• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የትኛው ኦህዴድ?

February 16, 2018 06:01 pm by Editor 8 Comments

  • በደም ወይስ በድርጅት አባልነት? ወርቅነህ ገበየሁ ወዴት ወዴት?

ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን ፍላጎት መኖሩን፣ እሱም ቦታውን እንደሚፈልገው የጎልጉል የመረጃ አቀባዮች ጠቆሙ። ወርቅነህ ቀደም ሲል ከነበረው ሃላፊነት፣ ኦሮሞ አይደለም በሚል የሚቀርብበት ክስ፣ በ1997 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለተካሄደው ግድያ ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው በሚል ስለሚወነጀል ኢህአዴግ ራሱ የበጠሰውን የሕዝብ እምነት ሊቀጥል አይችልም የሚል ስጋት መኖሩንም አመላክተዋል።

ቀደም ሲል በጄኔራል ማዕረግ የፌደራል ፖሊስ አዛዥ የነበረው፣ ከዚያም በጁነዲን ሳዶ እግር ተተክቶ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር የሆነው በኦሮሚያ ማሊያ ለትግራይ የሚጫወተው ወርቅነህ፣ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነትም የታጨው የኦሮሞን ሕዝብ ለማባባበል ነበር። እንደታሰበው ሳይሆን ግን በተሾመ ማግስት የኦሮሞን ሕዝብ ሊወክል እንደማይችልሉ ማስረጃ እየቀረበበት ሲተች ነበር። በወቅቱ አንዱ መስካሪ በዩኒቨርስቲ ፊደል ያስቆጠረው ዶ/ር መረራ ጉዲና ነበሩ። አንዳንዶች የመረራን እስርም ከዚሁ ጋር ያያይዙታል።

ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኦሮሞ ብሄር መሆን እንዳለበት በአብዛኛው እምነት ቢኖረም ህወሃትን የጨነቀውና ያሳሰበው የእነ ለማ መገርሳና አቢይ አህመድ አቋም ነው። ሁለቱም በህወሓት ደህንነት ተቋም ጥርሳቸውን ነቅለው፣ አፈር ፈጭተው ያደጉትና ኢህአዴግ የፈጠራቸው የበረሃ ልጆቹ የኦህዴድ መሪዎች ቢሆኑም በሕዝብና በፓርቲያቸው ዘንድ ተቀባይ መሆናቸውም ሌላው በሽታ ነው። በተለይ ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ለውጥ የሚሰጡት ዲስኩር የአገሪቱን የፖለቲካ መልከዓምድር እየቀየረው መጥቷል።

በዚህ መመዘኛ፣ በዳግም ውልደት በያዙት አቋም በህወሃት ደጋፊዎች ዘንድ ክፉኛ የሚጠላውን ለማ መገርሣን ወደ ጠቅላዩ ሃላፊነት ማምጣት ዘርፈ ብዙ ችግር ስለሚያስከትል ሌላ የኦሮሞ አማራጭ ሲፈለግ የተገኘው ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ነው።

ሻሸመኔ ያደገው የዛሬው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ይህንኑ በመረዳት ይመስላል አጋጣሚውን በመጠቀም ኦህዴድን በድርጅት፣ ህወሃትን በደም ወክለው የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ለመያዝ ዘመቻ የጀመረው። የጎልጉል የመረጃ ሰዎች እንደሚሉት ወርቅነህ ራሱን በማጨት “ረጅም መንገድ” መጓዙን ለቅርብ ወዳጆቹ በሚገባቸው መልኩ አመልክቷል። ዝርዝሩን ወደፊት እንደሚያቀርብላቸው መረጃውን ያቀበሉዋቸው ቃል እንደገቡላቸው ለጎልጉል ተናግረዋል።

የዕለት ጉርሱን ለማግኘት በሚሊዮን የሚቆጠር በሚሰቃይባት ኢትዮጵያ፤ ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ከ300 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚሸጠውን ሮሌክስ ሰዓት እያብለጨለጨና አለባበሱን በማሳመር የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከሆነ ወዲህ ለከፍተኛ ሥልጣን ራሱን እያዘጋጀ እንደሆነ ከመ/ቤቱ አካባቢ የሚያፈተልኩ መረጃዎች ያመለክታሉ። በለስ ከቀናውም አሁን በሚያደርገው የአሜሪካ ጉብኝት የጌቶቹን ይሁንታ ለማግኘትና “አዲሱ መለስ እኔ ነኝ” በማለት ቡራኬ ለማግኘት ደፋ ቀና እንደሚል ከኤምባሲ አካባቢ የመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በቅርቡ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “ከመለስ ሞት በኋላ በዓለምአቀፍ ግንኙነት ላይ የኢትዮጵያ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ቀንሷል” ማለቱንም እርሱ “አዲሱ መለስ” መሆኑን ለመናገር የተጠቀመበት ነው በማለት እንደ አስረጅ የሚጠቅሱ አሉ። ይህ የወርቅነህ እንቅስቃሴ እና የወቅቱ የአገሪቱ ሁኔታ በተለይም “በኦሮሞነት” ካርድ ለመጫወት የሚያካሂደው እንቅስቃሴ ህወሓት ካለው ፍላጎት በላይ ወርቅነህ ለቦታው ራሱን በማጨት ብቸኛ ተወዳዳሪ በማድረግ ራሱን እያነገሠ ነው።

ጎልጉል ባገኘው መረጃ መሠረት ህወሓት አሁን ተገዶም ቢሆን ከፈለፈላቸው ድርጅቶች መካከል ቢያንስ ሕዝብ ሊሰማው የሚችል መሪ መሰየም እንዳለበት በመታመኑ ወርቅነህ ምኞት ብቻ ሆኖ ሊቀር ይችላል የሚል ግምት አለ። “በአቻ ፓርቲዎች”፣ በራሱ በኦህዴድም በኩል ወርቅነህ ላይታጭ እንደሚችል መረጃ አለ። ይህ ከሆነ ደግሞ ለማ መገርሣ ወደ ፊት ይመጣል።

ለማ መገርሣ እንደ አዲስ የኢትዮጵያዊነት አስተማሪ ሆነው ከመጣ በኋላ ህዝብ ቀና ምላሽ ሰጥቶታል። በዚህ አቋሙ ከቀጠለና ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆነ አስቀድሞ የኢህአዴግም ሊቀመንበር ስለሚሆን ጡንቻው ከህዝብ ድጋፍ ጋር እንዳይፈረጥም በህወሓት በኩል ስጋት አለ። ይሁን እንጂ አሁን ካሉት ውስጥ ከለማ በቀር የተሻለ ሰው ወደፊት ሊመጣ እንደማይችል የሚናገሩ የድርጅት ሰዎች መኖራቸውን የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ በላከው መረጃ ላይ አመልክቷል።

ይህ ካልሆነ ደግሞ አናሳ ቢሆንም አብይ አህመድ ሌላው አማራጭ እንደሚሆኑ መጠነኛ ግምት አለ።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: abiy, Full Width Top, lemma, Middle Column, opdo, tplf, workineh

Reader Interactions

Comments

  1. Kemal says

    February 18, 2018 09:01 am at 9:01 am

    What do you mean by saying ” አናሳ ቢሆንም አብይ አህመድ ” ? Are you saying አብይ አህመድ is not an Oromo ? Just curious. Tell us more please!

    Reply
    • Editor says

      February 18, 2018 08:34 pm at 8:34 pm

      Kemal

      Thanks for your comment.

      The statement “ይህ ካልሆነ ደግሞ አናሳ ቢሆንም አብይ አህመድ ሌላው አማራጭ እንደሚሆኑ መጠነኛ ግምት አለ።” contextually talks about the chance for Abiy to be a prime minister from OPDO. It’s got nothing to do with who is.

      What you stated is not even remotely what we stand for.

      Hope this makes things clear.

      Editor

      Reply
  2. Ezira says

    February 18, 2018 05:46 pm at 5:46 pm

    kemal:
    “አናሳ ቢሆንም” ተብሎ የተጻፈው ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት የመምጣቱ ዕድል አናሳ ቢሆንም ለማለት ነው – እኔ እንደገባኝ። እንጅ አንተ እንደገባህ “አንሳ” የሚለው ብሄሩን የሚያመላክት አይደለም። ይሁንና አንተ በመሠለህና በገባህ መንገድ ለጠየከው ጥያቄ ደግሞ መልሱ ግልጽ እና ግልጽ የሆነው ነገር አብይ አህመድ ኦሮሞ መሆኑ ምንም ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም።
    አመሠግናለሁ

    Reply
  3. Tesfa says

    February 18, 2018 06:00 pm at 6:00 pm

    አቶ ከማል – አናሣ/ብዙሃን የሚባል ነገር የለም። ዶ/ር አብይ አህመድ ህዝባችን ከሚወዳቸውና ከሚያከብራቸው የሃገሪቱ የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል ከፊት ከቆሙት አንድ ናቸው። ጎልጉል የመጣጥፉ ባለቤት በመሆኑ የሚሰጥህን ምላሽ አላውቅም። እኔ ግን የገባኝን ትርጉም እንደ አንድ አንባቢ እንሆ። “ይህ ካልሆነ ደግሞ አናሳ ቢሆንም አብይ አህመድ ሌላው አማራጭ እንደሚሆኑ መጠነኛ ግምት አለ” አናሳ የሚለው ቃል በዚህ ዓረፍተ ነገር ላይ አንደተረዳህ ዘርን አመልካች አይደልም። ዶ/ር አብይ የሃገሪቱ መሪ ይሆናሉ የሚለው አስተሳሰብ አናሳ ጉልበት ያለው ይመስላል ለማለት ነው። In English, the content can be put this way.
    The rumors of Dr. Ahmed becoming a prime minster is not as strong as the two mentioned individuals. ከዚህ በዘለለ ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” በምንም የሂሳብ ስሌት ከለማና ከዶ/ር አቢይ ጋር አብሮ ስሙ መጠራት የሌለበት ግለሰብ ነው። እሱን የመሰሉ የወያኔ ወስላቶች ሥልጣን ላይ ከወጡ በምንም መልኩ ቢሆን የሃገራችን ህዝብ አመራራቸውን አይቀበልም። አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” የኦሮሞን ህዝብ አይወክልም። የወያኔ ቅጥረኛ ነው።

    Reply
  4. Editor says

    February 18, 2018 08:39 pm at 8:39 pm

    Ezira and Tesfa

    Greatly appreciate your prompt responses and thank you for being voices of Golgul. We also appreciate your regular readership of Golgul and all the comments you are posting. Our appreciation also goes to all others who comment in favor and against what we post – which includes TPLF diehard fanatics like Mulugeta Andargie – “That which does not kill us, makes us stronger”.

    Regards,

    Editor

    Reply
  5. Alem says

    February 19, 2018 03:09 am at 3:09 am

    Dear Golgul,
    If Workneh is Tigre and not Oromo is true then Opdo should remove him from membership. Otherwise, Tigrigna-speaking Oromo should join the leadership of Tplf. I am not joking.

    Reply
  6. Mulugeta Andargie says

    February 19, 2018 05:27 am at 5:27 am

    ሰዎች!!! እዚህ ጎልጉል ላይ፤ የሚጽፈው ኣንድ፣ ኮሜንት የሚያቀርበው ያው፣ የሚቃወመው እሱው፣ የሚያመሰግነውም እሱው ሆኖብኝ ግራ ተጋብቻለሁ። የጎልጉል ብልጣብልጦች ሁሉ ነገር በስድብ የሚሆን መስሏቸው ማንንም ይዘረጥጣሉ።

    Reply
  7. Destin says

    February 20, 2018 02:10 am at 2:10 am

    Lema is the right person to cooldown the current crisis provided he stands for Ethiopian unity as he is doing until now. If it’s the fake workineh it will be adding more fuel to the current crisis.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule