብስምና በፎቶግራፍ አስደግፈው ካወጧቸው ግለሰቦች ውስጥ አንዱ የአረናው ዋና መሠራች ነኝ ባዩ
ገብሩ አስራት በቅርቡ በ VOA “ኑ እንወያይ” በሚለው ፕሮግራም ላይ አንዱ ተወያይ ሆነው የቀርቡ ሰው ነበሩ። ፓርት 2 ይቀጥላል ተባሏልና ያኔም ይመጣሉ አቶ ገብሩ አስራት። በመጀመሪያው Part 1 ላይ በቀረቡበት ወቅት ያስሙት “የፈሲታ ተቆጢታ” አይነት የልነጣ ንግግር እንዲህ የሚል ነበር።
” አሁን በየቦታው የሚታየው በተለይም ዘርን ያማከል ግጭት ” በጣም የሚያስጨንቅና በእግር ኳስ ሜዳ ሳይቀር በዘር ላይ የተመሠረት ግዲያ መካሀዱና መታየቱ አሳፋሪ ነው ብለው ህዝቡንም ለመሳደብ መክረዋል አቶ ገብሩ አስራት። እነ አረጋዊ በርሄማ የ ወለቃይት መሬት በ “ሬፈረንደም” ይፈታል እያሉ ሚዲያ እየፈለጉ ያንኑ መሠሪ ደርጊታቸውን ሲያስተጋቡም አይፍሩም።ግን በእጃቸው ያለው ደም አያስቀምጣቸዉምና ሚዲያ ባገኙ ቁጥር መጮኃቸው የሚጠበቅ ነው። አቶ ገብረ መድህን እንዳሉት “ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ዉሻ ብቻ ነው ” እንዳሉት በሰው ደምና በሰው ነብስ ግድያ የተጨማለቁ የማፊያ ቡድን አለቆች ስለሆኑ ነው። እንዲህ በየመደረኩ የሚቀበዘበዙት ። ግን አሁን ጊዜው መሽቶባቸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብና ት.ህ.ነ.ግ/ ሕ.ወ.ሓ.ት ፊት ለፊት ተፋጠው ጉሮቦ ለጉርቦ ተናንቀዋል።
በታሪካችን አፄ ተዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ፣ አፄ ዮሐንስ ከደርቦሾች ጋር፣ ንጉስ ምኒሊክ ከጣሊያን ጋር፣ አጼ ሃይለስላሴ እንዲሁ ከጣላያኖች ጋር፣ ደርግ ከሻቢያና ከወያኔ ጋር ሲፋለሙ የታሪክ ምፀት ሆነና የትግሬው ወያኔ ሕ.ወ.ሓ.ት ደግሞ 27 ዓመት በሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቶ ከህዝብ ጋር ፊት ለፊት እየተሞሻለቀ ይገኛል። ሕ.ወ.ሓ.ት በዐጋዚ ህዝብን ይፈጃል፣ ህዝብ ደግሞ አገሩን እና ራሱን ለመከላከል ከወራሪው ጋር በመፋለም ወራሪውን ህወሃት ሊቀበር ሩጫ ላይ ነው።
God Bless Ethiopia!
አረጋዊ በርሄ በኢሳት ይመስለኛል ቃለመጠይቅ ሲደረግለት በመጀመሪያዎቹ የወያነ የትግል ዓመታት ላይ “ሕንፍሽፍሽ” ወይም ባማርኛ ‘ውዥምበር” በመባል የሚታወቀው ታጋዮች የመብትና የዲሞክራሲ ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት በገፍ የተረሸኑበት ጊዜ ነበር። ትእዛዝ ሰጪው እሱ ራሱ ሰለነበረ ምን ያህል ታጋዮች እንደተረሸኑ በትክክል ያውቃል ከሚገርመው ነገር ግን ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቆ የሞተው ሰው አንድ ብቻ ነው ብሎ ጥያቄውን አድበስብሶ አለፈው። በርገጥ የሞተው ሰው እንድ ሳይሆን ከፍተኛ እልቂት “massacre” ነበር የተፈጸመው። አሁን እነዚህ ግለሰቦች በጥቅም ግጭት conflict of interest ምክንያት ከፖለቲካው አለም ቢገለሉም የጋኔን ጡረተኛ retired demon የሚባል ነገር ስለሌለ ያው አፉ ቂቤ ሆዱ ጩቤ ነገሮች ነቸው። የዳያስፖራ ሚድያ ግን ለምን እንደሚያሞካሻቸው አላውቅም። በሽበትም ቢሆን አንድ ቀን ለፍርድ ቀርበው በሰፈሩት ቁና እንደሚሰፈርባቸው የታወቀ ነው።
የሚገረመው እኮ አቶ ገብረ መድህን ከላይ ብስምና በፎቶግራፍ አስደግፈው ካወጧቸው ግለሰቦች ውስጥ አንዱ የአረናው ዋና መሠራች ነኝ ባዩ
ገብሩ አስራት በቅርቡ በ VOA “ኑ እንወያይ” በሚለው ፕሮግራም ላይ አንዱ ተወያይ ሆነው የቀርቡ ሰው ነበሩ። ፓርት 2 ይቀጥላል ተባሏልና ያኔም ይመጣሉ አቶ ገብሩ አስራት። በመጀመሪያው Part 1 ላይ በቀረቡበት ወቅት ያስሙት “የፈሲታ ተቆጢታ” አይነት የለበጣ ንግግር እንዲህ የሚል ነበር።
” አሁን በየቦታው የሚታየው በተለይም ዘርን ያማከል ግጭት ” በጣም የሚያስጨንቅና በእግር ኳስ ሜዳ ሳይቀር በዘር ላይ የተመሠረት ግዲያ መካሀዱና መታየቱ አሳፋሪ ነው ብለው ህዝቡንም ለመሳደብ መክረዋል አቶ ገብሩ አስራት። እነ አረጋዊ በርሄማ የ ወለቃይት መሬት በ “ሬፈረንደም” ይፈታል እያሉ ሚዲያ እየፈለጉ ያንኑ መሠሪ ደርጊታቸውን ሲያስተጋቡም አይፍሩም።ግን በእጃቸው ያለው ደም አያስቀምጣቸዉምና ሚዲያ ባገኙ ቁጥር መጮኃቸው የሚጠበቅ ነው። አቶ ገብረ መድህን እንዳሉት “ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ዉሻ ብቻ ነው ” እንዳሉት በሰው ደምና በሰው ነብስ ግድያ የተጨማለቁ የማፊያ ቡድን አለቆች ስለሆኑ ነው። እንዲህ በየመደረኩ የሚቀበዘበዙት ። ግን አሁን ጊዜው መሽቶባቸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብና ት.ህ.ነ.ግ/ ሕ.ወ.ሓ.ት ፊት ለፊት ተፋጠው ጉሮቦ ለጉርቦ ተናንቀዋል።
በታሪካችን አፄ ተዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ፣ አፄ ዮሐንስ ከደርቦሾች ጋር፣ ንጉስ ምኒሊክ ከጣሊያን ጋር፣ አጼ ሃይለስላሴ እንዲሁ ከጣላያኖች ጋር፣ ደርግ ከሻቢያና ከወያኔ ጋር ሲፋለሙ የታሪክ ምፀት ሆነና የትግሬው ወያኔ ሕ.ወ.ሓ.ት ደግሞ 27 ዓመት በሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቶ ከህዝብ ጋር ፊት ለፊት እየተሞሻለቀ ይገኛል። ሕ.ወ.ሓ.ት በዐጋዚ ህዝብን ይፈጃል፣ ህዝብ ደግሞ አገሩን እና ራሱን ለመከላከል ከወራሪው ጋር በመፋለም ወራሪውን ህወሃት ሊቀበር ሩጫ ላይ ነው።
God Bless Ethiopia!
then whydo voa..esat and all et. news media even give the chance to speak for the likes of gebru asrat …tamrat lyne…siye abraha….these individuals will face our majestict court when the time comes….fool me once …and fool me twice….by godstop patronizing these sob’s
>›ክቡር ገብረመድክን አርዓያ በእውነት ተናጋሪነታቸው ተወዳዳሪ ያልተገኘላቸው ጥሩ ትግሬ ናቸው።…ከላይ እንደተጠቀሰው በአማራ ነን ባይ የሚዘወሩ ሚዲያዎች ድረገፅ ባለቤቶች ግን አማራ ጠል የሹምባሽ ልጅ ፡ የልጅ ልጆችን፡ የታሪክ ላጲሶችን፡ ‘በመናገር ነጻነት’ ሰበብ መድረክ እየሰጡ ማሰደባቸውን በፖለቲካ ተንታኝ ውዳሴ ሰርጎገብ በታኝነታቸውን እንዲቀጠሉ ተራድተዋል ይረዳሉም…ትግሬው ሰው በመሆኑ፡ በኢትዮጵያዊ ዜግነቱም ስለአማራው መፈናቀል፡ መገረፍ፡ መታሰር፡መጨፍጨፍ ሲናገር… ማን ውክልና ሰጠህ? እያሉም ሲሳደቡ፡ ሲያስፈራሩና ሲያወግዙም ይሰማል። የአቶ ገበረመድክን አርዓያ እና ጥቂት መሰል ሀቀኞች መልካም ሥራ መቼም የሚረሳ አደለም…እያወቁም መሞት አንድ ነገር ነው ለበለጠ መረጃ የሌላውን ታጋይ የመስዋዕት ሥራ አንበው ግፍን ተማሩበት…..መልካም ንባብ! ድል ለተገፋው ሕዝባችን እናመሠግናለን።
“የትግራይ ብሔርተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የነንጨ ነው?
አዲስ መጽሐፍ የገጽ ብዛት 457 2010 ዓ.ም
ደራሲ ጌታቸው ረዳ (2010 ዓ.ም)
ገብረመድህን እኮ በሽተኛ ነው፣ እናንተ የምትፈልጉተን ሰለሚናገርላችሁ ነው ኢት፣ያላችሁት፣ በምንም መልኩ የትግራየን ህዝብ ኣይወክልም፣ ድከሙ ብሎኣችሁ ነው እንጂ ከእንግዲህ ዳግም የክልሎች ድንበር ኣይከለሊም፣ ብታስቡይ ከእንግዲህ የሶማሊያ፣ኣፋር፣ደቡብ፣ኦሮሚያ ዳግም የከለል ቢባል እሺ ይላል? ሌላ ጣጣ ያስመጣል፣ትግራይም እንዲሁ የተከለለው በታሪክ ኣንጻር እንጂ ተቀምቶ ኣይደለም፣
ገ.መድህንን የሚሰማው የለም እንድ ነው ኣብራሃ ያየ አኮ ነግሮኣችሁ ነበር እብድ ነው ብሎ
አቶ አበበ – እናውቃለን እንዳንተ ያሉት ወስላቶች በድርጅት ስም ሚስጢር እንደያዙ አፈር እንደሚመለስባቸው። በሽተኛው አንተ እንጂ የወያኔን ገመና ለዘመናት የሚያጋልጡት እውነተኛ የትግራይ ልጆች አይደሉም። ወያኔን ከትግራይ ህዝብ ለይቶ ማየት የሚያስፈልገውም ለዚህ ነው። እንዳንተ ያሉ የጊዜው ተጠቃሚዎችንና ተለጣፊ (አጨብጫቢ) ድርጅቶችን ህዝባችን ለይቶ ያውቃቸዋል። በበረሃ ከጀርባቸው በወያኔ በጥይት ተመትተው የወደቁ ብዙ ናቸው። የዶ/ር አታክልቲ ግድያ ደግሞ በማን፤ ለምን እንዴት እንደተቀናበረ ከአሁን በፊት የምናውቀው እንጂ አዲስ ወሬ አይደለም። የተገደለው በራሱ ማሰብ በመቻሉና ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ወያኔ የተለመውን በመቃወሙ እንደሆነ ከእርሱ በህዋላ ወያኔ ግባ መሬታቸውን በበረሃና በከተማ በራሱ የግድያ ቡድን የፈጸመባቸው ነግረውናል። ወያኔ ሰውን መከፋፈል፤ ለአንድ እሳት በመስጠት ሌላው ለነፍሱ ሲሮጥና ሲሞት እያየ የሚስቅ ግዑዝ ፍጥረት ነው። በኢትዮጵያ የደፈረስና የጠራ የረጅም ታሪኳ ውስጥ እንደ ወያኔ ያለ አጥፊ ድርጅቶ የመሪ ቦታ ይዞ አያውቅም። ወያኔ ከጣሊያን ወራሪ የከፋ ድርጅት ነው። ዛሬ በሃገሪቱ የአመራር ቆንጮ ተቀምጠው የሚናጥጡት ባለስልጣኖች እጃቸው ባለፈና በዛሬ የሰው ደም የተነከሩ ናቸው። አንተ የምትኩራራበት ወያኔ አሽዋ የሞላ ጆኒያ ለነጭ የተራድኦ ድርጅት በማሳየት ዶላር እየሰበሰብ ለራሱ ጮቤ ይረግጥ የነበረ ድርጅት ነው። የትግራይ ህዝብ በሰሙ የተነገደበት ህዝብ ነው የምንለውም ከሚታይ እውነታ እንጂ እንዳንተ በጭፍን ጥላቻ አይደለም።
ኢትዮጵያዊያን ሶማሊዎችንና ኦሮሞዎች እርስ በርስ እንዲተራረድ የሚያደርገው ወያኔ ራሱ ነው። ከብት እረኛ ይመስል ክልል፤ ቅጥር፤ ኬላ እያለ ህዝባችንን በመከፋፈል የሚያፋጀው ወያኔ አረመኔ ድርጅት ነው። በግፍ ያሰራቸውንና እፈታለሁ እያለ የሚለፈውን የፓለቲካና የህሊና እስረኞች የይቅርታ ፈላጊ ፊርማ እንዲፈርሙ መጠየቁ ምን ያህል የወያኔ አሰራር ወልጋዳ መሆኑ ያመላክታል። ምህረት ሲደረግ ምህረት ነው። ወያኔ ግን የሚያስበውም ክፉ ብቻ በመሆኑ በየምክንያቱ አሳቦ ለማሰር እንዲመቸው ሰው ያልሆነውን ነኝ ብሎ እንዲፈርም ያስገድዳል። ወያኔ ምህረትን አያውቅም፤ ራሱም ምህረትን አያገኝም። ወያኔ ሃገር የማፈራረስ አላማው ገና ከጅምሩ እንደነበር እናውቃለን። ዛሬም ትግራይን ገንጥለን በሰላም እንኖራለን እያለ የሚለፈው በጠበንጃው ታምኖ ነው። ሰላም ግን የለም። የወያኔና የሱዳን ሽርክናም ጊዜአዊ ነው። የቱንም ያህል የሃገራችንን መሬት እየቀረሰ ለሱዳን ያስረክብ ዘላቂ ሰላም በወያኔና በሱዳን፤ በሻቢያና በወያኔ አይኖርም። ያው ከሌላው የሃገሪቱ ህዝብ ጋርም ደም የተቃባ አጥፊ ድርጅቶ በመሆኑ ሰላም አይኖረውም። ሞቶ የተነሳው ኢትዮጵያዊነትም በውጭም በሃገርም ውስጥ ያብባል። የወያኔንም የማይቀር ሞት ያፋጥናል!!
Is this so called Abebe Gela turned out to be a seye
apologist or what.
I heard him and some of the revisionist reactionary
elements who were dreaming to use G7 as cover for
their evil actions and conspiracies being apologetic
to Seye and his revisionist reactionary faction within
the TPLF. Why ? Abebe G. ? Isn’t that a shame ?