• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ስለ ለማ መገርሣ ጥቂት ምልከታዎች

January 9, 2018 07:09 pm by Editor 8 Comments

ማሳሰቢያ፤ ከዚህ በታች የሰፈሩት ጽሁፎች በቀጥታ ከተለያዩ ጸሐፍት (በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከሚሳተፉ) የተወሰዱ አስተያየቶችና ምልከታዎች ናቸው እንጂ የጎልጉል አቋም አይደሉም።


ዮሐንስ ሞላ እንዲህ ይላል፤

አቶ ለማ መገርሳ የመንግስት ባለስልጣን ሆኖ በቆየበት ጊዜ ሁሉ ሲያስገድል፣ በሀሰት ሲያስወነጅል፣ ሕዝብን ከሕዝብ ሲያባላ እና በድህነት እንድንሰቃይ ለሙስና ሲያጋፍር ነው የኖረው። ሌላውን የኢህአዴግ ባለስልጣን አስኮንኖ፣ አቶ ለማ እና ዶ/ር ዐብይን ነጻ የሚያስወጣ ምንም ዓይነት ምክንያት የለንም።

ማሽሞንሞን ሳያስፈልግ፥ አቶ ለማ መገርሳ የኢህአዴግ ሽንት ጨርቅ ነው። የአምባገነን ስርዓት ሽንት እንዳይታይ በማድረግ ረገድ የሚጫወተው የዳይፐርነት ሚና ከደረሱብን ጉዳቶችም የሚልቅ እና፣ ለዚህ ግብሩ መጨፈር እና መቀኘታችን ወደፊት ብዙ የሞራል ዋጋ የሚያስከፍለን ነገር ነው የሚሆነው።

ኢህአዴግ በሽንት መጨማለቁን ስላወቀ እና በሕዝብ ጠንካራ ተቃውሞ ስለተናጠ፣ እሱን የሚሰበስብለት እና የሚያቋቁመው ‘poker face’ ሲፈልግ ነው አቶ ለማን ያገኘው። በተቃውሞ ወቅት በታዩ ምልክቶች መሰረት፥ የሽንት ጨርቅ የሚሆነው እና የዘረኝነት ሀፍረቱን የሚጋርድለት የኢትዮጵያዊነት ጨርቅ መሆኑን ስለሚያውቅ፣ እሱን እያወሩ በተለይ ተቃውሞዎቹ ጠንክረው በነበረበት የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችን ልብ የሚያሸፍትለት ሲፈልግ ነው አቶ ለማን ከጉያው ፈልቅቆ፥ ፊት ያዋለው።

መንግስት ከወጣበት ማቅ ለመውጣት እና ዕድሜ ለመግዛት ያለውን ብቸኛ አማራጭ፥ ኢትዮጵያዊነትን ለማቀንቀን ፍላጎት እንዳለው ያየነው ቀደም ብሎ ሽንት ጨርቅ ኀሠሣ ላይ ሳለ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በደነገጉ ማግስት እንኳን “ኢትዮጵያዊነት ላይ አልሰራንም” ብለው በይፋ መናገር ጀምረው እንደነበረ አውስተነዋል። እሱን ተከትሎ፥ ከሌላ ጊዜው በተለየ መልኩ የአድዋ ድል በዓልን በመንግስት ደረጃ በሰፊው ለማክበር ላይ ታች መባሉ እና፣ አድዋ ድረስ ተሂዶ የእምዬ ሚኒልክ ፎቶ በሌለበት በእቴጌ ጣይቱ ፎቶ ብቻ መከበሩም አይዘነጋም።

በኢቲቪ እና ኤፍኤም ሬድዮዎች፥ ዘመቻ በሚመስል መልኩ፣ ሰዎችን ስለብሔራዊ የድል በዓላት እየጠየቁ ከመለሷቸው አሳቃቂ መልሶች ጋር ሳያፍሩ ማስተላለፍ እና በራሳቸው ጊዜ የቦረደሱትን ክፍተት ለመሙላት ፈቃደኝነት ያላቸው እስከማስመሰል ድረስ፣ የተላለፉትን ዝግጅቶችም ተመልክተናል። የነአቶ አባዱላ መግባት እና መውጣት፣ የወ/ሮ አዜብ መታገድም እንዲሁ ካለምክንያት አይደለም። ካለስሌት የሚያደርጉት ምንም ነገር የለም! እኛ ግን በዚህ ሁሉ ሂደት አልፈንም ሣሩ እንጂ ገደሉ እንዳይታየን በ“ኢትዮጵያዊነት” ስም መጥተው በእነሱ ጊዜ ይዘውሩናል።

አሁን ሰሞንኛ ሽውታ እና ትኩሳት ላይ ስላለን፥ ይህን መስማት የሚያስከፋቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ግን እውነቱ ባለበት ነው። የሚናፈቀው ለውጥ እና ከሰቆቃ አኗኗር ለመላቀቅ የሚደረገው ጥረት ለመጓተቱ እና እያንዳንዱ ተስፋ ብላሽ ለመቅረቱ፥ የእኛው ሚና ከፍተኛ ነው።

አቶ ለማ እንዴትም አድርጎ በንግግር ቢራቀቅ ኢህአዴግ በፈቀደለት ልክ ነው የሚንቀሳቀሰው። ገመዱን እነሱ ይዘውት ሲለቁት በረዥሙ ይሄዳል፣ ሲሰበስቡት ደግሞ ይሰበሰባል። ምክንያቱም ታማኝ ወዳጃቸው ነው። አቶ ለማን የመለመለው፣ ያሳደገው እና ጡት እያጠባ ጎኑ ያኖረው ኢህአዴግ ነው። ስለዚህ እሱ የሚናገረው ነገር በሙሉ ኢህአዴግ የሚያውቀው እና ክትትል የሚያደርግበት ነው እንጂ እኛ በገራገርነት እንደምናስበው መንግስት ላይ ነጥብ እያስቆጠረ እና ነጥብ እያስጣለ አይደለም። እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ምንም ነውር የማያውቁ ስለሆኑ፣ የፈለገውን ያደርጉ ነበር። እሱም ያንን እያወቀ የምር ኢትዮጵያዊ ስሜት ካለው ደግሞ፥ አብዮት ለማቀጣጠል እና ተጽህኖ ለመፍጠር ሽቁጥቁጥ የሚሆንበት ነገር የለም።

ሆኖም ግን፥ ለመንግስት ገጽታ ጥሩ ሽፋን ስለሆነ ከእኛ በላይ መንግስት ይወደዋል። (ኮካዎች ቢሰድቡት ለመላ ነው እንጂ ባለውለታዎቹ እንደሆኑ ግልጽ ነው። ሚሚ አባ ዱላን እንዴት እንዴት ስታብጠለጥል እና ወንጀለኛ መሆኑን ስትናገር እንደነበር አይረሳም።) እሱም እዚያ ያለው በስሌት እና በተልእኮ ነው እንጂ ሕዝብ አፍቅሮ ለውጥ ለማምጣት አይደለም። መፍትሄው በኢህአዴግ ዘንድ መሆኑን ለሕዝብ ለማስመስከር የሚተጋ ሀዋርያ ነው። ኢህአዴግ ጠላቱን አይንቅም። በግለሰብ ደረጃ ኑሮውን የሚኖር ጸሐፊ እንኳን እንደ ትልቅ ቁም ነገር አስልኮ ሲያስጠብቅ፣ አፉን ሲለካለት እና ሲያሰቃይ ነው የሚኖረው። የዚያኑ ያህል ደግሞ ከሂሳቡ የሚዛነፍ ወዳጅነት ቢኖርም አይራራም። “አብዮት ልጆቿን ትበላለች” ይሰራል። “ደማችን ፈሶለታል” ብለው በይፋ የሚናገሩለት ወንበር ዙሪያ መዝነው ያላከበዱትን ከፊት አያሰልፉም።

ሰፊው ሕዝብ ግን፥ ባህርዩ ሆኖ ንግግር ያስደምመዋል። ሲሰድቡት እና ሲያንገላቱት ኖረው “የኔ ጌታ” ሲሉት ልቡ በኀዘኔታ እና ፍቅር ትርክክ የሚል ሩህሩህ ሕዝብ ነው ያለን። ከዚህ ቀደም የነበሩ እምነት የተጣለባቸው ሰዎችን ታሪክ ብናይም እንዲሁ በንግግር ተማርከንባቸው ነው እንጂ… ሰው ተቀምሶ አይታይም መቼስ። እንዳንተባበር እና በጋራ እንዳንመክር፥ በአጀንዳቸው ለያይተውን ዞረን እንዳንገናኝ፣ በንግግር ያምታቱናል። ከዚህ ጉድ ይውጡ እንጂ፣ በኢቲቪ በቀጥታ የሚተላለፍ የጠንቋይ ማምለክ እና የድንጋይ ቅቤ መቀባት መርሀ ግብር ከማድረግ እንኳን ወደ ኋላ የማይሉ አፍረተ ቢሶች ናቸው።

መንግስት በእኛ የሆይሆይታ ድጋፍ እና ተቃውሞ ተደጋግፎ ከጉድ እየተረፈ፣ ሲጎነጉን የጎለመሰው ሴራ እንዳይጠልፈው ደርሰን እየፈታንለት አይዞህ እያልነው ነው ያለው እንጂ ከበቃው ድሮ ነበረ። ባልበሰለ እርካታ አባዜያችን (premature ejaculation) ተይዘን፣ በንግግር እየተማረክን ተባብረን አለን። ጠላትን መናቃችን፣ አሳንሰን ማየታችን እና ማጣጣላችን ይበልጥ እንዲፈነጭብንና እንዲያላግጥብን ነው የሚያደርገው።

ጠብ ገጥሞ የቆሰለ አውሬ ይበልጥ ይቆጣልና፥
“አያ በሬ ሆይ
ሣሩን አየህና፣ ገደሉን ሳታይ” እንዳይተረትብን፥ በእነሱ ዘንድ የሚወደስ፣ የሚገጠምለት እና የሚሳልለት መልካምነት ካላቸው እሱን ለእነሱ እንተውላቸውና እርስበርሳችን እንተያይ።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያችንን ይጠብቅልን!

ዮሐንስ ያቀረበውን ጽሁፍ ለተቃወሙ ዮናስ ሐጎስ ይህንን ምላሽ ሰጥቷል፤

  1. ለማ ኦህዴድ በነሙክታር ጊዜ ጭንቅ ውስጥ ሲገባ ከውጭ አፈላልጎ ያስመጣው አዲስ ሰው አይደለም። ለረዥም ጊዜ በደህንነቱ መ/ቤት ሲሰራ የኖረና ባሳየው ታማኝነትና በፈፀማቸው ወንጀሎች እየተለካ ወደ አመራርነት ደረጃ ያደገ ግለሰብ ነው። ለዚህ ፍጥጥ ያለ እውነታ ምን የሚሉት ማስረጃ ይቅረብ?
  2. ዶክተር አቢይ ይህ ዜጎችን እስከ ውጭ ሐገራት ድረስ እየሰለለ ነፃነት ያሳጣውን የኢንሳ ደህንነት ተቋም ከምስረታው ሐሳብ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ በዳይሬክተርነት ሲያገለግል የኖረ ሰው ለመሆኑ ማስረጃ እናቅርብ?
  3. ኢህአዴግ ከለማ በፊት ኢትዮጵያዊነት ላይ አልሰራንም ብሎ “ዘመኑ የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን ነው!” በሚል መርሃ ግብር ለአንድ ዓመት ያህል የጆሮ ታምቡራችንን ሲያደነቁር እንደነበረ ማስረጃ ይቅረብ?
  4. አቶ ለማ ቃላት አሳምሮ ዲስኩር ከመናገር ውጭ ምንም የሰራው አንዳችም ተግባራዊ ነገር ስላለመኖሩ ማስረጃ ይቅረብ?

አንዳንዴ የሰውን ፅሁፍ ከማጣጣል እውነታውን እየመረረንም ቢሆን መዋጥ ትልቅ ነገር ነው። ለማ የኢህአዴግ ዳይፐር ነው። በሱ ምክንያት ኢህአዴግ ጉዱ ተሸፋፍኖ ይኸው የአገዛዝ እድሜውን አራዝሟል። ይሄ ፍጥጥ ያለ እውነታ ነውና መቻል ይሻላል ዝም ብሎ ማስረጃ አምጡ ከማለት።

ሲራክ ተመስገን ግን ለማ መገርሳን ለምን እንደሚደግፍና ለምን “ሆዱ እንደራራለት” በዚህ መልኩ አስቀምጦታል፤

ለፕሬዘዳንት ለማ መገርሳ ሆዴ የራራለት ስምንት ምክንያቶች

  1. “ህወሃት እና ብአዴን ንብ ሆነው ማር ሲሰሩ፣ ኦህዴድ ማሩን ሊልስ የመጣ ዝንብ ነው” እየተባለ የሚጥላላ ድርጅትን ወደ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በመለወጡ ሂደት አጋፋሪው በመሆኑ።
  2. የዲሞክራሲ ስርዓት መአዘን የሆነውን ሃሳብን የመግለፅ ነፃነትን በሆደ ሰፊነት የሚቀበል ድርጅት ፊትአውራሪ በመሆኑ። (በመንግስት ሚዲያ የተከለከሉ ዘፈኖችን እንዲዘፈኑ በመፍቀዱ፣ ከደርጅቱ ተቃራኒ ሃሳብ ያላቸውን ግለሰቦች በOBN ሃሳባቸውን እንዲገልፁ ማድረጉ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ በሚሊኒየም አዳራሽ ሸንቋጭ ዘፈኑ በኦህዴድ አመራር ፊት ዘፍኖ ምንም አለመሆኑ (ታማኝ በየነ በታምራት ላይኔ ፊት ያን ታሪካዊ ስራ ሰርቶ የደረሰበትን ልብ ይሏል)…)
  3. ባንዲራን በተመለከተ … ህዝቡ በተለምዶ የኦነግ ባንዲራ የሚባለውን ባንዲራ በተደጋጋሚ በመያዙ “የህዝቡ ምርጫ እሱ ከሆነ የማይቀየርበት ምንም ምክንያት የለም” ማለቱ።
  4. በየወቅቱ የሚያደርጋቸው ሕብረ ብሔራዊ ንግግሮቹ። ታሪክ ለወቅታዊ ሁኔታ ያለው ጠቀሜታን የሚተነትንበት መንገድ።
  5. በ25 አመታት ውስጥ “ትምክተኛ” እና “ጠባብ” እየተባሉ ሲሸማቀቁ እና በቁርሾ እርስ በእርስ ሲተያዩ የነበሩ ህዝቦችን በመንግስታዊ ደረጃ ወደ ሰላም እና እርቅ እንዲመጡ መንገዱን በመጥረጉ።
  6. መከላከያ በየክልሉ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት በይፋ፣ በአደባባይ በማውገዙ።
  7. ህወሃት እና ጀሌዎቹ በህጋዊ ሽፋን (በፌደራል ፖሊስ እና መከላከያ ሽፋን) የሚያደርሱትን ህገወጥ የንግድ ዝውውር በማክሸፉ እና ለህግ በማቅረቡ።
  8. በኢሬቻ አከባበር ላይ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ጣልቃ ገብነትን በማስቀረቱ።

“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: abiy, change, eprdf, Ethiopia, Left Column, lemma, megerssa, opdo, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Ali says

    January 10, 2018 10:29 am at 10:29 am

    ዮሃንስ ሞላ ያለውን በመደገፍ፡ ቀደም ብዬ ስከራከር፡ ቤተሰብ አባላት ጋር «ዱላ ቀረሽ» ነበር የተጨቃጨክሁት፡፡ የመከራችን መራዘም የታየኝ፡ የኦህዴዱን ለማ ቅዱስ፤ የብአዴኑን ደግሞ ርኩስ አድርገው፡ «ህወሃት አለቀለት» ሲሉ የምሰማቸው ሰዎች መበራከት ነበር፡፡ እንድ ጉዳይ ግን እውነት ነው፡፡ ተዋዋሚዎች መተባበር እንኩዋን ቢሳናቸው፡ እየደረሰ ያለው ግፍ እና በደል መክፋት ብቻ፤ አገሪቱንም ይዞ ህወሃትም ይሞታል፡፡

    Reply
  2. አለም says

    January 10, 2018 06:13 pm at 6:13 pm

    ለማ መገርሳ በአደባባይ ስለ አንዲት ኢትዮጵያ ህልውና በግልጽ መናገሩ ብቻውን በቂ ነው። በአቋሙ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው መታየት ያለበት። ከደብረጽዮን ጎን ቁጭ ብሎ ደብረጽዮን ሊለው የማይፈቅደውን መናገሩ በሕዝብ ዘንድ ያስከተለው ተጽእኖ እጅግ ትልቅ ነው። ዮሐንስ ሞላ እና ዮናስ ሐጎስ የህወሓትን አጀንዳ ከማንጸባረቅ ውጭ የጨመሩት ነገር የለም። ይልቅ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ እያልን ጊዜ ከምናጠፋ ለማ መገርሳ በአደባባይ የተናገራቸውን እንደ መፈክር አንግበን እንነሳ። ሕዝብ ካነሳሳ ትልቅ ነገር ነው። እሳት ከተለኮሰ ጭራሮ ሰብስቦ ማፋፋም የእያንዳንዳችን ድርሻ ነው። ህወሓት መግቢያ አጥቷል፤ ሕዝቡ ድሮም ነቅቶበታል። የቸገረው አመራር ማጣቱ ነው። ብሶቱን በአደባባይ የሚያጎላለት ማጣቱ ነው። አመራር በነ ለማ ሲገኝ እንደ ማጎልበት የቆየ ወሬ ፈጥሮ ማዳፈን የሚጠቅመው ህወሓትን ብቻ ነው። በጠራራ ጸሐይ በኦሮምያ ክልሎች ወያኔ ዘረፋ ሲያካሄድ ማስቆም መቻል የሕዝብ ድጋፍ እና ግፊት ፈጣሪ ነው። መሪ ቆርጦ ሲነሳ ሕዝብም አብሮ ይነሳል፤ አንደኛው ያለሌላኛው አይሆንም።

    Reply
  3. Mulugeta Andargie says

    January 11, 2018 02:56 am at 2:56 am

    ጎልጉሎች!! መቼም ለኔም ዕድል ከሰጣችሁኝ: ለማ መገርሳ ባንድ ወቅት የተናገረውን ለመጥቀስ እፈልጋለሁ::“ ለከርሞ የሚሞት ሰው: ዘንድሮ መቃብርን ከጸሃይ መጠለያ ያደርገዋል::” ብሎ የወላይትኛ ታረቱን ለግሶን ነበር::አይገርምም?? ጎልጉሎች!!!

    Reply
  4. Aman says

    January 11, 2018 04:37 pm at 4:37 pm

    የመንግስት ተቃዋሚዎች፡ በተለይ የድያስፖራ ኣርበኞች ዋናው ችግር፡ ወያኔን በሚገባ የማያውቁ መሆናቸው ነው። በጫጫታና በቃላት ድንፋታ ወያኔን ከኢትዮጵያ ምድር እናጠፋታለን ብሎው የሚያድስቡ ከሆነ፡ ብያንስ 40 ዓመታይ ወደሃላ ቀርተዋል።

    Reply
  5. ብርሃን says

    January 11, 2018 06:44 pm at 6:44 pm

    አንዳርጌ፣ ነገሩ ዛቻ መሰለ። ቢያርፍ ይሻላል ነው የምትለን? ለመሆኑ ለማ ወላይትኛ እንደሚናገር እርግጠኛ ነህ?

    Reply
  6. Mechal Degu says

    January 12, 2018 12:13 am at 12:13 am

    Sirak said it all and all right!
    I don’t care about Lemma Megersa past; if we focus on what somebody did or has done, we are not open to change. To me, Lemma is now a MAN OF THE PEOPLE AND COUNTRY. he and Dr. Abiy (and Addisu Arega) have known woyane deep inside; they have now realized that the trend must change. To me, everything Lemma and his comrades do and say at this time shines a bright light on our people and our country. Their acts and statements are historic and monumental.
    Yohanes and Yonas are entitled to their opinions, but do they want Lemma and his group to continue in the same dirt as they were in for a long time? To me, I open my two arms for Woyane/EPRDF if they do and say the same Ethiopiawinet as Lemmas. I don’t want to reject Woyane because of their horrible deeds for many years. If they change, I am happy. So, now, I am happy that part of EPRDF is focusing on Ethiopia nad Ethiopiawinet. Qim, Tilacha, Beqel kehulachinim yiraku.

    Reply
  7. Ezira says

    January 17, 2018 02:30 am at 2:30 am

    ዮሐንስና ዮናስ ያቀረቡት አስተያየት 100/100 ወይም ሙሉ በሙሉ የእነ ደብረ ሠይጣን ስረዎ መንግሥት እንዲቀጠል የሚፈልጉ አስመስሏቸዋል። ምክንያቱም እነ ለማ መገረሳና ዶ/ር ኣብይ የት እንደነበሩና እንዴት ለዚህ ” ሥልጣን” እንደበቁ ሁላችንም እናውቃለን ። ዮሐንስና ዮናስ አንድ ያለገባችሁ ነገር ያል ይመስላል። ፖለቲካ ሳይንስ ነው። ሳይንስ ደግሞ ጥልቅ መርምርና ጥበብን ይጠይቃል። ስለዚህ የትግሬ ወያኔው ኃላ ቀረ ስረዎ መንግስት፣ ጸረ ኢትዮጵያ ሆኖ ለ26 ዓመት ኢትዮጵያን እንደጠላት አገር በመቆጥር ምን ሲያደረግ እንደነብርና አሁንም ምን እያደረገ እንደሆን የአደባባይ ምስጢር ነው። የትግሬ ወያኔ ኢትዮጵያን እንደ ይጎዝላቢያና ሱማሊያ ለማደረግ ባንድ እጁ ክብሪት በሌላ እጁ ደግሞ እንደጠላት ከሚቆጥራት ኢትዮጵያ ሃብታን ንብረቷን እየዘረፈ “ትግሬ እስክትልማ ኢትዮጵያ ትድማ” ብሎ ወደ ትግራይ በማሸሸ ያም አልበቃ በሎት ወደ ዉጭ አገርና ወደ አረብ አገሮች ዱባይ ደረስ ሃብት እያሸሸ መሆኑን አለም ሁሉ እያዬ ነው። ትግራይ ከኢትዮጵያ በሚዘረፈው ሃብት ጎብጣ ከምትችለው በላይ ሆኖባት ልትስምጥ መቅረቧን እያየን ነው።
    ስለዚህ እነ ለማ መገርሳ ከደብረ ሠይጣኑ አጋፋሪና “እሣትና ጭድ” የሆነው አማራና ኦሮሞ እንዴት አንድ ሆኑ ብለው ጨርቃቸውን ከጣሉት ከእነ ጌታቸው ረዳ፤ ሽ ጊዜ እነ ለማ መገርሳ ይሻሉናል። ምክንያቱም 1 ሆነው ኢትዮጵያን ከሠል ልያደረጓት አስበው ከተሰለፉበት መሠመር ወጥተው “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ያለ ኢትዮጵያ ኦሮሞነት የለም፤ ኦሮሞ ከኢትዮጵያው ውጭ ኦሮሞ ሊሆን አይችልም ሲሉን ከዚህ በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ ? በእርግጥ በሕዝባዊ አመጹ እና በህዝብ ግፊት ተገደውም ቢሆን እንደ ትግሬው ወያኔው እኮ በድንቁርናቸው ሊቀጥሉ ይችሉም ነበር። ነገር ግን ኦሮሞንና አማራውን እጂ ለእጅ እንዲያያዙ የተጨወቱት ሚና ከባድ ሚዛን የሚደፋ ነው። ለዚህም ነው ዶር አብይ እንዳለው ምንገዜም ከነበረህ ላይ መጨመር 2 እርምጃ ወደፊት እንደመራመድ ይቆጠራል። ደንቆሮውና በድንቁርናው እብሪት የሚወጠረው የትግሬው ወያኔማ ይሄንን መሠል እነ ለማ መገርሳ የወሰዱትን ሥር ነቅል እርምጃን ወይም መለወጥ ቀርቶ የዛሬ 40 ዓመት የያዘውን የደደቢት ቃላትን እንኳ አለቀየረም።
    ስለዚህ ቪቫ ለማ፡መገርሳ! ቪቫ ዶር አብይ !ብለናቸዋል። አማራ ኬኛ ኦሮሞ ኬኛ ኢትይጵያዊነት ወደፊት…..

    Reply
  8. Ezira says

    January 17, 2018 02:44 am at 2:44 am

    Mulugeta Andargie
    እንደራሳችሁ ማለትም እንደ ትግሬው ወያኔ ነፃ ሃሳብን “አሸባሪነት” እያላችሁ ቃሊቲ እንድምትከቱት ሁሉ እዚህም እንደዚህ ይመስልሃል። ምክንያታዊና የሚያሳምን ሃሳብ የለችሁም እንጅ እንደ አቅምህና እንደ ችሎታህማ ሃሳብክን እኮ እየገለጽክ ነው። “ከፈቀዳችሁልኝማ ” ምን አስባለህ? አስተያየቶችና ሃሳብ እንዲንሸራሸር አይደል እንዴ የሃሳብ መገለጫው BOX ተከፍቶ ሃሳብክን እየገለጽክ ያለኽው! ንገሩኝ ባይ ወያኔ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule